ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 17:9–11፣ ዘፀ. 31:13-17፣ ራእ. 13:17፣ ኤፌ. 1:13-14፣ ዕብ. 4:9-10.
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፡፡ የዘመናት ንጉሥ ሆይ፤ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው፡፡” (ራእ. 15፡3)፡፡
የዚህ ሣምንት ጥናታችን መግቢያ ጥቅስ የሚጀምረው በሙሴ እና በበጉ
መዝሙር ነው፡፡ በባሕሩ አጠገብ ቆመው ይህን መዝሙር የሚዘምሩት
“አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቁጥር ድል የነሡት” ናቸው (ራእ. 15፡2) ከዚህ
አሃዝ መሀል መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
በመጨረሻው ዘመን እውነተኞቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሚለዩባቸው
ምልክቶች አንዱ ሰዎች የአውሬውን ምልክት እንዳይቀበሉ የሚያስጠነቅቀውን
የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ማወጃቸው ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ
ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ጥቅስ አለመኖሩ በምልክቱ ምንነት ዙሪያ ለዓመታት
ብዛት ያላቸው ግራ አጋቢ አስተሳሰቦች ሲንጸባረቁ ኖረዋል፡-በግንባር ላይ
የሚታተም የምስጢር ቁልፍ፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥር ወይም የግለ ታሪክ
መታወቂያ ወዘተ...
ከባቢሎን በሚወጡ በፍጥነት የሚያድጉና የሚሰራጩ ግራ አጋቢ ጽንሰ ሃሳቦች
ፈጽሞ መደነቅ የለብንም፡፡ ደግሞስ ራሱ የስሙ ፍቺ “ድብልቅልቅ” አይደል?
የእግዚአብሔር ትሩፋን ሕዝቦች የሦስተኛውን መልአክ መልእክት በኃይል
ማወጅ ይችሉ ዘንድ በቅድሚያ በዚህ ርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ግልጽ ማስተዋል
ሊኖራቸው የግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ሣምንት የአውሬው ምልክት ምን እንደሆነና
የእግዚአብሔርን ማኅተም በመቀበል እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል በተሻለ
ለማስተዋል እንሞክራን፡፡
በብሉይ ኪዳን ዘመን እውነተኞቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሚለዩባቸው ሁለት
ውጪያዊ ምልክቶች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ አንዱ ደግሞ ግርዛት ነበር፡፡ ለመሆኑ
መጀመሪያ ይህ ምልክት የተሰጠው ለማን ነበር? ዘፍ. 17፡9-11፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አብርሃም እና ከእርሱ በኋላ የሚመጣው ትውልድ እንዲገረዝና ይህን መገረዝ
የደኅንነት ኪዳን ምልክትነት አድርጎ እንዲጠብቅ እግዚአብሔር አዞት ነበር፡፡
ወንዶች ልጆች በተወለዱ በስምንተኛው ቀን መገረዝ ነበረባቸው (ዘሌዋ. 12፡3)
፡፡ ሆኖም ይህ ሥነ ሥርዓት ከፍ ያለ ኃይማኖታዊ አንደምታ የነበረው ሲሆን፤
ተምሳሌትነቱ የልብን “መገረዝ” ወይም መታደስ የሚያመለክት ነበር (ዘዳ.
30፡6)፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፎአል “አንድ ሰው ለይምሰል
በውጫዊው ብቻ ይሁዲ ልሁን ቢል ይሁዲ አይሆንም፤ እውነተኛ ግዝረትም
ውጫዊና ሥጋዊ ሥርዓት አይደለም፡፡ ዳሩ ግን አንድ ሰው ይሁዲ የሚሆነው
በውስጣዊ ማንነቱ ይሁዲ ሁኖ ሲገኝ ነው፡፡ ግዝረትም ግዝረት የሚሆነው
በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ በመንፈስ የልብ ግዝረት ሲኖር ነው፡፡ እንዲህ ያለው
ሰው ምስጋናው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ (ሮሜ 2፡28-29)፡፡
እነዚህ በአዲስ ኪዳን የምናገኛቸው ጥቅሶች፡--1ቆሮ. 7፡19፣ ገላ. 5፡6 እና
6፡15 ግርዘት--ለኃጢአት በመሞት በአዲስ ሕይወት የመነሳት፣ የመለወጥና
“አዲስ ፍጥረት” የመሆን ተምሳሌት በሆነው ጥምቀት መተካቱን ያሳዩናል፡፡
(ሮሜ 6፡3-4)፡፡ የግርዘት አስፈላጊነት ያከተመ መሆኑንና ጉዳዩ ያለው “በፍቅር
ውስጥ በሚሠራ እምነት” እና “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ” ላይ መሆኑን
የሚናገረው ለዚህ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲለይበት የሰጠው ሁለተኛው ውጪያዊ ምልክት ምን
ነበር? ምልክቱ የተሰጠበት ምክንያት ምን ነበር? (ዘፀ. 31፡13፣ 17፣ ሕዝ.
20፡12፣20)፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሰንበት በምልክትነት የተሰጠው ከፍጥረት አንስቶ መሆኑን ልብ ይሏል (ዘፍ.
2፡2-3)፡፡ ሆኖም የግርዘት ሥርዓት ግን ከአብርሃም ይጀምራል፡፡ በዚህ የተነሳ
የሱስ የዘፍጥረት መጽሐፍን እንደ ማስረጃ በመውሰድ “ሰንበት ለሰው ተፈጠረ
እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም” (ማር. 2፡27) በማለት ተናግሮአል፡፡ ይህ
በፍጥረትም ሆነ (የእጆቹ ሥራ በመሆናችን) በመዋጀት (የሚያጸድቀንና
የሚቀድሰን እርሱ በመሆኑ) የእርሱ መሆናችንን ያሳያል፡፡ በዚህ የተነሳ ምንም
እንኳ ጳውሎስ የመገረዝ አስፈላጊነት ማክተሙን ቢናገርም የእግዚአብሔርን
ትእዛዝ መጠበቅ ግን (ሰንበትን ጨምሮ) ዛሬም አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል
(ዕብ. 4፡9)፡፡
ልብዎ በእውነት መገረዙን አስተሳሰቦም ሆነ ውጥንዎ የሚያሳየው እንዴት ነው?
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ “የአውሬውን ምልክት” እንዴት ማስወገድ
እንደሚቻል አስመልክቶ ምን ያስተምሩናል? ራእ. 13:17፣ 14:9፣ 10፡16:2
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከምህረት ጋር ያልተቀላቀለውን የእግዚአብሔር ቁጣ ተቀብለውና በሰባቱ
የመጨረሻ መቅሰፍቶች ተመትተው በመጨረሻም በእሳት ሀይቅ ውስጥ
የሚጣሉት--የአውሬውን ምልክት ላለመቀበል ጸንተው በድል አድራጊነት
በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ለእግዚአብሔርና ለበጉ የምስጋና ውዳሴ
ከሚያቀርቡት ጋር ያላቸው ልዩነት እንዴት ግዙፍ ነው!
ለመሆኑ ይህ ማንም ቢሆን ሊቀበለው የማይሻው ምልክት ምንድን ነው?
ከላይ የቀረቡት ጥቅሶች ጉዳዩን ከሐሰት አምልኮ ጋር በግልጽ ያገናኙታል፡፡
ቀደም ባለው ትምህርት በዳን. 7 የአራተኛውን አውሬ ኃይል እንደተመለከትነው
በቀጣይ የለውጥ ምዕራፉ (በተጨማሪ ከባሕር የወጣ አውሬ በሚል በራእ 13
የተገለጸው) “ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል” (ዳን. 7፡25)፡፡ ለመለወጥ
ያሰበው አንድ ሕግ ሲሆን እርሱም አራተኛው ሕግ ይኸውም ሰንበት ነው፡፡
ከአሥሩ ትእዛዛት ውስጥ በቀጥታ ስለ ጊዜ የሚናገርና እግዚአብሔርን እንደ
ፈጣሪ የሚያቀርብ ብቸኛው ትእዛዝ ይህ ብቻ ነው “ሰማይንና ምድርን፣
ባሕርንና በውስጡም ያሉትን ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን
አርፎአል” (ዘፀ. 20፡11)፡፡
የመጀመሪያው መልአክ መልእክት መለስ ብለን ወደዚህ ትእዛዝ እንድንመለከት
በማድረግ የአውሬው ኃይል ሕግን ለመለወጥ መሞከሩንና ጌታን ብቻ እንደ
ፈጣሪ ማምለክ እንዳለብን በግልጽ ያስቀምጥልናል፡፡ በእርግጥ በራእ. 12-14 ስለ
አምልኮ ከሚናገሩት ሰባት ቁጥሮች መካከል በእውነተኛ አምልኮ ዙሪያ
የሚናገረው ይህኛው (14፡7) ብቻ ነው፡፡ ሌሎቹ ስድስት ቁጥሮች ለአውሬውና
ለምስሉ የሚቀርቡ የሐሰት አምልኮዎችን ያስጠነቅቃሉ (ራእ. 13:4፣ 8፣ 12፣ 15፣
14:9፣ 11)፡፡ ሦስተኛው መልአክ በዚህ የሐሰት አምልኮ ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች
ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል እንደ ገለጠ፤ ወዲያውኑ እግዚአብሔርን
በእውነት የሚያመልኩ እንዲህ በሚሉ ሃረጎች ተወስተዋል፡ “የእግዚአብሔርን
ትእዛዛት የሚጠብቁና ለኢየሱስም ታማኝ ሆነው በትዕግሥት የሚጸኑ ቅዱሳን
የሚታወቁት በዚህ ነው” (ራእ. 14፡12)፡፡
በሌላ አነጋገር የእነዚህ ሦስት መልእክቶች እወጃ መላውን የሰው ዘር
በሁለት ጎራ ይከፍላል፡--ሰባተኛውን ቀን ሰንበት ጨምሮ ሁሉንም ትእዛዞች
በመጠበቅ ፈጣሪን የሚያመልኩ እና አውሬውንና የእርሱን ምስል የሚያመልኩ፡፡
ከዚያም ይህ ሐሰተኛ ቅርጽ የያዘ አምልኮ ሰንበትን በመጠበቅ ፈጣሪን እናምልክ
የሚል አማራጭ ይዞ ይመጣል፡፡
በአምልኮና በታማኝነት መካከል ስላለው ግንኙነት በደንብ ለማሰብ
ይሞክሩ፡፡ ለእግዚአብሔር ያለንን ታማኝነት ለማሳየት በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑት
የአምልኮ ገጽታዎች የትኞቹ ናቸው?
እንደ ፊርማ ሁሉ ማኅተምም ሰነድን ሕጋዊ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡ በጥንት
ዘመን ሕጋዊነትን ወይም ባለቤትነትን ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውል የነበረው
ማኅተም ለስላሳ በሆነ ሰም ወይም ሸክላ ላይ ይረገጥ ነበር፡፡
የእግዚአብሔር ማኅተም ምንድን ነው? ጥቅም ላይ የሚውለውስ እንዴትና መቼ
ነው? ኤፌ. 1:13-14፣ 4:30፣ 2ጢሞቴ. 2:19፣ ራእ. 7:1–4፣ 14:1፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የእግዚአብሔር ማኅተም የባለቤትነቱና የሕዝቡ ከለላነት ምልክት ነው፡፡
ጳውሎስ መታተምን ከመለወጥና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ከመቀበል ጋር አያይዞ
ይገልጸዋል፡፡ ጳውሎስ ይህን ለሁሉም አማኞች የተሰጠ ስጦታ “ዋስትና” ወይም
“መያዣ” ብሎ የሚጠራው ሲሆን ይኸውም ፍጹም የመዋጀታቸውና የሱስ
ዳግም ሲገለጥ የሚቀበሉት ወራሽነት ነው፡፡
የራእይ መጽሐፍ ከዳግም ምጽአቱ ቀደም ብሎ ገቢራዊ ስለሚሆን ሌላ
የመታተም ሥዕል ይሰጠናል፡፡ ይህ የመጨረሻ ማኅተም የሚሰጠው ለ144,000
ሲሆን ይኸውም የኋለኛው የመንፈስ ቅዱስ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ነው፡፡
እነዚህ ሰዎች በግንባራቸው ላይ የተጻፈ የእግዚአብሔር ስም (ወይም ፊርማ)
አላቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታቸው በሚሠራው ሥራ አማካኝነት
የእግዚአብሔርን ጸባይ ማንጸባረቅ ችለዋል፡፡
የእግዚአብሔርን ማኅተም ከአውሬው ምልክት ጋር ያስተያዩ፡፡ በሁለቱ መካከል
ምን ዓይነት ልዩነቶች ተጠቅሰዋል? ራእ. 7፡3፣ 14፡9፡፡
አምላካዊው ማኅተም ለእውነተኛዎቹ የእግዚአብሔር አምላኪዎች ሲሰጥ፤
አውሬውን የሚያመልኩ ደግሞ ምልክቱን ይቀበላሉ፡፡ ማኅተሙ የሚያርፈው
በግንባር ላይ ብቻ ሲሆን፤ ይህም ሰብዓዊው ፍጡር ነፃ የመምረጥ ችሎታውን
ተጠቅሞ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት እርሱን ማምለኩን ያመለክታል፡፡ በሌላ
በኩል ምልክቱ በግንባር ወይም በእጅ ላይ ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች በአንድ
ወይም በሌላ ምክንያት አውሬውን ሊያመልኩ እንደሚችሉ ያሳያል፡፡
እግዚአብሔርን በእውነት እያመለኩ እንደሆነ በማሰብና በአእምሮአቸው
ተስማምተው ወይም በጉዳዩ ሳያምኑ ግን ካልተመሳሰሉ ሊደርስባቸው
የሚችለውን የከፋ ውጤት በመፍራት--ካልተመሳሰሉ መግዛትም ሆነ መሸጥ
ካለመቻላቸው በተጨማሪ በስተመጨረሻ ስለሚገደሉ (ራእ. 13፡17-15)፡፡
“ከዓለም ጋር ሕብረት የሚፈጥሩ ዓለማዊውን ቅርጽ በመውሰድ
የአውሬውን ምልክት ለመቀበል ይዘጋጃሉ፡፡ ራሳቸውን የሚክዱ፣
በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት የሚቀርቡና እውነትን በመታዘዝ ነፍሳቸውን
የሚያነጹ፤ ሰማያዊውን ቅርጽ በመውሰድ የእግዚአብሔርን ማኅተም
በግንባራቸው ለመቀበል ይዘጋጃሉ””—Ellen G. White, Testimonies for the
Church, vol. 5, p. 216.
ለመሆኑ ይህ ከእኛ ልናርቀው የሚገባው ምልክት ምንድን ነው? ቀደም
ባለው ትምህርታችን እንደ ተመለከትነው በዳን. 7 የቀረበው የአራተኛው አውሬ
ኃይል በቀጣይ የለውጥ ምዕራፉ (በተጨማሪ በራእ. 13 ከባሕር በወጣው አውሬ
የተገለጸው) “ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል” (ዳን. 7፡25)፡፡ ለመለወጥ
ያሰበው አንድ ሕግ ሲሆን እርሱም አራተኛው ሕግ ይኸውም ሰንበት ነው፡፡
ከአሥሩ ትእዛዛት ውስጥ በቀጥታ ስለ ጊዜ የሚናገርና እግዚአብሔርን እንደ
ፈጣሪ የሚያቀርብ ብቸኛው ትእዛዝ ይህ ብቻ ነው “ሰማይንና ምድርን፣
ባሕርንና በውስጡም ያሉትን ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን
አርፎአል” (ዘፀ. 20፡11)፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጀመሪያው መልአክ መልእክት አንባቢውን
የአውሬው ኃይል ሊለውጥ ወደ ሞከረው ወደዚህ ተመሳሳይ ትእዛዝ
በማመላከት፤ እንደ ፈጣሪነቱ ልናመልከው የሚገባ ጌታን ብቻ እንደሆነ ግልጽ
ያደርግልናል፡፡ ከዚያም በዚህ ምትክ “አውሬውንና የእርሱን ምስል” (ራእ. 14፡9)
በሚያመልኩ ዕጣ ፈንታ ላይ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የእግዚአብሔር ታማኝ
ሕዝቦች በቁ. 12 ተገልጸዋል፡፡
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ራእ. 14፡12፡፡ ከዚህ ጥቅስ ዐውደ ሀሳብ በመነሳት ይህ
የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝቦች የተገለጹበት መንገድ ሰንበት ለምን
የመጨረሻዎቹ ክስተቶች ማዕከል እንደሆነ ማስተዋል እንድንችል እንዴት
ይረዳናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጥቅሱ እንደሚከተለው ይነበባል፡ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና
ለኢየሱስም ታማኝ ሆነው በትዕግሥት የሚጸኑ ቅዱሳን የሚታወቁት በዚህ
ነው፡፡” (ራእ. 14፡12)፡፡ በጥቅሱ እንደተመለከትነው እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪ
እና እርሱ ብቻ ሊመለክ እንደሚገባው አድርጎ ወደ እግዚአብሔር
የሚያመላክተው አራተኛው ትእዛዝ ሰንበት “የእግዚአብሔር ትእዛዛት” አካል
ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙዎች “የአውሬው ምልክት” ከእሑድ አምልኮ ጥያቄ ጋር
በቀጥታ መያያዙን በመመልከት አስመሳዩ “ሰንበት” በመጽሐፍ ቅዱስ ያልታዘዘና
አራተኛውን ትእዛዝ ከመጠበቅ በተቃራኒ የቆመ መሆኑን ቢመለከቱ የሚገርም
አይሆንም፡፡
በዚህ አባባል መሰረት ዛሬ በእሁድ ቀን አምልኮ የሚያደርጉ ክርስቲያኖች
የአውሬውን ምልክት ተቀብለዋል ማለት ይቻላል? በጭራሽ፡፡ በራእ. 13፡15
እንደቀረበው ይህን የአውሬውን የሐሰት አምልኮ ለመቀላቀል የሚቃወሙት
ይገደላሉ፡፡ እንደውም በስተመጨረሻ አምልኮው የሕይወትና የሞት ጉዳይ
ይሆናል፡፡ በእርግጥ ይህ ክስተት ገና ወደዚያ ነጥብ ባለመድረሱ የመጨረሻው
ፈተና አስኪመጣ የአውሬው ምልክት አይሰጥም፡፡ ስለዚህ አሁን የአውሬውን
ምልክት የተቀበለ ማንም የለም፡፡
የእግዚአብሔር ትእዛዛት፡፡ የየሱስ እምነት፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ለመባል
እነዚህ ባህሪያት ዛሬም ቢሆን ወሳኝ ገጽታ ያላቸው ለምንድን ነው?
በአዳምና ሔዋን የጀመረውና በዘመነ እስራኤል የቀጠለው ሰባተኛው ቀን
ሰንበት፤ በምድር ታሪክ የእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝቦች ምልክት መሆኑን
ተመልክተናል፡፡ እንዲሁም በየሱስ እና በደቀ መዛሙርት ፊት አውራሪነት
በአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን መቀጠሉን ተመልክተናል፡፡ የእግዚአብሔር
የመጨረሻው ቀን ሕዝቦች መለያ ምልክት “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት
የሚጠብቁና ለኢየሱስም ታማኝ” መሆናቸው ነው፡ (ራእ. 14፡12)፡፡
ሰንበት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ለክርስቲያኖች ያለው የተለየ
ትርጉም ምንድን ነው? ዘፀ. 20:8–11፣ ዕብ. 4:9-10፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሰንበት በአስሩ ትእዛዛት አማካይ ስፍራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ይህ ትእዛዝ
የሥልጣኑ ምልክት ወይም ማኅተም በመሆን በፈጣሪ ተሰጥቶአል፡፡ የስሙን
መለያ ይዞአል፡ “የእግዚአብሔር የአምላክህን”፡፡ የሥልጣኑን ግዛት መለያ
ይዞአል፡ “ሰማይንና ምድርን፤ ባሕርንና በውስጡም ያሉትን”፡፡ እንዲሁም
የሥልጣኑን ምንጭ መለያ ይዞአል፡ “እግዚአብሔር በስድስት ቀን ፈጥሮ፤
በሰባተኛው ቀን አርፎአልና”፡፡
እግዚአብሔር በየሱስ ሁሉንም ነገር እንደፈጠረ አዲስ ኪዳን ይናገራል
(ዮሐ. 1፡1-3፣ ቆለ. 1፡16፣ ዕብ. 1፡1-2)፡፡ ምድራችንን በስድስት ቀናት ፈጥሮ
በሰባተኛው ቀን ያረፈ የሱስ ነው፡፡ ስለዚህ የሱስ አርብ ከሰዓት በመስቀል ላይ
ከተሰቀለ በኋላ “ተፈጸመ!” (ዮሐ. 19፡30) ማለቱ ጥልቅ ትርጉም አለው፡፡ እርሱ
የፍጥረት ሥራውን ጨርሶ በሰንበት እንዳረፈ ሁሉ፤ እኛን ለመዋጀት ሲል በእኛ
ቦታ በመሞት ለኃጢአታችን መሥዋዕት የመሆን ሥራውን እንደ ፈጸመ፤ የሱስ
በሰንበት በመቃብር አረፈ፡፡ በመሆኑም ሰንበት መጀመሪያ በፍጥረት ከዚያም
በመስቀል ያለ ጥርጥር የተባረከ ነው፡፡ የዕብራውያን መጽሐፍ እንደሚናገረው
ክርስቲያን በሰንበት ሲያርፍ “እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እርሱም ደግሞ
ከሥራው ያርፋል” (ዕብ. 4፡10)፡፡ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻ
ክርስቶስ የሠራውን ሥራ በእምነት በመቀበል የዳንን እንደመሆናችን ሰንበት እኛ
ራሳችንን ማዳን እንደማንችል የሚያሳይ ፍጹም ምሳሌ ነው (ዕብ. 12፡2)፡፡
ሰንበት ከሥራችን የማረፋችን ተምሳሌት ከሆነ እሑድን መጠበቅ ምን
ይወክላል? ከባቢሎን መሰረታዊ ባህሪ ጋር ገጣሚ የሚሆነውስ እንዴት ነው?
“የእግዚአብሔር ሕዝቦች በግንባራቸው ሲታተሙ በዐይን
መታየት የሚችል ምንም ዓይነት ማኅተም ወይም ምልክት አይኖርም፡፡ ነገር ግን
በአእምሮአቸውም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወታቸው በእውነት ላይ ተመስርተው
ስለሚቆሙ መናወጥ አያገኛቸውም፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንደ ታተሙና
ለብጠራው እንደተዘጋጁ ጉዳዩ ገቢራዊ ይሆናል፡፡ በእርግጥ ገቢራዊ መሆን
ከጀመረ ውሎ አድሮአል፡፡ እየመጣ ያለውን ነገር እናውቅ ዘንድ. . . እነሆ አሁን
አምላካዊው ፍርድ በምድሪቱ ላይ ነው፡፡”—Ellen G. White, The Faith I
Live By, p. 285.
“ሰንበት አወዛጋቢውን እውነት ማሳያ እንደመሆኑ ታላቅ የታማኝነት
መፈተኛ ይሆናል፡፡ የመጨረሻው ፈተና በሰዎች ላይ በሚደርስበት ወቅት
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉትንና የማያገለግሉትን የሚለየው መስመር
ይሰመራል፡፡ ሐሰተኛው ሰንበት ከመንግሥት ሕግ ጋር እጅና ጓንት ሲሆንና
ከአራተኛው ሕግ ጋር ተቃርኖ ውስጥ ሲገባ፤ ሰንበት እግዚአብሔርን
ለሚቃወመው ኃይል የታማኝነት ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ
በመታዘዝ እውነተኛውን ሰንበት መጠበቅ ለፈጣሪ ያለንን ታማኝነት
የምናሳይበት ማስረጃ ነው፡፡ አንደኛው ክፍል ለምድራዊ ኃይላት በመታዘዝ
የአውሬውን ምልክት ሲቀበል፤ ሌላኛው ለመለኮታዊው ሥልጣን የታማኝነት
ምልክት የሆነውን የእግዚአብሔር ማኅተም ይቀበላላል”—Ellen G. White,
The Great Controversy, p. 605.
1.አላስፈላጊ ውዝግብ በማይፈጥር መልኩ ስለ አውሬው ምልክት እና ስለ
እግዚአብሔር ማኅተም እውነታ ለሌሎች ማሳየት የምንችልባቸው መንገዶች
የትኞቹ ናቸው?
2.ሰንበት እና በመንፈስ ቅዱስ መታተም የተዛመዱት እንዴት ነው?
ከላይ በቀረበው ሀሳብ “በአእምሮአቸውም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወታቸው
በእውነት ላይ ተመስርተው ስለሚቆሙ” በሚለው ሀረግ ትርጉም ዙሪያ
ተወያዩ፡፡
3.በመንፈሳዊቷ ባቢሎን እሴቶችና አሠራር መለያ ባህሪያት ላይ ተወያዩ፡፡
ባህሪያቱ ከእግዚአብሔር መንግሥት እሴቶች የሚለዩት እንዴት ነው? አንዳንድ
የባቢሎን እሴቶች ዛሬ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን አድብተው ሲገቡ
የሚስተዋሉባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? የእግዚአብሔርን መንግሥት
እሴቶች በሚያንጸባርቅ የክርስትና ምግባር የእነዚህን ነገሮች ምንነት መለየት
መማርና መፍትሔ ማምጣት የምንችለው እንዴት ነው?