ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሐዋ.13፣2ቆሮ.4፡7-10፣ሮሜ.10፡ 1-4፣ ሮሜ 3፡19፣ ሐዋ.ሥራ 14፡1-26፣ ሮሜ. ምዕ.9-11፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ፡- ፡-“እንግዲህ ወንድሞች ሆይ የኃጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በሙሴ ሕግ በኩል ማግኘት ያልቻለውን ጽድቅ ያገኛል፡ ፡”(ሐዋ. ሥራ 13፡38-39)“
ያ
ለ ጥርጥር ወንጌል ለአህዛብ ብሎም ለአይሁድ መዳረስ ነበረበት፡፡ ቀደምት
አይሁዳውያን ክርስትያኖች ቀስ በቀስናበእርግጠኝነት መቀበል የጀመሩትይህንን
መልእክት ነበር፡፡
አህዛብ በስፋት መቀላቀላቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በግልፅ የሚነግረን ስለ አንጾኪያ
የተነገረው ታሪክ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ጥቂት የማይባሉ የአይሁድ አማኞች የነበሩ
ቢሆንም(ገላ. 2፡11-13) የመጀመሪያው የአህዛብ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው
በአንጾኪያ ነበር፡፡ መስራቾቹ ለወንጌል ካላቸው ቅናት የተነሳ በርናባስና ጳውሎስ
እንደመጡ በተፈጠረው አዲስ ሃይል በመነሳሳት ቤተክርስትያን በፍጥነት አደገች፡
፡ ይህችስፍራም ከይሁዳ ውጪ የመጀመሪያዋየክርስትያኖች ማዕከል ሆነች፡፡ እንደ
እውነቱ ከሆነማ በአንዳንድ ጉዳዮች በኢየሩሳሌም ከሚገኘው ቤተክርስትያንም
ሳይቀርትልቃለች፡፡
ሐዋሪያት አሁንም ያሉት በእየሩሳሌም ቢሆንም አንጾኪያ የክርስትያን አገልግሎት
ተልዕኮ የውልደት ስፍራ ሆነች፡፡ ጳውሎስ የተጓዘባቸውን ሦስት ሚሲዮናዊ ጉዞዎች
በተቃና መንገድ እንዲያደርግ በመነሻነት እገዛ ያደረጉለት በዚህ ስፍራ ያሉ አማኞች
ነበሩ፡፡ ክርስትና የሱስ እንዳቀደው አለማቀፋዊ ሃይማኖት የሆነው፣ ወንጌልም
‹‹ለህዝብ፤ ለነገድ ለቋንቋ ሁሉ››(ራዕይ 14፡6) እንዲስፋፋ የሆነውበነዚህ ሰዎች
ቆራጥነት ምክንያት ነበር፡፡
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለነሐሴ 12 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡
ሐዋ. ሥራ 13 ላይ ሉቃስ በሁለት ሙሉ ምዕራፎች(ሐዋ. 13 እና 14)
የሰፈረውን የጳውሎስን የመጀመሪያ ጉዞ ለመተረክ ሲል ትኩረቱን ወደ አንፆኪያ
ይመልሳል፡፡ ከዚህ ጀምሮእስከ መጽሐፉማብቅያድረስትኩረቱን በጳውሎስ እና
ለአህዛብ ባለው ተልዕኮ ላይ ያነጣጥራል፡፡
ይህ በሐዋሪያት ስራ መጽሐፍ የምናገኘው ቀዳሚው የወንጌል እንቅስቃሴ
ሲሆን ይህ ጉዞ ደግሞ በቤተክርስትያኒቷ በጥንቃቄ ታቅዶ የተከናወነ ድርጊት ነበር፡፡
ቢሆንም ሉቃስ ይህ ጥረት የመነጨው ከአማኞች ከራሳቸው ሳይሆን ከእግዚአብሔር
እንደ ሆነ በአጽንኦት ይጠቅሳል፡፡ እዚህ ጋ የምናገኘው ወሳኙ ነጥብ እግዚአብሔር
ሊሰራ የሚችለው እርሱ እንዲጠቀምብን በገዛ ራሳችን ፈቃድ ራሳችንን መስጠት
ስንችል ነው፡፡
ሐዋ.13፡1-12ን ያንብቡ፡፡ በርናባስና ጳውሎስ በቆጵሮስ ስላደረጉት እንቅስቃሴ
በተመለከተ ሉቃስ አጽንኦት ሰጥቶ ሊያስተላለፍ የፈለጋቸው ነጥቦችምንድናቸው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ወንጌላውያኑ ተሰናብተው ከመሄዳቸው አስቀድሞ የምልጃ ጸሎትና ጾም ተደርጎ ነበር፡
፡ በዚህ አውድ መሠረት እጅን ጭኖ የመጸለይ ተግባር ለስራው ብቁ ይሆኑ ዘንድ
ለእግዚአብሄር ፀጋ አሳልፎ መስጠትንና መቀደስን ይወክላል(ሐዋ.14፡26)፡፡
የቆጵሮስ ደሴት ከአንጾኪያ እምብዛም ርቆ በማይገኘው ሰሜን ምስራቃዊ የሜዴትራንያን
ባህር ጥግ የሚገኝ ስፍራ ነው፡፡ በርናባስ አስቀድሞ በቆጵሮስ ስለነበረብቻ ሳይሆን
ወንጌልም በዚያ ደሴት ቀድሞ ደርሶ ስለነበር ጉዞውን ለመጀመር ምቹ ስፍራ ነበር፡፡
ነገር ግን በዚያ ቦታም ቢሆን እጅግ ብዙ መሰራት የሚገባው ሥራ ነበረ፡፡
በቆጵሮስ ውስጥ በርናባስ እና ጳውሎስ እንዲሁም የበርናባስ የአክስት ልጅ የሆነው
ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ (ሐዋ.15፡39፤ቆላ.4፡10) በስልማና ምኩራቦች ይሰብኩ
ነበር፡፡ ይህ የጳውሎስ የየእለት ተግባሩ ነበር፡፡ ወደ አህዛብ ፊቱን ከማዞሩ በፊት ቀድሞ
በምኩራብ መስበክ ማለት ነው፡፡ የሱስ እስራኤላዊ የሆነ መሲህ ስለነበር ወንጌልን
አስቀድሞ ለአይሁድ ማካፈል ትክክለኛና እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡
ከስልማና በኋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እየተጓዙ (በሃሳባችን መሳል እንችላለን) ጳፋ
ወደተባለችው ዋነኛ ከተማ እስኪደርሱ ድረስ በመንገድ ይሰብኩ ነበር፡፡ ከዚያም
የመጽሐፉ ትረካ በሁለት ሰዎች ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡እነሱም አይሁዳዊ ጠንቋይ የሆነው
በርያሱስ ወይም ኤልማስ እና የሮም አገር ገዥ የነበረው ሰርግዮስ ጳውሎስ ናቸው፡
፡ ታሪኩ ሲቀጥል በእንደዚህ ያለ ከባድ ምላሽ በሚሰጥበት ሁኔታ እንኳን ወንጌል
እንዴት እንደተሰበከ ያትታል፡፡ በአንድ በኩል ግልጽ ተቃውሞ በሌላ በኩል ደግሞ
ትልቅ ስፍራ ያላቸው የአህዛብ ሰዎች ወንጌልን አምነው ሲቀበሉ እናያለን፡፡ ሐዋ.13፡12
ላይ የምናገኘው ግልጽ ትረካ ስለ መለወጥ(ወንጌልን ስለ መቀበል) በደንብ ፍንትው
አድርጎ የሚያሳይነው፡፡
በዚህ ታሪክ አይሁድ የሆነው እውነትን ሲቃወም አህዛብ የሆነው ግን መቀበሉን
ያሰላስሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሌላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ክርስትያኖች ምንም
እምነት ከሌላቸው ሰዎች ይልቅ ‹‹የወቅቱን እውነት›› ለመቀበል ሲቸገሩ ስናይ ይህ ምን
እንድንረዳ ያደርገናል?
ጳውሎስና ጓደኞቹ ከቆጵሮስ ተነስተው በዛሬዋ ቱርክ ደቡብ ጫፍ በጵንፍሊያ
ወደምትገኘው ጴርጌን ተጓዙ፡፡ ወደ ጲስዲያ ከመሄዳቸው አስቀድሞ ሉቃስ ሁለት
የተከናወኑ ለውጦችን ይዘግብልናል፡፡ ጳውሎስ የመሪነቱን ሚና መያዙን (እስካሁን
ድረስ በርናባስ ነበር ቀድሞ ይጠቀስ የነበረው) ሉቃስ የጳውሎስን አይሁዳዊ ስም
(‹‹ሳውል››) መጠቀም ያቆምና ‹‹ጳውሎስ›› በሚለው ስም ብቻ መጠቀም ይጀምራል
(ሐዋ.13፡9)፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ምናልባትም ጳውሎስን ከዚህ በኋላ በብዛት
የምናገኘው በግሪክና ሮም ግዛት ውስጥ ስለሆነ ይሆናል፡፡
ሐዋ.13፡13 ላይ እንደተዘገበው ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ወደ እየሩሳሌም
ተመለሰ፡፡ ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ በምን ምክንያት ተለይቷቸው እንደሄደ
የተገለፀልን ነገር የለም፡፡ ኤለን.ጂ.ኋይት ስትገልጽ ግን ከፊትለፊታቸው ሊገጥማቸው
ያለው መከራን በመፍራትና ተስፋን በመቁረጥ ‹‹ማርቆስ ስለፈራናድፍረቱን ስላጣ
አብሯቸው ወደ ሩቅ ስፍራ እንዳይሄድ እንቢ በማለት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ››
ትለናለች፡፡ - The Acts of Apostles, P.170፡፡እግዚአብሔር ነገሮች ቀላል እንደሚሆኑ
ቃል አልገባም፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ግን ጳውሎስ ከመጀመሪያውኑ የሱስን ሲያገለግል
ስቃይና እንግልት እንደሚደርስበት አውቋል (ሐዋ.9፡16)፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር
ሃይል ላይ ሙሉ በሙሉ መደገፍን ተማረ፤ ይህም የጥንካሬው ሚስጥር ሆነለት
(2ቆሮ.4፡7-10)፡፡
ሐዋ.13፡38ን ያንብቡ፡፡ በጲስዲያ ምኩራብ ጳውሎስ ያስተላለፈው ወሳኝ መልእክት
ምን ነበር?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሐዋ.13፡16-41 በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ውስጥ የተቀመጠውን የጳውሎስን የመጀመርያ
ስብከት ይገልጽልናል፡፡የተፃፈው ይህ ሆነ እንጂ የጳውሎስ የመጀመሪያው ስብከቱ
እንዳልሆነ ሳንረሳ በአጭሩ ተጠቃሎ የቀረበ መሆኑም ሌላው ነጥብ ነው፡፡
ስብከቱ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልንና የዳዊትን
መንግስት ስለመምረጡ(ሐዋ.ሥራ 3፡17-23)፡፡ ይህ ክፍል ከአይሁድ አድማጮች ጋር
መግባባትን ለመፍጠር የተናገረው ነው፡፡ ቀጥሎም ኢየሱስ የእግዚአብሄር የተስፋ
ቃልፍጻሜበመሆንከዳዊት ዘር ግንድ ለእስራኤል ድነትን እንደሚያመጣ ተረከላቸው
(ሐዋ. ሥራ 13፡24-37)፡፡ነገሩን ሲደመድም ደግሞ በየሱስ የተሰጠውን ድነት እምቢ
ለሚሉ ማስጠንቀቂያን በመስጠት ነበር (ሐዋ. ሥራ 13፡38-41)፡፡
የስብከቱ ዋነኛ ጡዘት የሚገኘው በቁርጥ 38ና 39 ሲሆን ይህም የጳውሎስ መልእክት
አንኳር ነጥብ ወደ ሆነው ፅድቅ ያተኩራል፡፡ ይቅርታና ጽድቅ የሚገኘው በሙሴ ህግ
በኩል ሳይሆን በየሱስ ብቻ ነው፡፡ ይህ ክፍል ህጉ ተሽሯል አይለንም ነገር ግን አይሁዶች
ጽድቅ ያመጣልናል ያሉት ህጉ ይህን ማድረግ እንደማይችል ፍንጭ ለመስጠት ነው
(ሮሜ10፡1-4)፡፡ የዚህ ሁሉ ብቸኛ ባለመብት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው (ገላ.2፡16)፡፡
ድነት በየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? የእግዚአብሔርን የሞራል
ህግ መጠበቅ አስፈጊነትና ህጉ ሊያፀድቀን ስላለመቻሉ በማሰብ ሁለቱን ሀሳቦች
እንዴት ሊያስታርቋቸው ይችላሉ?
ሐዋ.13:38-39 የሚገልጽልን ህጉ ሊያፀድቀን እንደማይችል ሲሆን ይህ ደግሞ
ወሳኝ አስተምህሮ ነው፡፡ የህጉ ባህሪ መልካም ቢሆንም ህጉ ሊያፀድቀን አይችልም፤
ምክንያቱም ለሚጠብቁት ሰዎች ፍጹም መታዘዝን አይሰጣቸውም (ሐዋ.15፡10፣
ሮሜ 8፡3)፡፡ ህጉ ፍጹም መታዘዝን እንድንለማመድ ቢያደርገን እንኳን ያለፈውን
ኃጢያታችንን ሊያስተሰርይልን አይችልም(ሮሜ3፡19፣ ገላ.3፡10-11)፡፡ ለዚህ ነው
ጽድቅን በከፊልም እንኳን ማግኘትየማይቻለው፡፡ ፅድቅን ልንቀበል የምንችለው
ሊያስተሰርይ ብቁ በሆነው በየሱስ ላይ ባለን እምነት ብቻ ነው፡፡ (ሮሜ 3፡28፣ ገላ.2፡
16)፡፡ ይህ ስጦታ ደግሞ ፈጽሞ የማይገባን ነው፡፡ መታዘዝ ለክርስትና ህይወት ምንም
ያህል አስፈላጊ ቢሆን ድነትን ግን ሊያመጣልን አይችልም፡፡
ሐዋ.13፡42-49ን ያንብቡ፡፡ በምኩራብ ያሉ ሰዎች የጳውሎስን መልእክት እንዴት
ተቀበሉት?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ምንም እንኳን ጳውሎስ መልእክቱን የደመደመው ጠንከር ባለ መንገድ ቢሆንም
በምኩራብ የነበሩት አብዛኛዎቹ ሰዎች የሰጡት ምላሽ ደስ የሚያሰኝ ነበር፡፡
በሚቀጥለው ሰንበት ግን ነገሮች በአስደናቂ ሁኔታ ተለወጡ፡፡ የወንጌሉን መልዕክት
ሲቃወሙ የነበሩት ‹‹አይሁዳውያን››ምናልባትም ይሁዲነትን እንደተቋም የሚወክሉት
የምኩራብ መሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሉቃስም እጅግ ከመቅናታቸው የተነሳ
በጭካኔአይን ጳውሎስን ይመለከቱት እንደነበር ገልጧል፡፡
በጥንቱ አለም የአይሁድ እምነት መገለጫ የነበሩት በአንድ አምላክ ማመን፣
የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም ሰንበት ከአይሁድ ውጪ የሆኑትን ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ
ስለሳባቸው ብዙዎች የአይሁድን እምነት ተቀላቅለው ነበር፡፡ ግርዘት ግን ኋላቀር
እና አፀያፊ አድርገው ስለወሰዱት ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ
ብዙ አህዛብወደ አይሁዳዊነት በይፋ ሳይቀየሩም እግዚአብሔርን ለማምለክ ወደ
ምኩራብ ይመጡ ነበር፡፡ እነዚህም ‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ›› ተብለው ይጠሩ ነበር፡
፡ በምኩራብ የሚገኙ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ተብሎም ተጠርተዋል (ሐዋ.13፡
16፣43)፡፡በህዝቡ መካከል የጳውሎስ መልእክት እንዲሰራጭያደረጉትናበብዛትም
ይመጡ የነበሩት ‹‹እግዚአብሔርን የሚፈሩ›› የተባሉትና ወደ አይሁድነት በይፋ
የተቀላቀሉት እንደሆኑ ይገመታል፡፡ በቅድሚያ የአይሁድ እምነት ተከታይ ሳይኮን
ድነትን መለማመድ መቻሉ ያለጥርጥር ለብዙዎች ማራኪና ሳቢ ነበር፡፡
የአይሁድ መሪዎች ስላደረባቸው ቅናት ምክንያት ለመግለፅ ይህ ይረዳ ይሆናል፡፡
በዚህም አለ በዛ ወንጌልን በመቃወማቸው ከእግዚአብሔር ድነት ራሳቸውን እያገለሉ
ብቻ ሳያሆን ጳውሎስና በርናባስንም ነፃ ሆነው በድነት እቅድ ውስጥ ያካተታቸውን
አምላክ በማመስገን ወደተደሰቱት አህዛብ ሙሉ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ
አደረጓቸው፡፡
በአይሁድ መሪዎች አነሳሽነት የአካባቢው ባለስልጣናት የተቃውሞ ቅስቀሳን አነሳስተው
ጳውሎስንና በርናባስን ከከተማ አስወጧቸው(ሐዋ.13፡50)፡፡ ደቀመዛሙርቱ ግን
በደስታና በመንፈስቅዱስ ይበልጥ ተሞሉ (ሐዋ.13፡52)፡፡ወንጌላውያኑም ወደ
ኢቆንዮን ከተማ አቀኑ፡፡
ሐዋ. ሥራ 14፡1-7ን ያንብቡ፡፡የጳውሎስና የበርናባስ እንቅስቃሴ በኢቆንዮን ምን
ውጤት አመጣ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በኢቆንዮንም ጳውሎስና በርናባስ ፊታቸውን ወደ አህዛብ ከማዞራቸው አስቀድሞ
አይሁዶችን ለመድረስ ሞከሩ፡፡ በጲስድያዋ አንፆኪያ የነበረው የጳውሎስ ስብከት
(ሐዋ.13፡16-41) በአገልግሎቱ ለአይሁድ ቅድሚያ የሰጠበትን ዋነኛ ምክንያት ያም
ስለ እስራኤል መመረጥ መመረጡም ስለያዛቸው በረከቶች (ሮሜ3፡2፣ 9፡4-5)
እንዲሁም ከዳዊት የዘር ግንድ አዳኝ የመምጣቱ ተስፋ ቃል ስለተፈፀመ ነበር፡፡ አያሌ
አይሁዳውያን ወንጌልን መቃወማቸው እውነት ቢሆንም ጳውሎስ ግን ስለአይሁድ
መለወጥ ፈጽሞ ተስፋ አልቆረጠም፡፡
ሮሜ 9-11 ላይ ጳውሎስ ግልጽ አድርጎ እንደሚያስቀምጥልን ‹‹ከእስራኤል የተወለደ
ሁሉ እስራኤላዊ አይደለም›› (ሮሜ9፡6)፤አንዳንድ አይሁዳውያንም ሊያምኑ
የቻሉትበእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ህዝቡን
አልተወምነገር ግን ‹‹በአሁን ጊዜም እንደዚሁ በጸጋ የተመረጡ ትሩፋን አሉ››(ሮሜ
11፡5)፡፡አንድ ቀን አይሁዶች በእምነት ወደ የሱስ እንደሚመጡ ቢያምንም ጳውሎስ
ወንጌልን ለአህዛብ መስበኩን ቀጠለ፡፡
‹‹ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 9-11 ላይ ባቀረበው የመከራከሪያ ነጥብ በሐዋሪያት ሥራ
መጽሐፍ ስለተከተለው የተልዕኮስትራቴጂ የበለጠ የገለጸ ሲሆን በየትውልዱ ያሉ
ክርስትያኖች ላላመኑ አይሁዶች መመስከር እንዳለባቸውያሳየበትን ወሳኝ የስነ መለኮት
ትምህርት የምናገኝበት ነው፡፡›› David G. Peterson, The Acts of the Apostles
(Grand Rapids: Eerdmans, 2009),P.401::
ጉዳዩ በጲስዲያዋ አንፆኪያ ከሆነው እምብዛም አይለይም፡፡ በቅድሚያ ለጳውሎስ
መልእክት አይሁድም ይሁኑ አህዛብ የሰጡት ምላሽ ቀና ነበር፡፡ ግን አሁንም
በድጋሚ አማኝ ያልሆኑ አይሁዳውያን ምናልባትም የአይሁድ ማህበረሰብ መሪዎች
አህዛብ የሆኑትበወንጌላውያኑ (በእነ ጳውሎስ) ላይ ተቃውሞ እንዲያነሳሱባቸው
አዕምሮአቸውን መረዙባቸው፡፡ ይህም በህዝቡ መካከል ከባድ መከፋፈልን ፈጠረ፡
፡ ተቃዋሚዎቹም ጳውሎስ እና በርናባስን ለማጥቃትና ለመግደል ሲያሴሩ ሁለቱም
ወንጌላውያን ከተማውን ለቀው ወደ ቀጣዩ ስፍራ ለመሄድ ወሰኑ፡፡
አይሁዶች ወንጌልን ከመስማት ባለፈ የየሱስን ስም የሚጠሩ ሰዎች በህይወታቸው
ሲያሳዩት መመልከት ይፈልጋሉ፡፡ እርስዎ አይሁዳዊ የሆነ ጓደኛ ካለዎት ምን አይነት
ምስክርነትን ነው እየሰጡት ያሉት?
ቀጥሎ ጳውሎስና በርናባስ የጎበኙት ስፍራ ልስጥራ ሲሆን ከኢቆንዮን በደቡብ ምዕራብ
አቅጣጫ አስራ ስምንት ማይል (29 ኪ.ሜ አካባቢ) ርቆ የሚገኝ አነስተኛ መንደር
ነው፡፡ በዚያ ጥቂት ጊዜ ቢያሳልፉም (ሐዋ. ሥራ 14፡6-7፣15) ሉቃስ የዘገበልን ግን
አንዱን ታሪክ ብቻ ነው፤ይኸውም ከመወለዱ ጀምሮ ሲሰቃይ ስለኖረው ምናልባትም
ለማኝ ስለነበረው ሽባው ሰው መፈወስነበር፡፡
ሐዋ.14፡5-19ን ያንብቡ፡፡ ለጳውሎስ የመለሱለት ምላሽ ሕዝቦቹ ምን ያህል
ማስተዋላቸውየወረደእንደሆነ እንዴት ያሳያል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ሕዝቦች በተአምሩ እጅጉን ስለተደመሙ ጳውሎስና በርናባስ አማልክት እንደሆኑ
በማመን ስም አወጡላቸው፡፡ በርናባስን ‹‹ድያ(ዜውስ)›› ብለው ሲጠሩት እርሱም
የግሪክ አማልክት የበላይ አምላክ ሲሆን ጳውሎስን ደግሞ ‹‹ሄርሜን›› ብለው ጠሩት
እርሱም ‹‹የድያ›› አፈቀላጤ ነው፡፡እንደእውነቱ ከሆነሰዎቹ መስዋዕትም ጭምር
ሊያቀርቡላቸው ፈልገው ነበር፡፡
የላቲን ገጣሚ የሆነው ኦቪድ (43 ከክ.ል. በፊት -17 ከክ. ል በኋላ የኖረው) ሁለት
አማልክት በሰዎች ተመስለው ተመሳሳዩን አካባቢ (“የጵርግያን ከፍታዎችን”) ሲጎበኙና
ለማረፍ የሚበጃቸውን ስፍራ ሲፈልጉ የሚተርክን አፈ ታሪክ ቀደም ብሎፅፎ ነበር፡፡
እንደ አፈ-ታሪኩ ከሆነ ትሁትና በእድሜ የገፉ ጥንዶች እነዚህን እንግዶች ተቀብለው
ተንከባከቧቸው፤ ሌሎቹ ግን ቸልተኞች ነበሩ፡፡ለእነዚህ የማይታወቁ እንግዶች
መልካምነትንና ርህራሄን ስላሳዩዋቸው የእነዚህ ጥንዶች ቤት ወደ ቤተ መቅደስነት
ሲለወጥ እነርሱም ካህናት ሆኑ፡፡ የቀረው ከተማ ግን ሙሉ በሙሉ ጠፋ (Methamorphoses 611-724)::
በዚህ አካባቢ ይህ ታሪክ በመዳረሱ ለጳውሎስ ተአምር ህዝቡ የሰጠው ምላሽ
እምብዛም ላያስደንቅ ይችላል፡፡ ታሪኩ ህዝቡ እነዚህ የፈውስ አማልክት ብለው
የሚጠሩትን አስክሌፒየስ ናቸው ከማለት ይልቅወንጌላውያኑ ሁለቱ አማልክት ናቸው
ስላሉበት ምክንያት ይህ ታሪክ በደንብ ይገልፅልናል፡፡ ጳውሎስና በርናባስ ግን የሐሰት
አምልኮዋቸውንእንዲያቆሙ ከለከሏቸው፡፡ በስተመጨረሻ ከጲስዲያና ከኢቆንያን
የመጡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጉዳዩን እንዳልነበረ ገለባብጠው ጳውሎስን በድንጋይ
ወግረው ወደሞት እንዲቃረብ አደረጉት፡፡
ሐዋ.14፡20-26ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስና በርናባስ ጉዟቸውን ያጠናቀቁት በየትኛው
ስፍራ ነበር? ከመንገዳቸው ሲመለሱስ ምን አደረጉ?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ጳውሎስ ‹‹ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን››
(ሮሜ 14፡22) ሲል ምን ማለቱ ነው? እዚህ ጋ እየተናገረ ያለውን እርስዎእንዴት
ተለማምደውታል? ከምንም በላይ ምንም አይነት ከባድ ‹‹መከራ›› ቢደርስብን በእምነት
ማደግን እንዴት ልንማር እንችላለን?
ክርስቶስ በዚህ ምድር በነበረበት ጊዜ አይሁዶችንራሳቸውን
ከሌሎች ህዝቦች ከመለየት ሊያወጣቸው ተጋ፡፡ የመቶ አለቃው መለወጥ እና
የከንአናዊትዋ ሴት ታሪክ ከእስራኤል ህዝብ ውጪ የሱስ በቀጥታ የሰራባቸው
ምሳሌዎችነበሩ፡፡ አሁን ጊዜው በአህዛብ መካከል ንቁና ቀጣይነት ያለው ስራ
የሚሰራበት ሆነ፡፡ ሁሉም ማህበረሰብ ወንጌልን በደስታ ለመቀበል ስለበራላቸው
የእምነት ብርሃን እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ ጊዜው ደረሰ፡፡የአይሁዳውያን
አለማመንና ተንኮልየእግዚአብሄርን አላማ አላከሸፈም፤ ምክንያቱም አዲሶቹ
እስራኤሎች በወይራ ዛፉውስጥ ገብተዋል፡፡ምኩራቦች ለደቀመዛሙርቱ ዝግ
ሁኑባቸው ነገር ግን በተቃራኒው የግልቤቶችና የአህዛብ የነበሩ የህዝብ ህንጻዎች
የእግዚአብሄር ቃል ይሰበክባቸው ዘንድ ክፍት ሆኑ፡፡›› Ellen G, white, Sketches
from the life of paul, P. 51::
“በሚሲዮናዊ ጥረታቸው ሁሉ ጳውሎስና በርናባስ የክርስቶስን ምሳሌ በመከተል
መስዋዕት በመሆን ታማኝና ለነፍሳት የሚተጉ ሰራተኞች ለመሆን ፈቃደኛ ነበሩ፡
፡ በከፍተኛ ንቃትና፣በጉጉት ሳይታክቱና፣ ወደራሳቸው ጉዳይ ፈጽመው ሳያዘነብሉ
በጸሎት እየተጉ የእውነትን ዘር ለመዝራት ሳያቋርጡ ሰሩ፡፡ ዘሩን እየዘሩ ደቀመዛሙርቱ
ለወንጌል ብለው የነሱን አቋም ለሚወስዱ ሰዎች ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር፡፡ ተግባራዊ
የሚሆን መመሪያን በመስጠት የማይነገር ዋጋ ያለውን ነገር አስተባበሩ፡፡ ይህ ቅን
የሆነ መንፈሳቸውና እግዚአብሔርን ማክበራቸው አዲስ በመጡት ደቀመዛመርቱ ልብ
ውስጥ ስለ ወንጌል መልእክት ወሳኝነት ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር ቻለ፡፡” Ellen G.
white, The Acts of the Apostle, s P. 186
1. ትኩረትዎን ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ነገሮች ከባድሲሆኑ ሸሽቶአቸው
በነበረው ታሪክ ላይ ያድርጉ፡፡ ስለ ማርቆስ ጉዳይ ጳውሎስና በርናባስ
ክርክር ገጠሙ፡፡ በርናባስ አብሮአቸው እንዲሄድ ሲፈልግ ጳውሎስ ግን
እንቢ አለ (ሐዋ.15፡37ን ተመልከቱ)፡፡ ከአመታት በኋላ ግን ጳውሎስ ሲጽፍ
‹‹ማርቆስ በአገልግሎቴ ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋር ይዘኸውና›› (2ጢሞ.4፡11)
አለ፡፡ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለጥሪያቸው ታማኝነታቸውን ማሳየት ላልቻሉ
ሰዎችምን ማድረግ እንዳለብን ምን እንማራለን?
2. ጳውሎስንና በርናባስን የልስጥራ ሰዎች አምላክ አድርገው ሲቆጥሯቸው
የመለሱላቸውን ምላሽ እስቲ ተመልሰው ይቃኙ (ሐዋ.14፡14-18)፡፡
እግዚአብሔር ለኛ ህይወት ላደረገው ነገር ስፍራውን ለራሳችን ለመውሰድ
ስንፈተን እንዴት መመለስ አለብን?
3. ሐዋ.14፡21-23ን ያንብቡ፡፡ ጳውሎስና በርናባስን እንደመነሻነት
በመውሰድአዲስ የተለወጡ ሰዎች እምነታቸው እንዲዳብርና እንዲያድግ
በግል ብሎም በቤተክርስትያን ደረጃ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
4. ሰዎች የፈጠሩዋቸው ባህሎችም ሆኑ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እምነቶች ልክ
የሃይማኖት መሪዎች ጳውሎስን እንደተቃወሙት በእውነት መንገድ ላይ
ጣልቃ ስላለመግባታቸው እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?