መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከጥቅምት 18-24

አምስተኛ ትምህርት

October 28–November 3
 

የአብረሃም እምነት

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- ዘፍ. 15:6; 2 ሳሙ. 11, 12; ሮሜ 3:20, 31; 4:1–17; ገላ. 3:21 –23; 1 ዮሐ. 3:4ን ያንብቡ፡፡

 

የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ እንግዲህ ህግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም ህግን እናጸናለን እንጂ ” (ሮሜ 3፡31)

ብዙ መንገዶች ሮሜ ምዕራፍ 4 ድነት በእምነት ብቻ ለሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት መሰረት የጣለ እና የተሃድሶ መነሻ የነበረ ነው፡፡ በእርግጥም የዛሬ 500 ዓመት ገደማ በዚህ ሳምንት በሉተር የተጀመረና ታማኝ ፕሮቴስታንቶች ወደ ኋላ ያልተመለሱበት ጉዳይ ነው፡፡

አብረሃምን እንደ ቅድስና ተምሳሌት እና ትክክለኛ ጽኑ ባህርይ ያለው መሆኑን በመውሰድ እና በጸጋ እንጂ በሥራው እንደማይጸድቅ በማሳየት ጳውሎስ አንባቢዎቹን ለማስተዋል እንዲቸገሩ በሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ አልተወም፡፡ በጣም ጥሩ ናቸው የምንላቸው ሰዎች ሥራና ህግን መጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅን ለማስገኘት በቂ ካልሆነ፣ ሌላ ማንኛውም ሰው ምን ተስፋ አለው? ድነት ለአብረሃም በጸጋ ከሆነ ለሁሉም አይሁድ ሆነ ግሪክ ተመሳሳይ ነው፡፡

ጰውሎስ በሮሜ 4 ላይ የመዳንን እቅድ 3 ዋና ዋና ደረጃዎችን ይገልጻል፡፡

(1) መለኮታዊውን በረከት ተስፋ (የጸጋ ተስፋ) (2) የሰብአዊ ዘር ለተስፋው የሚሰጠው ምላሽ (የእምነት ምላሽ)፣ እና (3ኛ) መለኮት ለሚያምኑት የቆጠረላቸውን ጽድቅ ማወጅ (ጽድቅ)፡፡ ለአብረሃም የተደረገለት እንዲህ ስለሆነ ለእኛም የሚደረግልን እንዲህ ነው፡፡

መዳን በጸጋ እንደሆነ ማስታወስ ለጳውሎስ በጣም አስፈላጊ ነበር፡፡ ይህም ሳይገባን የተሰጠን ነው፡፡ የተገባን ሆኖ ቢሰጠን መመለስ ይጠበቅብን ነበር፣ ከዚያም ስጦታ መሆኑ ቀርቶ ዕዳ ይሆን ነበር፡፡ እንደ ወዳቂዎችና ኃጢአተኞች መዳን፣ ሥጦታ ነው፡፡

መዳን በእምነት ብቻ የሚለውን ለማረጋገጥ ወደ ዘፍጥረት 15፡6 ይሄዳል፡፡ ‹‹አብረሃምም አመነ ጽደቅም ሆኖ ተቆጠረለት›› ጽድቅ በሃይማኖት በቀደሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚገኘው እዚህ ነው፡፡

*ለጥቅምት 25 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
 

ጥቅምት 19
October 29
 

ህጉ

 

ሮሜ 3፡31ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ሥፈራ ጳውሎስ ማንሳት የፈለገው ነጥብ ምንድነው? ይህ ነጥብ ለአድቬንቲስቶች አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በዚህ ንባብ ጳውሎስ ትኩረት ሰጥቶ እየገለጸ ያለው እምነት ህግን ውድቅ እንደማያደርግ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ህግ አክባሪዎች በሙሉ ህግን ቢጠብቁም ነገር ግን ህግ መጠበቃቸው ሊያድናቸው አልቻለም፡፡ ልክ እንደ አዲስ ኪዳኑ ሁሉ የብሉይ ኪዳንም ሃይማኖት ቢሆን ሁልጊዜ ለኃጢአተኞች በእምነት የተሰጠ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው፡፡

ሮሜ 4:1–8ን ያንብቡ፡፡ ይህ ጥቅስ በብሉይ ኪዳንም እንኳ መዳን ህግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት እንደሆነ የሚያሳየን እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

እንደ ብሉይ ኪዳን ትረካ፣ አብረሃም ጻድቅ ሆኖ የተቆጠረው ‹‹በእግዚአብሔር ስላመነ›› ነው፡፡ሐ ስለዚህ ብሉይ ኪዳንም ስለ ጽድቅ በሃይማኖት ያስተምር ነበር፡፡ ስለዚህ ማንኛውም እምነትን የሚመለከት ጉዳይ ህግን ውድቅ ያደርጋል ማለት ውሸት ነው፡፡ በመሆኑም ጽድቅ በሃይማኖት የብሉይ ኪዳን ትልቁ ትምህርት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በሁሉም ስፍራ የጸጋ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ለምሳሌ የቤተ መቅደስ አገልገሎቶች በሙሉ አንድ ኃጢአተኛ በስራው ሳይሆን በምትኩ በሚሞተው እንስሳ አማካይነት መዳኑ ጸጋን ያመለክት ነበር፡፡

ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ካደረገው ምግባረ- ብልሹ ተግባር በኋላ የተደረገለት ምህረት ምንን ይገልጻል? በእርግጥም እርሱን ያዳነው ህግን መጠበቁ አይደለም፣ ምክንያቱም በተለያየ መልኩ ሊያስፈርድበት በሚችል ሁኔታ ህግን ተላልፏል፡፡ ዳዊት ህግን በመጠበቅ የሚድን ቢሆን ኖሮ እርሱ በፍጹም ባልዳነ ነበር፡፡

የዳዊት ወደ መለኮታዊ ምህረት ሥር መመለስን ጳውሎስ የጽድቅ በእምነት ምሳሌ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ይቅርታ የእግዚአብሔር ጸጋ ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ስፈራ እንደገና በብሉይ ኪዳን የተጻፈውን የጽድቅ በኃይማኖት ምሳሌ እንመለከታለን፡፡ ምንም እንኳ በጥንት ዘመን ብዙዎች ህግን በመጠበቅ እንድናለን የሚል አስተሳሳብ የነበራቸው ቢሆንም፣ የአይሁድ ኃይማኖት ግን ሁልጊዜ የጸጋ ኃይማኖት ነበር፡፡ ህጋዊነት የዚህ እምነት ስህተት ትርጓሜው እንጂ መሰረቱ አይደለም፡፡

ጥቂት ጊዜ በዳዊት ኃጢአትና ስለተደረገለት ምህረት ተነጋገሩ፡፡ (2ሳሙ. 11፡ 12፣ መዝ. 51) ከታሪኩ ለራስዎ ምን ዓይነት ተስፋ ያገኛሉ? በዚህ ሥፍራ በቤተክርስቲያናች የወደቁትን እንዴት መንከባከብ እንዳለብን ምን ትምህርት ይሰጠናል?
 

ጥቅምት 20
October 30
 

ዕዳ ወይስ ጸጋ?

 

ጰውሎስ በዚህ ስፍራ የሚያነሳቸው ጉዳዮች ከስነ-መለኮት ትምህርትነቱ ባሻገር የሚበልጥ ነገር አለበት፡፡ በዚህ ትምህርቱ ወደ ድነት ትምህርት ልብ እና ከእግዚአብሔር ጋር ወዳለን ዝምድና ዋና ነገር ያመራል፡፡ አንድ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት፣ ከመጽደቁና ይቅርታ ከማግኘቱ በፊት የተወሰነ የቅድስና ደረጃ ላይ መድረስ አለበት ብሎ ቢያምን ወደ ራሱ ተመልሶ ተግባሩን ለማየት ምንኛ ቀላል ነበር፡፡ ኃይማኖትም ሰው ለሚፈልገው ትልቁ ነገር ( ድነት) ከመጠን በላይ በራስ ላይ የሚያተኩር በሆነ ነበር፡፡

በተቃራኒው ግን፣ አንድ ሰው ድነት ሙሉ በሙሉ በሥራ የተገኘ ወይም ለሰው የተገባው ሳይሆን እንዲሁ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው የሚለውን መልካም ዜና ካስተዋለ ሰው በራስ በመተማመን ፋንታ ፊቱን ወደ እግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ለመመለስ ምን ያህል ቀላል በሆነ ነበር?

እና በመጨረሻ የእግዚአብሔርን ፍቅርና ባህርይ ለማንጸባረቅ የሚችለው የትኛው ነው? በራስ ላይ የሚያተኩር ወይስ ለእግዚአብሔር ሀሳብ የተገዛው?

ሮሜ 4፡ 6-8 ያንብቡ፡፡ በዚህ ስፍራ ጳውሎስ የጽድቅ በኃይማኖት ሀሳብን ያሰፋው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

“ኃጢአተኛው ወደ ክርስቶስ መምጣት አለበት፣ የራሱን ተግባር ወዲያ ትቶ፣ ኃጢአቱን ሊሸከምለት በሚችለው ላይ ጥሎ ይቅርታን መቀበል ያስፈልገዋል፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው ለዚሁ ተግባር ነበር፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ጽድቅ ንስሓ ለሚገባ አማኝ ይቆጠርለታል፡፡ እርሱም የንጉስ ቤተሰብ አባል ይሆናል፡፡” Ellen G. White, Selected Messages, book 1, p. 215.

በመቀጠልም ጳውሎስ በእምነት መዳን ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለአህዛብም ጭምር መሆኑን ገልጾዋል፡፡ (ሮሜ 4፡9-12)፡፡ የበለጠ ለማስተዋል ካስፈለገ አብረሃም አይሁዳዊ አልነበረም፣ የመጣው ከአረማውያን ነገደ-ዘር ነበር፡፡ (ኢያ. 24፡2)፡፡ በዚህ ዘመን የአይሁድና የአህዛብ ልዩነት አልነበረም፡፡ አብረሃም ጸድቋል( ዘፍ. 15፡6)፣ እርሱ እንዲያውም አልተገረዘም ነበር፡፡ ስለዚህ አብረሃም ለተገረዙትም ሆነ ላልተገረዙት አባት ሆኖአል፡፡ ለጳውሎስም የድነነትን ሁሉ- አቀፍነት ለማሳየት ትልቅ ምሳሌ በመሆን አገልግሏል፡፡ የክርስቶስ ሞትም በዘርና በወገን ልዩነት ያላደረገ ለሁሉ የሆነ ነበር (ዕብ. 2:9)፡፡

ሁሉን አቀፍ የሆነውን መስቀሉን ከግምት ውስጥ ስናስገባው ስለ ሰው ትልቅ ዋጋ ምን ይነግረናል? ይህን ስናስብ የወገናዊነት አባዜ እጅጉን ክፉ ነገር የሚሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔር ጸጋ ከአእምሮአችን የሚያስወግደው ቢሆንም፣ ስህተት የሆነ ግንዛቤ በውስጣችን መኖሩን የምናውቀው እንዴት ነው?
 

ጥቅምት 21
October 31
 

ተስፋው

 

ከ500 ዓመት በፊት በዚህ ቀን ነበር ማርቲን ሉተር 95 ነጥቦችን በዊተንበርግ ቤተክርስትያን ግድግዳ ላይ የሰቀለው፡፡ የዛሬ ትምህርትም የድነት በእምነት የሚለው ትምህርት ዋና ነጥብ መሆኑ እንዴት አስደናቂ ነው፡፡

በሮሜ 4፡16 ‹‹ተስፋ›› እና ‹‹ ህግ›› ተነጻጽሯል፡፡ ጳውሎስ ጽድቅ በኃይማኖትን ለማስተማር በብሉይ ኪዳን አውደ ታሪክ ላይ መሰረት መጣል ይፈልጋል፡፡ ጥሩ ምሳሌም ሁሉም አይሁዶች አባታችን ነው ብለው የሚያመኑትን አብረሃምን አገኘ፡፡ ተቀባይነትን ማግኘትና ጽድቅ ለአብረሃም የመጣለት እንደ ህግ ክፍል ሆኖ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለአብረሃም ‹‹ምድርን እንደሚወርስ›› ቃል ገብቶለት ነበር፡፡ አብረሃምም ይህንን አምኗል፣ በመሆኑም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ወስዷል፡፡

በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር እርሱን ተቀብሎት በእርሱ በኩል ዓለምን ለማዳን ሰርቷል፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ዘመን ጸጋ እንዴት ይሰራ እንደነበር ታላቅ ምሳሌ በመሆን ጳውሎስ ለምሳሌነት መጠቀሙ ትክክል እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡

ሮሜ 4:14–17ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ሥፍራ ጳውሎስ ጽድቅ በኃይማኖት በብሉይ ኪዳን ዋና ሃሳብ መሆኑን በማሳየት የሚቀጥለው እንዴት ነው? ገላ. 3:7–9ን ይመልከቱ፡፡

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በመጀመሪያ ለማስታወስ እንደሞከርነው ጳውሎስ እየጻፈ ያለው ለማን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ እነዚህ አይሁዶች በብሉይ ኪዳን ህግ በጣም ጠልቀው የገቡ ናቸው እናም ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳኑ አስተሳሳብ እንደዚህ ባይሆንም ይህንን ህግ በትክክል በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ አድርገው የሚያምኑ ነበሩ፡፡

ለዚህ ስህተት ለሆነ አስተሳሰብ ማስተካከያ በመፈለግ፣ አብረሃም ህጉ ከመሰጠቱ በፊት የነበረው እንኳ በቶራ (በአጠቃላይ የአይሁድ መተዳዳሪያ የሆኑትን ህጎች በሙሉ የሚያጠቃልል በመሆኑ ለመጠበቅ በጣም አስቸጋሪ ነበር) ወይም በህግ ሥራ ሳይሆን በእምነት መሆኑ ተስፋ ተሰጥቶት ነበር፡፡

በዚህ ሥፍራ ጳውሎስ እየተናገረ ያለው ስለ አሥርቱ ትዕዛዛት ቢሆን ኖሮ እነርሱም በመርህ ደረጃ ከሲና በፊት የነበሩ እንደመሆናቸው ነጥቡ ተመሳሳይ እንደሆነ ይቀጥላል፡፡ እንዲያውም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ፡፡ በህግ በኩል የእግዚአብሔርን ተስፋ ለመቀበል ማሰብ እምነትን ዋጋ ያሳጣዋል በማለት ይገልጸዋል፡፡ እነዚህ ጠንከር ያሉ ቃላት ናቸው ሆኖም ግን ነጥቡ እምነት ያድናል ህግ ግን ይኮንናል የሚለው ነው፡፡ እርሱ እየሞከረ ያለው በዚያው በሚኮንነው ህግ በራሱ ድነት ለማግኘት የመሞከርን አደገኝነት ነው፡፡ እኛ ሁላችንም፣ አይሁድ ሆንን አህዛብ ሁላችንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፈናል እና ሁላችንም አብርሃም ያስፈለገው ተመሳሰይ ነገር እኛም ያስፈልገናል፡፡ ወደ ፕሮቴስታንት ተሃድሶ የመራው ይህ እውነት፣ አዳኙ የክርስቶስ ጽድቅ በእምነት ለእኛ ተቆጥሮልናል፡፡
 

ጥቅምት 22
November 1
 

ህግና እምነት

 

ትናንትና እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ከአብረሃም ጋር በነበረው ሁኔታ መዳን የሚመጣው በጸጋው ተስፋ እንጂ በህግ አለመሆኑን ጳውሎስ አሳይቶናል፡፡ ስለዚህ አይሁዳውያን መዳን ከፈለጉ በራሳቸው ሥራ መታመንን ወዲያ ብለው አሁን በመሲሁ መምጣት ፍጻሜ ያገኘውን የአብረሃምን ተስፋ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረው ሥራ በቂ ነው ብሎ ለሚያስብ ማንኛውም ሰው አይሁድ ይሁን አህዛብ ነገሩ ተመሳሳይ ነው፡፡

“ሰው በሥራው ራሱን ለማዳን ይችላል የሚለው አስተምህሮ መሰረቱን ያደረገው በአረማውያን ኃይማኖት ላይ ነው፡፡ መነሻው የትም ይሁን የት ሰው ኃጢአቱን ሊሸከም የሚችል አቅም የለውም፡፡” —Ellen G. White, The Desire of Ages, pp. 35, 36:: ይህ ማለት ምን ማለት ነው?ራሳችንን በሥራችን ማዳን እንችላለን የሚለው አስተሳሳብ ወደ ኃጢአት በግልጽ የሚወስደን እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ጳውሎስ በገላትያ መጽሐፍ የህግንና የእምነትን ዝምድና የገለጸው እንዴት ነው? ገላ. 3:21–23::

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ህይወትን የሚያካፍል ህግ ቢኖር ኖሮ ያለ ጥርጥር እርሱ የእግዚአብሔር ህግ ይሆን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ማንኛውም ህግ ህይወት አይሰጥም፣ የእግዚአብሔርም ህግ ጭምር፣ ምክንያቱም ሁሉም ህግን ተላልፋዋል ስለዚህም ሁላቸውም በህጉ ተኮንነዋል፡፡

በክርስቶስ በኩል በሙላት የተገለጸውና የእምነት ተስፋ የሚያምኑትን ሁሉ ከህግ በታች ከመሆን ነጻ ያደርጋል፣ ይህም ከኩነኔና ድነትን በእርሱ በኩል ለማግኘት ከሚጫነው ሸክም ነጻ ያወጣል፡፡ ህግ ያለ እምነት፣ ያለ ጸጋ፣ በእምነት ከሚገኘው ጽድቅ ውጪ ሲቀርብ ሸክም ይሆናል፡፡ ከህግ በታች ማለት ከሸክምና በኃጢአት ኩነኔ በታች ማለት ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ሲራመዱ ሳለ ጽድቅ በእምነት ምን ያህል አስፈላጊ ነገር ነው? የዚህን እውነት እይታ ሌሎች እውነቶች እንዳይሸፍንዎ ምን ማድረግ ይችላሉ? በአጠቃለይ ያለዚህ መረዳት ሌሎች አስተምህሮዎች መልካምነታቸው ምን ያህል ነው?

ጥቅምት 23
November 2

ህጉና ኃጢአት

 

ብዙውን ጊዜ በአዲስ ኪዳን ህግ ተሸሯል የሚል ተረት እንሰማለን እናም ይህንን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጥቅሶች ይጠቅሳሉ፡፡ ከበስተጀርባው ያለው እሳቤ ግን ትክክለኛነትም ሆነ ስነ-መለኮታዊ እውነታ የለበትም፡፡

1ዮሐ. 2:3–6, 3:4፣ ሮሜ 3:20ን ያንብቡ፡፡ ይህ ጥቅስ ስለ ህግና ኃጢአት ዝምድና ምን ይነግረናል?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ከጥቂት መቶ ዓመታት በፊት አንድ ዮናታን የሚባል የአየርላንድ ጸሃፊ ‹‹ አንድ ሰው መጠጣት፣ ማጭበርበር፣ መስረቅ፣ መዋሸት የሚሉ ቃላት በፓርላማ ጸድቆ ከእንግሊዝኛ ቋንቋና ከመዝገበ ቃላት ተፍቀዋል ቢል በሚቀጥለው ቀን እያንዳንዱ ሰው ዝግ ያለ፣ ታማኝ፣ ቅን እና የእውነት ወዳጅ ይሆን ነበር? ›› —Jonathan Swift, A Modest Proposal and Other Satires (New York: Prometheus Books, 1995), p. 205.

በተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሔር ህግ ከተሻረ ታዲያ ለምንድነው መዋሸት ፣ መስረቅ ፣ መግደል ኃጢአት ወይም ትክክል ያልሆኑት? የእግዚአብሔር ህግ ተሸሮ ቢሆን የኃጢአትም ትርጓሜ በተቀየረ ነበር። ወይም የእግዚአብሔር ህግ ተወግዶ ቢሆን እንዲሁም ኃጢአት ደግሞ ቢጠፋ ይህ ያሳምነን ነበር፡፡ (1ዮሐ. 1፡7-10፣ ያዕ. 1፡14፣ 15ን ያንብቡ፡፡)

በአዲስ ኪዳን ህግና ወንጌል ሁለቱም ይታያል፡፡ ህጉ ኃጢአት ምን እንደሆነ ያስታውቃል፣ ወንጌል ደግሞ ወደ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ለኃጢአት ፈውስ ወደሚሆነው ያመላክታል፡፡ ህግ ባይኖር ኖሮ ፣ ኃጢአትም ባልኖረ ነበር ይህ ከሆነ ደግሞ መዳን ያስፈለገን ከምንድነው? በህግ አውድና ቀጣይ በሆነው ብቻ ወንጌል ትርጉም ያገኛል፡፡

ብዙ ጊዜ መስቀል ህግን ሽሮታል ሲባል እንሰማለን፡፡ ይህ ተቃራኒው ነው፣ ምክንያቱም መስቀል የሚያሳየው ህግ አለመቀየሩን ነው፡፡ እግዚአብሔር ከክርስቶስ የመስቀል ሞት በፊት ህግን ካልሻረ ወይም ካልለወጠ ከመስቀሉስ በኋላ ለምን ይቀይራል? ሰብአዊ ዘር ኃጢአትን በመስራትና ህግን በመተላለፍ ቅጣት ሳይበየንበት በፊት እግዚአብሔር ህግን ለምን አላስወገደውም? እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ክርስቶስ መሞት አያስፈልገውም ነበር፡፡ የክርስቶስ መስቀል የሚያሳየው ህግ መለወጥ ወይም መቀየር ቢኖርበት ከዚያ በፊት እንጂ ከዚያ በኋላ አለመሆኑን ነው፡፡ ህግ ባለመለወጡ ምክንያት ከተከሰተው ከክርስቶስ ሞት የበለጠ ምንም ነገር የህግን አስፈላጊነትና አለመለወጥ ሊነግረን አይችልም፡፡ እኛ እስከ ኃጢአታችን ተቀባይነት እንዲኖረን ህግ ተሸሮ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከመሰቀል የተሻለ አማራጭ አይሆንም ነበር?

አታመንዝር የሚል መለኮታዊ ህግ ባይኖር ኖሮ ፣ ድርጊቱ ለተጠቂዎቹ ችግሩና ህመሙ አሁን ከሚያመጣው የቀለለ ይሆን ነበር? የዚህ ጥያቄ ምላሽ ህግ እስከ አሁን ድረስ ተግባራዊ ስለመሆኑ ምን ይነግርዎታል? የእግዚአብሔርን ህግ በመተላለፍ የሚመጣውን ውጤት በሚመለከት የእርስዎ ልምምድ ምን ይመስላል?
 

ጥቅምት 24
November 3
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

ለተጨማሪ ጥናት፡- የሚከተሉትን የኤሌን ዋይት መጻህፍት ያንብቡ፡፡ “Christ the Center of the Message,” p. 388, in Selected Messages, book 1; “The Call of Abraham,” pp. 125–127; “The Law and the Covenants,” pp. 363, 364, in Patriarchs and Prophets; “The Sermon on the Mount,” pp. 307, 308; “Controversy,” p. 608; “ ‘It Is Finished,’ ” pp. 762, 763, in The Desire of Ages.

“ለሚሰራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፡፡ ሐዋሪያው ከዘፍ. 15፡4-6 ያለውን ጥቅስ ንባብ ቅድስና በእምነት እንጂ በሥራ አለመሆኑን ለመግለጽ ተጠቅሞበታል፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚጀምረው ‹‹ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት›› በሚለው ሐረግ ነው፡፡ ቃሉ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ኃጥአተኞችን የሚቀበላቸው በሥራቸው ሳይሆን በጸጋው መሆኑን ነው፡፡” —Martin Luther, Commentary on Romans, p. 82.

“ሰይጣን ሰዎችን ለራሳቸው ሥራ ትልቅ ቦታ እንዲሰጡ በማድረግ ድነትና ጽድቅ በሥራ ይገኛል ወደሚለው ሀሳብ በመምራት እንደሚያሸንፋቸውና የእርሱ ተጠቂዎች ሊያደርጋቸው እንደሚችል ስለሚያውቅ….የበራችሁን መቃን በቃራኒዮው በግ ደም ቀቡት ነጻም ትወጣላችሁ፡፡” —Ellen G. White, Advent Review and Sabbath Herald, Sept. 3, 1889.


 

የመወያያ ጥያቄዎች:-፡

 

  1. መዳን ያለ ህግ ሥራ በእምነት ብቻ መሆኑን መረዳት በጣም ጠቃሚ የሚሆነው ለምንድነው? ይህ ዕውቀት ከምን ዓይነት ስህተቶች ሊጠብቀን ይችላል? ይህን በጣም አስፈላጊ የሆነን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የማይረዱትን ምን አይነት አደጋ ይጠብቃቸዋል?

  2. ህግን ማወቅና መጠበቅ ሊያድነን እንደማይችል የምናውቅ ቢሆንም ቀጣይ ስለሆነው የእግዚአብሔር ህግ አስፈላጊነት ሌላ ምን ምክንያት መስጠት ይችላሉ?

  3. የተሃድሶ እምብርት የሆነው ጥያቄ የምንድነው እንዴት ነው? የሚል ነበር፡፡ የፕሮቴስታንትንና የካቶሊክን ልዩነት በሚመለከት የማንንም ሐይማኖት ሳንነቅፍና ግለሰቦችን ሳንነካ በግልጽ መናገር የምንችለው እንዴት ነው?

  4. እንደተቀደሱ ኃጥአን፣ ከበደልነው አምላክ ከራሱ ጸጋውንና ያልተገባንን መብት እንድናገኝ ተደርገናል፡፡ ይህ እውነታ ከሌሎች ጋር በምናደርገው ግንኙነት ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው? ለሚበድሉን ያልተገባቸውን ጸጋ ለማካፈል ምን ያህል ዝግጁዎች ነን?