ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- የሐዋሪያት ሥራ 27 እና 28፤ ሮሜ 1፡18-20፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ፡- ‹‹ጳውሎስ ሆይ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤›› (ሐዋ. 27፡24)
ጳ
ውሎስ ሮምን የመጎብኘት ከፍተኛ ናፍቆት ነበረው፤ በኢየሩሳሌም መታሰሩ ግን
ብዙ ነገሮችን ቀየረ፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተክርስትያን ለሚገኙ መሪዎች የህጋዊነት
ጫና እጅ ስለሰጠ በባህር ወደ ጣሊያን ያደረገውን ጉዞ ጨምሮ ወደ አምስት አመት
ለሚጠጋ ጊዜ በሮም ጥበቃ ስር እንዲቆይ ተደረገ፡፡ ይህ ለውጥ የጳውሎስን ወንጌልን
የማዳረስ ጉዞ እቅድ አበላሸበት፡፡
ምንም እንኳን ይህ እንቅፋት ቢገጥመውም ኢየሱስ ራሱ ሐዋሪያው በሮም
ቆሞ እንሚመሰክርለት ቃል ገብቶለታል(ሐዋ. 23፡11)፡፡ ተስፋ ብናስቆርጠውም
እግዚአብሔር በስራችን ከሚመጣብን መዘዝ ሁልጊዜ ባያተርፈንም እድልን ግን
ይሰጠናል፡፡ ጳውሎስ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም መወሰዱ ብቻ ሳይሆን ስፔንን (እስጳንያን)
ለመጎብኘት ናፍቆት ቢኖረውም (ሮሜ 15፡24) ወደዚያ ስለመሄዱ ግን መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ማስረጃ የለንም፡፡ ከመጀመሪያው የሮም እስራቱ ከተፈታ በኋላ ደግሞ በኔሮ
አገዛዝ በ67 ዓ.ም. ታስሮ እንደ ሰማዕት ስቃይ ይደርስበታል(2ኛ ጢሞ. 4፡6-8)፡፡
አዎን ጳውሎስ ወደ ሮም ደረሰ በሰንሰለት ታስሮ በገዥው ፊት ለመቅረብ ቀንን
ቢጠብቅም መናገሩን ግን አላቆመም (ኤፌ. 6፡20፤ ፊሊ.1፡13)፡፡ ወደርሱ የመጡትን
ሁሉ ያለመከልከል አስተማረ (ሐዋ. ሥራ 28፡30-31)፤ ከመጡት መካከል ከቄሳር
ቤተሰብ ጠቃሚ ሰዎችም ነበሩ (ፊሊ. 4፡22)፡፡
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለ መስከረም 19 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡
በቂሳርያ ለሁለት አመታት በእስራት ከቆየ በኋላ (ሐዋ. 24፡27) ጳውሎስ ወደ ሮም
ተላከ፡፡ እኛ ብሎ በመተረኩና ወደ ኢጣልያ ያደረጉትን ረዥምና አስቸጋሪ ጉዞ
በጣም ዝርዝር ባለ ሁኔታ በመግለፁ (ሐዋ.27፡1-28፡16) ሉቃስ ከጳውሎስ ጋር አብሮ
እንደነበረ መናገር ይቻላል፡፡ አርስጥሮኮስ የተባለ ክርስትያንም አብሯቸው ነበር (ሐዋ.
27፡2) ፡፡ ሌላው በዚህ ታሪክ ውስጥ የምናገኘው ዋነኛ ገፀባህሪ የመቶ አለቃ የሆነው
ዩሊዮስ ሲሆን ከእርሱም ጋር ሌሎች እስረኞችን በሃላፊነት እየወሰደ ነበር (ሐዋ. 27፡
1)፡፡
ጉዞአቸውን የጀመሩት የበጋ ወቅት በሚገባደድበት ጊዜ ነበር፡፡ የጾም ጊዜ ተብሎ
የተገለፀው (ሐዋ. 27፡9) ጊዜው በጥቅምት ወር ሁለተኛ አጋማሽ ውስጥ የሚካሄደው
የመንጻት ቀን አካባቢ እንደነበረ የሚያመላክት ነው፡፡ የክረምት ወቅት እየጀመረ
ስለነበረ ከህዳር እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚዴትራኒያን ባህር ላይ መጓዝ
የማይታሰብ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ግን ከጅማሬው አንስቶ እክል ገጠማቸው፡፡
በቀርጤስ ውስጥ መልካም ወደብ ወደተባለችው ደሴት የደረሱት ብዙ ቆይተው ነበር
(ሐዋ. 27፡8)፡፡
ሐዋ. 27፡9-12ን ያንብቡ፡፡ ወደ መልካም ወደበ እንደደረሱ ጳውሎስ በታሪኩ ውስጥ
ጣልቃ ገብቶ የምናገኘው እንዴት ነው? እርሱ ጣልቃ ገብቶ በመናገሩ ምን ምላሽ
አገኘ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የጳውሎስን ምክር ባለመስማት ማረፊያ ወደብን በመፈለግ በምዕራብ አቅጣጫ 40
ማይል ያክል በመርከብ ለመሔድ ወሰኑ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የአየር ሁኔታው ድንገት
ተቀየረና የመርከቧ መሪዎች መርከቧ ከመሬት ርቃ ወደ ደቡብ ምዕራብ እንድትጓዝ
ከመፍቀድ ውጪ ምርጫ እስኪያጡ ድረስ በሃይለኛ ማዕበል ተያዙ፡፡ ቀጥለውም
ውሃ ወደ መርከቧ እየገባ ስለነበረ ክብደቱን ለማቅለል ጭነቶቿን እንዲሁም የሸራ
ማውጫና ማውረጃ መሣሪያውን ነቃቅለው ወደ ባህር መጣል ጀመሩ፡፡ ሁኔታው
ድራማ ይመስል ነበር፡፡ ለብዙ ቀናት አነስተኛ የቀን ብርሃን በነበረበት ሁኔታ፣ በከባድ
ዝናብና ወጀብ እየተናወጡ፣ የት እንደደረሱ እንኳን ሳያውቁ እጅግ በመዛላቸው
“ለመትረፍ የነበራቸው ተስፋ ተሟጠጠ” (ሐዋ. ሥራ 27፡20) ፡፡
ሐዋ. ሥራ 27፡21-26ን ያንብቡ፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ ጣልቃ
ሲገባ ምን አለ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ትንቢታዊ በሆኑ ቃላት ጳውሎስ ለመርከቡ መሪዎች ከእግዚአብሔር የተቀበለውን
መልእክት ተናገረ፡፡ “ተስፋ ልትቆርጡና ልታዝኑ አይገባም፡፡ አሁንም ቢሆን አደጋና
ችግር ይመጣል፤ ነገር ግን ሁላችሁም በሕይወት ትተርፋላችሁ” አላቸው፡፡
እንደጳውሎስ ያለ ታማኝና የተሰጠ አገልጋይ ለምን ተብሎ ነው ይህ ሁሉ አበሳ
የደረሰበት? ከዚህ የህይወት ልምምዱ ምን የምንማረው ነገር አለ?
በታሪኩ ላይ ጳውሎስ ለሁለተኛ ጊዜ ጣልቃ ገብቶ ሲናገር በመርከቡ ላይ ለሚገኙ
276 ሰዎች በሙሉ (ሐዋ. ሥራ 27፡37) ከዚያ በኋላ ነገሮች መልካም እንደሆኑ
ባይቀጥሉም የሚሞት ሰው እንደማይኖርና መርከቧ ብቻ ጉዳት እንደሚደርስባት
(ሐዋ. ሥራ 27፡22) አረጋገጠላቸው፡፡ ከአስራ አራት ቀናት በኋላ የሐዋሪያው ቃል
ተፈጸመ፡፡ አሁንም ከባድ ማዕበል ገጥሟቸው መርከቧ ብትዋልልም ምናልባትም
ውሃው ከድንጋይ(ከመሬት) ጋር ተጋጭቶ አረፋ ሲደፍቅ ስለሰሙ መርከበኞቹ ወደ
መሬት የተቃረቡ መሰላቸው (ሐዋ. 27፡27) ፡፡ ከብዙ ድምፆች በኋላ መርከቡ ከቋጥኝ
ጋር ይላተማል ብለው ስለሰጉ ከመርከቡ ጀርባ አራት መልህቆችን በመወርወር
የመርከቢቱን ፍጥነት ለመቀነስ ጣሩ፡፡ አምላካቸውም የቀን ብርሃን እንዲሰጣቸው
ለመኑ (ሐዋ. 27፡28-29) ፡፡
ሐዋ. ሥራ 27፡30-44ን ያንብቡ፡፡ ከዚህ ታሪክ የምንማረው ትምህርት ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በጉዟቸው መነሻ ላይ የመቶ አለቃው ጳውሎስን በጥሩ መንገድ ቢያስተናገደውም
በጉዟቸው መካከል ላይ ወደፊት ስለሚገጥማቸው የነገረውን ንግግር ለማመን
አልደፈረም፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ፡፡ ስለ መርከቢቱ መሰበር
ጳውሎስ የተናገረው ትንቢታዊ ንግግር በመቶ አለቃው ተሰሚነትን አገኘ (ሐዋ. 27፡
21-26) ፤ ያም ሊፈፀም ቀርቦ ነበር፡፡
ጳውሎስ ሰዎቹን ምግብ እንዲበሉ ተማፀናቸው፤ ያ ካልሆነ ግን ለመዋኘትና ወደ ዳር
ለመድረስ አቅም እንደማያገኙ ነገራቸው፡፡ የመለኮት ሁኔታዎችን ማመቻቸት የእኛን
የየእለት ተግባር እንዳናከናውን አያግድም፡፡ “በዚህ ትረካ ውስጥ እግዚአብሔር
ደህና እንደሚሆኑ በማረጋገጡና ሰዎቹም ይህ እንዲረጋገጥ ባደረጉት ጥረት መካከል
መልካም የሆነ ሚዛናዊነት አለ” David J. Williams, Acts (Grand Rapids: Baker,
1990), p. 438
ማለዳው እየተቃረበ ሲመጣ መርከበኞቹ ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባህር ሰርጥን
አይተው መርከቢቱን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ፡፡ መርከቢቱ ግን ወደዛ
የውሃ ዳርቻ ለመድረስ አልተቻላትም፡፡ በዚህ ፈንታ ግን በአሸዋ ስትታነቅ በማዕበሉ
ሀይል የተነሳ መርከቢቷ ተሰባበረች፡፡ ወታደሮቹም እስረኞች እንዳያመልጧቸው
በመስጋት ሊገድሏቸው ሲያስቡ መቶ አለቃው በዋነኝነት ጳውሎስ እንዲተርፍ ስለፈለገ
ከለከላቸው፡፡ በስተመጨረሻም እግዚአብሔር ቃል እንደገባላቸው አንዲትም ነፍስ
አልጠፋችም፡፡
ጳውሎስን በህይወት ለማትረፍ ሲባል ወታደሮቹ እስረኞችን ከመግደል ተከልክለዋል፡
፡ ይህ ስለ ጳውሎስ የምስክርነት ኃይል እና ባህሪ የሚያስተምረን ምን ነገር አለ?
በህይወት ተርፈው ወደ ዳርቻው ሲደርሱ ነበር በሜዴትራኒያን ባህር ከሲሲሊ በስተ
ደቡብ በምትገኘው መላጥያ በምትባለው ትንሽ ደሴት መድረሳቸውን ያወቁት፡፡
በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በነፋሱ ኃይል አማካኝነት በባህሩ ላይ ከወዲያ ወዲህ
እየዋለሉ ከመልካም ወደብ አንስቶ አራት መቶ ሰባ አምስት ማይል የሚያክል ርቀት
ተጓዙ፡፡ አሁን ጉዟቸውን ከመቀጠላቸው በፊት የክረምቱን ሶስት ወራት መጠበቅ
ነበረባቸው (ሐዋ. 28፡11)
ሐዋ.28፡1-10ን ያንብቡ፡፡ በመላጥያ ደሴት ጳውሎስ ምን ገጠመው? እግዚአብሔርስ
እንዴት አድርጎ ተጠቀመበት?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የመላጥያ ሰዎች በጣም ደግና ጥሩ አቀባበል ማድረግ የሚያውቁ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም
ለጳውሎስና አብረውት ለነበሩት ሰዎች በስብሰውና በርዷቸው ስለነበር አንዲሞቃቸው
እሳት አነደዱላቸው፡፡ በዚህ ወቅት በመላጥያ የሚኖረው የሙቀት መጠን ከ50 ዲግሪ
ፋራናይት አይበልጥም ነበር፡፡
የእፉኝት እባብዋ ሁኔታ ሰዎች ትኩረታቸውን በጳውሎስ ላይ እንዲያደርጉ አደረጋቸው፡
፡ በመጀመሪያ እነዚህ እግዚአብሔርን የማያምኑ ህዝቦች የተነደፈው እግዚአብሔር
ስለተቆጣው እንደሆነ አስበው ነበር፡፡ ጳውሎስ ነፍሰ ገዳይ የነበረና መርከቢቱ
ስትሰጥም ከሞት ቢያመልጥም ከግሪክ አማልክት የፍትህና የበቀል አምላክ በሆነችው
‹‹ዳይክ›› በተባለችው አምላክ የተያዘ መሰላቸው፡፡ ሐዋሪያው ግን ሊሞት ባለመቻሉ
ከብዙ አመታት በፊት በልስጥራ እንደሆነው እንደ አምላክ ተቆጠረ (ሐዋ. 14፡8-18) ፡
፡ ምንም እንኳን ሉቃስ በዚህ ክፍል ላይ ትኩረት አድርጎ የበለጠ ነገር ባይጽፍልንም
ጳውሎስ ግን ይህንን ክስተት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ስለሚያገለግለው አምላክ
እንደ መሰከረ መገመት አይከብድም፡፡
ፑፕሊዮስ በሮማውያን የተሾመ ይሁን ወይንም የአካባቢው ባለስልጣን ባናውቅም
ጳውሎስና ጓደኞቹ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩበት ስፍራ እስኪያገኙ ድረስ ለ3ቀናት
አስተናገዳቸው፡፡ የዚህ ሰው አባት ፈውስ ደግሞ ለጳውሎስ በመላጥያ ህዝቦች መካከል
የፈውስ አገልግሎቱን እንዲያከናውን እድልን ፈጠረለት፡፡
እንደ ሉቃስ አገላለጽ ከሆነ አንድም ሰው ስለ መለወጡ ወይንም ጳውሎስ የመላጥያን
ደሴት ተለይቶ ሲሄድ ትቶ ስለሄደው ህብረት አይነግረንም፡፡ ይህ ያልተፃፈው በአጋጣሚ
ሊሆን ቢችልም ለአለም ያለን ተልዕኮ ግን ከጥምቀት ወይንም ቤተክርስቲያንን
ከማቋቋም የዘለለ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡ ስለ ሰዎችና ስለ ፍላጎቶቻቸው ጭምር
ግድ ሊለን ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ የወንጌል ተግባራዊ ገፅታ ነው (ሐዋ. 20፡35ን ከቲቶ
3፡14 ጋር ያነጻፅሩ) ፡፡
እነዚህ ምንም አያውቁም የምንላቸው የደሴቱ ነዋሪዎች እንኳን ስለ መለኮት ፍትህ
ያላቸው መረዳት በጣም አስደናቂ ነው፡፡ ይህ ከምን የመጣ ይመስሎታል? ሮሜ 1፡
18-20ን ይመልከቱ፡፡
ለ3 ወራት በመላጥያ ከቆዩ በኋላ ጳውሎስና አብረውት ያሉ ሰዎች ጉዞአቸውን ቀጠሉ
(ሐዋ. 28፡11)፡፡ ወደ ፑቲዮሎስ ማለትም ዛሬ በኔፓል ባህረ ሰላጤ ፖዙሊ በምትባል
ቦታ ደረሱ(ሐዋ. 28፡13)፡፡ ከዚህ ተነስተው በእግር መንገድ ወደ ሮም ተጓዙ (ሐዋ.
28፡11-16ን ይመልከቱ) ፡፡
የጳውሎስ የመምጣቱ ዜና በፍጥነት ወደ ሮም ደረሰ፤ የአማኞች ቡድን ከዚያ ተነስተው
ወደ ደቡብ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ጳውሎስን ለመቀበል ሄዱ፡፡ ከዚህ በፊት
ወደ ሮም የመጣ ባይሆንም ሐዋሪያው ግን በዚያች ከተማ አያሌ ወዳጆች፣ የስራ
ባልደረቦች፣ የተለወጡ አማኞች፤ ዘመዶችና ሌሎች ቅርብ የሆኑ ሰዎች ነበሩት (ሮሜ
16፡3-16)፡፡ ጳውሎስ እስረኛ ሆኖ መምጣቱ ከመርከብ አደጋ ከመትረፉ ጋር ተደምሮ
በአፍዮስ የተጓዙት መንገድ ልብ የሚነካ እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ ከተወደዱት
ወዳጆች ካገኘው ልዩ የሆነ ፍቅርና እንክብካቤ የተነሳ ሐዋሪያው እግዚአብሔርን
አመሰገነ፡፡ በገዥው ፊት ለፍርድ ሊቀርብ መሆኑን አስቦም ልቡ ተነካ፡፡
ህጋዊ በሆነ ደብዳቤው ውስጥ ፊስጦስ በሮማውያን ህግ መሠረት ጳውሎስ ምንም
አይነት ወንጀል እንዳልፈፀመ ተናግሯል ተብሎ ይገመታል (ሐዋ. 25፡26-27፤26፡3132) ፡፡ ምናልባትም እንደ ሮማውያን ልማድ በሰንሰለት ታስሮ ከወታደር ጋር ቢቆይም
በእስር ቤት ወይም በጦር ሰፈር ከመቆየት ይልቅ የግል መኖርያ ተከራይቶ እንዲኖር
የተፈቀደለት ለዚህ ይሆናል(ሐዋ. 28፡30)፡፡ ጳውሎስ ራሱ ቤቱን መከራየቱ የራሱን
ስራ መስራትን እንደቀጠለ ፍንጭ ይሰጣል(ሐዋ.18፡3)፡፡
ሐዋ. ሥራ 28፡17-22ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ በዛ ስፍራ ደርሶ እንዳረፈ ወዲያውኑ
ያደረገው ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ ወደ ምኩራብ መሄድ ባይችልም ምኩራቡ ግን ወደርሱ መምጣት ይችላል፡፡
ወድያው እንደ ደረሰ ቅድሚያ አይሁዶችን የማናገር ፓሊሲውን በመከተል(ሮሜ1፡16)
የአካባቢውን የአይሁድ መሪዎች በአንድ ላይ ሰብስቦ ንፁህ ስለመሆኑና
ያለምክንያት እንደታሰረ በመግለፅ እርሱ የተናገረው ስለ እስራኤል ተስፋ ብቻ
እንደነበር ገለጸላቸው(ሐዋ. 23፡6፤24፡15፤26፡6-8)፡፡ የርሱ የውስጥ ፍላጎት ራሱን
መከላከል ሳይሆን ወንጌልን እንዲሰብክ በእነርሱ ዘንድ አመኔታን እንዲያመጣለት
በማድረግ የኢየሱስ ትንሳኤ የእስራኤሎች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ተስፋ ፍጻሜ
ስለመሆኑ ለመመስከር ነበር፡፡ ከኢየሩሳሌም ስለ ጳውሎስ የሰሙት ምንም ነገር
አለመኖሩ ደንቋቸው አይሁዶቹ ከእርሱ መስማት ፈለጉ፡፡
ሐዋ. ሥራ 28፡22ን ያንብቡ፡፡ በዚያ ጊዜም ቢሆን አማኞች ይገጥማቸው ስለነበረው
ተቃውሞ ጥቅሱ ምን ይነግረናል? ሌሎች የኛን እምነት ተቃውመው ሲናገሩ እንኳን
ታማኝ ሆነን መቆም የምንችለው እንዴት ነው?
በተቀጠረው ቀን አያሌ አይሁዳውያን የጳውሎስን የወንጌል ገለጻ ለመስማት መጡ
(ሐዋ. ሥራ 28፡23)
ሐዋ. ሥራ 28፡24-31ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ የኢሳያስን ጥቅስ ለራሱ የንግግር አውድ
የተጠቀመበት አላማ ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከኢሳ. 6፡9-10 የተወሰደው ኃሳብ ሰዎች የመለኮትን መልዕክት እንቢ ሲሉ
ስለሚደርስባቸው ነገር ይገልጻል፡፡ አንዳንድ አይሁዶች ቢያምኑም ሌሎቹ ግን
አላመኑም፤ በዚህም ክርክር በመፈጠሩ ምክንያት ሐዋሪያው አሁንም ፊቱን ወደ
አህዛብ ከማዞር ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረውም (ሐዋ.13፡46-47፤18፡6)፡፡
ጳውሎስ በገዥው ፊት ለመቅረብ ሁለት አመት ሙሉ መጠበቅ ነበረበት፡፡ ምንም
እንኳን በቤቱ የቁም እስረኛ ቢሆንም ወደርሱ ለሚመጡት ሰዎች ያለመከልከል ወንጌልን
ያካፍል ነበር፡፡ የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ የመጨረሻው ትዕይንት የሚያውጠነጥነው
በወንጌል ድል አድራጊነት ዙሪያ ነው፡፡ ምንም አይነት ኃይል አይሁዶችም ቢሆኑ
ሮማውያን የወንጌሉን መስፋት ሊገቱ አልቻሉም፡፡
አንዳንድ መረጃዎች የጳውሎስ ጉዳይ ጠንካራ ማስረጃ ባለመገኘቱ ከእስር
መለቀቁንና ሌላ የሚሽነሪ ጉዞ ማድረጉን ከዚያም በድጋሚ ተይዞ ወደ ሮም
ተወስዶ መገደሉን (2ኛ ጢሞ. 4፡6-8) ስለሚጠቁሙ ሉቃስ የመጽሐፍ ትረካውን
በዚህ ስፍራ ላይ ለምን እንዳበቃ ግልጽ አይደለም፡፡ ምናልባትም ከሉቃስ
የጽሁፍ አላማ አንጻር ሩቅ በሆነቸው ሮም ሳይቀር ወንጌሉ በመሰበኩ ‹‹እስከ
ምድር ዳርቻ ድረስ››(ሐዋ. 1፡8) የሚለው ቃል በመፈፀሙ ሊሆን ይችላል፡፡
‹‹ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በእስር ሲቆይ በትዕግስትና በደስታ
ነበር፤ ድፍረትና እምነቱም ቀጣይነት ያለው ስብከት ነበር፡፡ ይህም በአለም ላይ ካለው
መንፈስ በተቃራኒ ከሁሉ በላይ የሆነው መንፈስ ከእርሱ ጋር እንደነበረ የሚመሰክር
ነው፡፡ የርሱ ምሳሌነት እርሱ በህዝብ ፊት ለክርስቶስ መቆም ባይችልም ክርስትያኖች
በበለጠ ብርታት ያንን እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል፡፡ የሐዋሪያው ተፅዕኖ ይሄን ያክል
ጠንካራ ነበር፤ በአይን ሲታይ የርሱ አቅምና ፋይዳ የደበዘዘ ቢመስልም የተወገደ
ከመሰለባቸው ማሳዎች እንኳን ብዙ የነፍሳት ነዶዎችን ለክርስቶስ ማርኮ አመጣ፡፡››
Ellen G. white, The Acts of the Apostle, P.464
ከቤተክርስትያን ተልእኮ አንፃር የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍ ወይንም ወንጌልን የማዳረስ
ታሪክ ገና አልተጨረሰም፤ እያንዳንዳችን ወደዚህ ምስል የምንገባው እዚህጋ ነው፡፡
በምዕተ አመታት ታሪክ ውስጥ አያሌ አስደናቂና ድራማዊ የሆኑ ምዕራፎች አንዳንዴም
ለእግዚአብሔር ታማኝ በሆኑ ምስክሮቹ ደም ጭምር ተፅፈዋል፡፡ አንድ ተጨማሪ
ምዕራፍ ለመጻፍ አሁን ተራው የኛ ነው፤ ምናልባትም የመጨረሻው ምዕራፍ ይሆናል
(ብለን ተስፋ እናደርጋለን)፡፡ የሱስ ለደቀመዛሙርቱ ትቶላቸው የሄደውን ተልዕኮ ወደ
ፍጻሜ ለማድረስ ተራው የኛ ነው ‹‹ከዚያም መጨረሻው ይመጣል›› (ማቴ. 24፡14)
‹‹ክርስቶስ ለቤተክርስትያን የተቀደሰ ሃላፊነትን ሰጥቷታል፡፡
እያንዳንዱ አባል እግዚአብሔር ለአለም የፀጋ ገፀ በረከቱንና ሊደረስበት የማይችለውን
የክርስቶስን ብልጽግና የሚያስተላልፍባቸው የመተላለፊያ መሳሪያ ሊሆን ይገባል፡፡
አዳኛችን የሚሻው ትልቁ ነገር ቢኖር የእርሱ ወኪሎች የሆኑ ሁሉ የእርሱን መንፈስና
ባህሪ ያንፀባርቁ ዘንድ ነው፡፡ የአዳኛቸው ፍቅር በሰብአዊ ፍጡራኑ ላይ ተገልጦ
የማየትን ያህል ይህ አለም የሚናፍቀው ነገር የለም፡፡ የክርስትና ኃይል የሚገለጥባቸውን
ወንድና ሴቶች ሰማይ በናፍቆት ይጠብቃል፡፡›› Ellen G. White, The Acts of the
Apostles, p. 600
‹‹የአገልግሎት መንፈስ ቤተክርስትያኒቱን ሁሉ ተቆጣጥሮ ሁሉም እንደችሎታው
ለእርሱ ስራ ይተጋ ዘንድ እግዚአብሔር ይናፍቃል፡፡ የእግዚአብሔር ቤተክርስትያን
አባላት ሁሉ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጉድለት በሚታይባቸው ቦታዎች
ሁሉ የተሰጣቸውን ሥራ በመስራት የወንጌልን ተልእኮ ሲፈጽሙ መላው አለም
ማስጠንቀቂያው ይደርሰዋል፤ ጌታ የሱስ በኃይልና በታላቅ ክብር ወደ ምድር
ይመለሳል›› page 111
1.
ጳውሎስ ወደ ሮም ባደረገው ጉዞ ሁሉ ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ የነበረውን
እምነት ሉቃስ የገለፀው እንዴት ነው? በዚህ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ጠንካራ
እምነት ሌሎቹ ሰዎች ተጽእኖ የተፈጠረባቸው እንዴት ነበረ?
2. ምንም ብዙ ነገሮች ቢያጋጥሙትም ጳውሎስ እምነቱንና ተልእኮውን አልተወም፡
፡ በሮም የተሰጠው ነፃነት ውሱን ቢሆንም መስበኩን አላቋረጠም፡፡ ለአንድ ሰው
ወንጌሉን ልንናገር ስንል እንድናቆም ስንፈተን ምን ማድረግ ይኖርብናል?
3. ሮሜ 1፡14-15ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስ ለሰው ሁሉ ወንጌልን የመስበክ ግዴታ
እንዳለበትና ባለ እዳ እንደሆነ የተሰማው ለምንድነው? ታዲያ እኛ ከርሱ ያነሰ
ግዴታ ነው ያለብን? ይህንን አባባል ያስቡበት “ክርስቶስን የሚያምን ሰው
ሁሉ ነፍሳትን ማዳን የህይወት ሙሉ ስራው ሊሆን ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር
የተሰጠንን ፀጋ፣ በእኛ ላይ የበራውን ብርሃንና የተገለጠውን ውብና ኃያል የሆነ
እውነት ለመላው አለም ለማካፈል ባለ እዳዎች ነን” Ellen G. white, Testimonies for The church, vol, 4,53
4. ጳውሎስ የጠቀሰውን የኢሳያስ መጽሐፍ ክፍል ደግመው ያንብቡ፡፡ ይህ ኃሳብ
እኛን የሚመለከተው እንዴት ነው? አዎን ትልቅ የሆነ እውነት ተሰጥቶናል፤ ነገር
ግን ለዚህ እውነት ልባችን ጠጣር ከሆነና ከእኛ መሻትና ፍላጎት ጋር የሚጣረስ
ከሆነ በመንፈሳዊነታችን ላይ የሚገጥመን አደጋ ምንድነው?
5. ጳውሎስን ለመጠበቅ ከርሱ ጋር ራሳችሁን ያሰራችሁ ወታደር አድርጋችሁ
ራሳችሁን አስቡ፡፡ በቅርበት አብሮት ታስሮ ስለነበረው ሰው ምን የሚመለከት
ይመስላችኃል?