የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ
ይህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ
የሚዘጋጀው በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መስሪያ ቤት
በሆነው በጀነራል ኮንፍረንስ ውስጥ ሆኖ፤ የጎልማሶች የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናት መምሪያን በሚያዘጋጀው ቢሮ ነው። መምሪያዎቹ የሚዘጋጁት
የጀነራል ኮንፈረንስ አስተዳደር ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሆነውና የመጽሐፍ
ቅዱስ ጥናት መምሪያዎችን በሚያሳትመው የሰንበት ትምህርት ሕትመት
ቦርድ ነው። የታተመው መምሪያ በውስጡ ዓለም አቀፋዊ የሆነ የምዘና
ኮሚቴ ሀሳቦችንና የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድን ማረጋገጫ
ስለሚያንጸባርቅ የአዘጋጁን (የአዘጋጆችን) ሀሳብ ብቻ የሚወክል አይደለም።
በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ማተሚያ ቤት ታተመ
እግዚአብሔር ሰብአዊ ፍጡርን የፈጠረው ከእርሱና ከፍጥረታቱ ጋር
የፍቅር ግንኙነት በመመስረት እንዲደሰት ነው። ሆኖም ይህ ግንኙነት በሰማያዊ
ሸንጎ ሰው ሊረዳው በማይችለው ኃጢአት ምክንያት ተበላሸ (ኢሳ. 14፡12-15፤
ህዝ. 28፡12-19፤ ራዕይ 12፡7-12) በዚህም ምክንያት አዳምና ሄዋን ወደቁ (ዘፍ.
3፡1-19፤ ሮሜ 5፡12)። በሚያሳዝን ሁኔታ ሞት በሰብአዊ ዘር ላይ ብቻ ሳይሆን
ህይወት ባለው ነገር ላይ ነገሰ። ዛሬ የሞት መገለጫዎችን ከዛፉ ላይ ከሚረግፉ
ቅጠሎች፤ ከአበባ ማስቀመጫ ላይ ከሚወድቁ አበቦች፣ ለመሞት ከምታጣጥር
ምንም ነገር ከማታውቅ ትንሽዬ ውሻ እና በጭካኔ ካጣናቸው የምንወዳቸው
ሰዎች ላይ እናገኛለን። አለማችን በስቃይ እና ባልታበሱ እንባዎች ተሞልታለች።
የተሻለችዋን አለም በመናፈቅ ሰዎች የራሳቸውንና ሊኖሩባት የሚፈልጉባትን
“ገነት” ስለው ያስቀምጣሉ። ለምሳሌ እንግሊዛዊው የረጅም ልብ ወለድ ደራሲ
ጄምስ ሂልተን 1933 እ.ኤ.አ ላይ “የጠፋው አድማስ” የሚል መፅሐፍ አውጥቶ
ነበር። ከጥቂት አመታት በኋላም መጽሐፉ በተመሳሳይ ርዕስ ወደ ፊልምነት
ተቀየረ። ፊልሙ አየር ላይ እያለ ነዳጅ ስላለቀው አውሮፕላን አስቸጋሪ
ገጠመኝ ይናገራል፤ በስተመጨረሻም በበረዶ በተሸፈነችው ሂማሊያ ተራራ
ላይ ይከሰከሳል። ፓይለቱ ሲሞት የተረፉት ጥቂት ግለሰቦች ከዚህ በአደጋ
ከተጨራመተ አውሮፕላን ላይ ቴቤታውያን በሚባሉ ሰዎች ታጅበው ይወጡና
ሻን ግሪላ ወደተባለች ሸለቆ ይወስዳሉ። ከቀረው አለምም ተነጥለው እነዚህ
ነዋሪዎች በፍቅር በጥበብ የማይሞት ህይወትን በመኖር በደስታና በተጣመመ
ኑሮ ያድጉ ነበር።
እርግጥ ነው ይህ ልብ ወለድ ነው።
ሟች እንደመሆናችን ለአሁን ብሎም ለወደፊቱ ተስፋን የሚያሰረግጥልንን
ነገር እንፈልጋለን። ኤሚል ብሩነር የተባለ ስዊዘርላንዳዊ የስነመለኮት አዋቂ
እንዲህ ባለ ጥሩ አገላለፅ ገልፆታል፡- “ኦክስጅን በሳንባ የሚያስፈልገውን ያክል
ለሰው ልጅ ህይወት ትርጉም ደግሞ ተስፋ የዛኑ ያክል ያስፈልጋታል። ኦክስጅን
ሲጠፋ አየር በማጣት ሞት እንደሚከሰት ሁሉ ከሰብአዊ ዘር ለይ ተስፋ
ሲታጣ የሰው ልጅ ትንፋሽ ያጥረዋል፡- ተስፋ መቁረጥ ወደ ህይወቱ ይገባል፤
የተመራማሪና መንፈሳዊነት ሀይል ትርጉም አልባና አላማ የለሽ በመሆን
ህይወቱ ይሽመደመዳል። የሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ለመኖር በኦክስጅን
አቅርቦት ላይ ጥገኛ የመሆናቸውን ያክል የሰው ልጅ እጣ ፈንታ የሚወሰነውም
ባለው ተስፋ መጠን ላይ ነው” Emil Brunner, External Hope (London:
Lutterworthpress, 1954), p.7:: ወደ ዘላለም ህይወት በምናደርገው ጉዞ
በሚያጋጥመን ቀውስ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ተስፋ በእርግጥም አጽንቶ
ይይዘናል።
በጠፋው አድማስ ልብወለድ ውስጥ ካለችው ሻንግሪላ በተቃራኒ የዘላለም
ህይወት ተስፋችን “በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት የተከተለ አይደለም”
(2ጴጥ. 1፡16)። ይህም እምባ፣ ስቃይ እና ሞት የሌለበት ፍጹም የሆነ አለም
እንደሚኖረን ታማኝ በሆነው አምላክ በተገባልን ቃል ላይ የተመሠረተ
ነው(ራዕይ 21፡1-5)። ይህ የከበረ የተስፋ ቃል የሐዋርያት ቤተክርስቲያንን
ያነቃቃ በምእተ ዓመታት ውስጥ ደግሞ ብዙ ክርስቲያኖች ይዘው ያቆዩት
ነው። ይህ የተስፋ ቃል ያለውን ሃይል ሳያጣ አሁንም ህይወታችን ትርጉምና
አላማ እንዲኖረው ያደርጋል። የወደፊት ህይወታችንን በድፍረት እንድንኖረው
ያደርገናል። በክርስቶስ ሆነው የሞቱ የምንወዳቸው ሰዎች በሙሉ ከሞት
ተነስተው የዘላለምን ህይወት እንደሚወርሱ ማስተማመኛን ይሰጠናል።
ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ የጥናት መመሪያ በመልካምና በክፉ መካከል ያለውን
ታላቅ ተጋድሎ ከሁለት ዋና ኃሳቦች አንፃር ያስቃኘናል። አንዱ ስለሀጢያትና
ሞት ጅማሮ እና ቆይታ የምናይበት ሲሆን ሁለተኛው ፍሬ ሀሳብ ደግሞ
እግዚአብሔር ይህንን ችግር ለመፍታት ያደረገውን ተግባር እና አለምን
መልሶ ወደነበረችበት የቀደመ ሁኔታ ለመመለስ ስለመስራቱ ነው። ሟች
ስለሆነው የሰው ልጅ ተፈጥሮ እና ትንሳኤ እንዴት አድርጎ ዘላለማዊነትን
እንደሚያላብሰንም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። እውነታው ክርስቶስ ለእኛ ሞቶ
በሞት ሃይል ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ስለተነሳ ሞትን ልንፈራው አይገባም። እንደ
እውነቱ ከሆነ ስለጌታ ይህ ማረጋገጫ ተሰጥቶናል “የሞትና የሲኦል መክፈቻም
በእጁ ነው” (ዮሐ. ራዕይ 1፡18)
በዚህ ሩብ ዓመት ስለሚያሳምመው የሞት ርዕሰ ጉዳይ እንመረምራለን፤ ነገር
ግን በየሱስ በኩል በተሰጠን የተስፋ መነፅር አንጻር እናየዋለን።
ዶ/ር አልቤርቶ ቲም የኤለን.ኃይት ፅሁፎች ላይ ተባባሪ ዳይሬክተር ሆነው
የሚሰሩና የመፅሐፍ ቅዱስ ምርምር ተቋምና የጂኦሳይንስ ምርምር ተቋም
የኮሚቴ አባል ናቸው። ከዚህ ቀደም ደግሞ የላቲን አሜሪካ አድቬንቲስት የስነ
መለኮት ሴሚናሪ ላይ ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል።