ልጆቻችንን እንዴት እናሳድግ?
ወላጆች ልጆቻቸውን በመንፈስና በስነ-ልቦና አንጾ ማሳደግ ግዴታቸው ነው።
የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ነውና። ለምሳሌ፤ “እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች።” (መሣፍንት 13:7) “ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው።” (ዘዳግም 6:7)ሀ) ጤናማ ቤተሰብ ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ምን ዓይነት ድርጊት መተግበር ይኖርባችዋል?
-
• እንደ ዋናነት የቤተሰብ መተዳደሪያ ደንብ መጠቀም፤ ያም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለበት። ለምሳሌ፤ “እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።”
( ኤፊሶን 6:4)
• “ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፤…ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።” (ምሳሌ 13:22 እና 22:6)
• “… ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ ሊያከማቹ አይገባቸውምና።” (2 ቆረንቶስ 12:14)
• ሳይንሳዊ የሆኑ ስነልቦናን የሚያጎለብቱ መጻሐፎችን ማንበብና ምክሮቹን እንደ ልጆች ጠባይ መጠቀም
የሚቀጥሉት ነጥቦች ከሥራ ላይ ቢውሉ ይጠቅማሉ። • አባት፣ እናት፣ ልጆች ቤተሰብ የምንላቸው እርስ በርሳቸው በመከባበር ፍቅራቸውን ይገልጻሉ።
• አባትና እናት እንደ መሪ ልጆች እራሳቸውን እስኪችሉ እንደ ተመሪ ማስተዳደር። ያም ከማህፀን እስክ 18 ዓመት ማለትም በወላጆች ቁጥጥር ሥር እስካሉ ድረስ - በእርግዝናም እንኳን የናትን የአካልና የመንፈሳዊ ጤና መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ምሳሌወች አሉ። ለምሳሌ (መሣፍንት 13:7) “እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች።”]
• አለመግባባት ሲኖር ጊዜን ወስዶ፣ በመወያየት እንዲግባቡና ለወደፊት እንዳይደገም መስማማት ያስፈልጋል። • አባትና እናት እንደ አስተዳዳሪ የቤተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅና ግንኙነታቸውን ለማጠንከር እቅድ ያውጡ።
-
• ወላጆች ልጆቻቸውን የነሱ ግልባጮች እንደሆኑ ማየትና አንዱን ከሌላው ማወዳደር አይገባም።
• ባሕልን ለማስተላለፍ ሲፈልጉም በማመዛዘን ማድረግ ይገባል። ባሕል በትምሀርት እንጂ በትውልደ ስጋ አይተላለፍም። ወላጆች ምን ማስተላለፍ እንዳለባቸው መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል። “አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የደንበር ምልክት አታፍልስ።” (ምሳሌ 22:28) “ልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ።” (ዘዳግም 6:7)
• የወላጆች ና የልጆች ግዴታና መብት እንዴት ነው? ልጆች የሚያድጉት መቸ ነው?
ወላጆች መገንዘብ ያለባቸው ሁሉም ልጆች አንድ ዓይነት አይደሉም! ስለሆነም፤
ሀ) እንደ ልዩነታቸው የተለያዩ ማስተማሪያ መንገዶች መትለም አስፈላጊ ነው።
ለ) የሚሉትን ማዳመጥ፣ የማይሉትንም የፊታቸውን ገጽታ በመመልከት በፍቅርና በርህራሄ እንዲገልጹ ማድረግ።
ማሳሰብያና ለመደምደሚያ ትምህርታዊ ምንጮች፤ በተጨማሪ የሚቀጥሉትን መጽሐፎች ተጠቀሙ።
Selective References:
Balter, Lawrence. Not in Front of the Children”: Helping Your Child Handle Tough Family
Matters. New York, Biking , 1993
Foster, Charles et.al, Parent/Teen Breakthrough. New York, Dutton, 1991
Tsabary, Shefali. The Conscious Parent. Namaste Pub., Vancouver, British Columbia, 1972
Peterson, Gayle. Making Healthy Family. Shadow and light Pub., Grass Valley, CA, 2011
White, E. G. White. The Adventist Home. Review and Herald Pub., Hagerstown, MD, 1952
© Lemlem Tsegaw, December 4, 2020