መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከጥቅምት 4-10

ሶስተኛ ትምህርት

October 14 - 20
 

የሰብዓዊ ሰው ሁኔታ

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ሮሜ 1:16, 17, 22–32; 2:1–10, 17–23; 3:1, 2, 10–18, 23ን ያንብቡ፡፡

 

የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ - “ሁሉም በድለዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል፡፡ ” (ሮሜ 3:23)

በ ሮሜ መጽሐፍ መጀመሪያ ጳውሎስ አንድ በጣም አስፈላጊና የወንጌል እምብርት የሆነ እውነት፣ እርሱም ስለ ሰዎች ሁኔታ አስረግጦ በእውነት ላይ እንዲመሰረት ለማድረግ ጥሯል፡፡ ይህ እውነት ይኖራል ምክንያቱም ከውድቀት በኋላ ሁላችንም በኃጢአት ተበክለናል፡፡ ልክ እንደ ዓይናችን ቀለም ከደም ሥሮቻችን ጋር ተዋህደዋል፡፡

ማርቲን ሉተር በሮሜ መጽሐፍ ላይ በሰጠው አስተያየት እንዲህ ብሏል፤ “ሁሉም በድሏል የሚለው በመንፈሳዊ አገላለጽ ሰዎች በሰዎች ፊት ወይም በሌሎች ሰዎች ፊት ኃጢአተኛ ሆነው ስለመታየታቸው ሳይሆን በእግዚአብሔር እይታ በእርሱ ፊት ምን እንደሚመስሉ ለማመልከት ነው፡፡ በደላቸው በሰዎች ፊት የታየ ቢሆን ወይም በራሳቸውና በሌሎች እይታ መልካም መስለው የሚታዩ ሁሉም በኃጢአት ሥር ናቸው ማለት ነው፡፡ ዝግጁና ፈቃደኛ ከሆነ ልብ ሳይሆን ውጫዊ መልካም ሥራን ቅጣትን ፍራቻ የሚያደርጉ ወይም ክብርን ስለሚወዱ ወይም አንድ ነገር ስለሚያስደስታቸው የሚያከናውኑትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሰዎች ውጫዊ የሆነን መልካም ስራ ይለማመዳሉ ነገር ግን በውስጡ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ፍላጎትና ክፉ ምኞት የተዘፈቀ ሲሆን ይህም መልካም ሥራን ከማድረግ ጋር እጅጉን የሚቃረን ነው፡፡” —Martin Luther, Commentary on Romans, p. 69.

ለጥቅምት 11 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
 

ጥቅምት 5
October 15
 

የእግዚአብሔር ኃይል

 

“በወንጌል አላፍርምና አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞ ለግሪክ ሰው ለሚያመምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡” (ሮሜ 1፡16- 17) ለእርስዎ ምን ይላል? በእነዚህ ቁጥሮች የሚገኘውን ተስፋ እንዴት ተለማመዱት?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በዚህ ንባብ ውስጥ ጥቂት ቁልፍ የሆኑ ቃላት ይገኛሉ፡-

1. ወንጌል: ይህ ቃል የመጣው ከግሪኩ ‹‹ጥሩ መልእክት›› ወይም ‹‹መልካምዜና›› ከሚለው ቃል ነው ፡፡ ቃሉ ለብቻው ሲቆም ማንኛውንም መልካም መልእክት ሊወክል ይችላል፣ ነገር ግን በዚህ አውድ እንደተገለጸው የክርስቶስ ከሚለው ሐረግ ጋር የተያያዘ በመሆኑ መልካሙ ዜና የሚለው የሚወክለው ‹‹የመሲሁን መልካም ዜና ነው›› ክርስቶስ የሚለው የግሪኩ ቃል ‹‹ መሲህ›› ለሚለው የተሰጠ ትርጉም ነው፡፡ ይህም መልካም ዜና መሲሁ ስለመጣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ይድናል የሚል ነው፡፡ አንድ ሰው መዳንን የሚያገኘው ፍጹም በሆነው በክርስቶስ ጽድቅ እንጂ፣ በራሳችን ወይም በእግዚአብሔር ህግ ማንም ድነትን አያገኝም፡፡

2. ጽድቅ: ይህ ቃል የሚያሳየው ከእግዚአብሔር ጋር መስማማትን ነው ፡፡ ለየት ያለው የዚህ ቃል ትርጉም የሮሜን መጽሐፍ ማጥናት ስንቀጥል ወደፊት ይመጣል፡፡ በሮሜ 1፣ 17 እንደተመለከተው ይህ ቃል ‹‹የእግዚአብሔር›› በሚለው ሐረግ ተገልጾዋል፡፡ ይህ ጽድቅ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ሲሆን የሚሰጠው እግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡ የዘላላምን ህይወት ተስፋ ሊያመጣልን የሚችል ብቃት ያለው ብቸኛ ጽድቅ ይህ ብቻ ነው፡፡

3. እምነት: ‹‹እመን›› እና ‹‹ እምነት›› ተብለው የተተረጎሙ የግርክ ቃላት አንዱ ቃል ራሱ ነው፡፡ ቃሉም pisteuo (እመን) pistis (ማመን ወይም እምነት):: እምነት የሚለው ቃል ትርጉም የሮሜን መጽሐፍ ማጥናት ስንቀጥል የበለጠ ይስተዋላል ፡፡

እርግጠኛ ስለመሆን ተጨንቀው ያውቃሉ? ድኛለሁ ወይም እድናለሁ የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቀው ያውቃሉ? ይህንን ፍርሃት የሚያመጣው ምንድን ነው? እነዚህ በምን ላይ የተመሰረቱ ናቸው? በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ናቸውን? ያ ማለት የሚኖሩት ከክርስትናዎ ጋር የማይስማማ አኗኗር ነውን? እንዲህ ከሆነ በክርስቶስ ያለዎትን ተስፋና ዋስትና የራስዎ ለማድረግ ምን ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ?
 

ጥቅምት 6
October 16
 

ሁሉም በድለዋል

 

ሮሜ 3:23ን ያንብቡ፡፡ ዛሬ ላለን ክርስትያኖች ይህንን መልዕክት ማመን በጣም ቀላል የሚሆነው ለምንድነው? በተመሳሰይ መልኩ አንዳንድ ሰዎች የዚህን ጥቅስ እውነተኛነት እንዲጠይቁ የሚያደርጋቸው ምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

አስገራሚ በሆነ መልኩ አንዳንድ ሰዎች ፣ ሰው እኮ በመሠረቱ ጥሩ ነበር በሚል ክርክር ስለ ሰዎች ኃጢአት መጸሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለመከራከር ይሞክራሉ፡፡ ይህም የሚመነጨው ትክክለኛውን መልካምነት ካለማወቅ ነው፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ከሌላው ሰው ጋር ያወዳድሩና እኔ የተሻልኩ ነኝ ብለው ያስባሉ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሁልጊዜ ለመወዳደር የምንችላቸውን ከእኛ የባሱ ሰዎችን እናገኛለን፡፡ ነገር ግን ራሳችንን ከእግዚአብሔር ቅድስናና ጽድቅ ጋር ስናነፃፅር ማናችንም ራሳችንን ከመጥላትና በጣም ከማፈር ስሜት ውጪ ምንም የምንለው አይኖረንም፡፡

ሮሜ 3፡23 ስለ ‹‹እግዚአብሔር ክብር›› ይናገራል፡፡ ይህ ሀረግ በተለያየ መልኩ ተተርጉሟል፡፡ ምናልባትም በጣም ቀላሉ ትርጉም በ1ቆሮ. 11፣7 ላይ ‹‹ወንድ የእግዚአብሔር ክብርና ምሳሌ›› የሚለው ትርጉም ሊሆን ይችላል፡፡ ቀለል ባለ መልኩ በግሪክ ‹‹ክብር›› እና ‹‹አምሳል›› የሚለውን ትርጉም የሰጠው ቃል ተመሳሳይ ነው፡፡ ኃጢአት በሰው የነበረውን የእግዚአብሔርን አምሳል አበላሽቶታል፡፡ ኃጢአተኛ የሆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብርና አምሳል ማንጸባረቅ ተስኗቸዋል፡

ሮሜ 3:10-18ን ያንብቡ፡፡ ዛሬ የተለወጠ ነገር አለ? ክርስቶስ በህይወትዎ ባይኖር ምን ይሆን ነበር?

እንደ መጥፎነታችን ጉዳያችን ተስፋ -ቢስ አይደለም፡፡ የመጀመርያው ነገር ኃጢአተኞችና ለራሳችን ረዳተ-ቢሶች ምንም ማድረግ የማንችል መሆናችንን መቀበል ነው፡፡ ይህንን አይነት አስተሳሰብ ሊሰጠን የሚችለው መንፈስ ቅዱስና ሥራውም የእርሱ ነው፡፡ ኃጢአተኛው እምቢ ካላለው በቀር መንፈስ ቅዱስ ራስን የመከላከል ጭንብልን፣ ማስመሰልን እና ራስን ጻድቅ ማድረግን ከእርሱ አስወግዶ ራሱን ወይም ራሷን በክርስቶስ ላይ በመጣል ‹‹ጌታ ሆይ ማረኝ›› ‹‹እኔ ኃጢአተኛ›› ነኝ በማለት እንዲማጸን ያደርገዋል፡፡ (ሉቃስ 8:13)፡፡

ስለ ሥራዎ፣ ምኞትዎና ስለሚሰማዎት ነገር በደንብ ወደ ራስዎ የተመለከቱት መቼ ነበር ? ይህ ተስፋ አስቆራጭ ልምምድ ሊሆን ይችላል አይደል? የእርሰዎ ተስፋ ምንድነው?
 

ጥቅምት 7
October 17
 

መሻሻል (ዕድገት)?

 

በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ አካባቢ ሰዎች የሰብዓዊ ዘር ሁኔታ እየተሻሻለ ነው ፣ ስለዚህ ግብረ-ገብ ይሻሻላል፣ ሰላማዊ የኑሮን ሥፍራ በመፍጠሩ ሂደት ሳይንስ ብዙ ይጠቅማል የሚል አመለካከት ነበራቸው፡፡ የሰው ልጆች ሁኔታ ወደ ፍጽምና ሊያደርስ በሚችል ጎዳና ላይ ነው ተብሎ ታምኖ ነበር ፡፡በትክክለኛ ትምህርትና የግብረ-ገብ ሥልጠና ሰዎች ራሳቸውንና ህብረተሰባቸውን በከፍተኛ ደረጃ ይለውጣሉ ተብሎ ታምኖ ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ድንቁ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደገባ መከሰት ይጀምራሉ ተበሎ ታስቦ ነበር፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ እነዚህ ሁሉ ይከሰታሉ የተባሉ ነገሮች ወደ ታሰበው አቅጣጫ አልመጡም፡፡ ሆነ እንዴ? ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታሪክ ከሁሉ እጅግ የከፋ ወንጀል የበዛበት በመሆኑ ሳይንሳዊ ግኝቶች ምስጋና ይግባቸውና እጅግ መጥፎና ክፉ አስተሳሰብ የነበራቸው የጥንቶቹ ሰዎች ሊያስቡት(ሊያልሙት) ከሚችሉት በላይ ብዙ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ለማጥፋት የሚቻልበትን ዘዴ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡ ችግሩ ምን ነበር?

ሮሜ 1፡22-23ን ያንብቡ፡፡ ይህ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው ዛሬ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እየታየ ያለው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በክርስትና ውስጥ የሚገኙ ብዙ ነገሮችን ለማመን እምነት ያስፈልገናል፣ ከእነዚህም መካከል የሙታን ትንሳኤ፣ ዳግም ምጻት እና አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚሉ ሀሳቦች ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን ስለ ሰብዓዊ ዘር ውድቀት ለማመን እምነት የሚያስፈልገው ማን ነው? ምክንያቱም ዛሬ እያንዳንዳችን የምንኖረው የሰው ውድቀት ባመጣው ውጤት ላይ ነው፡፡

በተለይም በሮሜ 1፡22-23 ላይ ትኩረት ያድርጉ፡፡ ይህ መርህ በዚህ ስፍራ እንዴት ተገለጸ? በእኛ ዘመን ሰዎች እግዚአብሔርን በመተው እያመለኩ ያሉትና ጣዖት ያደረጉት ነገር ምንድነው? እንዲህ በማድረጋቸው ምን ያህል ተሞኝተዋል? መልስዎን ወደ ሰንበት ትምህርት ክፍል ያምጡ፡፡

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

 

ጥቅምት 8
October 18
 

የአይሁድና የአህዛብ የጋራ የሆነው ነገር

 

በሮሜ 1 ላይ ጳውሎስ እያተኮረ ያለው ከረዥም ጊዜ በፊት ከእግዚአብሔር በመለየታቸው በጣም የወረደና አሳፋሪ የሆኑ ልምምዶች ስለነበሯቸው የአህዛብና አረማውያን ኃጢአት ነበር፡፡

ነገር ግን የራሱ የሆኑ ሰዎች ከወጥመዱ አላመለጡም፡፡ ከተሰጣቸው እጅግ ብዙ ከሆኑ እድሎች (ሮሜ 3፡ 1) አንጻር እነርሱም ጭምር ኃጢአተኞችና ከህግ በታች በመሆናቸው አዳኙ የክርስቶስ ጸጋ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ኃጢአተኛ እንደመሆናቸው፣ የእግዚአብሔርን ህግ በመተላለፋቸው እንዲሁም አዳኙ የክርስቶስ ጸጋ በማስፈለጉ አይሁድም አህዛብም እኩል ናቸው፡፡

ሮሜ 2:1–3, 17–24ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ እያስጠነቀቀ ያለው ከምንድነው? ከዚህ ማስጠንቀቂያ ሁላችንም አይሁድ ሆንን ወይም አህዛብ ልንወስደው የምንችለው ትምህርት ምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

‹‹ሐዋሪያው አህዛብ ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ከገለጸ በኋላ በተለየና ትኩረት ባለው ሁኔታ አይሁድ ሁሉ ህጉን የሚታዘዙት ለታይታ በውጫዊ ገጽታ እንደ ፊደል እንጂ በመንፈስ ባለመሆኑ በኃጢአት እየኖሩ መሆናቸውን አሳይቷል፡፡›› —Martin Luther, Commentary on Romans, p. 61.

ብዙውን ጊዜ የሌሎችን ኃጢአት መናገር ወይም መጥቀስ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምን ያህል ጊዜ ነው እኛ ሌሎችን በምንወቅስበት ኃጢአት እና ከዚያም በከፋ ውስጥ የምንገኘው? ችግራችን ጉዳዩ የእኛ ሲሆን ዓይናችንን እንጨፍንና ስለ ራሳችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ራሳችንን ከሌሎች መጥፎ ሥራ ጋር እናወዳድራለን፡፡

ጳውሎስ እንዲህ አላደረገም፡፡ እርሱ የእርሱ ወገን የሆኑ አይሁዶችን በአህዛብ ላይ ለመፍረድ እንዳይቸኩሉ እነርሱ ራሳቸው የተመረጡ ሆነው እንኳ ኃጢአተኞች መሆናቸውን እየነገራቸው ነበር፡፡ ከተሰጣቸው ብዙ ብርሃን የተነሳ በአንዳንድ ሁኔታዎች ሲታይ ለመፍረድ ከሚቸኩሏቸው አህዛብ ይልቅ ኃጢአተኞች ሆነው ይገኛሉ ፡፡

በዚህ ሁሉ ንግግር ውስጥ የጳውሎስ ዋና ነጥብ ፣ ማናችንም ጻድቅ አለመሆናችንን ፣መለኮታዊ መስፈርትን ማናችንም ማሟላት እንደማንችል፣ ማናችንም በተፈጥሮ መልካም ወይም የወረስነው ጥሩ ባህሪይ የሌለን መሆኑን ማሳየት ነው፡፡ አይሁድ ይሁን አረማዊ፣ ወንድ ወይም ሴት፣ ሀብታም ወይም ደሃ፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ ወይም የሚቃወም፣ ሁላችንም ተፈርዶብናል፡፡ በወንጌል እንደተገለጸው የእግዚአብሄር ጸጋ ባይሆን ኖሮ ለማናችንም ምንም ተስፋ ባልኖረ ነበር፡፡

በራስዎ አእምሮ ውስጥ ብቻ እንኳ ራስዎ ስለሚያደርጉት ኃጢአት ሌሎችን ኮንነው የሚያውቁት ምን ያህል ጊዜ ነው? በዚህ ሥፍራ ጳውሎስ የጻፈውን በመውሰድ እንዴት መለወጥ ይችላሉ?

ጥቅምት 9
October 19

ወንጌልና ንሰሐ

 

"ወይስ የእግዚአብሄር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግስቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?" (ሮሜ 2፡4) በዚህ ሥፈራ ስለ ንስሐ ባለን ማንኛውም ጥያቄ ላይ የተሰጠን መልዕክት ምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ማስተዋል ያለብን ነገር የእግዚአብሔር መልካምነት ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ይመራል አንጂ አያስገድድም፡፡ እግዚአብሔር አያስገድድምና፡፡ እርሱ ወሰን የለሽ ትዕግስት ባለቤት በመሆኑ ሁሉን በፍቅር ወደ ራሱ መሳብ ይፈልጋል፡፡ ንስሐ በግድ ሲሆን የንሐሰን ትርጉም ሙሉ ዋጋ -ቢስ ያደርገዋል፡፡ እግዚአብሔር ለንሰሐ የሚያስገድድ ቢሆን ኖሮ አንዳንዶቹን አስገድዶ ሌሎቹን ለምን ይተዋቸዋል? ሁሉም አይድኑም ነበር? ንሰሐ በህይወታችን ውስጥ ለሚመላለሰው የእግዚአብሔር መንፈስ በፈቃድ ራስን ማስገዛት ነው፡፡ አዎ ንስሐ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው ነገር ግን እኛ ብቻ ለራሳችን በምናደርገው ትልቅ ምርጫ በፈቃዳችን ልንቀበለው ዝግጁዎች መሆን ያስፈልገናል፡፡

የእግዚአብሔርን ፍቅር እምቢ በማለት ንስሐ ሳይገቡ በእምቢተኝነት የሚቀጥሉ ት ላይ ምን ይመጣል? (ሮሜ 2:5–10)::

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በሮሜ 2፡5-10 እና በተደጋጋሚ በሮሜ መጽሐፍ ጳውሎስ የመልካም ሥራን አስፈላጊነት ይናገራል፡፡ ጽድቅ በእምነት እንጂ በህግ ስራ አይደለም ማለት ሥራ በክርስትያን ህይወት ምንም ቦታ የለውም ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በሮሜ 2፡ 7 መዳን ለሚፈልጉት እንደሚሆን ተገልጿል ፡፡ ‹‹በበጎ ሥራ በመጽናት ›› ፡፡ ምንም እንኳ የሰው ጥረት ደህንነትን ባያመጣም ፣ህግን መፈጸም ግን ከአጠቃላይ የደህንነት ልምምዶች አንዱ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ ሰው ሥራና ተግባር ለደህንነታችን ምንም አስፈላጊ አይደሉም የሚል ሀሳብ ይዞ ለመምጣት በጣም ከባድ ነው፡፡ ከፈቃደኛ ልብ የሚመነጭ እውነተኛ ንስሐን ተከትሎ የሚመጣው ነገር ሁልጊዜ ንስሐ እንድንገባ ያደረገንን ተግባር ለመተው የሚደረግ ውሳኔ ነው፡፡

እርስዎ በንስሐ ዝንባሌ ውስጥ የሚገኙት ምን ያህል ጊዜ ነው? ከእውነተኛ ልብ ነው ወይም ስህተትዎን ለመሸፈን ያህል ነው? መልስዎ የኋለኛው ከሆነ እንዴት ሊለወጡ ይችላሉ?
 

ጥቅምት 10
October 20
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

“መጸሐፍ ቅዱሳዊ አጠራሩ እንደሚያሳየው ኃጢአት በሰው ልጆች ላይ ሳያውቁት የወደቀ መቅሰፍት ሳይሆን የዝንባሌውና የምርጫው እንዲሁም የድርጊቱ ውጤት ነው፡፡ በተጨማሪ ኃጢአት የመልካም ነገር መታጣት ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚጠብቀው ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡ እርሱ ሰዎች እያወቁ መርጠው የሚፈጽሙት ክፉ ድርጊት ነው፡፡ እርሱም የሰው ልጆች መፈጸም ስለማይችሉ በኃላፊነት የማይጠየቁበት ሳይሆን ሰዎች በምርጫቸው እያወቁ ህጉን ባለመታዘዝ በእግዚአብሔር ላይ የሚያምጹበት፣ እናም የእርሱን ቃል አለመስማት ነው፡፡ ኃጢአት እግዚአብሄር ያስቀመጠውን ገደብ ማለፍ ነው፡፡ በአጭሩ ኃጢአት በእግዚአብሄር ለይ ማመጽ ነው፡፡” —The Handbook of Seventh-day Adventist Theology (Hagerstown, Md.: Review and Herald Publishing Association, 2000), p. 239.

“አሳዛኝ የሆነውን የዓለማችንን ሁኔታ እንዳይ በፊቴ ቀረበልኝ፡፡ የግብረ-ገብ ውድቀት በየሥፍራው ይታያል፡፡ የወሲብ ልቅነት የዘመኑ መገለጫ ነው ፡፡ ማታለል እንደዚህ ዘመን በግልጽ የተበላሸ ማንነቱን ከፍ አድርጎ አያውቅም ፡፡ ህዝቦች ግድየለሽ እና ታይታን የሚወዱ ይመስላሉ፡፡ እውነተኛው መልካምነት፣ ግልጽነት፣ እና ጥንካሬ ወዲያ ተጥለዋል፡፡ ክህደት በዘባቾችና ባላመኑ ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ የክርስቶስ ሃይማኖት ተከታይ ነን የሚሉ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ኃጢአተኞች ናቸው፡፡ የእርሱን ዳግም ምጻት እንጠባበቃለን የሚሉ እንኳ ከሰይጣን በተሻለ ራሳቸውን አላዘጋጁም፡፡ ከብክለቶች ሁሉ ራሳቸውን አላነጹም፡፡ እስከ አሁን ራሳቸውን ሲያገለግሉ ኖረዋል ፣ ምኞት በእነርሱ አመለካከት ቀላል እና ተፈጥሮአዊ ነገር ነው፡፡ የሚያስቡት ሁሉ ተበላሽቷል፡፡.” —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 2, p. 346.

 

የውይይት ጥያቄዎች፡

 

  1. የሆነው ነገር ሁሉ ቢሆን የሰው ሁኔታ እየተሸሻለ ነው ለሚሉ ምን መልስ ይሰጣሉ? እነርሱ የሚያቀርቡት መከራከሪያ ምንድነው? የእርስዎ ምላሽስ?

  2. በዓርብ ቀኑ ትምህርት ላይ የተሰጠውን የኤሌን ዋይት ጥቅስ ይመልከቱ፡፡ ራስዎን በዚያ ውስጥ ካገኙ መልሱ ምን ይሆናል ? ተስፋ ቆርጦ መተው የማያስፈልገው ለምንድነው? ነገር ግን መጀመሪያ ለይቅርታ ፣ ቀጥሎ ለመንጻት የእግዚአብሔርን ተስፋዎች የሙጥኝ ማለት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የእኔ ነገር አበቃ የሚል ማነው ? እኔ በጣም ኃጢአተኛ ነኝ፡፡ እኔ በፍጹም ልድን አልችልም፣ ስለዚህ ተስፋዬን ልቁረጥ፡፡ ‹‹ እኔም አልፈርድብሽም ደግመሽ ኃጥአት አትስሪ›› ዮሐ 8፡11 የሚለውን የክርስቶስን ቃል ትሰማለህን?

  3. እንደ ክርስትያን መሰረታዊ የሆነውን የሰውን ኃጢአተኝነት ማስተዋል አስፈላጊ የሚሆነው ለምነድነው? የዚህን አሳዛኝ እውነታ ምንነት ሳናስተውል ስንቀር ምን ይፈጠራል ? እውነተኛ ባህሪያችንን አለማስተዋል ወደ ምን ስህተት ይመራናል?

  4. እምነታቸውን ላለመተው ሲሉ የሞቱትን ከቁጥር በላይ የሆኑ ፕሮቴስታንቶችን ያስቧቸው፡፡ እኛ በእምነታችን ምን ያህል ጠንካሮች ነን? ለእምነታችን እስክንሞት ጣንካሮች ነን?