የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- 1 ዮሐ. 4፡7-16፣ ሕዝ. 28፡12-19፣ ኢሳ. 14፡12-15፣ ዮሐ. ራዕይ 12።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፣ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አንተ ቀድሞ መንግስታትን ያዋረድህ፤ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!” ኢሳ. 14፡12
አ
ያሌ ጠበብት ስለ ክፋት መነሻ ለመግለፅ ጥረት አድርገዋል።
አንዳንዶቹ እንደሚሉት ለመልካም ነገሮች የበለጠ ስፍራ ለመስጠት
የምንችልበት ብቸኛ መንገድ ክፋት ሁልጊዜ ሲኖር ብቻ ነው። ሌሎች
ደግሞ እንደሚያምኑት አለም የተፈጠረችው ፍጹም ሆና ነው ነገር ግን እንዲሁ
ክፋት ተጀመረባት። ለምሳሌ በግሪኮች አፈታሪክ ክፋት የጀመረው የታሸገውን
ሳጥን ለመክፈት የጓጓችው ፓንዶራ ልክ ስትከፍተው ከዛ ውስጥ በአለም ላይ
ያሉ ክፋቶች ሁሉ አምልጠው ወጡ (ሆኖም ይህ አፈ ታሪክ በሳጥን ውስጥ
ስለተደበቀው ክፋት አመጣጥ የሚያብራራው ነገር የለም)።
በተቃራኒው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን አፍቃሪ የሆነው ጌታ
ኃያል (1 ዜና 29፡10-11) እና ፍጹም መሆኑን ነው (ማቴ. 5፡48)። እርሱ
ያደረገው ነገር ሁሉ ፍጹም ነው (ዘዳ. 32፡4) ይህ ደግሞ አለምን የፈጠረበትን
ሁኔታም ያካትታል። ታዲያ ይህ ክፋት እና ሀጢያት እንዴት ሆኖ ነው ፍጹም
በሆነው አለም ውስጥ የጀመረው በዘፍጥረት 3 መሠረት የአዳምና ሄዋን
ውድቀት ኃጢያትን፣ ክፋት እና ሞትን አመጣ።
ይህ ምላሽ ግን ሌላ ጉዳይን ያስነሳል። ከውድቀት በፊት ክፋት ነበረ፤
ይህም ክፋት ሔዋንን ባሳታት እባብ በኩል ተገለጠ (ዘፍ. 3፡1-5)። ስለዚህ
ከውድቀት በፊት ወደነበረው ጊዜ ሄደን አሁን ላይ ስለተቆጣጠረንና ህይወትን
ምስቅልቅሉን ስላወጣው የክፋት ጅማሮ እናያለን።
* የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለመስከረም 21 ሰንበት
ይዘጋጁ።
ፍጥረት አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በጎና ክፉ ተቀላቅሎ በሚያሻማ መልኩ
ይንጸባረቅበታል። የጽጌረዳ አበቦች ባሉበት ስፍራ ላይ በጣም ተወዳጅ፣
መልካም መአዛ ያላቸው አበቦች ይበቅላሉ ነገር ግን ጎጂና የሚያሳምሙ
እሾኮችም አሉባቸው።
ቱካን የምትባለው በቀለም ያሸበረቀች የአዕዋፍ ዝርያ ውበት እጅግ
ቢያስደንቀንም በሌሎች የአእዋፍ ዝርያ ጎጆ ላይ ጥቃት በማድረስ ደካማ
የሆኑ ጫጩቶችን መብላታቸው ሲታሰብ ተስፋ ያስቆርጠናል። ሰዎች እንኳን
በአንድ ቅፅበት ላይ ርህራሄን ሲያደርጉ ቆይተው በሌላ ጊዜ ደግሞ አረመኔያዊ፣
በጥላቻ የተሞላ ብሎም የአመጽ ተግባርን ሲከውኑ ሊታዩ ይችላሉ።
በስንዴውና በእንክርዳዱ ምሳሌ ውስጥ አገልጋዮቹ የእርሻውን ባለቤት
እንዲህ ብለው መጠየቃቸው እምብዛም አያስደንቅም “ጌታ ሆይ፤ በእርሻህ
ቦታ ጥሩ ዘር ዘርተህ አልነበረምን እንክርዳዱስ ከየት መጣ?” (ማቴ. 13፡27)።
የእርሻው ባለቤትም ሲመልስ “ጠላት ይህን አደረገ” አላቸው (ማቴ. 13፡28)።
ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር ምድርን ፍጹም አድርጎ ሰራት ነገር ግን ጠላት
የኃጢያት ዘር በሚስጥር ዘርቶ አበላሻት።
1 ዮሐ. 4፡8፣16ን ያንብቡ። ስለ “እግዚአብሔር ፍቅርነት”
እርግጠኝነታችን ከፈጣሪነቱ ጋር በተያያዘ ምን የሚነግረን ነገር
አለው?
“እግዚአብሔር ፍቅር ነው” የሚለው እውነታ (1ዮሐ. 4፡8፤16) ቢያንስ ሶስት
መሰረታዊ ነገሮችን ያመለክተናል። የመጀመሪያው ፍቅር በተፈጥሮው በራሱ
በአንድ ስፍራ ብቻ ተደብቆ የሚቆይ ሳይሆን ራሱን የሚገልጽ ነው (የትኛው
የፍቅር አይነት ነው ሊገለጽ የማይችለው?)። የእግዚአብሔር ፍቅር ከውስጥ
በሶስቱ የስላሴ አካላት መካከል እና ከውጪ ደግሞ ከፍጥረታቱ ጋር ባለው
ግንኙነት ተገልጾአል። ሁለተኛ እግዚአብሔር ያደረገው ነገር ሁሉ በሁኔታዎች
ላይ ያልተመሰረተውንና የማይለዋወጠውን ፍቅሩን ይገልጽልናል። ይህም
የፍጥረት ስራውን፣ የድነት ተግባሩን፣ እንዲሁም የቅጣት ፍርድ ተግባሩን
ያካትታል። እንደ እውነቱ ከሆነ “ከምህረቱ ባልተናነሰ መልኩ ፍትሁን (ፍርዱን)
ሲያመጣም የእግዚአብሔር ፍቅር ተገልጧል።
ፍትህ የዙፋኑ መሠረት እና
የፍቅሩ ፍሬ ነውና” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 762።ሶስተኛው
ደግሞ እግዚአብሔር ፍቅር እስከሆነ ድረስ ተግባሩ ሁሉ ፍቅሩን የሚገልጽ
ከሆነ የእርሱ ባህሪ ተቃራኒ የሆነውን ኃጢአት ሊፈጥር አይችልም።
እግዚአብሔር አጽናፈ አለምን መፍጠር ያሻው ነበር? አንድ ሰው ከእርሱ
ሉአላዊነት አንጻር ተመልክቶ “በፍጹም አያስፈልገውም” ብሎ ሊመልስ
ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ የበጎ ፈቃድ ውሳኔ ነውና። አፍቃሪ ከሆነው
ተፈጥሮው አንፃር ስናይ ግን ፍቅሩን ሊገልፅላቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች
ለማግኘት አፅናፈ አለምን ፈጠረ። ህይወት ያላቸውን ነገሮች እንደ ሰው ልጆች
ያሉ ለእግዚአብሔር ፍቅር ምላሽ መስጠት የሚችሉ ብቻ ሳይሆኑ ለእርሱ ብቻ
ሳይሆን ለሌሎች ፍቅርን ማጋራትና መግለፅ የሚችሉ ሰዎችን መፍጠሩ ምን
ያክል አስደማሚ ነው!(ማር. 12፡30-31)።
የተፈጠረውን አለም መለስ ብለው ይቃኙ። አጥፊ ከሆነው ሀጢያት
ባሻገር የእግዚአብሔርን የፍቅር ነፀብራቅ የምናየው በምን አይነት
መንገድ ነው? እግዚአብሔር በፍጥረቱ ላይ ከገለፀው ፍቅር
የተስፋን ትምህርት ልንማር የምንችለው እንዴት ነው?
1 ዮሐ. 4፡7-16ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ነፃ ፈቃድ ፍቅርን ለመቀበል ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ የሚነግረን እንዴት ነው?
ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ አበቦች የተዋቡ ቢሆኑም እንደ እውነተኛ አበቦች ሊያድጉና
ሊያቆጠቁጡ አይቻላቸውም። ሮቦቶች አያሌ ተግባሮች እንዲከውኑና መናገር
እንዲችሉ ተደርገው ቀድመው ተሞልተዋል። ነገር ግን ህይወትም ሆነ
ስሜት የላቸውም። በገሃዱ አለም ህይወት እና ነፃ ፈቃድ አንድ ሰው ፍቅርን
እንዲቀበል፣ እንዲያሳድግና እንዲያጋራ የሚያደርጉ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው።
ስለዚህ አፍቃሪ የሆነው አምላካችን መላዕክታቱን (ሉሲፈርን ጨምሮ) እና
ሰብአዊ ዘርን የፈጠረው የተሳሳቱ መንገድን መከተልን ጨምሮ የራሳቸውን
ምርጫ ነፃ ሆነው እንዲመርጡ ነው። በሌላ አባባል እግዚአብሔር መላውን
አጽናፈ አለም ፍጹምና ተስማምቶ እንዲኖር የፈጠረው ፍጥረታቱ በፍቅር እና
በጥበብ እንዲያድጉ ነው።
1 ዮሐ. 4፡7-16 ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” ብሎ
ዘግቦልናል፤ ስለዚህም አንድያ ልጁን ለኃጢአታችን እንዲሞትልን በማድረግ
ፍቅሩን ገለፀ። በዚህም ምክንያት ገደብ የለሽ በሆነው ፍቅሩ ምስጋናችንን
የምንገልፀው እርስ በርስ በመዋደድ ነው። ከመለኮት የመነጨ ይህ ፍቅር
እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ እና እኛ ደግሞ በእርሱ ውስጥ እንደምንኖር
ማረጋገጫን ይሰጠናል። የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች እንዲያንጸባርቁ
ጥሪ ማድረጉ ትርጉም የሚኖረው ይህን ፍቅር ለማሳደግና ለሌሎች ለመግለፅ
ምርጫቸው ላደረጉ ብቻ የሚሰጥ እንጂ በተቃራኒው ራስ ወዳድ ሆነው
ለሚኖሩ ሰዎች አይደለም። ሆኖም የመምረጥ ነፃነት በቀላሉ ባልተገባ መንገድ
ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ ይህም በሰማይ በሚያሳዝን ሁኔታ ሲያሳምጽ
ተስተውሏል።
የነፃ ፈቃድን አስፈላጊነት ሰዎች ቢረዱም አንዳንድ ሰዎች ግን “እግዚአብሔር
ሉሲፈር እንደሚያምጽበት ካወቀ ታዲያ ለምን ፈጠረው?” በማለት ይደነቃሉ።
የሉሲፈር መፈጠር ለኃጢያት መጀመር እግዚአብሔር የመጨረሻውን ሀላፊነት
እንዲወስድ አያደርገውምን?
ይህ ቀድመን ልንገምት የሚያዳግተን ከባድ ጥያቄ ነው ምክንያቱም “ሐላፊነት
መውሰድ” የሚለው ቃል ራሱ ምን ማለት ነው? የሚለውን ኃሳብ ጨምሮ
ከብዙ ነገር ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው። የኃጢአት ጅማሮ እና ተፈጥሮ
ሚስጥራዊ ከመሆኑ የተነሳ ማንም ሙሉ በሙሉ ሊገልጸው አይችልም።
ምንም እንኳን ኃጢአት እንዲፈጠር ያደረገው እግዚአብሔር ባይሆንም
ኃጢአት እንዲኖር ግን ፈቅዷል፤ ከዛም በመስቀል ላይ የሀጢያትን ቅጣት ራሱ
መውስዱ ኃጢአትን ለማስወገድ አቅምን ሰጠው። በክፋት ምክንያት ምንም
ያክል ከባድ ህመም ቢሰማንም እግዚአብሔር ለኃጢአትና ክፋት የከፈለው
ታላቅ ዋጋ ሊዘነጋ የሚችል አይደለም (ማቴ. 5፡43-48፤ ሮሜ 5፡6-11)
በኃጢአት ምክንያት እኛ ከደረሰብንና ሊደርስብን ከሚችለው ጉዳት በላይ
እርሱ ጉዳት ደርሶበታል።
ከእግዚአብሔር የተሰጠን ነፃ ፈቃድ ልዩ ስጦታ ነው፤ ነገር ግን
ለኛም ሆነ ለሌሎች ከፍተኛ መዘዝን ይዞ የመጣ ታላቅ ቀንበር ነው።
እርስዎ ይህንን ስጦታ በመጠቀም ምን አይነት ወሳኝ ውሳኔዎችን
ሊወስኑ ተዘጋጅተው ይሆን? የምርጫዎቻችሁ ውጤትስ ምን
ሊሆን ይችላል?
ህዝ. 28፡12-19ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ስለ ሚስጥራዊው የሀጢያት ጅማሮ ምን ያስተምረናል?
አብዛኛውን የህዝቅኤል መፅሐፍ የተፃፈው ለመጨረሻው ጊዜ
የምንጠቀምባቸውን ተምሳሌታዊ ቋንቋዎችን በመጠቀም ነው። በብዙ
ምሳሌዎች አማካኝነት የተወሰኑ አካላት (እንደ ሰው፣ እንስሳት እና ቁስ አካላት)
እና በአንድ ስፍራ ላይ የተከሰተ ክስተት የመላውን አለም ሁኔታ ወይንም
ታሪካዊ እውነታ ሲገልጽልን ይታያል። ሕዝ. 28፡1-10 ላይ እግዚአብሔር
ስለጢሮስ ንጉስ (ጢሮስ ራስዋ በጥንት ጊዜ የነበረች የበለጸገች የወደብ ከተማ
ነች) ሲናገር “ሰው” ብቻ የሆነ ባለፀጋና በስልጣኑ ኩሩ የሆነ ነገር ግን አምላክ
ለመሆን እንደፈለገና እንደውም በአምላክ ዙፋን እንደተቀመጠ (እንደተመኘ)
ይገልጽልናል።
ከዚያም በህዝ. 28፡12-19 ላይ ያለው ይህ ታሪካዊ እውነታ ሉሲፈር ከሰማይ
ሸንጎ ከተጣለበት የቀደመ ሁኔታ ጋር ተመሳስሏል። ሰብአዊ ፍጡር የሆነው
ይህ የጢሮስ ንጉስ “በባህሮችም ልብ ተቀምጦ የነበረ” ሲሆን (ህዝ. 28፡2፤8)
በዚህ ቦታ የወከለው “በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በኤደን” እንዲሁም
“በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ” ላይ (ህዝ. 28፡14) የሚኖረውን “ጠባቂ
ኪሩብ”(ህዝ. 28፡13) ነው።
ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆነው ሀሳብ የሚገኘው ህዝ. 28፡15 ላይ ነው፤
“ከተፈጠርክበት ቀን ጀምሮ ክፋት እስከተገኘብህ ድረስ በመንገድህ ነቀፌታ
አልነበረብህም” ይላል። ስለዚህ ወሳኙ ሃሳብ ሉሲፈር መጥፎና የተሳሳተ ነገርን
ለማድረግ አቅም የተሰጠው ነው እንጂ ግብረገባዊ ተፈጥሮ የነበረው ፍጹም
ተደርጎ የተሰራ ነበር። ስለዚህም ሉሲፈር ነፃ ፈቃድ ያለው ስለሆነ ይህ ክፍልም
ፍጹም የሆነ ፍጡርነቱን ይገልጽልናል።
እውነታው ሉሲፈር ፍጹም ሆኖ ተፈጥሮአል ይህም በነፃነት የሚፈልገውን
እንዲመርጥ የተሰጠውን ችሎታም ያካትታል። ሆኖም ይህንን ነፃ ፈቃዱን
ባልተገባ መንገድ ስለተጠቀመ ከሆነው በላይ ራሱን ተፈላጊ እንደሆነ በማሰቡ
ተበላሸ።
እግዚአብሔር እርሱን የፈጠረበትና ያከበረበትን ሁኔታ በቃኝ ሳይል ሉሲፈር
ከተገባው በላይ የበለጠ እውቅናን ለማግኘት ስለተመኘ ለእግዚአብሔር
የሚገባውን ምስጋና መስጠት አቆመ። ፍጹም በሆነው አጽናፈ ሰማይ በሚገኙ
ፍጹም መላዕክት መካከል ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ቻለ? ከዚህ ቀደም
እንዳልነው ይህ ሚስጥር ነው።
“ኃጢአት ሚስጥራዊና ልንገልጸው የማንችለው ነገር ነው። ለምን ወደ
መኖር እንደመጣ ምክንያቱን መናገር አይቻልም፤ ይህን ለመግለፅ መሞከር
ማለት ለጉዳዩ ምክንያት መፈለግ ማለት ነው፤ ይህም ነገሩን አሳማኝ አድርጎ
እንደማቅረብ ነው። ሀጢያት ፍጹም በሆነ አለም ውስጥ መታየቱ በቀላሉ
የሚታለፍ አልነበረም።” Ellen G. White, The truth About Angels, p.30
1 ተሰ. 5፡18 ላይ ጳውሎስ ሲናገር “በማንኛውም ሁኔታ”
አመስግኑ ይለናል። በተለይም በመከራ ጊዜ የመከፋትና የማማረር
ስሜት ሲሰማን እነዚህ ቃላቶች እንዴት ሊረዱን ይችላሉ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሁለት
ዋነኛ ፍሬ ሃሳቦች እርስ በርሳቸው እየተፎካከሩ እንደሆነ አንድ ሰው ሊረዳ
ይችለል። አንዱ ፍሬ ሀሳብ ሳሌም፣ የጽዮን ተራራ፣ ኢየሩሳሌም እና አዲሲቱ
ኢየሩሳሌም ሲሆን ይህም የእግዚአብሔርን መንግስት ይወክላል። ሌላኛው
ፍሬ ሀሳብ ደግሞ የባቤል እና የባቢሎን ሃሳብ ሲሆን ይህም የሰይጣን የሃሰት
ግዛትን የሚወክል ነው። ለአያሌ ጊዜያት እግዚአብሔር ህዝቦቹ አረማዊ
ከሆነችው ባቢሎን አምልጠው በተስፋይቱ ምድር ላይ እርሱን እንዲያገለግሉ
ጥሪውን አቅርቦላቸዋል።
ለምሳሌ አብራም (በኋላም አብርሃም የተባለው) ከኡር ምድር ወጥቶ
ወደ ከነዓን ምድር እንዲሄድ ጠየቀው (ዘፍ. 11፡31፤ 12፡9)። ከረጅም የስደት
ጊዜ በኋላ የአይሁድ ህዝብ ባቢሎንን ለቀው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ
(ዕዝራ 2)። በራዕይ ዮሐንስ ላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ህዝብ በመጨረሻ
ዘመን ላይ ከምትገኘዋ ባቢሎን እንዲወጡና (ራዕይ 14፡8) በስተመጨረሻም
በጽዮን ተራራ እና በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ጥሪውን
ያቀርብላቸዋል (ራዕይ 14፡1፣ ራዕይ 21፡1-3፣10)።
ኢሳ. 14፡12-15ን ያንብቡ። በሰማይ የነበረው የሉሲፈር ኩራት
ለአፅናፈ ዓለም እና ለዚህች ምድር ምን ያክል ሰፋ ያለ መዘዝን
አመጣ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የባቢሎን ከተማ ከእግዚአብሔርና ከእርሱ መንግስት
ተጻራሪ የቆመን ሀይል ሲወክል የባቢሎን ንጉስ (በተለይም ናቡከደናፆር)
የኩራትና የእብሪት ተምሳሌት ሆኗል። እግዚአብሔር ለንጉስ በታየው
ምስል ላይ ናቡከደነጾር የገለጸለት ባቢሎን ተከታትለው ከሚመጡ ነገስታት
ውስጥ ራሱ ያውም ወርቁ እርሱ እንደነበረ ነው(ዳን. 2፡37-38)። ነገር ግን
የእግዚአብሔርን ራዕይ በመገዳደር የርሱ መንግስት ለዘላለም ፀንቶ እንዲኖር
በማሰብ ሙሉውን ምስል በወርቅ አሠራ፤ ሁሉም ሰው እንዲሰግድለትም
ጠየቀ (ዳን. 3)። ልክ እንደጢሮስ ንጉስ (ህዝ. 28፡12-19) የባቢሎን ንጉስም
የሉሲፈር ተምሳሌት ሆኖ ተገልጾአል።
ኢሳ. 14፡3-11 ላይም ኩሩውና ጨቋኙ የባቢሎን ንጉስ እንዴት እንደወደቀ
ይተርክልናል። ከዚያም ኢሳ. 14፡12-15 ላይ ሃሳቡን ከታሪካዊ እይታ ወደ
ሰማያዊ ሸንጎ ያዞርና ሉሲፈር ቀድሞ በተመሳሳይ ኩራትና የዕብሪት መንፈስ
እንዴት ሊወድቅ እንደቻለ ያወጋናል። ጥቅሱ እንደሚተርክልን ሉሲፈር
ዙፋኑን ከሰማይ ሰራዊት በላይ አድርጎ ራሱን “በልዑል እመሰላለሁ” (ኢሳ.
14፡14) አለ። ከእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር እና ትብብር በተቃራኒ የሰይጣን
ራስ ወዳድነት እና ፉክክር ተግዳሮት አዲሱ የግጭት ጅማሬ ሆነ። ጠላት
እግዚአብሔርን ስለማንነቱ ለመክሰስና የሀሰት ወሬውን ለመንዛት አልፈራም።
እንግዲህ በአጽናፈ አለም ላይ የተጀመረው ሚስጥራዊ ክፋት ጅማሮ ይህ ነው።
ባለን ስልጠና ወይም ስኬት መኩራትና መታበይ ቀላል የሆነው
ለምንድነው የክርስቶስን መስቀል ከፊት ለፊታችን ማድረጋችን
በዚህ ወጥመድ እንዳንወድቅ የሚጠብቀን እንዴት አድርጎ ነው?
“ዮሐንስ ራእይ 12ን ያንብቡ። ይህ ምዕራፍ ስለ አመፅ ከሰማይ ወደ ምድር መስፋፋት ምን ያስተምረናል?
የሉሲፈር ውድቀት እንዲሁ ቀለል ያለ የኃሳቦች ግጭት አልነበረም። ዮሐንስ
ራእይ 12 እንደሚነግረን በሰማይ ታላቅ ጦርነት ሆነ፤ በአንድ በኩል ሉሲፈርና
የእርሱ መላዕክት በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቶስና መላዕክቱ። በዚሁ ምዕራፍ
ላይ ሉሲፈር “ታላቁ ዘንዶ”፣ “የጥንቱ እባብ”፣ “ዲያብሎስና ሰይጣን”
እና የወንድሞች ከሳሽ” ተብሎ ተጠርቷል(ራእይ 12፡9-10)። ክርስቶስ
ደግሞ “ሚካኤል” ተብሎ የተጠራ ሲሆን (ራዕይ 12፡7) ትርጉሙም “እንደ
እግዚአብሔር ያለ” ማለት ነው።
“የመላዕክት አለቃ ሚካኤል”(ይሁዳ 9) የሚለውን አጠራር መሰረት አድርገው
አንዳንድ ተርጓሚዎች ሚካኤል መልዓክ ብቻ ነው ይላሉ። በዳንኤል መፅሐፍ
ላይ ግን እያንዳንዱ ትልልቅ ራዕይ የሚደመደመው በክርስቶስ እና በዘላለማዊ
መንግስቱ፣ ማለትም እጅ ሳይነካው ተወርውሮ እንደ መጣው ድንጋይ (ዳን. 2፡
34፣ 45)፤ እንደ ሰው ልጅ (ዳን. 7፡13)፤ እንደልዑልና የልኡላን ልኡል (ዳን.
8፡11፣ 25) እና ታላቁ አለቃ ሚካኤል ነዉ (ዳን. 12፡1)። ስለዚህ የጌታ መላዕክት
አለቃ ራሱ ጌታ ነው (ዘጸ. 3፡1-6፣ ሐዋ. ሥራ 7፡30-33)፤ ሚካኤልም መለኮታዊ
ማንነት የተላበሰው ራሱ ክርስቶስ ነው።
ራዕይ 12 እየተከናወነ ስላለው ተጋድሎ አጠቃላይ ምልከታን ሰጥቶናል፤
ያም (1) የተጀመረው በሰማይ ሲሆን አመፅ ያስነሳው ሉሲፈርና ሲሶ ሰማያዊ
መላዕክት ናቸው (2) የተደመደመውም ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባመጣው
ድል ነው (3) አሁንም ግን እስከፈፃሜው ዘመን ድረስ የእግዚአብሔርን ቅሬታ
ህዝቦች በመቃወም ቀጥሏል።
የዚህን ተጋድሎ ጅማሮ ኤለን ጂ. ኋይት ስታብራራ “እግዚአብሔር በታላቅ
ምህረቱ ሉሲፈርን ሊመልሰው ሩቅ ተጉዟል። ካለመርካት ስሜቱ የተነሳ
የሀሰት ወሬውን ታማኝ በሆኑ መላዕክት ዘንድ እንዳሰራጨ ወዲያውኑ ከከበረ
ስፍራው ዝቅ አልተደረገም። በሰማይ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይቶ ነበር። በተደጋጋሚ
በንስሃና ራስን አሳልፎ በመስጠት እንዲመለስ ይቅርታ የማግኘት እድል
ተሰጥቶት ነበር።” Ellen G. white, The Great Controversy, pp. 495,
496.
በሰማይ ግዛት ይህ ጦርነት ምን ያህል ጊዜ እንደቆየ አናውቅም። ምን ያክል
የተፋፋመና ምን ያክል ጊዜ የፈጀ ነው የሚለውን ትተን ለኛ በጣም አስፈላጊው
ነገር በትግሉ ሰይጣንና መላዕክቱ “በሰማይ ነበራቸውን ስፍራ አጡ” የሚለው
ነው (ራዕይ 12፡8 ሉቃስ 10፡18ንም ይመልከቱ)። ችግሩ ግን ወደዚህች ምድር
መምጣታቸው ነው።
ይህ ተጋድሎ በእርግጥም በምድር ላይ እየተከናወነ
ስለመሆኑ የምናይባቸው ምን አይነት መንገዶች አሉ በዚህ
ጦርነት ጠላታችንን ድል ለማድረግ ያለን ብቸኛ ተስፋ ምንድነው?
የሃይማኖት አባቶችና ነብያት ከሚለው መጽሐፍ “ኃጢአት
ለምን ተፈቀደ?” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍና ታላቁ ተጋድሎ ከሚለው
መጽሐፍ ላይ “የክፋት አጀማመር” የሚል ርዕስ ያለውን ምዕራፍ ያንብቡ።
“ሊገለጽ የማይችለውን ሰማያዊ ክብር እና አስፈሪ የሆነውን የእግዚአብሔርን
ግርማ ክብር በደንብ አጣጥመው ነገር ግን በእርሱ ላይ ላመፁ (ሰይጣንና
መላዕክቱ) የመዳን ተስፋ ፈጽሞ የላቸውም። ይህንን ላጣጣሙ ሁሉ
ከዚህ በላይ አዲስ እና አስደናቂ ሆኖ እነርሱን የሚያስደምም ሌላ ታላቅ
የእግዚአብሔር ክብር የለም። በዚህ ሊገለፅ በማይቻል ክብር ውስጥ ሆነው
ካመፁ ራሳቸው ማንነታቸው የሚታይበት ሌላ የተሻለ ስፍራ ላይ ሊቀመጡ
አይችሉም።
የቅናትና የጥርጣሬ ብሎም የማጉረምመረም አመፃቸውን በልጦ ሊሸፍን
የሚችል ታላቅ ከፍ ያለና መጨረሻ የሌለው ሌላ ተጠባባቂ ሃይል አልነበረም።
በሰማይ ሸንጎ ፊት በነበራቸው ክብርና ከፍታ ልክ የጥፋተኝነት ስሜት
ሊሰማቸውና ሊቀጡ ይገባቸዋል። Ellen G. White, Confrontation, p.21.
“ከጅማሮው እግዚአብሔር አብና ክርስቶስ የሰይጣንን ክህደት እና በርሱ
የማሳሳት ሀይል የተነሳ የሰው ልጅ ለውድቀት እንደሚዳረግ ያውቃሉ።
እግዚአብሔር ኃጢያት እንዲኖር አላደረገም፤ ነገር ግን ኃጢያት ሊኖር
እንደሚችል ቀድሞ ተገነዘበና ለዚህ አስደንጋጭ አደጋ መፍትሄ አመጣ።
ለአለም ያለው ፍቅር እጅጉን ሀያል ስለሆነ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም
ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16) አንድያ ልጁን ለመስጠት
ቃል ገባ” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 22
1.በውይይት ክፍልዎ ውስጥ እግዚአብሔር በአለም ላይ ላለው
የክፋት ጅማሮ እና መኖር የመጨረሻውን ሀላፊነት መውሰድ
አለበት ወይንም የለበትም በሚለው ጥያቄ ላይ ይወያዩበት።
ይህንን ጥያቄ እንዴት ልንመልስ እንችላለን?
2.ስለ ክፋት ባለን ጥያቄና መረዳት ላይ የክርስቶስ መስቀል ገጣሚ
ሊሆንልን የሚችለው እንዴት ነው? መስቀሉና በመስቀሉ ላይ
የተደረገው ነገር በክፋት ጅማሮ ባለን መረዳት ላይ ማዕከላዊ
ስፍራን ሊይዝ የሚችለው እንዴት ነው?
3.በአለማችን ላይ ለብዙ ሺ ዓመታት ኃጢአት እና ስቃዮች
ተስተውለዋል፤ ሰይጣን አሁን ላይ በአመፁ ምክንያት የመጣውን
አሳዛኝ ውጤት ሙሉ በሙሉ ተገንዝቧል። ታዲያ አሁንም ድረስ
በእግዚአብሔር ላይ ማመፁን የቀጠለው ለምንድነው?
4.ማቴ. 5፡43-48 ላይ ክርስቶስ እርስ በርሳችን እንዴት መኖር
እንዳለብን መንገዱን በማሳየት ለሰብአዊ ዘር ሁሉ ምክንያት አልባ
ስለሆነው ፍቅሩ ገለፀልን። ይህንን አካሄድ በቅርበት በቤተሰብዎ
እና በቤተክርስቲያንዎ እንዴት ማንጸባረቅ አለብዎ?
5.የሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቀናል “ጠላታችን
ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችን
ይዞራል” (1ጴጥ. 5፡8)። በተጨማሪም ኤፌ.6፡10-20ን
ያንብቡ። የዲያብሎስ “የተንኮል ሥራ” መቋቋም የምንችለው
እንዴት ነው (ኤፌ. 6፡11)?