የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. 2፡1-11፤ ዮሐ. 4፡
46-54፤ ዮሐ. 5፡1-16፤ ማር. 3፡22፣ 23፤ ማቴ. 12፡9-14፤ ዮሐ. 5፡16-47።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ
ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።” (ዮሐ. 20፡30፣ 31)
ዮ
ሐንስ ወንጌሉን የጻፈው ለምንድን ነው? የኢየሱስን ተአምራት ለማጉላት ፈልጎ ይሆን?
ወይስ በተወሰኑት የኢየሱስ ትምህርቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ ነው? የጻፈውን ለመጻፍ
ምክንያት የሆነው ምን ነበር?
ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና ተጽዕኖ ሥር ሆኖ ምክንያቱን ያስረዳል። ስለ ክርስቶስ
ሕይወት ብዙ ተጨማሪ ነገሮች ሊጻፉ ቢችሉም (ዮሐ. 21:25) እርሱ በጻፋቸው ውስጥ የተካተቱት
ታሪኮች “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ” ነው (ዮሐ. 20፡31)።
በዚህ ሳምንት በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የሱስ ካደረጋቸው ተአምራቶች መካከል
ጥቂቶቹን፣ ማለትም ውሃውን ወደ ወይን ከቀየረበት ሠርግ አንስቶ የአንድ ሰውን በጣም
የታመመ ልጅ ወደ ቀድሞ የጤና ሁኔታ እስከመለሰበትና፣ እንዲሁም በቤተ ሳይዳ መጠመቂያ
ስፍራ የነበረውን ሰው እስከ ፈወሰበት ድረስ እንመለከታለን።
ዮሐንስ እነዚህን ተአምራቶች “ምልክቶች” በማለት ይጠራቸዋል። እርሱ ይህንን ሲል፣
ልክ በመንገድ ዳር ላይ እንዳለ ምልክት ሳይሆን ይልቁንም ወደ ጥልቅ እውነታ የሚያመላክት
ተአምራዊ ክስተት ነው ማለቱ ነው፤ ይሄም ኢየሱስ መሲሕ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። በእነዚህ
ሁሉ ዘገባዎች ውስጥ፣ በእምነት ምላሽ የሰጡትን የሰዎችን ምሳሌዎች እንመለከታለን።
ምሳሌዎቻቸውም እኛም እንዲሁ እንድናደርግ ይጋብዙናል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለመስከረም 25 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዮሐንስ 2፡1-11ን ያንብቡ። ኢየሱስ በቃና ያደረገውና ደቀ መዛሙርቱ እርሱን ወደማመን እንዲመጡ የረዳቸው ምን ነበር?
ኢየሱስ ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ ተአምር ሲሠራ መመልከቱ፣ ደቀ መዛሙርቱ
ኢየሱስን ለመከተል ያደረጉትን ውሳኔ የሚደግፍ ማስረጃ እንዲቀርብ አድርጓል። ይህ እንዴት
እርሱን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነ የሚያመላክት ኃይለኛ ምልክት ሊሆን አይችልም? (ምን
አልባት እነርሱ በዚያ ሰዓት እርሱ አምላክ መሆኑን ለመረዳት ገና ዝግጁ አልነበሩም ይሆናል)
ሙሴ የእስራኤላውያን መሪ ነበር፣ እናም እስራኤላውያንን በብዙ “ምልክት ተዓምራትም”
ከግብፅ አወጣቸው (ዘዳ. 6፡22፣ ዘዳ. 26፡8)። እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፃውያን ነፃ
ለማውጣት የተጠቀመው እርሱን ነው (እርሱ በተወሰነ መልኩ “አዳኛቸው” ነበር)።
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል፣ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ እንደሚመጣ ትንቢት ተናግሯል።
እርሱንም እንዲሰሙት እግዚአብሔር እስራኤልን ጠይቋቸው ነበር (ዘዳ. 18፡15፣ ማቴ. 17፡
5፣ የሐዋ. ሥራ 7፡37)። ያ “ነቢይ” ኢየሱስ ነበር እናም በዮሐንስ 2፣ የሱስ የእስራኤል ልጆች
ከግብፅ ነፃ መውጣታቸውን የሚያመላክተውን የመጀመሪያውን ምልክቱን አድርጓል።
የአባይ ወንዝ ለግብፃውያን ቁልፍ ሐብትና እንዲሁም አምላክ ነበር። አንደኛው
መቅሰፍት በወንዙ ላይ ነበር፤ ውሃን ወደ ደም በመቀየር ተፈጽሟል። በቃና የሱስም ተመሳሳይ
ተአምር አደረገ፤ ነገር ግን ውሃውን ወደ ደም ከመቀየር ይልቅ ወደ ወይን ለወጠው።
ውሃው የመጣው በአይሁድ የኃይማኖት ሥርዓቶች ውስጥ ለመንጻት ከሚውሉ
ስድስት የውኃ ጋኖች ሲሆን ይህም ተአምሩን የበለጠ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን ጭብጦች
ጋር የሚያያዝ አድርጎታል። ዮሐንስ ውኃውን ወደ ወይን ወደ ለወጠበት ሁኔታ በማመላከትና ወደ
ዘጸአት መለስ ብሎ በመጥቀስ፣ የሱስ አዳኛችን መሆኑን እየጠቆመ ነበር።
የበዓሉ አለቃ ኢየሱስ ስላዘጋጀው ያልፈላ [አልኮል የሌለበት] ወይን ምን ነበር ያሰበው?
በእርግጥም ኢየሱስ በዚያ ያደረገውን ተአምር ባለማወቅ እና ምርጡን ወይን ለመጨረሻው
ጊዜ ደብቀው እንዳቆዩ በማሰብ በመጠጡ ጥራት ተገርሞ ነበር።
የግሪክ ቃል የሆነው “ኦኢኖስ” (“oinos”) ጥቅም ላይ የሚውለው አዲስ
ለተጨመቀና ለፈላ የወይን ጭማቂ ነው። (The Seventh-day Adventist Bible
Dictionary, p. 1177 ይመልከቱ) ኤለን ጂ ዋይት በተአምር የተፈጠረው ጭማቂ የአልኮል
መጠጥ እንዳልነበረ ተናግራለች። (“የሠርግ ግብዣ” የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 135 ይመልከቱ)
የሆነውን ነገር ያወቁት ሰዎች በተፈጠረው ነገር እንደተገረሙ ምንም ጥርጥር የለውም።
የሱስን የምትከተሉባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው? (ብዙ ተሰጥቶናል አይደል?
አልተሰጠንም እንዴ?)
ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ፣ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ የረዳቸውን ተአምራት አድርጓል። ዮሐንስ እነዚህን ተአምራት ዘገበ፤ ይህም ሌሎች በኢየሱስ ያምኑ ዘንድ ነው። ዮሐንስ 4:46-54ን ያንብቡ። ወንጌላዊው ለምንድን ነው በሠርጉ ግብዣ ላይ ወደ ተፈፀመው ጉዳይ በመመለስ ግንኙነት የሚፈጥረው?
ዮሐንስ ኢየሱስ በገሊላ ስላደረገው ሁለተኛ ምልክት በሚናገርበት ጊዜ፣ በቃና ሠርግ
ላይ ወደተደረገው የመጀመሪያው ምልክት ይጠቁማል። ዮሐንስ ኢየሱስ ያደረጋቸው ምልክቶች፣
ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ እንድታዩ ይረዳችኋል የሚል ይመስላል። ከዚያም አክሎ “ይህም ደግሞ
ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛ ምልክት ነው” ይላል (ዮሐ. 4:54)።
በመጀመሪያ፣ ኢየሱስ ለመኳንንቱ ልመና የሰጠው ምላሽ ከባድ ሊመስል ይችላል።
ሆኖም ይህ ባለሥልጣን የልጁ መፈወስ በኢየሱስ ለማመን መስፈርት እንዲሆን አድርጓል።
ኢየሱስ የልቡን አንብቦ፣ ከልጁ ለሕይወት አስጊ ከሆነው አካላዊ ሕመም የበለጠ ከባድ
የሆነውን መንፈሳዊ ሕመም ጠቁሟል። ከሰማይ እንደሚወርድ የመብረቅ ብልጭታ፣ ሰውዬው
በድንገት መንፈሳዊ ድህነቱ የልጁን ሕይወት ሊያጠፋ እንደሚችል ተገነዘበ።
ተአምራቶች በራሳቸው ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን እንደማያረጋገጡ ማወቅ አስፈላጊ
ነው። ሌሎችም ተአምራትን አድርገዋልና። አንዳንዶቹ እውነተኛ ነቢያት ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ
ሐሰተኞች ነበሩ። ተአምራቶች ከተፈጥሮ በላይ (ውጭ) የሆነ ነገር መኖሩን ብቻ ይገልጣሉ፤ ነገር
ግን የግድ እግዚአብሔር ያደርጋቸው ናቸው ማለት አይደለም። (“ተአምራቶች” ስንል ከተፈጥሮ
በላይ የሆኑ ድርጊቶች ናቸው የምንል ከሆነ ሰይጣንም “ተአምራት” ማድረግ ይችላል)።
የተጨነቀው መኳንንት ልጁን እንዲፈውስለት በመለመን ራሱን በኢየሱስ ምህረት ሥር
ጣለ። የኢየሱስ ምላሽ የሚያጽናና ነበር። እርሱም፡- “ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ አለው” (ዮሐ.
4:50)። “አለ” የሚለው በግሪኩ ቋንቋ የአሁን ግስ ነው። አጠቃቀሙም “የወደፊት ጊዜ” ተብሎ
ሲጠቀስ፣ ወደፊት ሊሆን ያለው ክስተት አሁን እንደተከሰተ በእርግጠኝነት ሲነገር ማለት ነው።
ሰውዬው ወደ ቤቱ አልተጣደፈም፣ ነገር ግን ኢየሱስን አምኖ በማግስቱ ወደ ቤቱ ገባ፤ የሱስ
እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ ትኩሳቱ ልጁን ለቆት እንደሄደም ተረዳ።
ይህ በኢየሱስ ለማመን እንዴት ያለ ጠንካራ ምክንያት ነው!
ተአምር ብንመለከትም እንኳን፣ ተአምሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሆነ
ከመገመታችን በፊት ምን ሌሎች መመዘኛዎችን መመልከት ይኖርብናል?
ዮሐንስ የዘገበው ሁለተኛው ምልክት በቤተሳይዳ መጠመቂያ አጠገብ የተከናወነ
ነበር። (ዮሐ. 5፡1-9)። አንድ መልአክ ውሃውን በሚያንቀሳቅስበት ጊዜ ወደ ውሃ ውስጥ
የሚገባው የመጀመሪያው ታማሚ ሰው እንደሚድን ይታመን ነበር። በዚህም ምክንያት
የመጠመቂያው ሥፍራ ውሃው ቀጥሎ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ለመፈወስ ተስፋ በሚያደርጉ
ሰዎች ተጨናንቆ ነበር። ኢየሱስ ወደ የሩሳሌም በሄደበት ጊዜ፣ በመጠመቂያው አጠገብ
ሲያልፍ የሚጠባበቁትን ሰዎች አየ።
እንዴት ያለ ትእይንት ይሆን! እነዚህ ሁሉ ሰዎች፣ አንዳንዶቹም በጠና የታመሙ
በእርግጠኝነት ከውሃው ውስጥ የማይመጣን ፈውስ እየተጠባበቁ ነበር። ለኢየሱስ እንዴት ያለ
አጋጣሚ ይሆን!
ዮሐንስ 5:1-9ን ያንብቡ። በመጠመቂያው አጠገብ ያለ ማንኛውም ሰው ለመዳን
እንደሚፈልግ ግልጽ ሆኖ ሳለ፣ ኢየሱስ ሽባውን መፈወስ ይፈልግ እንደሆነ ለምን
ጠየቀው (ዮሐንስ 5: 6)?
እንግዳ ቢመስልም፣ አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ሲታመም ህመሙ የተለመደ ይሆንና አካል
ጉዳተኝነት ወደ ኋላ መተው ትንሽ ሊረብሽ የሚችል ሐሳብ ሊሆንበት ይችላል። ሰውዬው በመልሱ
ውስጥ ፈውስ እንደሚፈልግ ይጠቁማል። ችግሩ የሰውን እግር የሠራው ከፊት ለፊቱ ቆሞ ሳለ
ከተሳሳተ ቦታ ፈውስን መፈለጉ ነው። ምንም እንኳን ከፈውሱ በኋላ ኢየሱስ በእርግጥም ልዩ ሰው
መሆኑን መረዳት ጀምሮ ሊሆን ቢችልም፣ ሰውዬው ከእርሱ ጋር እየተነጋገረ ያለው ሰው ማን እንደሆነ
እምብዛም አያውቅም ነበር።
“የሱስ በስቃይ ላይ የነበረውን ሰው በእርሱ ላይ ያለውን እምነት እንዲገልጽ
አልጠየቀውም። እንዲሁ “ተነሥ አልጋህን ተሸክምና ሂድ” አለው። ሰውየው ቃሉን በእምነት
ተቀበለ። በእያንዳንዱ የስሜት መስመርና ጡንቻ አዲስ የሕይወት ስሜት ሰረጸበት፣ ስንኩል
የነበሩት እጅና እግሮቹም ጤነኛ ሆኑ። የክርስቶስን ትእዛዝ ያለ አንዳች ጥያቄ አከበረ፣
ጡንቻዎቹም ታዘዙት። ብድግ ብሎ በመቆም ሙሉ ጤነኛ ሰው መሆኑን አወቀ። … የሱስ ስለ
መለኮታዊ ዕርዳታ የሰጠው ማረጋገጫ አልነበረም። ሰውየው በመጠራጠር የመፈወስ ዕድሉን ሊያጣ ይችል ነበር። ነገር ግን የክርስቶስን ቃል በማመንና እምነቱንም በተግባር በመግለጹ
ብርታትን አገኘ” (ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 190)።
ኢየሱስ በኋላ ላይ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሰውዬውን አገኘውና “እነሆ፥ ድነሃል፤
ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው” (ዮሐ. 5፡14)።
በሕመም እና በኃጢአት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? ሁሉም ሕመም
በሕይወታችን ውስጥ ሊዘረዘሩ ከሚችሉ ኃጢአቶች የተነሳ በቀጥታ የሚመጡ
እንዳልሆኑ መረዳት ያለብን ደግሞ ለምንድን ነው?
ምልክቶች፣ ድንቆች እና ተአምራቶች በራሳቸው አንድ ነገር ከእግዚአብሔር መሆኑን አያረጋግጡም። ነገር ግን በሌላ በኩል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲሆኑ ሳለ፣ እነርሱን አለመቀበል አደገኛ ነገር ነው። ዮሐንስ 5:10–16ን ያንብቡ። የኃይማኖት መሪዎቹ ኢየሱስን እና እርሱ ያደረገውን ተአምር በተመለከተ ስላሳዩት አስደናቂ ልበ ደንዳናነት ምን ትምህርት ልንወስድ እንችላለን?
ኢየሱስ ለተፈወሰው ሰው ራሱን ሲገልጥ ሰውዬው ወዲያውኑ የፈወሰው ኢየሱስ
መሆኑን ለኃይማኖት መሪዎች ነገራቸው። አንድ ሰው ይህ ጊዜ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት
ምክንያት ነው ብሎ ያስብ ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህ ይልቅ መሪዎቹ “ስለዚህም በሰንበት ይህን
ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር” (ዮሐንስ 5፡16)።
በሰንበት ቀን ፈውስ የሚፈቀደው በድንገተኛ ጊዜ ብቻ ነበር። ይህ ሰው ለ 38 ዓመታት
አካል ጉዳተኛ ነበር፤ ስለዚህም ፈውሱ የድንገተኛ ጊዜ አልነበረም። ደግሞ አልጋውን ተሸክሞ
እንዲወስድ የማድረግ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው? እንዲህ ያለ ተአምር ለማድረግ ከእግዚአብሔር
ኃይል ያለው ሰው፣ በሰንበት ቀን አልጋውን ወደ ቤት መሸከም ይፈቀድ እንደሆነ ያውቃል ብሎ
አንድ ሰው ያስብ ይሆናል። ኢየሱስ በግልጽ በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ እውነተኛውን እምነትን
ከሚከለክሉ ሰው ሠራሽ ሕጎችና መመሪያዎች ውጭ ወደ ሆነው ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ
እውነቶች ሰዎችን ሊወስዳቸው ፈልጎ ነበር።
እነዚህ ሌሎች ዘገባዎች፣ ማስረጃው ምንም ይሁን ምን፣ ሰዎች መንፈሳዊ
በሆነው ነገር እንዴት ልበ ደንዳና ሊሆኑ ስለሚችሉበት ሁኔታ ያስተምራሉ? (ዮሐ.
9:1-16፣ ማር. 3:22፣ 23፣ ማቴ. 12:9-14)
እነዚህ የኃይማኖት መሪዎች እንዴት ይህን ያህል ዕውር ሊሆኑ ቻሉ? መልሱ ብልሹ
ከሆነው ልባቸው የተነሳ፣ መሲሑ ከሮም እንደሚያድናቸው በማመናቸው እና ለሥልጣን ባላቸው
ፍቅር እና ለእግዚአብሔር ባለመገዛታቸው ነው የሚል ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሁሉ በፊታቸው
የቆመውን እውነት እንዳይቀበሉ አድርጓቸዋል።
ዮሐንስ 5:38-42ን ያንብቡ። የኢየሱስ ማስጠንቀቂያ ምን ነበር? ከእነዚህ ቃላት
ምን እንማራለን? ማለትም፣ ማወቅ ያለብንን እና በሕይወታችን ላይ ተግባራዊ
ማድረግ የሚገባንን እውነት እንዳንቀበል ሊያሳውረን የሚችለው ምን ሊሆን ይችላል?
በቤተሳይዳ መጥመቂያ የተፈፀመው ተአምር፣ ለዮሐንስ ኢየሱስ ማን እንደሆነ አጽንኦት እንዲሰጥ ጥሩ አጋጣሚ ፈጠረለት። ዮሐንስ ተአምሩን ለመግለፅ ዘጠኝ ቁጥሮችን ወስዶ ወደ 40 የሚጠጉ ቁጥሮች ደግሞ (ከዚህ በታች ይመልከቱ) ተአምሩን የሠራውን ማንነት ለመግለጽ ተጠቅሟል። ዮሐንስ 5:16–18ን ያንብቡ። የሱስ በሰንበት ባደረገው ድርጊቱ ለምን ስደት ደረሰበት?
ዮሐንስ 5፡18 ኢየሱስ ሰንበትን እያፈረሰ ነው ስለሚል የሚረብሽ ጥቅስ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ዮሐንስ 5፡16-18ን ጠለቅ ብለን ስንመረምር ኢየሱስ የሰንበት “ሥራው” ከአባቱ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር የሚስማማ መሆኑን መናገሩን ያሳያል። እግዚአብሔር ሕዋን በሰንበት መደገፉን አያቆምም። ስለዚህ የኢየሱስ የሰንበት ተግባሩ ስለ መለኮት የይገባኛል ጥያቄም ጭምር ነው ማለት ይቻላል። የኃይማኖት መሪዎች፣ ሰንበትን ሽሯል እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር እኩልነት ይገባኛል ብሏል ብለው በማሰብ አሳደዱት። ዮሐንስ 5:19-47ን ያንብቡ። ኢየሱስ ባደረገው ተአምር በጠንካራ ሁኔታ በተረጋገጠው የይገባኛል ጥያቄ፣ መሪዎቹ እርሱን በእውነተኛ ማንነቱን እንዲያዩት ለመርዳት ሲል ምን እያለ ነበር?
ኢየሱስ ድርጊቱን በሦስት ደረጃዎች ይከላከላል። በመጀመሪያ ከአብ ጋር ያለውን
የጠበቀ ግንኙነት ያስረዳል (ዮሐ. 5፡19-30)። ኢየሱስ እርሱ እና አባቱ ተስማምተው
እንደሚሠሩና የሱስም የመፍረድም ሆነ ሙታንን የማስነሳት ኃይል ያለው እንደሆነ አመላክቷል
(ዮሐ. 5፡25-30)።
ሁለተኛ፣ ኢየሱስ መከላከያውን ፈጥኖ በማከታተል አራት “ምሥክሮችን” ይጠራል፤
መጥምቁ ዮሐንስን (ዮሐ. 5፡31-35) የሱስ ያደረጋቸውን ተአምራቶች (ዮሐ. 5: 36)፣
አብን (ዮሐ. 5: 37-38) እና ቅዱሳት መጻሕፍትን (ዮሐንስ 5:39)። እነዚህ “ምሥክሮች”
እያንዳንዳቸው ኢየሱስን በመደገፍ ይመሰክራሉ።
በመጨረሻም፣ በዮሐንስ 5፡40-47፣ ኢየሱስ በእርሱ አገልግሎት እና በእነርሱ የራስን
ነገር በመሻት መካከል ያለውን ልዩነት በመግለጥ፣ በከሳሾቹ ፊት የራሳቸውን ኩነኔ አቅርቦላቸዋል።
ይህም ኩነኔያቸው ተስፋቸውን ካደረጉበት ከሙሴ እንደሚመጣ ተናግሯል (ዮሐ. 5፡45-47)።
በእግዚአብሔር በማመን፣ ትክክለኛ የሆኑትን አስተምሕሮዎች እንኳን በመያዝ፣ ነገር
ግን ሙሉ በሙሉ ለክርስቶስ ባለመገዛት ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ እንዴት መጠንቀቅ
እንችላለን? መልሳችሁን በሰንበት ቀን ወደ ጥናት ቡድናችሁ ይዛችሁ ኑ።
“የሱስ [ለሽባው ሰው] ስለ መለኮታዊ ዕርዳታ የሰጠው ማረጋገጫ አልነበረም። ሰውየው በመጠራጠር የመፈወስ ዕድሉን ሊያጣ ይችል ነበር። ነገር ግን የክርስቶስን ቃል በማመንና እምነቱንም በተግባር በመግለጹ ብርታትን አገኘ።”
“በዚያው ዓይነት እምነት እኛም መንፈሳዊ ፈውስ ማግኘት እንችላለን። በኃጢአት
ምክንያት እግዚአብሔር ከሰጠን ሕይወት ተቋርጠናል። ነፍሳችን ሰሏል። ሽባው ሰው መራመድ
እንዳልቻለ ሁሉ እኛም በራሳችን ኃይል የተቀደሰ ሕይወት መኖር አንችልም። … እነዚህ ተስፋ
የቆረጡ ተፍጨርጫሪዎች ቀና ብለው ወደ ላይ ይመልከቱ። አዳኛችን በደሙ በገዛቸው ላይ
ጎንበስ ብሎ በአንደበት ሊገለጽ በማይቻል ርኅራኄ “መዳን ትፈልጋለህን?” ይላል፣ በጤናና ሰላም
እንድትነሳ ያዝሃል። ጤንነትህ [ሙሉ መሆንህ] እስኪሰማህ ድረስ አትጠብቅ። ቃሉን እመን
ይፈጸምልሃል። ፈቃድህን ለክርስቶስ ስጥ። እርሱን ለማገልገል ፈቃደኛ ከሆንህና በቃሉም
መሠረት ከሠራህ ብርታት ታገኛለህ። ሥራችን ምንም ያህል የከፋ ቢሆንና የረጅም ጊዜ ሥጋዊ
ፍትወት ሥጋንና ነፍስን አዋህዶ ቢያስርም ቅሉ ክርስቶስ ነጻ ሊያወጣን ይናፍቃል፣ ይችላልም።
በኃጢአት የሞተችን ነፍስ ሕይወት ይዘራባታል (ኤፌ. 2፡1)። በደካማነት፣ በመጥፎ አጋጣሚና
በኃጢአት ሰንሰለት የታሰሩትን ሁሉ ክርስቶስ አርነት ያወጣቸዋል።” (ኤለን ጂ ዋይት፣ የዘመናት
ምኞት፣ ገጽ 190-191)።
“የሱስ እግዚአብሔርን ሰድበሃል ተብሎ የቀረበበትን ክስ ተቃወመ። አድርገሃል ብላችሁ
የተከሰስሁበትን ሥራ ለመፈጸም ሥልጣኑን ያገኘሁት የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኔ እርሱና እኔ
በባሕርይ፣ በአስተሳሰብና በዓላማ አንድ ስለሆነን ነው አላቸው” (ኤለን ጂ ዋይት፣ የዘመናት
ምኞት፣ 197)።
1. በዚህን ሳምንት ትምህርት ላይ ሐሳባችሁን አንፀባርቁ። እነዚህ ፈውሶች
እውን እንዲሆኑ ያደረገው ቁልፍ ነገር እምነት ነበር። መሪዎቹ በተቃራኒው
የጥርጣሬ እና የአለማመንን አደጋዎች ምን እንደሆኑ ገልፀዋል። ለምንድን
ነው ጥያቄዎቻችንን (ሁላችንም ሊኖረን የሚችለውን) ከመጠራጠር ጋራ ግራ
ማጋባት የሌለብን? ሁለቱ አንድ ዓይነት እንዳልሆኑ እና በመካከላቸው ያለውን
ልዩነት ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
2. የሐሙሱን የመጨረሻ ጥያቄ ተመልከቱ። ለምንድን ነው፣ እንደ ሰባተኛ
ቀን አድቬንቲስቶች፣ በተለይ ስለዚህ አደጋ መጠንቀቅ ያለብን? ለምሳሌ
ትክክለኛውን የሰንበት ቀን ማወቅ እና ማክበር፣ ወይም ስለ ሙታን (ነፍስ)
ሁኔታ ማወቅ ምንም ያህል አስፈላጊ ቢሆኑም፣ እነዚህ እውነቶች የማያድኑት
ለምንድን ነው? የሚያድነን ምንድን ነው፣ እንዴትስ ያድነናል?
3. ዮሐንስ 5:47ን በጥንቃቄ ተመልከቱ። ለምሳሌ ያህል፣ የጥፋት ውኃን ዓለም
አቀፋዊነት ወይም የስድስት ቀን ፍጥረትን የሚክዱ ሰዎች፣ ልክ ኢየሱስ በዚህ
ሥፍራ እንዳስጠነቀቀው ያለ ስሕተት ዛሬ እየፈጸሙ ያሉት እንዴት ነው?