በተናጠል ልጆችን የሚያሳድጉ እናቶች የሚያጋጥሟቸው ችግሮች



መግቢያ

ባጠቃላይ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። በተናጠል ለሚያሳድጉ ወላጆች ግን እጥፍ ድርብ ጫና ይሆንባቸዋል። በተለይም ለሴቶች። የሚቀጥሉት ነጥቦች ከተገዳደሯቸው በጥቂቱ ናቸው። በጣም የሚያስቸግረው ልጆችን ማስተማርና በግብረ ገብ አንጾ የማሳደግ አመራር ከአባታቸው አመለካከት የተለየ ሲሆን ነው ። ወላጆች ያን ይዘት- ልጆቹን የከፋፍለህ ግዛን ስልት እንዳይጠቀሙ ማድረግ መገንዘብ ይኖርባችዋል። ስለዚህ “አባትህ ይህን አደረገኝ፣ እናትህ ይህን አደረገችኝ” ከማለት መቆጠብ አለባቸው። ልጆች የወላጅ አማካሪወች መሆን የለባቸውም። አማካሪ በስነ ልቦና ወይንም ከማያዳላ ሰው ማግኘት ያስፈልጋል።

ጥያቄ፤ የተለያዩ ወላጆች እንዴት ልጆቻቸውን በመተባበር የማስተዳደር እቅድ እንዲኖራቸው ይደረጋል? ጥያቄውን ለመመለስ በተለይ እናቶች ያለ አባት ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ አምስት ዓይነት አስቸጋሪ ይዘቶች እንደሚያጋጥሟቸው መገንዘብ ያስፈልጋል።

1. ብቸኝነት
2. ልጆችንበሥነሥርዓትለመምራት
3. ችሎታቸውን/ብቁነታቸውን የመጠራጠር ስሜት
4. ጸጸት - ራስን የመውቀስ አመለካከት
5. የገንዘብ ውስን ውጥረት

ጥያቄውን ለመመለስ ወላጆች ልጆቻቸውን እንደ ስፖርተኛ ቡድን ሆነው ማሳደግ ይኖርባቸዋል። ማለትም አባትና እናት እንደመሪ ልጆች እንደተማሪ መሆን አለባቸው። ይህ ዓይነቱ አመለካከት በመስማማት ወይንም በፍቅር ይዘት ውስጥ ባሉበት ጊዜ ነው። አባትና እናት ከተለያዩ በኋላ ማለትም በተናጠል ማሳደግ አማራጭ የሌለው ሁናቴ መሆኑን ተገንዝበው ሁለቱም የልጆቻቸውን የአካልና የስነ-ልቦና ደህነት ለመጠበቅ ማቀድ ያስፈልጋል።

1. አባትና እናት ልጆቻቸውን ለማነጋገር አስቀድመው እንዴት ረጋ ባለና በልጆቹ ሁኔታ ያተኮረ ውይይት ማድረግ እንዳለባቸው መስማማት አስፈላጊ ነው።

2. የልጆቹ አባትነት ዘላለማዊ መሆኑን መገንዘብም ያስፈልጋል። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ አባታቸው ስለ ልጆቹ ግድ የሌለው ቢመስልም ልጆቹ በህይወታቸው ይዘት አባታቸው የሚያስፈልጋቸው ጊዜ መኖሩ የማይካድ እውነት ነው። ለምሳሌ አንድ ወንድ ልጅ ሲጎረምስ እናት ሴት ስለሆነች ልታስረዳው የማትችለው ነገር አለ - ለምሳሌ የግበረ ሥጋ ግንኙነት ምኞት - በእንቅልፍ የሚገለጽ ይዘት ከሴት ልጆች የማይገለጽ ሁናቴ አባት ወይንም ሌላ የሚታመን ወንድ የሚገልጸው ነው።

3. ሴት ልጅም ኮረዳ ሆና ሳለ ለወንዶች ስላላት አመለካከትና ወንዶች ልጆች በጉርምስናቸው ስለ ሴት ልጅ ያላቸውን አመለካከት አባቷ ስላላለፈበት ከናቷ ይልቅ ለማስረዳት ይቸገራል።

የማስተዳደሪያ እቅድን በሚመለከት ወላጆች የሚቀጥሉትን የልጆች ጠባዮች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

1. ልጆች በወላጆች መካከል የከፋፍሎ-ግዛን አቀራረብ ይጠቀማሉ። አባቴ እሽ ብሏሎ ወዘተ - ቢሆንም ልጆች ሥነ-ሥራዓት ያለው ገደብ ያስፈልጋቸዋል። ወላጆቹ ልጆቹ ሳይኖሩ ተገናኝተው ጉዳዩ ስለልጆቹ አስተዳደግ እንጂ ስለግላቸው ስላልሆነ የሥነ-ሥራዓት ገደብን ለመትለም በመሥማማት፣ ለልጆቹ ለማስረዳት- መብታቸውንና ግዴታቸውን በግልጽ ማሳወቅ አለባቸው።

2. ልጆቹን ባንድ ላይ ሆነው (አባትና እናት) አስቸጋሪ ይዘቶችን በሚነጋግሩበት ጊዜ ረጋ ባለ አነጋገር መቅረብ - የልጆቹን ደህንነት ማስቀደም። “የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል” የሚለው አባባል መገንዘብ ይረዳል።

3. በስሜት የሚመጡትን ፍርኃትንም ሆነ ጸጸትን አለማስተናገድ - ጠንካራ መሆን - አንድ ፈራጅ ያልሆነ ቤተሰብ ወይንም አማካሪ ማግኘት እጅግ ያስፈልጋል።

ጥያቄ፤ በተናጠል ልጆችን የምታሳድግ እናት ራሷንም ሳትጎዳ ቅደም-ተከተል ሁኔታዎችን በማስፈር የምታቅደው እንዴት ነው?
መጀመሪያ ራሷን መንከባከብ፤ ለምሳሌ፤
 ምግብ-ፍራፍሬ፣ ብዙ ውሃን መጠጣት።
 ልጆቹ እንደ እድሜያቸው ቀደም ብለው እንዲተኙ ማድረግ።
 ለምን የቤተሰብ መመሪያ አስፈላጊ መሆኑንም በግልጽ ማስረዳት።
 የመጽሐፍ ቤትን እርዳታ ወይንም ከጓደኞች መጠየቅ
 የቤተሰብ መድረክ ለጸሎት መጠቀሚያ መለየት።

ጥያቄ፤   ወላጆች ለፍች በሚወስኑበት ሂደት ላይ እያሉ በምን ላይ ያተኩሩ?
 ለመለያየት እንደወሰኑ ለልጆቹ ባንድ ላይ በመሆን ረጋ ባለ መንፈስ መንገር።
 ሁናቴውን የፈጠሩት ልጆቹ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ
 ልጆቹን የሆነ ቢሆን እንደሚያፈቅሯቸውና እንደሚጠነቀቁላቸው ማስረዳት
 ልጆቹ የሥነልቦና አማካሪወችን እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ
• ስለ ገንዘብና ባጠቃላይ የንብረትን አጠቃቀም የማያዳላ ሰው ፈልጎ ምክርን ማገኘት።
• በሚያስፈልግ ጊዜ ለልጆቹ ድጋፍ የሚሆን ቤተሰብም ሆነ ጓደኛ ማን እንደሚሆን መስማማት።

ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች የተወሰዱት ከዚህ መጽሐፍ ትንተና ነው። - The Challenges of single parenting and how to overcome them (www.drjohnrich.com) © Lemlem Tsegaw, December 6, 2020
Note