ጤናማ ቤተሰብን ለመገንባት መደረግ ያለባቸው ጥረቶችና ስልቶች
ጤናማ ቤተሰብ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይገለጻል?
መግቢያ ጥቅስች፤
“እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍጥረት 2:18, 21-24)
Home is the heart of all activity – Society is composed of families, and what the heads of families make it. Out of the house are ‘the issue of life’: and the heart of the community, of the church, and of the nation is the household. The well-being of society , the success of the church, the prosperity of the nation, depends upon home influence.
- E. G. white, The Adventist Home, P. 151)
የተለያዩ የቤተሰብ አገልጋዮች ባለሙያና የቤተሰብን ውቅቅርም ሆነ ግንኙነት ያጠኑ ቤተሰብ ማለት ባጠቃላይ እንደሚከ ተለው ነው ብለው ይገልጹታል። በተለይም ልጆችን በሚመለከት፤ ልጆች የሚከተሉትን መግባሮች የሚማሩበት ቦታ ነው ይላሉ። ለምሳሌ፤
ሀ) የሰውን ግንኙነት በሚመለከት - ከሰው ጋር ለመግባባት አክብሮትን፣ ማካፈልን፣ ማመሥገንን፣ ማጽናናትን... ወዘተ ይለማመዳሉ
ለ) አጎልባች በሆነ ግብረ-ገብ ይታነፃሉ - ያም ባህልን ስነሥራአትን፣ ገደብ / ነውር ያለው በሆነ ምሪት መብትንና ግዴታቸውን እንዲገነዘቡ ይሆናሉ።
ሐ) በተለይም እንደ አካባቢው ባህል መኖርን በሚመለከት፤ • የኢትዮጵያ አባባል፣ “ጅብ እንዳገሩ ይጮሃል”፤ እንደ አሜሪካም “When you live in Rome do as the Romans do.” የሚለው ገጣሚ ምሳሌ ነው። • ገደብን በሚመለከት ደግሞ፤
የኢትዮጵያ አባባልም፣ “ሰው እንደ ቤቱ እንጅ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም” በአሜሪካም “We don’t live like Jones” ሌላው ምሳሌ ነው።
የጤናማ ቤተሰብ ይዘት በውሥጥና በአካባቤው ማለትም በመንደሩ፣ በጎጡ፣ በሐገሩ አልፎም የዓለም ይዘቶች ጫና ያደርጉበታል። ከዚያ የተነሳ በተለይ ወጣቶችን ለችግር ይዳርጋቸዋል፡፡ (የዓለም ኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ... ወዘተ. ) ለምሳሌ ኢትዮጵያን ብንወስድ - ከቻይና የምትገዛቸው የቤት ቁሳቁሶች ከቻይና ጎረቤቶች ካሉ ሀገሮች ጋር ሲወዳደር መጓጓዣው ብዙ ስለሚያስከፍል ኢትዮጵያ ሲደርሱ ብዙ ያስከፍላሉ። ፓለቲካውንም ብንወስድ አሜሪካና ሱማሊያ በተጣሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከጎረቤት ሱማሊያ ጋር አሜሪካ ጫና አድርጋ - የኢትዮጵያ ጦር ዘምቷል። እንደዚህ ዓይነት ሁናቴወች፣ መልካም ግንኙነትን ከማዳበርና ከማጎልበት/ከማካበት ይልቅ በቤተሰብ ላይ ጉዳትን የሚያስከትል ጫና የሚያደርጉ ይሆናሉ። ሃይማኖትም እንዲሁ ጫና ያደርጋል። ለምሳሌ፣ ክርስትና/እስልምና፣ አምነት የለሽነት፣ የትምህርትና የብልጽግና ክፍተት...፣ ወዘተ ሌሎች ጫና አድራጊዎች ናቸው።
ጤናማ ቤተሰብ ለመሆኑ መለከያው ምንድነው ተብሎ ቢጠየቅ፤ ባጠቃላይ የሚቀጥሉት ሁናቴዎች ናቸው።
• የቤተሰብ መምሪያ ደንብ አለው፤ ያም ሁሉ የቤተሰብ አባላት የሚተገብሩት ይሆናል።
• ወላጆችም ሆኑ ልጆች ፍቅርንና መመሪያውን ካልተገበሩት በአክብሮት ይወያዩበታል።
ቤተሰቡ ጤናማ ከሆነ ጤንነቱ እንዲቀጥል ምን መደረግ አለበት?
• በእምነት መጠንከርና መሻትን መግዛት፣
• ምሪትን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ሁልጊዜ መጸለይና ቃሉንማጥናት
የእግዚአብሔር ቃል የሚለውም ይህንን ነው።ለጤናማቤተሰብ ምሪት ቁልፍ ነውና። ለምሳሌ “የመንፈስፍሬግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።” (ገላትያ5:22) “ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” (1 ተሰሎንቄ 5:16-18)
የጤናማ ቤተሰብ ይዘት መመሪያ አንኳር ነጥቦች፤
1. ባለቤቶች (ባልና ሚስት) መፈቃቀርና እርስ በርስ መንከባከብ ይኖርባቸዋል፤ ድርጊቱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነውና • ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም “እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”
4. ጤናማ ቤተሰብ የሕዝብ መገናኛ መስመሮችን እንዴት ሊጠቀምባቸው ይገባል?
• ልጆችስ እንዴት ነው ሊጠቀሙባቸው የሚገባው - ለመዝናኛ ከሆነ በሰዓት ገደብ እንዲጠቀሙ ወላጆች መቆጣጠር አለባቸው።
5. ወላጆች ልጆችን በማነጽ እንዲያሳድጉ አንኳር ስልቶች አሉ ወይ? አወን አሉ።
• ልጆችን በተለያዩ ባህሎች አጣምሮ ማሳደግ ይቻላል ወይ? - አዎን ያም በማስተዋልና በውይይት ነው።
ልጆችን እንዴት እናሳድግ በሚለው አርዕስት እንመለስበታለን። ተከታተሉን !!! ከላይ የተዘረዘሩትን ለማድረግ ግን የየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይብዛላችሁ። ቤተሰባችሁም ጤናማ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ ይምራችሁ። “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” (1 ቆሮንቶስ 1:3)