መዳን በእምነት ብቻ:ሮሜ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2017

ከህዳር 16-22

ዘጠነኛ ትምህርት

November 25–December 1
 

ኩነኔ የለም

 

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት:- ሮሜ 8፡1-17ን ያንብቡ፡፡

 

የመታሰቢያ ጥቅስ፦ “ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ኩነኔ የለባቸውም ፣ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ አይመላለሱምና ” (ሮሜ 8፡1)

ሮሜ 8 ጳውሎስ ለሮሜ 7 የሰጠው ምላሽ ነው፡፡ በሮሜ 7 ጳውሎስ ስለ ውድቀት፣ ፍርሃትና ኩነኔ ይናገራል፡፡ በሮሜ 8 ኩነኔ የለም በኢየሱስ ክርስቶስ በተገኘ ድል በነጻነት ተተክቷል ፡፡

በሮሜ 7 ጳውሎስ የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆንህ አስቀያሚው የሮሜ 7 ልምምድ የአንተ ነው፡፡ ለማድረግ የመረጥከውን ማድረግ የማትችል የኃጥአት ባሪያ፡፡ በሮሜ 8 የሚለው የምትፈልገውን መልካም ነገር እንድታደርግ ክርስቶስ ከኃጢአት ነጻ አውጥቶሃል ነገር ግን ሥጋህ አይፈቅድም፡፡

ጳውሎስ በመቀጠል ሲገልጽ ይህ ነጻነት የመጣው ከተመን በላይ በሆነ ዋጋ ነው፡፡ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሰብዓዊነትን በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ይህ ብቸኛው ከእኛ ጋር ሊዛመድ እና ምሳሌያችን በመሆን በእኛ ፋንታ የሞተበት መንገድ ነው፡፡ ‹‹በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ ተገለጠ›› (ሮሜ 8፡3)፡፡ በዚህ ምክንያት ህግ የሚፈልገው ጽድቅ በእኛ ይፈጸማል (ሮሜ 8፡4)፡፡ በሌላ አነጋገር ክርስቶስ የህግን ጥያቄዎች ሁሉ በመመለስ በኃጢአት ላይ ድል አድርጓል፣ ይህም ለሚያምኑት መዳኛ ሳይሆን ውጤቱ መሆን ይችላል፡፡ ህግን መታዘዝ የድነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም ሊሆንም አይችልም፡፡ ይህ የጳውሎስና የሉተር መልዕክት እንዲሁም የእኛም መልዕክት ሊሆን ይገባል፡፡

*ለህዳር 23 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያንብቡ፡፡
 

ህዳር 17
November 26
 

በኢየሱስ ክርስቶስ

 

‹‹ እንግዲህ አሁን በክርስቶስ ላሉት ኩነኔ የለባቸውም (ሮሜ 8፡1)፡፡ ኩነኔ የለባቸውም ማለት ምን ማለት ነው? ከምን? ይህ መልካም ዜና የሚሆነው ለምንድነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በጳውሎስ አጻጻፍ ዘይቤ ‹‹ በኢየሱስ ክርስቶስ›› የሚለው የተለመደ ሐረግ ነው ፡፡ አንድ ሰው በክርስቶስ ሆነ ማለት ክርስቶስን የግል አዳኙ አደረገ ማለት ነው፡፡ ያ ሰው በግልጽ ክርስቶስን ይተማመነዋል እርሱ በሄደበት መንገድም ለመሄድ ራሱን አስገዝቷል ማለት ነው፡፡ ውጤቱም ከክርስቶስ ጋር የጠበቀ ህብረት ነው ፡፡

‹‹ በክርስቶስ ›› የሚለው ‹‹ በሥጋ›› ከሚለው ጋር ተነጻጽሯል፡፡ በተጨማሪም በሮሜ 7 ጳውሎስ አንድ ሰው ራሱን ለክርስቶስ ከማስረከቡ በፊት ማለትም የኃጢአት ባሪያ ሳለ ከሚለው ጋር ተነጻጽሯል፡፡ ሰውዬው ከሞት ኩነኔ በታች ነው (ሮሜ 7፡11 ፣ 13 ፣ 24)፡፡ እርሱ ወይም እርሷ ‹‹ የኃጢአትን ህግ›› ያገለግላሉ (ሮሜ 7፡23፣ 25 )፡፡ ይህ ሰው አስቸጋሪ በሆነ ኃጢአት ውስጥ ነው (ሮሜ 7፡24)፡፡

ነገር ግን ከዚያ በኋላ ይህ ሰው ራሱን ለክርስቶስ ያስረክባል ከዚያም ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አቋም በአንዴ ይለወጣል፡፡ በፊት እንደ ህግ ተላላፊ የተኮነነ ሲሆን አሁን ግን የክርስቶስ ጽድቅ ስለሚሸፍነው በእግዚአብሔር እይታ ፍጹም ሆኖ ምንም ኃጢአት እንዳላደረገ ይታያል፡፡ ከዚህ በኋላ ምንም ኩነኔ የለም ፣ ምክንያቱም ሰውዬው ኃጢአት የለሽ ስለሆነ፣ ስህተት የሌለው ወይም የዘላለም ህይወት የተገባው በመሆኑ ሳይሆን ነገር ግን የክርስቶስ ፍጹም ህይወት መዝገብ በኃጢአታቸው ሰው ፋንታ ስለሚቆም ኩነኔ አይኖርም፡፡ ነገር ግን መልካሙ ዜና በዚህ አያበቃም፡፡

አንድን ሰው ከኃጢአት ባርነት ነጻ የሚያወጣው ምንድን ነው? ሮሜ 8፡ 2

‹‹የህይወት መንፈስ ህግ›› ይህ ማለት የክርስቶስ የማዳኑ ዕቅድ፣ ‹‹የሞትና የኃጢአት ህግ ›› በምዕራፍ 7 ኃጢአት እንደሚገዛው ህግ- መጨረሻውም ሞት ነው ከተባለው ጋር ተነጻጽሯል፡፡ የክርስቶስ ህግ በተቃራኒው ህይወትና ነጻነትን ያመጣል፡፡

‹‹ ራሱን ለእግዚአብሔር ያልሰጠ እያንዳንዱ ነፍስ በሌላው ኃይል ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ እርሱ የራሱ አይደለም፡፡ ስለ ነጻነት ያወራ ይሆናል ነገር ግን በከፋ ባርነት ውስጥ ነው፡፡ ራሱን በማታለል የህሊናውን ፍርድ እንደሚከተል ቢናገርም ፣ እርሱ የጨለማውን መስፍን ፈቃድ ይታዘዛል፡፡ ክርስቶስ የመጣው ከነፍስ የኃጢአትን ባርነት ለማስወገድ ነው፡፡ -Ellen G white , The Desire of Ages, p. 466.

ባሪያ ነህ ወይስ በክርስቶስ ነጻ ነህ? ይህንን በእርግጠኝነት የምታውቀው እንዴት ነው?
 

ህዳር 18
November 27
 

ህግ ማድረግ ያልቻለው

 

ምንም እንኳ ‹‹ህግ›› ጥሩ ቢሆንም (የበአላቶች ህግ ፣ አሥርቱ ትዕዛዛት ወይም ሁለቱም) ለእኛ በጣም አስፈላጊ ለሆነው መዳን ምክንያት ሊሆኑና ኃጢአት ከሚያመጣብን ሞት ሊያድኑን አይችሉም ስለዚህ ክርስቶስ ያስፈልገናል፡፡

ሮሜ 8፡3 4ን ያንብቡ፡፡ ህግ በባህሪዩ ሊያደርገው ያልቻለው ክርስቶስ ያደረገልን ነገር ምንድነው?

-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- እግዚአብሔር ‹‹ በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ አድርጎ ልጁን በመላክ›› እርምጃ እና ‹‹ኃጢአትን በሥጋ በመኮነን›› ፈውስን ላከ፡፡ በመዳን ዕቅድ ውስጥ የክርስቶስ ሥጋ መልበስ አስፈላጊ እርምጃ ነበር፡፡ መስቀልን ከፍ ማድረግ አስፈላጊ ነው ነገር ግን በመዳን ዕቅድ ትግበራ ውስጥ የክርስቶስ ህይወት ‹‹ በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ መሆን›› እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሄር ልጁን በመላኩ ምክንያት ህግ የሚፈልግብንን ጽድቅ ማግኘት ችለናል፤ ይህም ማለት ህግ የሚፈልገውን መልካም ሥራ ለማድረግ ያስችለናል ማለት ነው፡፡ ‹‹ ከህግ በታች›› (ሮሜ 6፡14)፣ ይህ የማይቻል የነበረው አሁን በክርስቶስ ተችሏል፡፡

ሆኖም ግን ማስተዋል ያለብን ነገር ህግ የሚፈልገውን መፈጸም መቻላችን መዳንን ለማግኘት በቂ አይደለም፡፡ ይህም አማራጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር እንድንኖር ያስቻለንን ዓይነት ህይወት መኖር፤ ይህም የመታዘዝ ሕይወት፣ ‹‹ ሥጋ ከምኞቱ ጋር የተሰቀለበት›› (ገላ. 5፡24) የክርስቶስን ባህሪይ የምናንጸባርቅበት ህይወት ነው፡፡

በሮሜ 8፡4 ‹‹መሄድ›› የራስን ባህሪይ መግለጽ›› ለሚለው ዘይቤያዊ አነጋጋር ነው፡፡ ሥጋ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከማመኑ በፊትም ሆነ በኋላ ያልተለወጠን ሰው ነው፡፡ በስጋ መመላለስ ማለት በስጋ ቁጥጥር ሥር መሆን ማለት ነው፡፡

በተቃራኒው መንፈስን ተከትሎ መሄድ ማለት ህግ የሚፈልገውን ጽድቅ መፈጸም ማለት ነው፡፡ ይህን ልንፈጽመው የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብቻ ነው፡፡ ህግ የሚፈልገውን ነገር ለማከናወን የምንችልበት ነጻነት የሚገኘው በክርስቶስ ብቻ ነው፡፡

ከክርስቶስ ውጭ እንዲህ ዓይነት ነጻነት የለም፡፡ በኃጢአት ባርነት ውስጥ የሚኖር ሰው የሚወደውን ለማድረግ ከባድ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ (ሮሜ 7፡ 15፣ 17) ይመልከቱ፡፡

ህግን እንዴት በጥሩ ሁኔታ እየጠበቁ ነው? ህግን በመጠበቅ ድነትን ለማግኘት የሚደረገውን ማንኛውንም ነገር ወዲያ ይተው፡፡ የእርስዎ ህይወት ህግ የሚፈልገውን ጽድቅ ያሟላ ነው? ካልሆነ ለምን ? ባህሪይዎን ለማስተባበል ምን ምክንያት እየሰጡ ነው?
 

ህዳር 19
November 28
 

ሥጋ ወይስ መንፈስ

 

‹‹ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ፡፡ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ህይወትና ሰላም ነው፡፡›› (ሮሜ 8፡5 ፣6)፡፡ በዚህ ጥቅስ ትኩረት ያድርጉ፡፡ ከነዚህ ጥቅሶች የሚገኝ መሰረታዊ መልእክት ምንድነው? ህይወትዎን እንዴት እየኖሩ እንደሆነ እነዚህ ጥቅሶች ምን እያሉ ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

‹‹በኋላ›› የሚለው ቃል በዚህ ሥፍራ ጥቅም ላይ የዋለው ‹‹ እንደ ›› በሚል ሥሜት ነው፡፡ ‹‹ አእምሮ›› የሚለው ደግሞ አእምሮን እንዲሰራ ማድረግ ከሚለው ጋር ይመሳሰላል፡፡ አንዱ ቡድን ሰዎች አእምሮአቸውን ተፈጥሮአዊ ፍላጎታቸውን ለመፈጻም ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ አእምሮአቸውን መንፈሳዊ ለሆኑ ነገሮች እና የእርሱን ነገር ለመፈጸም ይጠቀማሉ፡፡ ምክንያቱም ድርጊት በአስተሳሰብ ስለሚመራ ነው ፣ በዚህ ምክንያት ሁለቱም ቡድኖች የተለያያ ዓይነት ህይወት ይኖራሉ፡፡

ሥጋዊ አእምሮ ማድረግ የተሳነው ምንድነው ? ሮሜ 8፡7፣ 8 ፡፡

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

አእምሮን ሥጋዊ ፈቃዱን እንዲከተል መፍቀድ ማለት ፣ በትክክል ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት በሆነ ሁኔታ መገኘት ማለት ነው፡፡ ይህም አእምሮን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለማድረግ ግድ-የለሽ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህን የሚያደርጉ ከእርሱ ጋር ግልጽ በሆነ ተቃውሞ የሚገኙና ህጉንም በግልጽ የሚቃወሙ ናቸው፡፡

ጳውሎስ በተለየ መልኩ ማሳየት የፈለገው በክርስቶስ ካልሆነ የእግዚአብሔርን ህግ መጠበቅ እንደማይቻል ነው፡፡ ጳውሎስ በተደጋጋሚ ወደዚህ ዋና ነጥብ ይመልሰናል፣ ማንም ምንም ዓይነት ጥረት ቢያደርግ ያለ ኢየሱስ ህግን መጠበቅ አይችልም፡፡

የጳውሎስ ዋነኛ ዓላማ አይሁዳውያንን ከህግ የሚበልጥ ነገር እንደሚያስፈልጋቸው መንገር ነበር፡፡ እነርሱ በባህሪያቸው ከሰማያዊው መገለጥን በመቀበል ፋንታ፣ አህዛብ የሚያደርጉትን ያንኑ ኃጢአት አድርገው ተገኙ (ሮሜ 2)፡፡ የዚህ ሁሉ ትምህርት ዓላማ እነርሱ መሲህ ያስፈልጋቸዋል የሚለው ነው፡፡ ያለ እርሱ የኃጢአት ባሮች በመሆን ከቁጥጥሩ ነጻ መውጣት አይችሉም፡፡

እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን የሰጠው ነገር ለድነት በቂ አለመሆኑን ላልተረዱ አይሁዳውያን የጳውሎስ ምላሽ ይህ ነው፡፡ ጳውሎስ እነርሱ ይሰሩ የነበሩት ነገር ሁሉ ጥሩ መሆኑን ያምናል፣ ነገር ግን አሁን የመጣውን መሲህ መቀበል አለባቸው፡፡

ያለፈውን 24 ሰዓት ይመልከቱ፡፡ ድርጊቶችዎ የሥጋ ወይስ የመንፈስ? መልስዎ ስለ ራስዎ ምን ይናገራል? የሥጋ ከሆኑ ምን ዓይነት ለውጥ ማድረግ ያስፈልግዎታል? ይህንን እንዴት ማድረግ ይችላሉ?
 

ህዳር 20
November 29
 

ክርስቶስ በአንተ

 

ጳውሎስ ሰዎች ከሚኖሩት ኑሮ የተነሳ ሊገጥሟቸው የሚችሉትን ሁለቱን መዳረሻዎች ፣ ተስፋ እንደተሰጠን ፣ እንደ መንፈስ ፈቃድ ያም የእግዚአብሔር መንፈስ ፈቃድ ወይም ኃጢአተኛ እንደሆነው የሥጋ ፈቃድ የሚሉትን ሁለቱን ዋና ሀሳቦች ማነጻጻሩን ይቀጥላል፡፡ አንዱ ወደ ዘላላም ህይወት ሌላኛው ወደ ዘላላም ሞት ያደርሳል፡፡ መካከለኛ የሚባል ሥፍራ የለም፡፡ ኢየሱስ ራሱ እንዳለው፡ ‹‹ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል ፣ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል፡፡›› (ማቴ. 12፡ 30) ከዚህ በላይ ግልጽ ወይም ነጭና ጥቁር አድርጎ ማስቀመጥ ከባድ ነው፡፡

ሮሜ 8፡9-14 ያለውን ያንብቡ፡፡ ሁለመናቸውን ለክርስቶስ ለሚሰጡ የተሰጠ ተስፋ ምንድነው?

በስጋ ያለ ህይወትና በመንፈስ ያለ ህይወት ተነጻጽረዋል፡፡ በመንፈስ ያለ ህይወት በእግዚአብሔር መንፈስ፣ በመንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡ በዚህ ምዕራፍ የክርስቶስ መንፈስ በመባል ተጠርቷል፣ ምናልባትም በዚህ ስሜት የክርስቶስ ወኪል በመሆን በአማኙ ውስጥ ይኖራል፡፡ (ሮሜ 8፡9፣10 )

በዚህ ቁጥር ጳውሎስ በሮሜ 6፡1-11 የተጠቀመውን ምሳሌ ይጠቀማል፡፡ ስለ ጥምቀት በተሰጠው ምሳሌያዊ አነጋገር ኃጢአትን የሚያገለግለው ‹‹ የኃጢአት ሥጋ›› ተደምስሷል፡፡ ‹‹አሮጌው ሰው ከእርሱ ጋር ተሰቅሏል›› (ሮሜ 6፡6)፡፡ በጥምቀት እንደሚታየው መቀበር ብቻ ሳይሆን ትንሳኤም እንዳለ ሁሉ የተጠመቀ ሰው በአዲስ ህይወት ለመመላለስ ይነሳል፡፡ ይህ ማለት አሮጌውን ማንነታችንን ዕለት በዕለት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሞት ማድረግ የእኛ ምርጫ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ነጻነት አይከለክልም፡፡ አሮጌው የሃጢአት ሰው ከሞተ በኋላ እንኳ፣ አሁንም ኃጢአት ለማድረግ ይቻላል፡፡ ጳውሎስ ለቆላስያስ ሰዎች ‹‹ በምድር ያሉትን ስሜቶቻችሁን ግደሉ›› በማለት ጽፏል፡፡ (ቆላ. 3፡5)፡፡

ስለዚህ ከተለወጡ በኋላም ቢሆን ከኃጢአት ጋር ትግል አለ፡፡ ልዩነቱ መንፈስ በውስጡ የሚኖርበት ሰው አሁን ድል ለማድረግ የሚያስችል መለኮታዊ ኃይል በውስጡ አለ፡፡ በተጨማሪ ሰውዬው አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ከኃጢአት ባርነት ነጻ ስለወጣ፣ እንደገና በፍጹም ለኃጢአት አይታዘዝም፡፡

ኢየሱስን ከሞት ያስነሳውን የእግዚአብሔርን መንፈስ በሚመለከት ተወያዩበት፣ ይህ ተመሳሳዩ መንፈስ ካመንንበት በውስጣችን ያድራል፡፡ ለእኛ ስላላው ተስፋ ኃይል ያስቡ፡፡ መሆን እንደሚገባን ሆነን እንዳንገኝ የሚከለክለን ምንድነው?

ህዳር 21
November 30

የራሳችን አድርገን የወሰድነው መንፈስ

 

በክርስቶስ ያለንን አዲሱን ግንኙነት ጳውሎስ የገለጸው እንዴት ነው? ሮሜ 8፡15፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ ምን ተስፋ አለን? ይህንን በህይወታችን እውን የምናደርገው እንዴት ነው?

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

አዲሱ ግንኙነት ከፍርሃት ነጻነት በመባል ተነግሯል፡፡ ባሪያ ሁልጊዜ ቀንበር ሥር ነው፡፡ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ በጌታው ፍርሃት ይኖራል፡፡ ከረዥም ዓመት አገልግሎቱ ምንም አያገኝም፡፡

ኢየሱስን የተቀበለው ሰው እንዲህ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ እርሱ ወይም እርሷ የሚሰጡት አገልግሎት በፈቃዳቸው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ እርሱ ወይም እርሷ የሚያገለግሉት ያለ ፍርሃት ነው፡፡ ‹‹እውነተኛ ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፡፡›› (1ዮሐ. 4፡18)፡፡ ሶስተኛ ፣ እንደ ልጅ ሆኖ ተቀባይነትን አግኝቷል፣ ዘላላማዊ ክብር ያለው ነገር ወራሽ ሆኗል፡፡

‹‹ የባርነት መንፈስ በራስ ጥንካሬ ህግ የሚፈልገውን ለማከናወን በመድከም በህጋዊ ኃይማኖት ለመኖር ምክንያት ይሰጣል፡፡ ለእኛ ብቸኛ ተስፋ ሊኖረን የሚችለው ወደ አብረሃሙ ኪዳን ይህም በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋ ኪዳን ስንመጣ ብቻ ነው፡፡›› -Ellen G. white comments, The SDA Bible commentary, vol. 6 1077.

እግዚአብሄር በእርግጥ እንደ ልጆቹ እንደተቀበለን የምናውቀው እንዴት ነው? ሮሜ 8፡16.

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በውስጣችን ያለ መንፈስ በሚሰጠን ምስክርነት ተቀባይነት ማግኘታችንን እናውቃለን፡፡ ዝም ብሎ በስሜት መነዳት አስፈላጊ ባይሆንም፣ በደንብ እስኪያስተውሉ ድረስ በቃሉ ብርሃን የተመሩ ግን ከውስጣቸው የሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን እንዳገኙ የሚናገር ሥልጣን ያለው ድምጽ ይሰማሉ፡፡

ሮሜ 8፡17 እኛ በእርግጠኝነት የእርሱ ወራሾች መሆናችንን ይነግረናል፡፡ ይህም ማለት እኛ የእግዚአብሔር ቤተሰቦቹ ነን፣ እና እንደ ወራሾች፣ እንደ ልጆች እጅግ አስደናቂ ውርስ ከአባታችን እናገኛለን፡፡ የተገባን ሆኖ ሳይሆን በጸጋው በኩል እንዲሁ ኢየሱስ በእኛ ፋንታ በመሞቱ በእርሱ በተሰጠን አዲስ ህይወት አማካይነት ለእኛ የሚሆን ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ያለዎት ቅርበት ምን ያህል ነው? በእውነት ያውቁታል ወይስ ስለ እርሱ ያውቃሉ? ከፈጣሪዎና ከአዳኝዎ ጋር የቅርብ ጉዞ እንዲኖርዎ ምን ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ? ወደ ኋላ የሚይዝዎት ነገር ምንድን ነው? ለምን?
 

ህዳር 22
December 1
 

ለተጨማሪ ጥናት፡-

 

‹‹ የመዳን ዕቅድ አማኞችን በዚህ መንግስት ከመከራና ፈተና ነጻ የሆነ ህይወት እንዲኖሩ አያደርግም፡፡ በተቃራኒው ክርስትያኖችን ራስን በመካድ መንገድ እንዲኖሩ ይጠራቸዋል፡፡ የክርስቶስ ባሕሪይ በህዝቡ ሊታይና ሊንጻባረቅ የሚችለው በዚህ ዓይነት መከራና ፈተና አማካይነት ነው፡፡ የክርስቶስ ፈተና ተካፋዮች ስንሆን ሥርዓትን በመለማመድ የሚመጣውን ክብሩን ለመካፈል ዝግጁዎች እንሆናለን፡፡ ›› -The SDA Bible commentary, vol. 6, pp. 568, 569.

ከእግዚአብሔር ዙፋን ወደ ምድር የተላከው ሰንሰለት ወደ ጥልቅ ሥፍራዎች ሊደርስ የሚችል ነው፡፡ ክርስቶስ በጣም የተዋረዱትን ኃጢአተኞች ከጉድጓድ ውስጥ በማውጣት እና የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን ተቀባይነት ወደሚያገኙበት፣ ‹‹ከክርስቶስም ጋር የማይጠፋ ርስት ወራሾች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።›› Ellen G . white, Testimonies for the church, vol. 7, p. 229.

ለወደቁት መላዕክትና ላልወደቁ ዓለማት በመለኮት በተዘጋጀው እርዳታ ሰዎች በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት መጓዝ እንደሚችሉ ለመመስከር፣ በሰማያት ሁሉ የተከበረው ጌታችን ኢየሱስ የሰውን ባህሪይ በመልበስ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡

‹‹የመዋጀት ዋጋችን በክርስቶስ ተከፍሎልናል፡፡ ማንም የሰይጣን እስረኛ መሆንን አይፈልግም፡፡ ክርስቶስ በጎናችን ሁሉን ሊያደርግ የሚችል አጋዣችን በመሆን ይቆምልናል፡፡›› -Ellen G. Whit, selected messages, book 1, p. 309.
 

የመወያያ ጥያቄዎች:-፡

 

  1. በዓርብ ቀን ትምህርት ላይ ያለውን የኤሌን ዋይትን ጥቅሶች እንደገና ያንብቡ፡፡ ከነዚህ ጥቅሶች ለራሳችን የምናገኘው ተስፋ ምንድነው? እነዚህን የድል ተስፋዎች የራሳችን ልናደርግ የምንችለው እንዴት ነው? በክርስቶስ እጅግ ብዙ ተደርጎልን ሳለ ለምንድነው መሆን ካለብን እጅግ ዝቅ ብለን የምንገኘው?

  2. በየዕለቱ ኑሮ፣ ተግባራዊ በሆነ መልኩ አእምሮን መንፈሳዊ ለሆነ ነገር ዝግጁ ሊያደርጉ የሚችሉት እንዴት ነው? ያ ማለት ምን ማለት ነው ? መንፈስ የሚመኘው ምንድነው? የሚያነቡት፣ የሚያዩትና የሚያስቡት ነገር ይህንን በህይወትዎ እንዳይተገብሩ የሚያደርገው እንዴት ነው?

  3. በተጋድሎው ውስጥ ከአንዱ ወይም ከሌለው ወገን ነን እንጂ መካከለኛ ሥፍራ የለም በሚለው ሀሳብ ላይ ይወያዩበት፡፡ ይህ ቀጥ ያለ ንግግር እንደምታው ምንድነው? በዚህ ነገር ላይ ያለን ማስተዋል በምናደርገው ምርጫና በምንኖረው ኑሮ ‹‹በጥቂቶቹ ነገሮችም›› ቢሆን ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው?