ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡-- 1 ዮሐ. 2:16-17፣ ሉቃ. 14:26–33፣ 12:15–21፣ ዘዳ. 8:10–14፣ 1 ጢሞቴ. 6:10፣ ዮሐ. 15:5፣ ገላ. 2:20፡፡
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ - “መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታወቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ሮሜ 12፡2)፡፡
አምላካዊው ቃል “ይህን ዓለም አትምሰሉ” እያለ ምክሩን ለሰብዓዊው ዘርእየለገሰ ቢገኝም ነገር ግን የዓለማዊው ቁሳዊ ሐብትና ንብረት ምኞት የማባበልና የመማረክ ተጽእኖው እጅግ ብርቱ እንደመሆኑ፤ እኛ ከምናስበው በላይ በሥርዓት ከመመላለስ ሊገታን የሚችል ኃይል አለው፡፡ ቢደኸዩ ወይም በሐብት ቢበለጽጉ ትኩረታቸውን ከቁስ አካላዊው ነገር ባሻገር ያደረጉ በጣም ጥቂት ሕዝቦች አሉ፡፡ ክርስቲያኖች ከእነዚህ ጥቂት ሕዝቦች መሃል ይካተታሉ፡፡
ሐብታም መሆን ወይም ብዙ ሐብት ለማካበት ጠንክረው ሠርተው ከፍ ያለው ማማ ላይ መውጣት፣ ለራስም ሆነ ለተወዳጅ የቤተሰብ አባላት ምቾት ማምጣት ስህተት የለበትም፡፡ ነገር ግን ፍቅረ ንዋይ አቅላችንን ሲያስተንና ብር የደም ስር ሲሆን ያኔ በዲያብሎስ ወጥመድ እንወድቅና በእርግጥም “ይህን ዓለም” እንመስላለን፡፡
ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ዓይነቱ ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ የተትረፈተፈ ህይወት ቁልፉ ንዋይ ብቻ ነው--የተሰኘውን ጽንሰ ሀሳብ ዓለም ሲያስተጋባ ይደመጣል፡፡ ሰይጣን አድብቶ ታማኝነታችንን ከእጁ ለማስገባት የሚጠቀምበት ጭምብል ገንዘብ ነው፡፡ የክርስቲያኖችን ምርጫ ከሚዋጋባቸው መሣሪያዎቹም አንዱ ይኸው ብልጭልጭ ነገር ነው፡፡ ለነገሩ ዛሬ ከምንገኝበት ሁኔታ አኳያ ገንዘብን የሚጠላ ማን ነው? ገንዘብ ዛሬ የምንፈልገውን በፍጥነት እጃችን በማስገባት ደስ ቢያሰኘንና ቢያረካንም ውሎ አድሮ ጥልቅ ለሆነው ውስጣዊ ፍላጎታችን ጉድለት ምላሽ መስጠት ግን አይሆንለትም፡፡
እነሆ ገንዘብ ለሰብዓዊው ዘር አምላኩ፣ ተብለጭላጩ ነገር ደግሞ ኃይማኖቱ በሆነበት ዓለም እንገኛለን፡፡ እጅግ የተራቀቀውና የሚያነሆልለው ተብለጭላጭ ነገር ጊዜያዊ ከለላ ከመሆን ባሻገር ዘላቂ ደኅንነት ሊያስገኝልን አይችልም፡፡
የአንድ ሰው ትኩረት ከመንፈሳዊው ተጨባጭ ነገር ባሻገር ባለው ምድራዊ ግዑዝ፣ ብልጭልጭ ሐብትና ንብረት ምኞት ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረት ዓለምን ለመምሰል ዓይነተኛ ፍቺ መሆን ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ተብለጭላጩ ቁሳዊ ነገር ምድራዊ ዋጋ ሊኖረው ቢችልም እኛን ሊቆጣጠር ግን አይገባም፡፡ “ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፣ ብልጽግናም የሚወድ በትርፉ አይረካም” (መክ. 5፡10) እንደተባለው በዚህ ዓለም የቱንም ያህል የተትረፈረፈ ሐብት ብናካብት አብልጠን ከመመኘት ወደ ኋላ አለማለታችን አንዱና ዋንኛው ችግር ነው፡፡ እንደውም ከቀድሞው የበለጠ ለማግኘት አብልጠን በገፋን ቁጥር ፈጽሞ ወደ እርካታ መምጣት የማንችል እንሆናለን፡፡ ወጥመድ ሊሆኑብን በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋገሩ፡፡
የሚከተሉት ጥቅሶች ትኩረት ልንሰጠው ስለሚገባው ፍሬ ነገር አስመልክቶ ምን
ይላሉ 1ዮሐ. 2፡16-17
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በተጨማሪ የሱስ በሉቃ. 14፡26-33 መልእክቱ አንድ ክርስቲያን ብርቱ አጽንኦት ሊሰጠው ስለሚገባው ነገር ምን እያለን ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ገንዘብን እንደ ጣኦት እያመለኩ ህይወታቸው በተጨባጭ በፍቅረ ነዋይ አዙሪት ስር የወደቀ ሰዎች በእርግጥም ይህ ውሳኔያቸው የሚያስከፍለውን ዋጋ ሊያጤኑ የተገባ ነው “ሰው ዓለሙ ሁሉ የእርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?” (ማር. 8፡36)፡፡
“ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ሰብዓዊነት በፍጥነት አሽቆልቁሎ የአንድ ማኅበረሰብ መሰረት የሚባሉ እሴቶች የመሸርሸር አደጋ ገጥሟቸው ነበር፡፡ ህይወት የታይታና ኢ-ተፈጥሮአዊ ገጽታ ይዞ ነበር… በዓለም ዙሪያ የነበሩ ኃይማኖቶች በሰብዓዊው አእምሮና ነፍስ ላይ የነበራቸውን ተጽእኖ አጥተው ነበር፡፡ ይቀርቡላቸው በነበሩ ልቦለድ ተረቶችና በሬ ወለደ አስተምህሮዎች የተንገፈገፉት ሕዝቦች ከእንዲህ ዓይነቱ ሁናቴ ለመውጣት ከነበራቸው ብርቱ ምኞት የተነሳ የእምነት ኪዳናቸውን እያፈረሱ ፊቶቻቸውን ወደ ዓለማዊው ብልጭልጭ ነገር አዞሩ፡፡ ዘላለማዊውን ነገር ከአእምሮአቸው እያወጡ ለጊዜው ብቻ ኖሩ” —Ellen G. White, Education, pp. 74, 75.
ሰዎች ዘላለማዊውን ነገር ከአእምሮአቸው እያወጡ ለጊዜው ብቻ የመኖራቸው ነገር ዛሬስ የተለመደ አይደል?
ሐብትም ሆነ ንብረት ማፍራት የማይፈልግ ማን አለ? ጥያቄው ግን እንዲህ ነው፡ ያፈራነው ሐብትና ንብረት ምናልባት ብዙ ሊባል የማይችል እንኳ ቢሆን ነገር ግን ማን ማንን እየገዛ እንደሆነ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? ንብረታችን እኛን ወይስ እኛ ንብረታችንን? እኛን በብቸኝነት እንዲገዛ የተገባው ማን ነው? ለእርሱ እየተገዛን ለመሆኑ እርግጠኞች መሆን የምንችለውስ እንዴት ነው?
በሉቃስ 12:15–21 የተሰጠን መልእክት ምን ይመስላል? መቼም አንድ ሰው የግድ ሀብታም መሆን ባይጠበቅበትም በመልእክቱ የቀረበውን መርኅ ገቢራዊ ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሀብታም ሆንን ወይም ደሃ ቁሳዊውን ነገር ለማፍራት የሚኖረን ብርቱ ምኞት የአእምሮአችንን ትኩረት ሚዛን ከሚደፋው የከበረ ነገር ላይ እያማለለ ወስዶ በጊዜያዊው፣ በብልጭልጩና በአላፊው ምድራዊ ነገር ላይ እንዲተከል የማድረግ
ኃይል አለው፡፡
እንደ ጥንቱ ሁሉ በዚህ ዘመን ከንጹህ ወርቅ ወይም ብር ለተሠራ ምስል አጎንብሰን ባንሰግድም ወርቅና ብር የማምለክ አደጋ ውስጥ ልንወድቅ ግን እንችላለን፡፡
ምንም እንኳ ህይወት ሀብትና ንብረት እንዲፈራበት ብቻ የተበረከተ ገጸ በረከት ባይሆንም ምሳሌው ለአብዛኛው የዓለማችን ክፍል ገጣሚ ነው፡፡ ነጋዴዎች ለገበያ የሚያወጧቸው አማላይ ሸቀጦች እዚህ ቀረሽ ሳይባል በዓለማቀፍ ደረጃ የገበያተኛውን ቀልብ ከመዳፍ ያስገቡ ናቸው፡፡ አጠቃላዩ የንግድ ስልታቸው የሚሸጡልንን ሸቀጥ ካልገዛን በቀር ደስተኛ እንደማንሆን ወይም እርካታ እንደማናገኝ ተደርጎ በረቂቅ የተነደፈ ነው፡፡ ማንኛውም የተሳካለት የተባለ ሸቀጥ አምራች ተቋም ሸቀጡ እንደሚያስፈልገን እንድናስብ አድርጎ በመቅረጽ ይሸጥልናል፡፡ የሽያጩ እርከን እየጨመረ መሄድ አካሄዱ እየተሳካለት የመሆኑ እውነታ ማሳያ ነው፡፡ ተስፋቸውን በዚህ ዓለም ላይ ያላደረጉት ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ከዚህ መደለያ የተጠበቁ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ (ዘዳ. 8፡10-14) ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አባል ከላይ ከቀረበው አደጋ መጠበቅ የሚችለው በምን መንገድ ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የምድራዊው ሀብትና ንብረቱ መከማቸት መንፈሳዊ ህይወቱ እንዲያድግ፣ ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና ለሰማያዊው ነገር ያለው ምኞት እንዲበለጽግ የረዳውን ግለሰብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ዛሬ በዚህ ዘመን በምሳሌ ሊያቀርቡ የሚችሉት ማን ይሆን? መልስዎን በሰንበት ትምህርት ጥናት ላይ ተወያዩበት፡፡
ዛሬ ማስታወቂያ በዓለም ላይ ብርቱ ኃይል አለው፡፡ የንግድ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ከእያንዳንዳችን ዐይንና ጆሮ ለማድረስ አያሌ ቢሊዮን ብሮች ይረጫሉ፡፡ ሸቀጦቻቸውን ለመሸጥ የሚጠቀሙባቸው የሽያጭ ሠራተኞች ውብና
ዐይነ ግቡ ናቸው፡፡ በዚህም ትኩረታችን ምርቱ ላይ መሆኑ ቀርቶ ማስታወቂያውን የሠሩት ላይ ይሆንና እነሱን፣ እነሱን እያየን ሸቀጡን እንገበያለን፡፡
የሸቀጥ ንግድ ሥራ ስሜትን የሚኮረኩሩ ማማለያዎችን በማስታወቂያ አማካይነት ጥቅም ላይ ባያውል፤ ገበያው እንዲህ እንደምናየው ባልደራ ነበር፡፡ ዘዴን ከብልሃት ለተካነው የማስታወቂያ ሥራ ምስጋና ይግባውና የሸቀጥ ሥራ አመርቂ ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ሆኖም ግብስብሱ ነገር ከሚያስከትለው አደጋ ለመጠበቅ ብርቱ ግብግብ ላይ ያሉትን ክርስቲያኖች ማስታወቂያ እየገዘገዘ ይገኛል፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ ማቴ. 6፡22-24፡፡ ከክርስትና እሳቦትና ግብር አኳያ ዐይን ምን ይወክላል? እንደ ክርስቲያን የማያስፈልጉንን ሸቀጦች እንድንገዛ ለሚፈትኑን አማላይ ማስታወቂያዎች አጸፋችን ምን ሊሆን ይገባል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የገበያተኛውን ስሜት ከብልጭልጩ በአንድ ያቆራኘው ማስታወቂያ እንደ ብርቱ መሣሪያ ሊቆጠር ይችላል፡፡ የጅምላም ሆነ የችርቻሮ ነጋዴዎች በገበያተኛው አእምሮ ላይ ደስ የሚል ስሜት እየፈጠሩ ብልጭልጩን በዘዴ ይቸበችባሉ፡፡ በማስታወቂያ ሥራ የሚጠቀሙት የማማለያ ዘዴ ከተጨባጩ እውነታ ያፈነገጠ ቢሆንም ይሠራል፡፡ አላፊ ለሆነው ነገር የሰዎችን ስሜት ወደ ሌላ ዓለም ጭልጥ አድርጎ መውሰድ በእርግጥም ረቂቅ አካሄድ ነው፡፡ ማስታወቂያ ሰዎችን አነሁልሎ ይሁንታቸውን ከእጁ ካስገባ፤ አንዳች ዕውቀትም ሆነ መንፈሳዊ እውነት የማይገበይበት ሃሳዊሐሐሀ ስብከት ይሆናል፡፡ ይኸው ስብከት ግብስብሱ ሁሉ እንደሚያስፈልገን አድርጎ ይሞላንና--ታዲያ የማልገዛው ለምንድን ነው? ወደሚለው ውሳኔ ያደርሰናል፡፡ የማስታወቂያ ባለሟሎች አሰሱን፣ ገሰሱን አንገብጋቢ አድርገው ሰብዓዊውን አእምሮ እያሳመኑ ከየኪስ እንዲመዘዝ የሚያደርጉትን ረብጣ ብር
መጠን የሚያውቀው አንድ እርሱ ብቻ ነው፡፡
“እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ እላለሁ፤ የሥጋንም ምኞት አትፈጽሙ” (ገላ. 5፡16)፡፡ ብዙውን ጊዜ “የሥጋን ምኞት” የሚለውን አነጋገር ከፍትዎት ጋር ብቻ ማያያዝ ቢቀናንም፤ ሃሳቡ አደጋ ያላቸው ሌሎች ምን ዓይነት ፍቺዎችን ይዞአል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ በሰጣችሁ እምነት መጠን ራሳችሁን በአግባቡ መዝኑ እንጂ፣ ከሆናችሁት በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ እያንዳንዳችሁን እመክራለሁ” (ሮሜ 12፡3)፡፡
“በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሳም ጥበብህን አረከስህ፡፡” (ሕዝ. 28፡17) በማለት እግዚአብሔር ተናግሮአል፡፡ ሉሲፈር ከሆነው በላይ ማንነቱን አግዝፎ በማሰብ ራሱን አታለለ፡፡ በልቡ “ራሴንም እንደ ልዑል አደርጋለሁ” ብሎ ሲያስብ የሌለውን መብት አለኝ የሚል ክፉ ምኞት በእርሱ እየተገለጠ ነበር፡፡ ራስን መሸንገልና ከንቱ ክብር የሚሻ ምኞት እነዚህ ሁለቱ የወደቀው የሉሲፈር ልብ ባሕርዮች ነበሩ፡፡
በሉሲፈር ውድቀት ዙሪያ የሚያጠነጥኑት እነዚህ ጥቅሶች ያ የቀደመው ኃጢአት ራስን ማምለክ መሆኑን ከብዙ አቅጣጫዎች ሊነግሩን ይገባል፡፡ ለመሆኑ ራስን ስለ መሸንገል ከእነዚህ በላይ ግዙፍ ማሳያ ባህሪዎች የትኞቹ መሆን ይችላሉ?
እነዚህ ባህሪዎች አንድ ሰው ከሚያስበው በላይ የተለመዱና ተደጋግመው የሚስተዋሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ናቡከደነፆር ዕብሪት በተሞላ አስተሳሰብ ከተጨባጭ ማንነቱ በላይ ራሱን አግዝፎ ይመለከት ነበር (ዳን. 4፡30)፡፡ እንዲሁም ፈሪሳውያን ከዚህ ተመሳሳይ የሆነውን አሳች የቁም ቅዠት አስተምህሮ የእምነታቸው አካል አድርገው ነበር (ሉቃ. 18፡11-12)፡፡ እኛም ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረግን በቀር ሀብት በራሱ ወደ ተመሳሳይ ሽንገላ ሊመራን ይችላል፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ጢሞቴ. 6፡10 መልእክቱ ከምን ዓይነት አደጋ መጠበቅ እንደሚኖርብን እያስጠነቀቀን ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ በ2ጢሞቴ. 3፡1-5 መልእክቱ ጢሞቴዎስ “ገንዘብን የሚወዱትን” ጨምሮ ሊጠነቀቃቸው ስለሚገባ አጉል ሰዎች ያሰፈረውን ሃሳብ እናገኛለን፡፡ አፍቅሮተ ንዋይ ሰዎችን ወደ ትምክህትና መታበይ የመምራት ኃይል አለው፡፡ የብልጭልጩ ነገር ክምችት በሰዎች ላይ አጉል የተፈላጊነት ስሜት እንዲያይል አድርጎ ይሞላቸዋል፡፡ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ የተትረፈረፈ ገንዘብ ያለው ሰው ከሌለው ይልቅ ራሱን አግዝፎ ማየት ይቀናዋል፡፡ ለነገሩ ሁሉም ሰው ሀብታም መሆን ቢፈልግም የሚሳካላቸው ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ መመጻደቅ፣ ኩራትና ትዕቢት ለሀብታም ቅርቡ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
ይህን ጥቅስ ያንብቡ--ፊልጵ. 2፡3፡፡ ከክርስትና አስተሳሰብ በተቃራኒ የሚጓዘውን ብልጭልጩን ነገር ሊያበረታታ የሚችለውን መንፈስ እንድናስተውል ጥቅሱ እንዴት ሊረዳን ይችላል?
ማንነታቸው ቁሳዊው ነገር ሊፈነቅለው እንዳይችል ሆኖ ከእርሱ ጋር በአንድ የተዋሃደ፤ እግዚአብሔርን የሚወዱ አያሌ ሕዝቦች አሉ፡፡
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘዳ.7:6፣ 1ጴጥ. 2:9፣ ዮሐ. 15:5፣ ገላ. 2:20፡፡ የእግዚአብሔር ርስት መሆን ምን ማለት ነው? እውነተኛውን ማንነት ማግኘት የምንችለው ከወዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“እኔ የወይን ተክል ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ” (ዮሐ. 15፡5) በማለት ጌታ ይናገራል፡፡ ይህ ግንኙነት ቀጥተኛ፣ ደህንነቱም አስተማማኝና የተጠበቀ ነው፡፡ “ማንኛውም እውነተኛ መታዘዝ ከልብ ይመነጫል፡፡ መታዘዝ ከክርስቶስ ጋር በልብ ውስጥ የሚሠራ ሥራ ነው፡፡ እኛ ፈቃዳችንን የምንሰጠው ከሆነ እርሱ የአስተሳሰባችንም ሆነ ለመድረስ ያሰብነው ግብ አካል ይሆናል፡፡ ልባችንንና አእምሮአችን ከእርሱ ፈቃድ ጋር ውህደት ሲፈጥር እርሱን መታዘዝ ዱብ-ዕዳ ሳይሆን ውስጣችን የተቀመጠውን መከወን ይሆናል፡፡” —Ellen G. White, The
Desire of Ages, p. 668.
በሌላ በኩል በብልጭልጩ ነገር ላይ ያለን ትኩረት ከሃብትና ንብረት ጋር ውሁድ ማንነት ያሰጠናል፡፡ በሌላ አነጋገር ለገዛ ማንነታችን የምንሰጠው ፍቺ ካፈራነውና የዚህን ዓለም ሸቀጥ መግዛት ከምንችለው አቅም አኳያ ነው፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብ ከዚህ ተጠበቁ ሲል ይመክረናል “ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፣ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል፡፡” (ያዕ. 5፡3)፡፡ በጥቅሱ “አከማችታችኋል” በሚል የቀረበው ቃል--ምድራዊ ሃብት ንብረት ሰብስባችኋል የሚል ፍቺ አለው፡፡ ሰዎች ጥቂት ሃብት ያፍሩ ወይም ብዙ--አያሌዎች ማንነታቸውን የሚያገኙት በዚያ ውስጥ መሆኑ ሊስተዋል የተገባ ዋና ነጥብ ነው (ሉቃስ 12፡19-21)፡፡
ብልጭልጩን ነገር ብቻ ለማፍራት የሚደረግ ሩጫ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይከታል፡፡ ይህ ማለት የአብዛኞቻችን ማንነት ያፈራነው ሃብትና ንብረት ውሁድ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ምድራዊው ሃብትና ንብረት ጣኦት ሆኖብናል (ማቴ. 6፡1921)፡፡ “በዚህ ምድር ካፈራሁት ሃብትና ንብረት ውጪ እኔ ምንም ነኝ” ሲል አንድ ሰው በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር፡፡ ራሳችንን የምንገልጸው ከምድራዊ ሀብታችን አኳያ ብቻ መሆኑ እንዴት አሳዛኝ ነው! በተለይ ራሱን ክርስቲያን ብሎ የሚጠራ የእንዲህ ያለው ገለባና ብልጭ ብሎ የሚጠፋ ከንቱ ህይወት አካል መሆኑ በእርግጥም ልብ ይሰብራል፡፡ ራሳችንን የምንገልጸው እንዴት ነው--ከሀብት ንብረታችን ወይስ የእግዚአብሔር ርስት ከመሆናችን አኳያ? ውሎ አድሮ ከአንዱ ጎን መሰለፋችን አይቀሬ ነው፡፡ ግላዊ ማንነትዎ አሉኝ ከሚሏቸው ነገሮች ጋር ምን ያህል ተዛምዶ አለው?
“ዛሬ ጠላት ነፍሳትን እጅግ በወደቀ ዋጋ እየገዛ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ‘ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር’ ሲል ይናገራል፡፡ አንዱ ነፍሱን ለዚህ ዓለም ክብርና ዝና ሲሸጥ ሌላው ደግሞ ለገንዘብ ይሸጣል፡፡ አንዱ ጥልቅ ስሜቱን ለማርካት ሌላው ደግሞ ለምድራዊው ተድላና ጨዋታ ራሱን ይሸጣል፡፡ እነዚህ የሽያጭና የግዢ ስምምነቶች በየቀኑ ይከናወናሉ፡፡ ምንም ዓይነት ተመን ሊወጣለት በማይችለው በክርስቶስ ደም የተገዙትን ነፍሳት ሰይጣን በወደቀ
ዋጋ እየሸመታቸው ይገኛል፡፡” —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 5, p. 133.
የሰይጣን እቅድ አሰሱን ገሰሱን ተጠቅሞ ነፍሳትን መግዛት ነው፡፡ እንደ ነገሩ ከፊታችን የተደነቀሩት እነዚህ መሰናክሎች የእያንዳንዱን ልብ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡ ምንም እንኳ ይኸው ምድራዊ ሀብትና ንብረት የሚናገርበት አንደበት ባይኖረውም ነገር ግን ሁሉንም ቋንቋ ያውቃል፡፡ ሀብታሙንም ሆነ ደሃውን እንዴት ጮቤ ማስረገጥ እንዳለበት ስለሚረዳ “ለጊዜው የሚያሻኝ ተሟልቷል፤ ታዲያ ስለ ሌላው ነገር ምን አጨናነቀኝ?” ብለው እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ከመታመን በተቃራኒ ባላቸው ነገር ላይ እንዲታመኑ የሚያደርገው ቁሳዊው ነገር አእምሮን ያበላሻል፡፡ ታዲያ ለዚህ ማርከሻ አለው፡፡ “‘በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት” (ዘካ. 4፡6)፡፡
ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥና በአምላካዊው ጸጋ ብልጭልጩ ነገር ህይወታችንን እንዳይገዛ ቁርጥ ሃሳብ ስናደርግ ቁሳዊው ነገር በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር የሚመላለስን ነፍስ መቋቋም አይችልም፡፡