ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢሳ. 22:14–18፣ 1ቆሮ. 4:1-2፣ ቆለ. 2:2-3፣ ኤፌ. 6:13–17፣ 2ቆሮ. 5:10፡፡
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፦ “ ነገር ግን ወንጌልን በዐደራ ለመቀበል እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ እንደ ቆጠራቸው ሰዎች ሆነን እንናገራለን፡፡ ይህንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን እንጂ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት ብለን አይደለም፡ ” (1ተሰ. 2፡4)፡፡
የአዳምና ሔዋን የመጀመሪያ ሥራ መጋቢነትን ያካተተ ነበር፡፡ የኤደን አትክልት ስፍራና በውስጧ የነበሩ ፍጥረታት የጥንዶቹ የእጅ ሥራ አንጡራ ሀብት ባይሆኑም ነገር ግን እንዲጠብቋቸው፣ ሐሴት እንዲያረጉባቸውና እንዲንከባከቧቸው ኃላፊነት ተሰጣቸው (ዘፍ. 2፡15)፡፡ አዳምና ሔዋን የጌታን አደራ የተቀበሉ መጋቢዎች ነበሩ፡፡
በዚህ ሳምንት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ከወደቁና ከኤደን የአትክልት ስፍራ ከተባረሩ በኋላ ባለው የመጋቢነት ፍቺ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ምልከታ እናደርጋለን፡፡ እኛም እንደ እነሱ መጋቢዎች ብንሆንም ነገር ግን የእኛ መጋቢነት እነርሱ ከኖሩበት ሁኔታ አኳያ ሲታይ በጣም የተለየ ነው፡፡
ለመሆኑ መጋቢነት ምንድን ነው? የመጋቢነት ምንነት በመጽሐፍ ቅዱስ በተጠቀሱ አንዳንድ ሰዎች ህይወት የተገለጠው እንዴት እንደኖሩ በማሳየት ነው፡፡ የእግዚአብሔር መጋቢዎች ስንሆን በምድርና ቁሳዊ እሴቶች ላይ የሚኖረን ትኩረት ሁሉን ወደ ፈጠረውና ወደ አምላካዊው ተልዕኮ ይቀየራል፡፡ ልክ እንደ አዳምና ሔዋን ሁሉ እግዚአብሔር እነዚያን ቀደምት መለኮታዊ ዐደራዎች ለእኛም ሰጥቶናል፡፡ ሆኖም ከኤደን ውድቀት ወዲህ የመጋቢነት ኃላፊነት ተለውጧል፡፡ ለቁሳዊው ዓለም ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ ከማድረግ ኃላፊነት በተጓዳኝ ለመንፈሳዊው እውነትም መልካም መጋቢዎች እንድንሆን ዐደራ ተጥሎብናል፡፡
“መጋቢ” የተሰኘው ቃል በብሉይ ኪዳን ተተርጉሞ የምናገኘው በጥቂት ስፍራዎች ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ መጋቢነት በአብዛኛው የተገለጸው “የቤቱ አዛዥ” በሚሉ የማስተዳደር ኃላፊነትን ያካተቱ ቃላቶች ነው (ዘፍ. 43፡19፣ 44፡1፣ 4፣ 1ነገሥ. 16፡9)፡፡ በቤቱ ላይ በመጋቢነት የተሾሙ ኃላፊዎች የቤቱን ጉዳይና የጌታቸውን ሀብት በተጠየቁት ሁኔታ የማስተዳደር ዐደራ ተቀብለው ነበር፡፡ የመጋቢነትን ባህሪያት ለይቶ በማወቅ በብሉይ ኪዳን የነበረውን የመጋቢነት ፍቺ ማግኘት ይቻላል፡፡ መጋቢዎች ማንነታቸውን ገልጾ ከሚያሳየው የመጋቢነት ኃላፊነት ተለይተው መታየት አይችሉም፡፡
የመጋቢነት አንዳንድ ባህሪዎች በብሉይ ኪዳን በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ መጋቢነት በጊዜው ከነበሩ ታላላቅ ኃላፊነቶች አንዱ መሆኑ--በቅድሚያ ሊታይ የሚገባው ነጥብ ነው (ዘፍ. 39፡4)፡፡ መጋቢዎች በነበራቸው ችሎታ ምክንያት ይመረጡ የነበረ ሲሆን፤ ሥራውን በአግባቡ በመሥራታቸው ከአሳዳሪዎቻቸው ከበሬታና አመኔታ ያገኙ ነበር፡፡ ሁለተኛው ነጥብ--መጋቢዎች እንዲያስተዳድሩት በኃላፊነት የተሰጣቸው ንብረት የጌታቸው መሆኑን ያውቁ ነበር (ዘፍ. 24፡34-38)፡፡ ይህ እንግዲህ በአንድ መጋቢና ባለቤት መሃል የነበረው ከፍተኛ ልዩነት ነው፡፡ መጋቢዎች የተሰጣቸውን ዐደራ ክብደት ጠንቅቀው ያስተውሉ ነበር፡፡ መጋቢዎች በዐደራ ከተቀበሉት ንብረት ላይ ለግል ጥቅማቸው ካዋሉ በእነርሱና በአሳዳሪያቸው መካከል የነበረው የመተማመን ግንኙነት ስለሚበጠስ ከኃላፊነታቸው ይሰናበታሉ
(ዘፍ. 3፡23፣ ሆሴዕ 6፡7)፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ--ኢሳ. 22፡14-18፡፡ በሕዝቅያስ የግዛት ዘመን ሳምናስ በጣም ቁልፍ የሆኑ ሥልጣኖችን ማለትም የመጋቢነትና የገንዘብ ያዥነት ሹመት ተቀብሎ ነበር፡፡ ሳምናስ የተቀበለውን አደራ አላግባብ ሲጠቀም ምን ተከሰተ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“አንድ መጋቢ ራሱን ከጌታው ጋር አንድ አድርጎ ያያል፡፡ የመጋቢነት ኃላፊነቶችን በመቀበል ለጌታው ተጠሪ ሆኖ ልክ እንደ ጌታው ይሠራል፡፡ የጌታው ፍላጎት የእርሱ ይሆናል፡፡ መጋቢው ከአሳዳሪው አመኔታ ማግኘቱ--የመጋቢነትን ዐደራ እጅግ የከበረ ያደርገዋል፡፡ ሆኖም በራስ ወዳድነት ስሜት ተገፋፍቶ በኃላፊነት የተቀበለውን የጌታውን ንብረት ለግል ጥቅሙ ካዋለ አደራ በላ ይሆናል”—Ellen
G. White, Testimonies for the Church, vol. 9, p. 246.
በምድራዊው ህይወታችን ባፈራነው ነገር መጋቢ የመሆናችንን አስፈላጊ ጽንሰ ሃሳብ እንዴት በተሻለ መገንዘብ እችላለን? ይህ ግንዛቤአችን በምናደርገው እያንዳንዱ ነገር ላይ ተጽእኖ ሊኖረው የሚችለው እንዴት ነው?
በአዲስ ኪዳን “መጋቢ” በሚል ጥቅም ላይ ለዋለው ቃል ግሪክኛው ሁለት መሰረታዊ ቃላቶችን የያዘ ሲሆን እነርሱም ኤፒትሮፖስ (3 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ) እና ኦይኮኖሞስ (10 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ) ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱም ቃላት መጋቢው የባለጠጋውን ንብረት በአደራ እንዲያስተዳድርና እንዲጠብቅ መሾሙን ይገልጻሉ፡፡
በአዲስ ኪዳንም ሆነ በብሉይ ኪዳን መጋቢዎች በሚሠሩት ነገር ይወሰናሉ፡፡ አዲስ ኪዳን መጋቢው ያለበትን ተጠያቂነት (ሉቃ. 12፡48) እና ዐደራ (1ቆሮ. 4፡2) ልዩ በሆነ መንገድ ይገልጻል፡፡ ነገር ግን ብሉይ ኪዳን እኛን እንደ መጋቢ በቀጥታ ከመግለጽ ይልቅ የእግዚአብሔርን ባለቤትነት በማወጅ ላይ ያተኩራል፡፡ ስለዚህ የመጋቢነት ጽንሰ ሃሳብ በሁለቱም ኪዳኖች ተመሳሳይ ሲሆን--አዲስ ኪዳን ግን ጽንሰ ሃሳቡን ከቤተሰብ አስተዳደር በሻገር አስፋፍቶ ያቀርበዋል፡፡
የሱስ ስለ ብልሁ አጭበርባሪ መጋቢ በተናገረው ምሳሌያዊ ታሪክ (ሉቃ. 16፡1-15) የመጋቢነትን ፍቺ ሰፋ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም የእርሱ ትምህርት መጋቢው ከገንዘብ ቀውስ ለመውጣት ከቀየሰው ዘዴ የላቀ አንደምታ አለው፡፡ በተጨማሪ እምነታቸውን ብልህ በሆነ አካሄድ እየገለጹ ከመንፈሳዊ ውድቀት ለሚያመልጡ ገጣሚ ነው፡፡ ብልህ መጋቢ ዛሬን አልፎ ገቢራዊ ለሚሆነው የየሱስ
ዳግም ምጽአት ይዘጋጃል (ማቴ. 25፡31)፡፡
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 1ቆሮ. 4፡1-2፣ ቲቶ 1፡7፣ 1ጴጥ. 4፡10፡፡ ጥቅሶቹ ስለ መጋቢዎችና መጋቢነት ምን ይላሉ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“እግዚአብሔር በዐደራ የሰጠኝ እያንዳንዱ ኃይልና ጉልበት መነሳሳት ያገኝ ዘንድ ልቤን ለመንፈስ ቅዱስ ልክፈት? እኔ የክርስቶስ ንብረት በመሆኔ የአገልግሎቱ ተቀጣሪ፣ የጸጋውም መጋቢ ነኝ፡፡” —Ellen G. White, Fundamentals of Christian
Education, p. 301.
በሉቃ. 12፡35-48 እንደምንመለከተው የሱስ “መጋቢ” የተሰኘውን ቃል ዘይቤአዊ በሆነ መንገድ ሲጠቀም ይስተዋላል፡፡ ታማኙና ብልሁ መጋቢ የሰው ልጅ ሲገለጥ ዝግጁ ሆኖ እንደሚገኝ--ታማኝ ያልሆነው መጋቢ ግን ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፣ ይዘገያል ብሎ በማሰብ የተቀበለውን ዐደራ ሳይወጣ እንደቀረ ይነግረናል፡፡ ታማኝ ያልሆነው መጋቢ በዐደራ የተሰጡትን ወገኖች የሚጨቁንና በዙሪያው ባሉ ላይ ግፍ የሚሠራ ሆነ፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ከዚህ በኋላ የመልካም ተግባር ምሳሌ ወይም
የጸጋ ሥራ መሪ አይደለም፡፡
ክርስቶስን የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል የእግዚአብሔርን ሀብት ለመቆጣጠር የተሾምን መጋቢዎች እንሆናለን፡፡ ከዚያ በላይ ግን--ለሰማይ ገጣሚ አድርጎ የሚያዘጋጀውን የክርስትናን ተጨባጭ መንፈሳዊ ህይወት የመምራት ኃላፊነት አለብን፡፡
ይህን ጥቅስ ያንብቡ፡ ሉቃ. 12:45፡፡ ክርስቶስ “ዘግይቷል” የሚል ስሜት የምንጋራ አንዳንዶቻችን እንዲህ ባለው ማታለያ እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?
እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ቆለ. 2:2-3፣ 1ጢሞቴ. 3:16፡፡ ጥቅሶቹ “ምስጢር” ብለው ያስቀመጡት ምንድን ነው? “ምስጢር” የሚለው አባባል ይህን ለማስተዋል ያለን ዕውቀት የተገደበ ስለመሆኑ ምን ይነግረና?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ነዕማታዊው ሶፋር ኢዮብን “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?” (ኢዮብ 11:7) ብሎት ነበር፡፡ “ምስጠር” የሚባለው ቃል--እንቆቅልሽ፣ የተሰወረ፣ የማይታወቅ፣ ያልተብራራ ወይም ለመረዳት የማይቻል የሚል ፍቺ አለው፡፡ ምንም እንኳ አምላካዊውን ቃል ሙሉ ለሙሉ መረዳት አሁንም ከአቅማችን በላይ ቢሆንብንም፤ የእግዚአብሔር ምስጢራት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሰፍረዋል፡፡ ምስጢር የሆኑትም ለዚህ ነው፡፡ ሁኔታው አጠገባችን ያለውን የቅርብ ሩቅ ማየት ሳንችል--ሰማይ ላይ ያሉትን ጥቃቅን ነገሮች ለማየት ተስፋ እንደማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ካልገለጠልን በቀር ያን ያህል አርቀን ማየት አንችልም፡፡
ለእኛ ስለተገለጠው ነገር ዘዳ. 29፡29 ምን ይላል?
እኛ ሙሉ ለሙሉ ለማናስተውላቸው ነገሮች መጋቢዎች ነን፡፡ የእኛ የዕውቀት አድማስ በራዕይና በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውን ያህል ብቻ ነው፡፡ ከፍ ያለው የመጋቢነት ኃላፊነታችን “እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለ ዐደራዎች” (1ቆሮ. 4፡1) መኖር ነው፡፡
እግዚአብሔር እንደ መጋቢነታችን የገለጠልንን መለኮታዊ እውነት ጠብቀን እንድናቆይ፣ እንድናስተምርና እንድንንከባከብ ይፈልጋል፡፡ ይህ የመጨረሻው የመጋቢነት ሥራ ሲሆን ይኸውም “የእምነትንም ጥልቅ ምስጢር በንጹህ ኅሊና መጠበቅ” መቻል ነው (1ጢሞቴ. 3፡9)፡፡
“የክብር ተስፋ” የሆነውን ክርስቶስ መለማመድ መቻላችን ከምስጢር ሁሉ እጅግ የላቀው ምስጢር ነው፡፡ የደኅንነት ዕቅድ ከሰብዓዊው አስተሳሰብ አድማስ እጅግ የገዘፈ እንደመሆኑ ሙሉ ለሙሉ መረዳት አዳጋች ነው፡፡ ሁሉ ነገር በእርሱ የተፈጠረውና ከፍጥረት ሥራ አንዳችም ከእርሱ ውጪ ያልሆነው (ዮሐ. 1፡1-3)፤ ፈጣሪ ራሱ ወደዚህ ምድር ወርዶ “በሥጋ መገለጡ” (Ellen G. White, Manuscript Releases, vol. 6, p. 112) እና ራሱን ለሰብዓዊው ዘር ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ መስጠቱ--የያዘው ምስጢር ፍጡራን ሙሉ ለሙሉ ሊያስተውሉ የማይችሉት ዓይነት ነው፡፡ መላእክት ሳይቀሩ የሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበትን ምስጢር ለመረዳት ይማራሉ (1ጴጥ. 1፡12)፡፡ ሆኖም እነርሱ የሚያውቁት ነገር እግዚአብሔርን ስለ ክብሩና ስለ በጎነቱ እንድናወድስ ያደርገናል (ራእ. 5፡13)፡፡
እርስዎ የወንጌል መጋቢ ሆነው ተጠርተዋል፡፡ ዐደራው የያዛቸው ኃላፊነቶች ሲነሱ ከፊትዎ ድቅን የሚለው ምንድን ነው?
ስለ መጋቢነት ዐደራ ስናስብ ተጨባጭና ተገቢነት ያላቸው ነገሮች ቶሎ ወደ አእምሮአችን ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አሁን እንደተመለከትነው መጋቢነት ከዚህ ባሻገር ይሄዳል፡፡ ልክ እንደ ተጨባጭ ንብረት ሁሉ የማይታዩ ስጦታዎችም ከእግዚአብሔር ይመጣሉ፡፡ በክርስቶስ የክርስትናን ጸባይ በማጎልበት በእርሱ መሆን የሚገባንን ሕዝቦች እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን የማይታዩ መንፈሳዊ ሀብቶች ሰጥቶናል (1ጴጥ. 4፡10)፡፡ ሰለዚህ እነዚህን ስጦታዎች ከተጨባጮቹ ይበልጥ በጥንቃቄ ልንይዝና ልናስተዳድር ይገባል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ስጦታዎች አለቅጥ የላቀ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኤፌ. 6፡13-17፡፡ መጋቢዎች እንሆን ዘንድ በእግዚአብሔር ምን ተሰጥቶናል? እነዚህን ነገሮች ባግባቡ ማስተዳደርና ጥቅም ላይ ማዋል ወሳኝ የሆነው ለምንድን ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
“የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡23)፡፡ ዓለምና ሙላቷ በክርስቶስ ያገኘነውን ቤዛነት ልትሰጠን አትችልም፡፡ ከእግዚአብሔር በነፃ የተበረከተልን የቤዛነት ስጦታ እጅግ የከበረውና ከሁሉ የላቀው ሀብታችን ነው፡፡ ይህን የቤዛነት ተጨባጭ እውነታ ሁሌም ጠብቀን መጓዛችን እንደ አንድ መጋቢ በእግዚአብሔር የተሰጡንን ሌሎች ንብረቶች በአስተማማኝ እንድንጠብቅ ይረዳናል፡፡
“ከተፈጥሮ የሚገኘው ትምህርት ከቀራኒዮ በሚፈነጥቀው ብርሀን ብቻ በትክክል መነበብ ይችላል፡፡ መልካም የሆነው ነገር ክፉውን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችል በቤተልሔም ብሎም በመስቀሉ ታሪክ ይፋ ይሁን፡፡ እያንዳንዱ ወደ እኛ የሚወርደው በረከት የቤዛነት ስጦታ መሆኑ ይታይ፡፡”—Ellen G. White, Education, p. 101.
መቤዠታችን እውን ሆኗል ምክንያቱም የሱስ የመጨረሻውን ዋጋ ከፍሏል፡፡ “በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገልን ቤዛነት፣ የኃጢአትን ይቅርታ አገኘን” (ኤፌ. 1፡7)፡፡ በጥቅሱ “አገኘን” የሚለው ቃል ዳንን የሚል ፍቺ አለው፡፡ የደኅንነት ባለቤት መሆን የቻልነው እግዚአብሔር በስጦታ ስላበረከተልን ነው፡፡ ክፉው እንዳይነጥቀን “የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ” መልበሳችን (ኤፌ. 6፡11) እጅግ ወሳኝና አንገብጋቢ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ እርሱ ይህን ለማድረግ የሚያስችለው ብቸኛ መንገድ የእኛ ፈቃደኝነት ሲሆን ይኸውም “የእግዚአብሔር ቃል” (ኤፌ. 6፡17) በግልጽ ያስቀመጠልንን ካልታዘዝን ነው፡፡ ታላቁ ከለላችን የተሰጠንን ብርሃን በእምነት መጠበቃችንና
መታዘዛችን ነው፡፡
ይህን ጥቅስ ደግመው ያንብቡ፡--ኤፌ. 6፡13-17፡፡ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ የምንለብሰው እንዴት ነው? በተሰጠን ሙሉ የጦር ዕቃ መጋቢዎች መሆን የምንችለውስ እንዴት ነው?
ብልህ መጋቢዎች የግብረገብ መርኅዎችን ተቀብለው በሥራ ላይ ለማዋል ባላቸው ፈቃደኝነት ይገለጻሉ፡፡ ኃላፊነትን በግል መቀበል ምርጫ ነው፤ በተግባር የሚገለጽም ድርጊት ነው፡፡ በመንስዔና ውጤት መካከል ያለውን ግንኙነት ለይቶ ይገነዘባል፡፡ ዐደራን በግል ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን ቸል ሊባል የማይችል ቁልፍ ባህሪ መሆኑን የመጋቢነት ፍቺ ያስረዳል፡፡ መጋቢው እግዚአብሔር በልቡ ውስጥ ያስቀመጠውን ነገር በከፍተኛ ፍላጎትና ንቃት የሚጠብቅ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለው ፈቃደኝነት መጋቢው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲኖረው የታለመውን ግንኙነት የሚገልጽ ምርጫ ነው፡፡
“እግዚአብሔር ሰዎችን ከራሱ ጋር ቀጥተኛ ወደ ሆነ ዝምድና ለማምጣት ይመኛል፡፡ ከሰብዓዊው ፍጡር ጋር ባለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እያንዳንዱ ሰው በግል ዐደራ የመውሰዱን መርኅ ይቀበላል፡፡ ሰዎች ለየግላቸው መወሰን የሚያስችላቸው ነፃነትና ምሪት እንዲያገኙ የእርሱ ምኞት ነው፡፡ እርሱ ስጦታዎቹን ለእያንዳንዱ በግል ሰጥቶአል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የተቀደሰው ዐደራ መጋቢ ተደርጎ ተወስዶአል፡፡ የሁሉ ባለቤት የሆነው አምላክ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ እያንዳንዱ የመጋቢነት ችሮታ በታማኝነት ወደ እግዚአብሔር ይዘርጋ፡፡” —Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 7, p. 176.
መጋቢዎች ስንሆን ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ዐደራ ለግለሰብ ወይም ለድርጅት አናውለውም፡፡ የግል ኃላፊነታችንም ሆነ ተጠሪነታችን ለእግዚአብሔር እንደመሆኑ ይኸው ዐደራ በማናቸውም መልኩ በዙሪያችን ካሉ ጋር መስተጋብር ይፈጥራል (ዘፍ. 39፡9፣ ዳን. 3፡16)፡፡ የተሰጠንን ዐደራ በደስታ በመቀበል አቅማችን የፈቀደውን ምርጥ ሥራ እንሠራለን፡፡ በእግዚአብሔር ዐይን የስኬት መሠረቱ
እምነታችንና ንጽህናችን እንጂ ዕውቀታችንና ችሎታችን አይደለም፡፡
ይህን ጥቅስ ያንብቡ፡--2ቆሮ 5፡10፡፡ ጥቅሱን ከብልሁ መጋቢ ዐውደ ሃሳብ ፍቺ አኳያ እንዴት እናስተውለዋለን?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የነገረ መለኮት ምሁራንና ፈላስፎች በመምረጥ ነፃነት ዙሪያ ለበርካታ ምዕተ ዓመታት ሲሟገቱ ኖረዋል፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዙሪያ ግልጽ አቋም አለው፡ እኛ እንደ ሰብዓዊ ፍጡርነታችን ነፃ ፈቃድ እና ነፃ የመምረጥ ችሎታ አለን፡፡ ይህ ካልሆነ እንደ ሥራችን ለፍርድ እንቀርባለን የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ትርጉመ ቢስ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ጌታ ለሰጠን ንብረት ታማኝ መጋቢ መሆናችንን ጨምሮ ሁላችንም በየግላችን ትክክለኛውን ምርጫ የማድረግ ኃላፊነት አለብን፡፡
በብሉይ ኪዳን “መጋቢ” በሚል ጥቅም ላይ የዋለውና በጥቂት ቦታዎች ብቻ የተጠቀሰው ይህ ቃል፤ የተተረጎመው ከአንድ ቃል ሳይሆን “የቤቱ አዛዥ” ከሚል ሀረግ ነው፡፡ ለምሳሌ ዘፍ. 43፡19 እንደሚከተለው መተርጎም ይችላል፡ “ወደ መጋቢው ዮሴፍ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፡፡” አንድ መጋቢ የመጋቢነት ዐደራ በወሰደበት ቤት ውስጥ የሚኖረው ቤተሰብ--የቤቱ አካል አድርጎ ከተቀበለው ከዚያቤት ይልቅ ለእርሱ የከበረ ዋጋ ያለው ምን ሊሆን ይችላል? ስለዚህ መጋቢው በጣም ውድ ነገር በዐደራ ተሰጠው እንጂ በእጁ እያስተዳደረ ያለው ንብረት አንጡራ ሀብቱ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ መጋቢው ለገዛ ንብረቱ ቢሆን ያደርግ ከነበረው ጥንቃቄ በላይ ኃላፊነት እንዲሰማው ያደርገዋል፡፡
ይኸው ተመሳሳይ ጽንሰ ሀሳብ በአዲስ ኪዳን መቀጠሉን እንመለከታለን፡፡ “አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ጽንሰ ሀሳቦችን ወስዶ ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ጽንሰ ሀሳቦችና ቃላቶች ጋር በማገናገኘት መጽሐፍ ቅዱስ በመጋቢነት ዙሪያ ያለው አስተምህሮ እንዲበለጽግና እንዲስፋፉ አድርጓል፡፡ ከመጋቢነት ጋር ዝምድና ኖሯቸው ጥቅም ላይ የዋሉት የተለመዱ የግሪክ ቃላት ምንጫቸው--ኦይኮስ እና ኦይኪያ ሲሆን ‘ቤት’ የሚል ፍቺ አካተዋል፡፡ ኦይኮኖሞሰ ደግሞ ቤቱን የሚቆጣጠር፣ መጋቢ ወይም ባለ ዐደራ የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን ‘የቤቱ አዛዥ’ በሚል የተተረጎመው ኦይኮኖሚያ ብዙውን ጊዜ ሰፊ ትርጉም አለው፡፡” —
Handbook of Seventh-day Adventist Theology (Hagerstown, Md.: Review and Herald Publishing Association, 2000), p. 653.