የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሉቃስ 2፡52፣ ማቴ. 4፡23፣ 1ኛ ቆሮ. 6፡19-20፣ መዝ. 24፡3-4፣ ሐዋ. ሥራ 8፡4-24፣ 1 ዮሐ. 3፡1-3።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ የሰላም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ያለነቀፋ ይጠበቁ፡፡ 1 ተሰሎንቄ 5፡23
የ
ዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ከክርስቶስ ዳግም ምፃት በፊት ስለሚከሰቱ ሁለት
ዓይነት ዋና የዓለምዓቀፍ ትስስሮች (ግሎባላይዜሽን) ይናገራል። ዮሐንስ
ራዕይ 13 ዓለም ሁሉ ከባህር በወጣው አውሬ እየተደነቀ የሚከተልበትን
የስህተት መንገድ ትስስር ይጠቅስልናል(ዮሐ. ራዕይ 13፡3፣7፣8፣ 12፣ 16)።
ራዕይ 14 ደግሞ የዘላለሙ ወንጌል ለህዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋ ሲሰበክ(ዮሐ. ራዕ.
14፡6-7) የሚፈጠረውን ስለእውነቱ ሲሉ ህብረት የፈጠሩትን ሰዎች ትስስር
ያሳየናል። በነዚያ አስጨናቂ ዘመናት(2 ጢሞ. 3፡1)
እያንዳንዱ የትምህርት
ነፋስ ይነፍስና(ኤፌ. 4፡14) ሰዎች እውነቱን ከመስማት በተቃራኒ ወደ
ተረትተረት ይዞራሉ(2ጢሞ. 4፡4)፤ በሁለት ታላላቅ የስህተት ትምህርቶች
ማለትም የማትሞት ነፍስ አለች በሚለውና በእሁድ ቅድስና ትምህርት
በመጠቀም ሰይጣን ሰዎችን ያታልላቸዋል። የመጀመሪያው ለመናፍስት
ጠሪነት በር የሚከፍት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሮም ቤተክርስትያን ጋር
ቁርኝት እንዲፈጠር ያደርጋል። Ellen G. White, The Great Controversy,
p. 588
እነዚህ የመጨረሻ ክስተቶች እስኪከሰቱ ድረስ በተሰጠን እውነት ሁሉ የሰውን
ልጅ ተፈጥሮ እና የሞት ሁኔታን ጨምሮ በእምነታችን በመፅናት በመንፈስ
ቅዱስ እየተመራን ለክርስቶስ በክብር መገለጥ ዝግጁ መሆን አለብን።
*ለታህሳስ 8 ለሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ሉቃስ 2:52ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ የትኞቹ የኢየሱስ እድገት አራት ገጽታዎች ተጠቅሰዋል?
ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነበር፣ እናም እድገቱ ሁሉንም መሰረታዊ የሰው ልጅ
ህልውና ገጽታዎችን ያካተተ ነበር። በሉቃስ 2፡52 መሠረት፣ “ኢየሱስ በጥበብ
[በአእምሮ] በቁመት [በአካል] እንዲሁም በእግዚአብሔር [በመንፈሳዊ]
በሰውም [በማህበረሰቡ] ፊት በሞገስ ያድግ ነበር”። የአእምሮ ንቃቱ፣
አሳቢነቱ እና ጥበቡ ከእድሜው በላይ ነበር። ሆኖም ባህሪው ተመጣጣኝና
ውብ ነበር። የልጅነት ሕጎችን በጠበቀ መልኩ የአእምሮ እና የአካል ኃይሉ ቀስ
በቀስ እየዳበሩ ነበር። ኢየሱስ በልጅነቱ ልዩ የሆነ ፍቅር አሳይቷል። ፍቃደኛ
እጆቹ ሌሎችን ለማገልገል ምንጊዜም ዝግጁ ነበሩ።
በምንም ነገር የማይረበሽ
ትዕግስት እና ቅንነትን ፈጽሞ የማይሰዋ እውነተኝነት አሳይቷል። በመርህ
እንደ ቋጥኝ የፀና ሆኖ ሕይወቱ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የአክብሮት መንፈስ
ያለውን ጸጋ አሳይቷል።”— ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 68-69
ማቴዎስ 4:23ን ያንብቡ። የኢየሱስ ሦስት ገፅ ያለው አገልግሎት
ይኸውም ማስተማር፣ መስበክ እና መፈወስ ዛሬ በእኛ ውጤታማ
በሆነ መንገድ መከወን የሚቻለው እንዴት ነው?
ሰው የተዋሃደ እና የማይከፋፈል አካል መሆኑን ከተገነዘብን ሃይማኖታችንን
በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ልንገድበው አንችልም። እውነቱ ሙሉ
ማንነታችንን ያቅፋል፤ መላ እድሜያችንን ይሸፍናል እናም ሁሉንም
የህይወታችንን ገጽታዎች ይነካል። የእኛ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ አካላት
በኃይል የተዋሃዱ ከመሆናቸው የተነሳ ሊነጣጠሉ አይችሉም። ምንም
እንኳን፣ እንደወደቁ ሰዎች፣ ከላይ እንደተገለጸው የኢየሱስን መግለጫ
ፈጽሞ ልንተካከለው ባንችልም፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ልንመስለው ይገባናል።
ምክንያቱም በሰው ውስጥ የፈጣሪውን መልክ ለመመለስ፣ ሲፈጠር ወደነበረበት
ፍፁምነት ለመመለስ፤ የአካል፣ የአዕምሮ እና የነፍስ እድገትን ለማበረታታት
ነው - ይህም የመቤዠት ስራ ነው። እግዚአብሔር ህዝቡን ለዳግም ምጽአቱ
በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ እንዲካተት የሚፈልገው ይህንን ነው።
ራሳችንን ከኢየሱስ ጋር በማነፃፀር፣ በልዩነቱ በቀላሉ ተስፋ
ልንቆርጥ እንችላለን።
ታዲያ በመስቀሉ ላይ ማተኮር እና
የመስቀሉን ትርጉም መረዳት ከኢየሱስ ጋር ሲነጻጸር በራሳችን
ውስጥ በምናየው ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚጠብቀን እንዴት ነው?
የማትሞት ነፍስ ያለው አካል አለን የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ስለ ሰው አካል የተለያዩ
ንድፈ ሐሳቦችን ፈጥሯል። ለምሳሌ ለጥንቶቹ የግሪክ ፈላስፎች የሰው አካል
የነፍስ እስር ቤት ነበር፤ ከዚያም በሞት ነፃ ይወጣል። ይህንን የአረማውያን
ፅንሰ-ሀሳብ በማስተጋባት ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች አካላችን በትንሣኤ ጊዜ
ከሥጋ ጋር የሚዋሐድ የማትሞት ነፍስ ጊዜያዊ መኖሪያ እንደሆነ ያምናሉ።
በተቃራኒው የፓንቴይዝም እምነት ተከታዮች የሰውን አካል መለኮታዊ
ያደርጉታል፤ እግዚአብሔር እና አጽናፈ ሰማይ አንድ እና አንድ ናቸው ብለው
ያምናሉ። ለነሱ፣ ሁሉም ነገሮች አምላክ ናቸው እና የሰው አካል አንድ ነጠላ
የተቀናጀ እና ሁለንተናዊ የመለኮታዊ ንጥረ ነገር አካል ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ
እርስ በርስ በሚጋጩ ንድፈ ሐሳቦች ብንከበብም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው
ልጅ ተፈጥሮ በሚያስተምረው ነገር ላይ ጸንተን መቆም አለብን።
1ኛ ቆሮንቶስ 6:19-20 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 10:31ን ያንብቡ።
ሰውነታችን “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” እና “የመንፈስ
ቅዱስ ቤተ መቅደስ” መሆኑን መረዳታችን በአኗኗራችን ላይ በጎ
ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው?
አዳምና ሔዋን የተፈጠሩት በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ነው (ዘፍ. 1፡26፣
27) ይህም በባህሪያቸው ብቻ ሳይሆን በሥጋዊ ገጽታቸውም ተንጸባርቋል።
ያ ምስል በኃጢአት ምክንያት ተበላሽቶ አልፎ ተርፎም ተደብቆ ስለነበር፣
የመቤዠት ሥራ የሰውን ልጅ ከሕይወት ዛፍ መካፈል ባይችልም ሥጋዊ
ጤንነቱን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለስ ነው።
ይህ መታደስ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ የሚሞተውም
የማይሞት በሚሆንበት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ብቻ የሚጠናቀቅ የሕይወት
ሂደት ነው (1ኛቆሮ. 15፡53፣ 54)።
ሐዋርያው ዮሐንስ ለወዳጁ ለጋይዮስ እንዲህ ሲል ጽፎለታል፡- “ወዳጄ ሆይ፣
ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ
እጸልያለሁ።” 1 (ዮሐ. 3፡2)።
ሰው የማይከፋፈል አካል መሆኑን ከተገነዘብን እና ሀይማኖት ሁሉንም የሰው
ልጅ የህይወት ገፅታዎችን እንደሚይዝ ከተገነዘብን ስጋዊ ጤንነታችንንም
እንደ ሀይማኖታዊ ግዴታ ልንመለከተው ይገባል። “የምትበሉ ወይም
የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር
ክብር አድርጉት።” (1ኛ ቆሮ. 10፡31) በሚለው ቅዱስ መመሪያ ልንመራ
ይገባናል። ነገር ግን አሁንም የምንኖረው መልካም ሰዎች የተቻላቸውን ሁሉ
በሚያደርጉበት ነገር ግን በኃጢአተኛ ሰብዓዊ ተፈጥሮ እና በኃጢአተኞች
መከበባቸው በሚያስከትለው መዘዝ ምክንያት በሚሰቃዩበት ዓለም ውስጥ
እንዳለን ያስታውሱ። ስለዚህ በእግዚአብሔር ታምነን የምንችለውን ሁሉ
ማድረግ ይኖርብናል ውጤቱንም ለእግዚአብሔር እንተዋለን።
አንዳንድ ሰዎች አካባቢውን በመለወጥ ግለሰቡ እንደሚለወጥ ያምናሉ።
በእርግጥ፣ ለፈተና የበለጠ እንድንጋለጥ ከሚያደርጉን ቦታዎችና ሁኔታዎች
መራቅ አለብን (መዝ. 1፡1፣ ምሳ. 5፡1-8)። ነገር ግን ከፈተና እና ከኃጢአት ጋር
ያለን ችግር ሊፈታ የሚችለው በልባችን (ወይም አእምሮአችን) በመለወጥ ብቻ
ነው። ክርስቶስ የጉዳዩን ዋና ነገር ሲገልፅ፡- “ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ
ክፉ አሳብ፥—ዝሙት፣ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥
ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸው፤” (ማር.
7:21-22) ብሎ ተናግሯል። ይህ ማለት ባህሪያችን እንዲለወጥ አእምሯችን
መለወጥ አለበት ማለት ነው።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 2:16፣ መዝሙረ
ዳዊት 24:3-4፣ ሮሜ 12:2፣ ፊልጵስዩስ 4:8፣ እና ቆላስይስ
3:2። “የክርስቶስን ልብ” መያዝ ሲባል ምን ማለት ነው?
ጌታ በ“አዲሱ ኪዳን” ሕጉን በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ አስቀምጦ በልባቸውም
እንደሚጽፈው ቃል ገብቶ ነበር (ኤር. 31፡31–33ን ከዕብ. 8፡8–10ና ዕብ. 10፡
16 ጋር ያነፃፅሩ)። እንግዲህ፣ በተራራ ስብከቱ፣ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን
ትእዛዛት ወደ አስተሳሰቦች እና ሀሳቦች ደረጃ ማስፋቱ እና ጥልቅ ማድረጉ
ሊያስደንቅ አይገባም (ማቴ. 5፡17-48 ይመልከቱ)። ስለዚህ፣ በፈተና ላይ
ድልን ልናገኝ የምንችለው በሚለውጠው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው፤
እናም በአስተሳሰብ እና በዓላማ ደረጃ ያንን የተስፋ ቃል በመጠየቅ ኃጢአተኛ
አስተሳሰቦችን ማስቆም እንችላለን።
በዚህ ሕይወት ውስጥ፣ ምንም እንኳን
የቱንም ያህል ታማኝ ብንሆን፣ ፈጽሞ ኃጢአት የለሽነት ደረጃ ላይ መድረስ
አንችልም። በክርስቶስ ከሆንን ግን ሙሉ በሙሉ በእርሱ ፅድቅ ተሸፍነናል።
እኛ ገና ፍጹማን ባንሆንም፣ በእርሱ ውስጥ እንደ ፍጹም ተቆጥረናል (ፊልጵ.
3፡12-15)። “ከክርስቶስ ጋር አንድ ስንሆን የክርስቶስ አስተሳሰብ ይኖረናል።
ንጽህና እና ፍቅር በባህሪያችን ውስጥ ይበራሉ፣ የዋህነት እና እውነት
ህይወታችንን ይቆጣጠራሉ። የፊት ገጽታችን ራሱ ይለወጣል። ክርስቶስ
በነፍስ ውስጥ ሲኖር የመለወጥ ኃይል አለው፤ ውጫዊው ገጽታ ደግሞ በውስጥ
ስለሚገዛው ሰላምና ደስታ ይመሰክራል።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ የተመረጡ
መልእክቶች፣ መጽሐፍ 1፣ ገጽ. 337.
በየዕለቱ ራስን በመስጠት፣ በየቀኑ ለራስ በመሞት፣ በዕለት ተዕለት ቁርጠኝነት፣
በእምነት፣ ለኢየሱስ በመታዘዝ ብቻ ይህን የመሰለ ለውጥ በሕይወታችን
ውስጥ ማግኘት እንችላለን።
የኃጢአት አስተሳሰቦችን እንኳን ማቆም ከቻሉ ሕይወትዎ ምን
እንደሚመስል ያስቡ። ሕይወትዎ ምን ያህል የተለየ ይሆናል?
ይህ የእርስዎ ተሞክሮ እንዲሆን ብቸኛው መንገድ ምንድን ነው?
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባችን ውስጥ የሚያፈስስ
የእግዚአብሔር ኃያል ወኪል ነው (ሮሜ. 5፡5)። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነተኛ
የመዳን ልምምድ ይመራናል (ዮሐ. 16፡7-11)፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል
(ዮሐ. 16) 13)፣ እናም የወንጌልን ተልእኮ እንድንፈጽም ኃይል ይሰጠናል
(ሐዋ. 1፡8)። እየፈራረሰ የሚሄደውን የሰይጣን ሥራ የሚቃወመው መንፈስ
ቅዱስ ስለሆነ ሰይጣን በምንም መንገድ ስለ መንፈስ ቅዱስ ተፈጥሮና ሥራ
ያለንን ግንዛቤ ለማጣመም ቢሞክር አያስደንቅም። አንዳንዶች የእርሱን
ማንነት ሲክዱ፣ ሌሎች ደግሞ ከመለወጥ ኃይሉ በላይ የመንፈስ ስጦታዎች
ላይ ያተኩራሉ።
የሐዋርያት ሥራ 8:4-24ን ያንብቡ። የሰማርያው ጠንቋይ ስምዖን
የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በመንፈስ ሳይታደስ መቀበል ፈለገ።
በዘመናችን ይህ ተመሳሳይ አስተሳሰብ እየታየ ያለው እንዴት ነው?
የእግዚአብሔር ልጆች ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ሁሉ (ዮሐ. 16፡
13፣ ዮሐ. 17፡17) በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ (ሮሜ 8፡14) ናቸው። ኢየሱስ
በግልጽ ሲያሰጠነቅቅ፣ “በሰማይ ያለውን ያባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ
ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም። “በዚያ
ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን?
በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’
ይሉኛል።በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ
በግልጽ እነግራቸዋለሁ።”(ማቴ. 7:21–23)። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ እሱ
ራሱ ካነሳሳው ከቃሉ በተቃራኒ ማንንም አይመራም - ይልቁንም ሁልጊዜ
ከዚያ ቃል ጋር እንድንስማማ ይመራናል።
ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን ያው መንፈስ ቅዱስ ሌሎችን ወደዚያ አስደናቂ
እውነት እንድንመራም ኃይል ይሰጠናል (ማቴ. 28፡18–20፣ ሐዋ. 1፡8)።
ቅዱሱን ተልእኳችንን በምንፈጽምበት ጊዜ፣ የእርሱ ልዩ እርዳታ ከጎናች
አለልን። ስለዚህ በየጠዋቱ በጌታ ፊት ተንበርክከን ለእርሱ ለመቀደስ
የገባነውን ቃል ማደስ አለብን። ይህን ካደረግን እርሱ በመንፈሱ አማካኝነት
የሚያነቃቃና የሚቀድስ ኃይል ይሰጠናል።
እኛ ግን ትክክለኛ እንደሆነ የምናውቀውን ለማድረግ እና ስህተት መሆኑን
ከምናውቀው ነገር ለመራቅ በየእለቱ በማስተዋል ምርጫዎችን በማድረግ
ለእርሱ አመራር ክፍት መሆን አለብን። ማለትም፣ እግዚአብሔር በሚሰጠን
ጥንካሬ፣ መኖር እንዳለብን ለመኖር ስንሻ እግዚአብሔር ቃል የገባልንን
የመንፈስ ቅዱስን ኃይል በህይወታችን ለመቀበል ክፍት እንሆናለን።
በየጠዋቱ እራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ክፍት በማድረግ
መጸለይ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
የምንኖረው ብዙ ሰው ሰራሽ ፍላጎቶች በሞሉበትና ትኩረትን በሚስብ ዓለም
ውስጥ ነው። ካልተጠነቀቅን እነዚህ ሁሉ ጊዜያችንን ሊወስዱና ቅድሚያ
የምንሰጣቸውን ነገሮች ሊያጣምሙ ይችላሉ። ይህ የእኛ የተሳሰረ የቴክኖሎጂ
ዓለም ሌላ ውጤት አይደለም፤ በየትኛውም ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች፣ በአንድም
ሆነ በሌላ መልኩ በዚህ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች
ሰይጣን እነሱን ለማዘናጋት ከሚያደርገው ጥረት መጠንቀቅ አለባቸው።
ካልተጠነቀቀ ከጌታ ርቆ በመመልከት፣ በዓለማዊና ሥጋዊ ነገሮች
ላይ በማተኮር በመጨረሻ ሊያረኩ በማይችሉ ነገሮች የማይጠመድ
እናም በመጨረሻ ወደ መንፈሳዊ ጥፋት ሊያመራ የሚችል ስጋት
የማይገጥመው ማን ነው?
2ኛ ጴጥሮስ 3:14 እና 1 ዮሐንስ 3:1-3ን ያንብቡ። እራሳችንን
ለዳግም ምጽአቱ በማዘጋጀት እና ለዚያ ክቡር ክስተት በመዘጋጀት
መካከል ምን ልዩነት እናያለን?
ብዙ ጊዜ ለዳግም ምጽአት ቀጣይነት ያለው ዝግጅት ማድረግ አለብን የሚለው ኃሳብ ዝግጅትን ለነገ ለማለት ሰበብ ይሆናል። ይህ አስተሳሰብ እንደዚያ ክፉ አገልጋይ “ጌታዬ ይዘገያል” (ማቴ. 24፡48) ብለን በቀላሉ ዘና እንድንል ሊያደርገን ይችላል። መዝሙር 95:7-8፣ ዕብራውያን 3:7፣ 8፣15፣ እና ዕብራውያን 4፡7ን ያንብቡ። አሁን ስለመዘጋጀት እነዚህ ጥቅሶች ምን እያሉን ነው?
ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተያይ አንፃር የመዳን ጊዜ ሁልጊዜ “ዛሬ” እንጂ ነገ
አይሆንም (መዝ. 95፡7፣ 8፤ ዕብ. 3፡7፣ 8፣ 15፤ ዕብ. 4፡7)። በተጨማሪም
ዋና ለውጥ እስካልተደረገ ድረስ፣ አሁን እንዳለነው እንቀጥላለን። ጊዜ ራሱ
ያልተለወጠውን አይለውጥም። አንድ ሰው ያለማቋረጥ በጸጋ እያደገ ካልሆነ፣
እና በእምነቱ ወደፊት ካልገፋ፣ ዝንባሌው መውደቅ፣ መደንደን፣ መጠራጠር፣
አልፎ ተርፎም አለማመን ነው።
ከዚህ አንፃር እያንዳንዱ የህይወታችን ቀን ትንሹ ህይወት ነው ማለት
እንችላለን። ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ስለወደፊቱ ማቀድ አለብን፣
ነገር ግን እያንዳንዱን ቀን ለኢየሱስ መምጣት ዝግጁ ሆነን መኖር አለብን—
በተለይም በዚህ ህይወት ውስጥ ካሉት ድንገተኛ ሁኔታዎች አንጻር፣ ዛሬ
የእርስዎ የመጨረሻ ቀን ሊሆን ስለሚችል ነው።
ዛሬ የሚመለስ ቢሆን ለኢየሱስ መምጣት እንዴት ዝግጁ መሆን
ይችላሉ? መልስዎን በሰንበት ክፍልዎ ውስጥ ይወያዩ።
በኤለን ጂ. ኋይት ከተፃፈውና “የፈውስ አገልግሎት”
ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ “የአእምሮ ሕክምና” የሚል ርዕስ ያለውን
ምዕራፍ ያንብቡ። “የተቀደሰ ሕይወት” ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ
“የእውነተኛ እና ሐሰተኛ ንድፈ ሐሳቦች ንፅፅር” የሚል ርዕስ ያለውን
ምዕራፍ ያንብቡ።
“ታላቁ ተጋድሎ ወደ ማብቂያው ተቃርቧል። በባህርም ሆነ በየብስ የሚነገረው
እያንዳንዱ የጥፋት ዘገባ የሁሉም ነገር ፍጻሜ ቅርብ ለመሆኑ ምስክር ነው።
ጦርና የጦርነት ወሬ ይህንን ያውጃል። በፊታችን የሚገለጡትን ታላላቅ
ክንውኖች እያሰላሰለ የልብ ምቱ በፍጥነት የማይመታ ክርስቲያን አለ? ጌታ
እየመጣ ነው። ወደእኛ አየመጣ ያለ አምላክን የእግር ኮቴ እየሰማን ነው።”—
ኤለን ጂ. ኋይት፣ ማራናታ፣ ገጽ. 220.
“በየዕለቱ የእምነትን ህይወት ኑር። ስለመከራው ጊዜ አትጨነቅ ፣ ችግሩ
ሳይመጣ በራስህ ላይ ችግርን አትፍጠር። ‘በታላቁ የፈተና ቀን አልቆምም
ብዬ እፈራለሁ’ ብለህ አታስብ። የምትኖረው ዛሬን ብቻ ነው። ነገ ያንተ
አይደለም። ዛሬ በራስህ ላይ የተቀዳጀኸውን ድል ማስጠበቅ አለብህ። ዛሬ
የጸሎት ህይወት መኖር አለብህ። ዛሬ መልካሙን የእምነት ገድል መዋጋት
አለብህ። ዛሬ እግዚአብሔር እንደባረከህ ማመን አለብህ። እናም በጨለማ
እና ባለማመን ላይ ድልን ስትቀዳጅ የመምህሩን መስፈርቶች ታሟላለህ እናም
በዙሪያህ ላሉ ሰዎች በረከት ትሆናለህ።”—Ellen G. White፣ Signs of the
Times፣ October 20, 1887
“ጌታ በቅርቡ ይመጣል፣ እና እሱን በሰላም ለመገናኘት ዝግጁ መሆን አለብን።
በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ብርሃን ለመስጠት የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጥ
ውሳኔ እናድርግ። ደስተኞች መሆን እንጂ ማዘን የለብንም፤ እና ጌታ ኢየሱስን
ከፊታችን ልናየው ይገባል። . . . የእርሱን መገለጥ ለመጠባበቅ ዝግጁ መሆን
አለብን። ኦ፣ እርሱን ማየት፣ እና በእርሱ ለዳንን የሚደረግልን አቀባበል እንዴት
ያለ ክቡር ይሆን! ለረጅም ጊዜ ጠብቀን ነበር፤ ነገር ግን እምነታችን ሊዳከም
አይገባም። ንጉሱን በውበቱ ማየት ከቻልን ለዘላለም እና ለዘላለም ተባርከናል።
“ወደቤታችሁ ተመልከቱ” ብዬ መጮህ ያለብኝ ያህል ይሰማኛል፤ ክርስቶስ
የተቤዣቸውን ወደ ዘላለማዊ ቤታቸው ለመውሰድ በኃይልና በታላቅ ክብር
ወደሚመጣበት ጊዜ እየተቃረብን ነው።”—Ellen G. White, Heaven, p.
165, 166.
1. የሰው አካል፣ ነፍስና መንፈስ የማይነጣጠሉ መሆናቸውን
ማወቃችን የሃይማኖትን ሁሉን አቀፍነትና የግል አኗኗራችንን
አስፈላጊነት በተሻለ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?
2. ሁሉም እውነተኛ መነቃቃቶች እና ተሐድሶዎች ቲኦሴንትሪክ
ናቸው (እግዚአብሔርን ማዕከል ያደርጋሉ) እና በጭራሽ
አንትሮፖሴንትሪክ (በሰው ልጅ ባህሪ ላይ ያተኮሩ) አይደሉም።
የፈሪሳዊው እና የቀረጥ ሰብሳቢው ምሳሌ (ሉቃስ 18፡9–14)
ይህንን መሠረታዊ ሥርዓት የሚያሳየው እንዴት ነው?
3. በክፍልዎ ውስጥ በሐሙሱ ክፍልየመጨረሻ ጥያቄ መልስ
ላይ ይወያዩ። ዝግጁ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ? እና
በራሳችን ድምዳሜ ሳንሰጥ እርግጠኛ መሆን እንችላለን?