በቤተሰብ ግንኙነት ግጭት ሲነሳ ምን ይደረግ? 



በቤተሰብ ግንኙነት ውስጥ አለመግባባት ማለትም ግጭት አይቀሬ ነው። ግጭት ሁለት ጎኖች አሉት፤ እነሱም ጥቅምና ጉዳት ናቸው። ጥቅሙ፣ ራሥን በመመርመር ጥሩ እድገት ያስገኛል። ግጭቱን ግን በውይይት ካላስተካከሉት ቤተሰብን ይበትናል፣ ወንድማማችን ያገዳድላል፣ አገርን ለጦርነት ይዳርጋል። ስለ ግጭት የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል?

“የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች፤ ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች።” (ምሳሌ 15:1) “ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።” (የማቴዎስ ወንጌል 18:15-17) መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።” (ኤፌሶን 4:31-32)

Understanding the perversity of human nature, Jesus gave explicit rules for our dealing with one another – our Redeemer understood the perversity of human nature; and in order to save the souls for whom He sacrificed His life, and establish His church in unity and prosperity upon the earth, He has given explicit rules for church- members to follow in dealing with one another. [Matthew 18:15-17] E. G. White, The Review and Herald, April 15, 1880. [She adds,] Problems are solved when we approach others in a spirit of meekness, kindness, and mercy – Never question the motives of your brethren; for as you judge them, God declared you will e judged. - E. G. White, The Review and Herald, March 12, 1895.  & Pastoral Ministry, P. 268

እንግዲህ በቤተሰብ መካከልም ሆነ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ምክኒያት ግጭት ሲፈጥር፤ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ የሚቀጥሉት ድርጊቶች መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ።
1. እንደ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ምሪት መውሰድ - ያም በጸሎትና ቃሉን በማጥናት ነው።
2. ምን አይነት ድርጊት ነው እንዳይደገም የምንፈልገው/ ማድረግም የሌለብኝ ብሎ ራስን መመርመርም ቁልፍ ነው።
3. ደግሞም የሚከተሉትን ነጥቦች በመጠቀም አለመግባባትንም ሆነ ግጭትን መፍታት ይቻላል።

  • ከግጭቱ የተነሳ ስሜትን በግልጽ መናገር (አናዶኛል፣ ስሜቴ ተነክቶ እንዳለቅስ አድርጎኛል ... ወዘት ብሎ መግለጽ)
  • በተነገረው ስሜት ስምምነት ባይኖርም የተገለጸውን ስሜት ከገለጸው ሰው መቀበልና መገንዘብ፣ ግጭቱን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን ማስተናገድ።
  • ለራስም ሆነ ለሌላው በማሰብ ግትርነትንና መልካም ያልሆነ አስተሳሰብን ማስወገድ። ግጭትን ለመፍታት አማካሪ ለመሆን የተማሩን ሰዎች ማማከር … ወዘተ።


ማሳሰቢያ፤ ግጭት ከሃሳብ/ከልብ ማለትም ከስሜት ስለሚመነጭ ራስን መመርመርና ስሜትን መግታት ቁልፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስም የሚመክረው ይህ ነው። “በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?” (ያዕቆብ 4:1) ስለዚህ ግጭትን ለማስወገድም ይሁን ፍትህ ለማግኘት የሚያስችሉ ብዙ ልምድ ባላቸው ሰወች የተጻፉን መጽሐፍት ማንበብም እጅግ ጠቃሚ ነው። - ከታች የተጠቀሱት ምሳሌወች ናቸው።


Selective References:

Beck, C. J. A., & Sales, B. D. (2001). Family mediation: Facts, myths, and future prospects. Washington, DC: American Psychological Association. Sande, Ken, (2004). The Peace Maker: A Biblical Guide To Resolving Personal Conflict. The Holy Bible, New International Version (1984). White, Ellen. G., (Pacific Press) The Adventist Home. Willie & Elaine Oliver, Pacific Press (2015). Real Family Talk. Answers to Questions About love, Marriage, and Sex
Note