ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሐዋ.21፣ ሮሜ 2፡28-29፣ ገላ.5፡6፣ ሐዋ.22፣ ሐዋ. 23፡1-30፣ ማቴ. 22፡23-32፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ፡- “በሚቀጥለውም ሌሊት ጌታ በአጠገቡ ቆሞ፡፡ ‹‹ጳውሎስ ሆይ አይዞህ በኢየሩሳሌም እንደመሰከርህልኝ በሮምም ደግሞ ልትመሰክርልኝ ይገባሃል›› አለው፡፡” (ሐዋ. ሥራ 23፡11)
ከ
ጳውሎስ የመጀመርያ ሚሲዮናዊ ጉዞ በኋላ በቤተክርስትያን ውስጥ አህዛብ
እንዴት ወደ እምነቱ መቀላቀል አንደሚገባቸው በተመለከተ መሰረታዊ የሆነ
አለመግባባት መፈጠሩ ግልጽ ሆነ (ሐዋ.15፡1-5)። ግጭቱ እያየለ ቢመጣም ጳውሎስ
ግን በቤተክርስትያን ውስጥ አንድነት የሚመጣበትን መንገድ ያቅድ ነበር። የመማክርት
ጉባኤው ድሆችን እንዲያስብ ስላሳሰቡት(ገላ. 2፡10) የአህዛብ ቤተክርስትያናት በይሁዳ
ለሚገኙ ወንድሞች ‹‹ቅዱሳን ቤተሰቦች›› (1ኛ ቆሮ.16፡1) የገንዘብ እገዛ እንዲያደርጉ
ጋበዛቸው፤ ምናልባትም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለማፍረስ እንደ
ድልድይ ይሆናል ብሎ ተስፋ አደረገ፡፡
አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ቢያውቅም ጳውሎስ በሦስተኛው ጉዞ መጨረሻ ላይ ወደ
ኢየሩሳሌም ለመሄድ ወሰነ። በአንድ በኩል ወገኖቹ ለሆኑት አይሁዳውያን ያለውን
እውነተኛ ፍቅር ለማሳየት ሲሆን (ሮሜ 9፡1-5) በሌላ በኩል ደግሞ አንድ የሆነ
ቤተክርስትያን እንዲኖር ይናፍቅ ስለነበር(ገላ. 3፡28፤5፡6) ነው። አይሁዳውያንም
ይሁኑ አህዛብ ህግን በመጠበቅ ሳይሆን በእምነት እኩል ስለዳኑ (ሮሜ 3፡28-30)
አብሮ ላለመሆን የህግ ቅድመ ሁኔታዎችን መደርደር ሁሉን የሚያካትተውን የወንጌልን
ባህሪ የሚጣረስ ሃሳብ ነው (ኤፌ. 2፡11-22)። በህይወቱ አዲስ ምዕራፍንና ተልእኮን
አንግቦ የሚሄደውን ጳውሎስ እስቲ እንከተለው፡፡
የዚህን ሳምንት ጥናት አንብበው ለ ሰንበት ይዘጋጁ፡፡
ጳውሎስ ልክ እየሩሳሌም አንደደረሰ ምዕመናን ምናሶን ቤት እንዲቆይ በማድረግ ሞቅ
ያለ አቀባበል አደረጉለት (ሐዋ. 21፡16-17)።
በሐዋ.21፡18-22 ላይ ያዕቆብና የእየሩሳሌም ሽማግሌዎች ጳውሎስ በአካባቢው በሚገኙና
ለሙሴ ህግ ቅናት በነበራቸው አይሁዳውያን ዘንድ ስለሚኖረው ተቀባይነትተጨነቁ፡
፡ ለአይሁዳውያኑ የተነገራቸው እርሱ በውጪ የሚገኙ አይሁዳውያን የሙሴን ህግ
እንዲተው ‹‹ልጆቻቸውም እንዳይገረዙ ልማዳቸውንም እንዲተው››እንደሚያስተምር
ነው፡፡ (ሐዋ. 21፡21)
ነገር ግን ይህ ፈጽሞ ትክክል አልነበረም፡፡ ጳውሎስ እያስተማረ የነበረው ድነትን
ለማግኘት መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም ምክንያቱም አይሁድም
ይሁኑ አህዛብ በየሱስ ላይ ባላቸው እምነት እኩል ድነዋል(ሮሜ 2፡28-29፣ ገላ. 5፡
6፣ ቆላ. 3፡11)፡፡ ይህ አይሁዳውያንን በግልጽ ህጉንና መስፈርቱን ፈጽመው እንዲረሱ
ከማስተማር ፈፅሞ የተለየ ነው፡፡ መታዘዝ ብዙ ጊዜ የሚተረጎመው ህግ በመጠበቅ
መዳን ‹‹Legalism›› ተብሎ ቢሆንም ትክክለኛ ትርጉሙ ግን ያ ብቻ አይደለም፡፡
ሐዋ. 21፡ 23-26ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ አንዴት አድርጎ ነው አሁንም ታማኝ አይሁዳዊ
መሆኑን ያሳየው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ አሳማኝ በሆነ መልኩ እንዲራመድ(ግጭትን የሚያነሳሳ ነገር እንዳይናገር)
ተመክሮ ነበር፡፡ የሚወራበት አሉባልታ ሐሰት መሆኑን ለማረጋገጥ የግድ አይሁዶች
የሚያደርጉትን ነገር አድርጎ እንዲያሳይ ተመከረ፡፡ ይህም ለተወሰኑ ስለት ላለባቸው
ሰዎች ራሳቸውን ናዝራዊ እንዲያደርጉ ወጪያቸውን በመሸፈን ይገለጣል፡፡ ይህ
ስለት ደግሞ አንድ አይሁድ ራሱን ለእግዚአብሔር በተለየ መንገድ የሚያስረክብበት
ሐይማኖታዊ ስነስርአት ነበር፡፡
የሚያሳዝነው ግን ጳውሎስ እጁን ሰጠ(ይህንን ምክር ሰማ)፡፡ ጀግና የምንላቸው ሰዎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ ያሉትን ጨምሮ የራሳቸው የሆነ ጉድለት ነበራቸው። ለምሳሌ
የአብርሃምን፣ የሙሴን፣ የጴጥሮስ እና የሌሎችንም ህይወት እንደምንመለከተው
ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ ይህንን ያደረገው ከአይሁዳውያን ጋር እንደ አይሁዳውያን
ሆንኩ ያለውን የራሱን መርህ ለመከተል ይሆናል(1 ቆሮ. 9፡19-23) ወይንም የስለቱ
ይዘት ግልፅ ባይሆንም እንኳን ጳውሎስ እራሱ ጥቂት ቀደም ብሎ ስለት ስለተሳለም
ሊሆን ይችላል(ሐዋ. 18፡18) ብለን የመከራከሪያ ነጥቦችን ልናስቀምጥ እንችላለን።
በዚህ ጊዜ ግን ያደረገው ከምክሩ በስተጀርባ ያለውን ህግን ወይንም ስርአትን ፈፅሞ
መዳንን በሚደግፍ መልኩ ሀሳቡን ድርድር ውስጥ እንዲገባ አደረገ(አመቻመቸ)። ይህ
ጳውሎስ በብርቱ ይቃወመው የነበረውን የሁለት ወንጌል አመለካከት ያንፀባርቃል።
ይህም ሁለት ወንጌል አንዱ ለአህዛብ መዳን በእምነት ለአይሁድ ደግሞ መዳን በስራ
ነው የሚለው ነበር፡፡ ‹‹ጳውሎስእነርሱ የጠየቁትን ነገረ ሁሉ ለመስጠት ከእግዚአብሔር
ዘንድ ስልጣን አልተሰጠውም›› Ellen G. white, The Acts of the Apostlees, P
405
ትክክል(ጠቃሚ) ለመሆን በምናደርገው ጥረት ውሰጥ እንዲህ አይነት ተመሳሳይ
ስህተትን ከመስራት ልንጠነቀቅ የምንችለው አንዴት ነው?
የቤተክርስትያን መሪዎች ያቀረቡትን ሀሳብ ጳውሎስ ስለተቀበለ የሰዎቹ ስለት
እንዲጠናቀቅ ለማገዝ የሰባት ቀን የመንጻት ስርአት መፈፀም ነበረበት(ዘዳ.19፡
11-13)፡፡ በአይሁድ ባህል ከአህዛብ መንደር የመጣ ማንኛውም ሰው እርኩስ ነው
ተብሎ ስለሚታሰብ ወደ ቤተመቅደስ መግባት አይችልም ነበር፡፡ ጳውሎስ ለካህናት
ከናዝራውያኑ መንፃት ስርዓት ጋር በተያያዘ ስለ መንፃቱ ከማሳወቁ በፊት ራሱን ማንፃት
የተገባው ለዚህ ነበር(ሐዋ. 21፡26)።
ሐዋ.21፡27-36ን ያንብቡ፡፡ ከሰባቱ ቀን መንፃት በኋላ ጳውሎስምን ገጠመው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
አመፅ ተቀሰቀሰ። በጳውሎስ ላይ አመጽ እንዲነሳ ያደረጉት ሰዎች የአይሁድን ሃይማኖት
በተለይም የተቀደሰውን የቤተመቅደስ ስርአት ያራክሳል በማለት ክስ አቀረቡበት።
ከጳውሎስ ጋር አብሮ የተጓዘው የኤፌሶን ሰው ጥሮፊሞስ አማኝ አህዛብ ስለነበር
(ሐዋ21፡ 29) አይሁዳውያን ብቻ በሚገቡበት ቤተመቅደስ ውስጥ ጳውሎስ ይዞት
የገባ መሰላቸው፡፡ ያንን አድርጎ ቢሆን ኖሮ ጳውሎስ ከባድ ጥፋትን ያጠፋ ነበር፡፡
ውጫዊውንና ውስጣዊውን ጉባኤ በሚለየው ግንብ ላይ በግሪክና በላቲን ቋንቋ የተፃፈ
አህዛብ ጎብኚዎች መግባት እንደማይችሉ የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች ነበሩ፡፡ ከገቡ ግን
ለሚከተላቸው ሞት ራሳቸው ሃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡
‹‹በአይሁዶች ህግ መሰረት ያልተገረዘ ሰው ወደ ተቀደሰው ስፍራ ውስጠኛ ክፍል ከገባ
የወንጀል ቅጣቱ ሞት ነው። ጳውሎስ ከኤፌሶን ሰው ጥሮፊሞስ ጋር በከተማው ውስጥ
ስለታየ ወደ ቤተመቅደስ አስገብቶት ይሆናል ተብሎ ተገመተ፡፡ ያንን አላደረገም፤
እርሱ ራሱ ደግሞ አይሁዳዊ ስለነበር ወደ ቤተመቅደስ መግባቱ ህግን አንደጣሰ
አያስቆጥረውም፡፡ ምንም እንኳን ክሱ ሙሉ በሙሉ የሐሰት ቢሆንም ቀድሞ
ይታማበት በነበረው ነገር ጥፋተኛ እንዲባል ግን ሰዎችን አነሳስቷል፡፡ የከተማው
ጩኸት በርክቶ ከቤተመቅደሱ ደጃፍ አልፎ ስፍራው ወደ ሁከትና ረብሻ ቦታነት
ተለወጠ፡፡››Ellen G white, The Acts of the Apostles, P. 407::
የአመጽ ወሬው ወደ ሮም ጦር ሰፈር ሲደርስ የጦር አዛዡ ቀላውዲዮስ ሉስዮስ
(ሐዋ. 21፡31-32፤23፡26) ከጦር መኮንኖቹና ሠራዊቶቹ ጋር ደርሶ ህዝቡ ጳውሎስን
ሳይገድሉት አተረፈው፡፡
የጥቃቱ አላማ የሆነው ጳውሎስ እንደመሆኑ መጠን በሰንሰለት ታሰረ፤ የጦር አዛዡም
ስለተፈጠረው ነገር መመርመር ጀመረ፡፡ በህዝቡ ሁከት መካከል ጳውሎስ ወደ ጦር
ምሽጉ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ይህ አመጽ እንዲቀሰቀስ የሆነው በሐሰት አሉባልታ ምክንያት ነበር፡፡ ጆሮ
ስለምንሰጣቸው ሲብስም ስለምናስተላልፋቸው የአሉባልታ አይነቶች መጠንቀቅ
ያለብን እንዴት ነው?
ሐዋ. ሥራ21፡37-40 ቀጥሎ ምን እደተከናወነ ይነግረናል። ጳውሎስ ወደ ሮም የጦር
ሰፈር ለምርመራ እየተወሰደ እያለ እንዲሞት እየወተወተ ላለውህዝብ ንግግር ማድረግ
እንዲችል አዛዡን ፈቃድ ጠየቀ፡፡
ከአዛዡ ጋር በግሪክ ቋንቋ በሚነጋገርበት ጊዜ አዣዡም ከሦስት አመት
በፊት በእየሩሳሌም ሮማውያንን ተቃውመው ሰዎች አመፅ እንዲያነሳሱ ያደረገው
የግብፅ አይሁዳዊ እሱ መሰለው፡፡ አመፁም በሮማውያን ሃይል አማካኝነት በቁጥጥር
ስር ሲውል በዚህ አመጽ ላይ የተሳተፉ ብዙዎች ሲሞቱና ሲታሰሩ ግብፃዊው ሰው
ደግሞ አምልጦ ነበር፡፡
ጳውሎስእርሱ የመጣው ከግብጽ ሳይሆን ከጠርሴስ እንደሆነ ሲያረጋገጥ
እንዲናገር ተፈቀደለት፡፡ በንግግሩም ላይ የቀረበበትን ክስ ለማስተባበል ዝርዝር
ምላሽ አላቀረበም (ሐዋ. 21፡28)። ነገር ግን እንዴት እደተለወጠ፣ለአይሁድ ስርአት
ያለውን መሰጠትና ቅንነት በዚያም ምክንያትበየሱስ የሚያምኑትን አማኞች ያሳድድ
እንደነበር ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ጌታ በተለያዩ ራእዮች ከተገናኘው ጀምሮ እርሱን
ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳልነበረው ይህም ሙሉ በሙሉ የህይወቱን
አቅጣጫ እንደቀየረውና ለአህዛብም ይሰብክ ዘንድ እንደተጠራ ነገራቸው፡፡ ከእነርሱ
ጋር ስነ መለኮታዊ የሆነ ውይይት ውስጥ ከመግባት ይልቅ የራሱን የሕይወት ልምምድ
በማካፈል እያደረገ ያለውን ነገር ለምን እንዳደረገ አስረዳቸው፡፡
ሐዋ.22፡22-29ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ለአህዛብ ሐዋሪያ ሆኖ እንደተጠራ ሲናገር ህዝቡ
ምን አይነት ምላሽ ሰጡ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ እንዲናገር እድል መስጠቱ ምንም ለውጥ አላመጣም፡፡ እንደውም ለአህዛብ
ያለውን መሰጠት ስለጠቀሰ በርሱ ላይ ክስን ላቀረቡ ሰዎች እውነት መሆናቸውን
አረጋገጠላቸው (ሐዋ. 21፡28)። ስለዚህ ህዝቡ ደግሞ አመፃቸውን አፋፋሙ፡፡
የሮሙ አዛዥ ጳውሎስ የተናገረውን ነገር በሙሉ ማስተዋል ስላልቻለእየተገረፈ
ምርመራ እንዲደረግበት ወሰነ፡፡ ጳውሎስ ንፁህ የአይሁድ ደም
ያለው ግለሰብ ቢሆንም (ፊሊ. 3፡5) የሮም ዜግነትም ነበረው፡፡ ይህን በሚናገርበት
ጊዜ አዛዡ ትዕዛዙን ማስቆም ነበረበት። ጳውሎስ እንደ ሮም ዜጋ ይህ አይነት ግርፋት
ሊደርስበት ፈፅሞ አይገባም።
የጳውሎስን ንግግር እሰቲ ያንብቡ(ሐዋ. 22፡1-21)። ጳውሎስ ራሱን ከመከላከል ባለፈ
ለአይሁድ ወገኖቹ ይሰብክ እንደነበር የሚያሳይ ምን ማስረጃ ተመለከታችሁ? የርሱን
የመለወጥ ታሪክ የነገራቸው ለምንድነው? የሰዎች የመለወጥ ታሪኮች ከፍተኛ ሃይል
ያላቸው እንዴት ነው?
የሮሙ አዛዥ ጳውሎስ የሮምን መንግስት ለአደጋ እንደማይዳርገውና ጉዳዩ የአይሁድ
ህዝብ የውስጥ አለመስማማት መሆኑንሲረዳ የአይሁድ መማክርት ሸንጎ ጉዳዩን
እንዲይዝ ጠየቀ (ሐዋ. 22፡30፤ 23፡29)።
ሐዋ.23፡1-5ን ያንብቡ፡፡ በሸንጎ ፊት ጳውሎስ በምን አይነት መንገድ ነበር ራሱን
የተከላከለው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የጳውሎስ የመግቢያ ንግግር እንደእስረኛ የእግዚአብሔርን ስም እንደተሳደበ ተቆጥሮ
ወዲያው አፉ ላይ ተመታ። ይህ ሲሆን ወዲያው ያሳየው ባህሪ የጳውሎስን ቁጡነት
በጨረፍታ አሳይቶናል፡፡ ሊቀ ካህናቱን ‹‹በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ›› (ሐዋ.23፡2)
ብሎ ሲናገረው የሱስ ግብዝ የሆኑ ፈሪሳውያንን የኮነነበትን መንገድ እያስተጋባ ነበር
(ማቴ.23፡27)፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ ይህንን ያለው ሊቀ ካህናቱን መሆኑን አለማወቁን
መግለጡ የአይን ችግር ስለነበረበት ይሆናል የሚለውን ግምት ሙሉ ለሙሉ ባዶ
አያደርገውም።
ሐዋ.23፡6-10ን ያንብቡ፡፡ ጰውሎስ በምን አይነት ብልሃት ነበር የፍርድ ሂደቱ እዲረበሽ
ያደረገው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሸንጐው የተመሰረተው በሰዱቃውያንና በፈሪሳውያን ሲሆን ሁለቱ ጎራዎች ደግሞ
ቀኖናን ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ፈጽመው የማይስማሙ ነበሩ። ሰዱቃውያን ለምሳሌ
የሃይማኖት መጽሐፎቻቸው የያዙት አምስቱን የሙሴን መጽሐፍት (ፔንታቱክ) ሲሆን
በሙታን ትንሣኤም አያምኑም (ማቴ. 22፡23-32) ነበር።
የጳውሎስ ንግግር (ሐዋ. 23፡6) ግን የሸንጎውን ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የበለጠ
ጠንካራ ስልት ነበር፡፡ በደማስቆ መንገድ ላይ ከሞት የተነሳውን የሱስን በማግኘቱ
ስለተለወጠና ወደ ሐዋሪያዊ አገልግሎቱ ስለገባ የተከሰሰበት ዋና ጉዳይ በትንሳኤው
ማመኑ ነበር (ሐዋ. 24፡20-21፤26፡6-8)። ቀድሞ ከነበረው ቅንአት አሁን ያለበትን
ሁኔታ ሌላ ምንም ሊገልፅ አይችልም፡፡ የሱስ ከሞት ካልተነሳ አገልግሎቱ ሁሉ ከንቱ
ይሆን ነበር። እርሱም ይህንን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር (1 ቆሮ.15፡14-17)።
በዛ ምሽት ጳውሎስ በጦር ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ ጌታ በሚያበረታታ
ቃል ተገናኘው፡- ‹‹ጳውሎስ ሆይ አይዞህ! በኢየሩሳሌም እንደመሰከርክልኝ በሮምም
ደግሞ ልትመሰክርልኝ ይገባሃል›› አለው (ሐዋ.23፡11)። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ይህ
የተስፋ ቃል መነገሩ ለጳውሎስ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ በሮም ለመስበክ የነበረው
ከፍተኛ ጉጉት (ሐዋ. 19፡21፤ሮሜ1፡13-15፤15፡22-29) እውን ሊሆን ነበረ፡፡
በህጋዊ መንገድ ጳውሎስን ማስወገድ ባለመቻላቸው ስለተበሳጩ በራሳቸው መንገድ
በቡድን ጳውሎስን በማጥቃት ለመግደል አሴሩ።
ሐዋ.23፡12-17ን ያንብቡ። ሴራቸው ምን ነበር? እንዴትስ ሆኖ ነበር የተጨናገፈው?
ቅንአት ያላቸው ሰዎች ለትልቅ ጥፋት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይህ ታሪክ ምን
ያስተምረናል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከአርባ በላይ የሆኑ አይሁዳውያን በጳውሎስ ላይ በማሴር እርሱን ለመግደል መሃላ
መግባታቸው ሐዋሪያው በእየሩሳሌም ምን ያክል ጥላቻን እንዳነሳሳ የሚያሳይ ነው፡፡
ሉቃስ ስለነዚህ ሰዎች ማንነት በግልጽ አይጠቅስልንም፤ ነገር ግን የአይሁድን እምነት
አሉ ከተባሉ ከሃዲዎችና ባለንጣዎች ለመከላከል ማንኛውንም መስዋዕት ለመክፈል
የተዘጋጁ አክራሪ አይሁዳውያን ናቸው፡፡ በመጀመርያው ከፍለ ዘመን በይሁዳና
አካባቢዋ እንዲህ ያለ የሃይማኖት ጽንፈኝነት ከፍተኛ ነውጥ ካለው የጋለ ብሔራዊ
ስሜት ጋር ሲጣመር መመልከት የተለመደ ነበር፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያዘጋጅ የሴራው ወሬ የጳውሎስእህት ልጅ ጆሮ ደረሰ። ስለ
ጳውሎስ የቤተሰብ ሁኔታ ምንም ማወቅ ባለመቻላችን ትንሽ ቢያሳዝነንም እርሱና
እህቱ ግን ያደጉት በእየሩሳሌም ነበር(ሐዋ. 22፡3)። ከዛም አግብታ ቢያንስ አንድ
ወንድ ልጅ እንዳላት እናውቃለን፡ለማንኛውም የጳውሎስ እህት ልጅ የሆነው ትንሽ
ልጅ (ሐዋ.23፡18፣22) ‹‹እጁን ይዞ›› ስለሚል(ሐዋ.23፡19) ልጁ በአስራዎቹ የእድሜ
ክልል በመገኘቱ ወደ ጦር ሰፈር ሄዶ ለመጎብኘትና የተፈጠረውን ለመናገርም እድል
እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡
ሐዋ.23፡26-30ን ያንብቡ፡፡ የጦር አዛዥ የሆነው ሉስዮስ ለአገረ ገዥ ፈሊክስ
ያስተላለፈው መልእከት ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ደብዳቤው ስለተፈጠረው ጉዳይ ሚዛናዊ የሆነ ሪፖርትን ይዞ ለፊልክስ ደረሰው።
ከዚያም በተጨማሪ ጳውሎስየሮም ዜጋ ሰለሆነ ያገኘውን ጥቅም ያትታል፡፡
የሮማውያን ህግ መብት ያላቸውን የራሱን ዜጎች ለምሳሌ በህጋዊ ሁኔታ እንዲዳኙ፣
በዚያም ራሳቸውን የመከላከል መብት እንዲያገኙ (ሐዋ. 25፡16) እንዲሁም ያልተገባ
የፍርድ ሂደት ቢኖር እንኳን ለአገረ ገዥው አቤቱታቸውን እንዲያቀርቡ መብት
ይሰጣቸዋል(ሐዋ. 25፡10-11)።
ፊልክስም ግላዊ ክብሩን ለማሳየት ሳይሞክር ጳውሎስን ትክክለኛውን የህግ መንገድ
ተከትሎ በተገቢ መንገድ አስተናገደው። ቃሉን ከጠየቀ በኋላ ከሳሾቹ እስኪመጡ
ድረስ እንዲጠበቅ አዘዘ፡፡
እስቲ በጳውሎስ ህይወት ላይ የእግዚአብሔር ነገሮችን ማመቻቸት ምን እንደሚመስል
ያስቡ፡፡ በምንም ያክል ከባድ ፈተናና መከራ ብናልፍ እግዚአብሔር ላደረገልን ነገር
ምን ያክል በትህትና ምላሽ ሰጥተናል?
‹‹በዚህ ወቅት ጰውሎስና አጋሮቹ በእየሩሳሌም መሪዎች ወደሆኑት
ሰዎች ቀርበው የአህዛብ ቤተክርስትያናት ለተቸገሩ አይሁድ ወንድሞቻቸው የላኩትን
አመጡ፡፡…
‹‹በራሳቸው ፍላጎት ያደረጉት ይህ ስጦታ አህዛብ ሆነው የተለወጡ ሰዎች በአለምአቀፍ
ደረጃ ተደራጅቶ ላለው የእግዚአብሔር ሰራ ታማኝነታቸውንማሳያ ሲሆን ይህ ደግሞ
በሁሉም ዘንድ መልካም የሆነ ተቀባይነት ማግኘት እንደሚገባው ያሳያል፡፡ ነገር ግን
ለጳውሎስና አጋሮቹ ግልጽ በሆነ መንገድ አንዳንዶች ለወንድሞች ያላቸውን ፍቅር
ስጦታ በመስጠት የገለጹትበን የወንድማማች መንፈስ ማድነቅ ተሳናቸው፡፡›› Ellen
G. white, The acts of the Aposttles, pp.399-400
‹‹በቤተክርስትያን ያሉ መሪዎች እንደ ተጠራ ጌታም ወደ አህዛብ እንዲደርስ እንደላከው
ለማመን ፈቃደኛ ቢሆኑ ኖሮ እግዚአብሔር ጳውሎስን ለነርሱ ያቆይላቸው ነበር።
የጳውሎስን ስራ በአጭሩ እንዲጠናቀቅ ፈልጎ አልቀባውም፤ በእየሩሳሌም ያሉ
የቤተክርስትያን መሪዎች ተነስተውበት ብዙ ነገር ሲያደርጉበትም ያንን ለመቋቋም
እግዚአብሔር ተዓምርም አላደረገም፡፡
‹‹ተመሳሳይ የሆነ መንፈስ አሁንም ድረስ ተመሳሳይ ውጤትን ያመጣል፡፡ የመለኮት
የፀጋ ስጦታን ለማድነቅና ለማሳደግ ችላ ማለታችን ቤተክርስትያን ልታገኝ የሚገባትን
ብዙ በረከት እንዲቀርባት አድርጓል፡፡ እግዚአብሔር ስራው ተቀባይነት ቢያገኝ
ኖሮ የአንዳንድ ታማኝ አገልጋዮችን አገልግሎት ምን ያክል ያረዝመው ይሆን፡፡
ቤተክርስትያን ግን ማስተዋላችንን የነፍሳት ጠላት እንዲነጥቅና የክርስቶስ አገልጋዮች
የሚሉትንና የሚያደርጉትን ነገር በተሳሳተ መንገድ እንዲተረጎምና እንዲቀርብ
የምትፈቅድ ከሆነ፣ በርሱ መንገድ በመቆም ለስራው እንቅፋት የሚሆኑ ከሆነ ጌታም
የሰጣቸውን ባርኮት ይነጥቃቸዋል። . . .
‹‹እጆች ህይወት አልባ በሆኑ ደረቶች ላይ ሲያርፉ፣ የማስጠንቀቂያና የማበረታቻ
ድምጽ ፀጥ ሲል ያኔ እምቢተኞች የነበሩት እነርሱ ያካፈሉትን በረከት አይተው ይቀበሉ
ይሆናል፡፡ በህይወታቸው ቆይታ ማሳካት ያልቻሉትን በሞታቻው ያሳኩ ይሆናል፡፡”
ገፅ 417, 418
1.
ወደእየሩሳሌም ሲመጣ በመልካም ሁኔታ እንደማይቀበሉት ጳውሎስ
ቢያውቅም ከግላዊ ጥቅሙ በላይ ለቤተክርቲያን ጥቅም የቆመ ነበር፡፡
የእርሱን ፈለግ መከተል ያለብን እስከምን ድረስ ነው?
2. በኢየሩሳሌም ጳውሎስ እንዲደራደር ካደረገው ሁኔታ ምን የምንማረው
ነገር አለ? መርሆቻችንን ሳንጥስ እንዴት አድርገን ነው ከአካባቢው ጋር
መስማማት የምንችለው? ግን ይህን ማድረግስ ይቻለናል?
3. የቤተክርስትያን ህብረት ሁልጊዜም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳን
ለነገሮች ያለን አመለካከት የተለያየ ቢሆንም እንዴት አድርገን ነው አብረን
በመስራት አንድ መሆን መቻልን የምንማረው?