ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሐዋ. 4:8-12፣ ሐዋ. 1:11፣ ማቴ. 25:1-13፣ ዕብ. 9:11-12፣ ዘፀ. 20:8-11፣ 1ቆሮ. 15:51-54፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ :--“‘ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና’” (ሐዋ. 4፡12)፡፡
ሰ
ባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች በ1888 ዓ.ም. በአንዳንድ ቁልፍ የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥቅሶች ዙሪያ ብርቱ ሙግት አድርገው ነበር፡፡ መጋቢዎችና የቤተ ክርስቲያን
መሪዎች በዳን. 7 ስለሚገኙት አሥሩ ቀንዶች ትንቢት ምንነት እንዲሁም በገላ.
3፡24 በቀረበው ሕግ ዙሪያ በሚከራከሩበት ወቅት አንዱ ለሌላው የነበረው በጥላቻ
የተሞላ አመለካከት ኅብረታቸውንና ጓደኝነታቸውን ብሎም የቤተ ክርስቲያንን
አንድነትና ተልዕኮ ማጥፋቱን የተገነዘቡ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ፡፡
በሁኔታው አብልጣ ያዘነችው ኤለን ጂ. ኋይት በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁሉ
ከየሱስ ጋር ያላላቸውን ግንኙነት በጥንቃቄ እንዲያስቡበት እና በተለይ ደግሞ በሃሳብ
በማንስማማ ጊዜ ለየሱስ የሚኖረን ፍቅር እንዴት በባህሪያችን መታየት እንደሚኖርበት
ታበረታታ ነበር፡፡ በተጨማሪም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባላት በእያንንዳንዱ
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ተመሳሳይ አቋም እንዲይዝ መጠበቅ የለብንም ስትል
ተናግራለች፡፡ ሆኖም መሰረታዊ የሆኑትን የአድቬንቲስት እምነቶች በማስተዋል ረገድ
ግን አንድነት ሊኖረን እንደሚገባ አጽንኦት ትሰጣለች (Ellen G. White, Counsels to
Writers and Editors, pp. 28-32)፡፡ በዚህ ሣምንት አድቬንቲስት የሚያሰኙንንና
አንድነታችንን የሚቀርጹ አንዳንድ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን
እንመለከታለን፡፡
ምንም እንኳ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን ከሌሎች የክርስትና አካላት ጋር
አንድነት ለመፍጠር የሚያስችሉንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነጥቦች ብንጋራም፤ ኃይማኖታዊ
አስተምህሮአችን በክርስትናው ዓለም ማንም እያወጀው የማይገኘውን የተለየ እውነት
ይዞአል፡፡ እነዚህ እውነቶች እኛን የመጨረሻዎቹ የእግዚአብሔር ትሩፋን አድርገው
ይገልጹናል፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሐዋ. 4፡8-12፣ 10፡43፡፡ ከደኅንነት ዕቅድ አኳያ ባለው ማስተዋል
ጴጥሮስ ስለ የሱስ ክርስቶስ ምን ዓይነት አጽንኦት ይሰጣል?
እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ማስታረቁን (2ቆሮ. 5፡19) ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ነግሯቸዋል፡፡ የክርስቶስ ሞት በኃጢአት ጥልቅ ሸለቆ እና በሞት ላይ ድልድይ በመሥራት እነሆ ከአብ ጋር አስታረቀን፡፡ ክርስቲያኖች የሱስ በዚህ ምድር ለመፈጸም የመጣውን የሞቱን፣ የትንሣኤውንና የአስታራቂነቱን ፍቺ ለምዕተ ዓመታት ያጤኑት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የእርቅ ሂደት ሥርየት በሚል ይታወቃል፡ ፡ ሥርየት የተሰኘው ቃል አንዱ አማኝ ከሌላው ጋር ባለው ግንኙነት በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብ መሆንን ይወክላል፡፡ መለያየትና መከፋፈል በሚከሰትበት ወቅት ይህ ኅብር የእርቅ ውጤት ይሆናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ኅብረት የዚህ እርቅ ስጦታ ነው፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ የሱስ ሞትና ትንሣኤ ምን ያስተምሩናል? ሮሜ. 3:24-25
1ዮሐ. 2:2
1ዮሐ. 4:9-10
1ጴጥ. 2:21-24
ምንም እንኳ በክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ላይ ያለንን እምነት ከሌሎች የክርስትና
አካላት ጋር በተመሳሳይ ብንጋራም፤ ነገር ግን እኛ የምናውጀው የሦስቱ መላእክት
መልእክት ክፍል ከሆነው (ራእ. 14፡6-13) “ከዘላለማዊው ወንጌል” ዐውድ ነው (ራእ.
14፡6)፡፡ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን ከሌሎች የክርስትና አካላት በተለየ
ለእነዚህ መልእክቶች አጽንኦት እንሰጣለን፡፡
የክርስቶስ ሞት ተጨባጭ እውነታና ትንሣኤ የሚያስገኘውን ተስፋ ሁሌም
ከፊትዎ ጠብቀው መጓዝን መማር የሚችሉት እንዴት ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ሁሉም ትንቢቶች እና የተስፋ ቃሎች በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ፍጻሜ እንደሚያገኙ ተስፋ የሚያደርጉት ሐዋርያትና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ክስተቱን “የተባረከ ተስፋችን” (ቲቶ 2፡13) ሲሉ ይጠሩታል፡፡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የእምነታቸው አካል የሆነውን ዳግም ምጽአት ዛሬም አጽንተው ይዘዋል፡፡ ለነገሩ “አድቬንቲስት” የተሰኘው ስማችን ራሱ ይህንኑ በሚገባ ይገልጻል፡ ፡ ክርስቶስን የሚወዱ ክርስቲያኖች በሙሉ ጌታን ፊት ለፊት እያዩ አምልኮ የሚያቀርቡባትን ያቺን ዕለት በታላቅ ጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡ እስከዚያው ግን የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተስፋ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች በአንድ እንዳስተሳሰረ ይኖራል፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሁናቴ ምን ያስተምራሉ? ዳግም ምጽአቱን ከሚጠቁሙ አንዳንድ እሳቤዎች የሚለዩት እንዴት ነው? ሐዋ. 1:11፣ ማቴ. 24:26-27፣ ራእ. 1:7፣ 1ተሰ. 4:13-18፣ ራእ. 19:11-16፡፡
የሱስ የዳኑ ሕዝቦቹን ሊዋጅ ዳግም እንደሚገለጥ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ
ያረጋግጥልናል፡፡ የሱስ ራሱ “ያን ቀንና ሰዓት ግን ከአብ በስተቀር የሰማይ መላእክት
ቢሆኑ፣ ወልድም ቢሆን ማንም አያውቀውም፡፡” በማለት በዚህ ጊዜ ይሆናል ብሎ
መናገር እንደማይቻል ይጠቁማል፡፡ የሱስ ክርስቶስ ዳግም የሚገለጥበትን ጊዜ
የማናውቅ ብቻ ሳንሆን አታውቁትም ተብሎ ተነግሮናል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ዳግም ምጽአቱን በምትጠባበቅበት ወቅት ሊኖራት የሚችለውን
ተሞክሮ ለማሳየት የሱስ በአገልግሎቱ መጨረሻ አካባቢ የዐሥሩን ልጃገረዶች ምሳሌ
(ማቴ. 25፡1-13) ተናግሮአል፡፡ እነዚህ በሁለት ቡድን የተከፈሉ ልጃገረዶች ዳግም
ምጽአቱን እንጠባበቃለን ብለው የሚያምኑ ሁለት ዓይነት አማኞችን ይወክላሉ፡፡
ምንም እንኳ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የነበሩ ልዩነቶች እምብዛም ባይታዩም ነገር
ግን የየሱስ ምጽአት በዘገየ ጊዜ ልዩነቶቻቸው በገሃድ ጎልተው መውጣት ችለው ነበር፡
፡ መዘግየት ቢኖርም ነገር ግን አንደኛው ቡድን ተስፋውን አለምልሞና ተጨማሪ
መንፈሳዊ ዝግጅቶችም አድርጎ ነበር፡፡ የአምላካዊውን ተስፋ ፍጻሜ የሚያሳይ
ተጨባጭ ማስረጃ ባይኖርም እንኳ ክርስቲያናዊው ተሞክሮ ስሜታዊ ደስታ ላይ
መመስረት የለበትም፡፡ ይልቁንም ባለማቋረጥ በእግዚአብሔር ጸጋ እየታመኑ መኖር
እንደሚገባ የሱስ ይህን ምሳሌያዊ አነጋገር ተጠቅሞ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር
ተስፋ አድርጎአል፡፡ ተግተን እንድንጠባበቅና በማናቸውም ቢዜ ለዳግም ምጽአቱ
ዝግጁ ሆነን እንድንገኝ የሱስ ዛሬም ግብዣውን ያቀርብልናል፡፡
ምንም እንኳ “ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት” የሚለው ስማችን ዳግም ምጽአቱ ምን
ያህል ለእኛ ወሳኝ እንደሆነ ቢመሰክርም ነገር ግን ይኸው ተጨባጭ እውነታ ከፊታችን
መሆኑን እያስተዋልንና እየተጠባበቅን ምን ያህል በግል እንመላለሳለን? ዓመታት ባለፉ
ቁጥር የሱስ በዐሥሩ ልጃገረዶች ምሳሌያዊ አነጋገር የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሳንስት
መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ሙሴ ለአምላካዊው ማደሪያ የሚሆን የመገናኛ ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ
እንዲሠራ እግዚአብሔር አዞት እንደ ነበር በብሉይ ኪዳን መጽሐፍ እናነባለን (ዘፀ.
25፡8)፡፡ በመገናኛ ድንኳኑ አገልግሎት አማካይነት የእስራኤል ሕዝቦች የደኅንነትን
እቅድ ይማሩ ነበር፡፡ ይህ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀስ ሆኖ የተሠራ መገናኛ ድንኳን ቆየት
ብሎ፣ በንጉሥ ሰለሞን ዘመን ውብ በሆነ ቤተ መቅደስ ተቀየረ (1ነገሥ. 5-8)፡፡ መገናኛ
ድንኳኑም ሆነ ቤተ መቅደሱ የተሠሩት ከሰማያዊው መቅደስ ንድፍ አኳያ ነበር (ዘፀ.
25፡9፣ 40)፡፡
በሰማይ ዋንኛው የእግዚአብሔር መኖሪያ ቤተ መቅደስ መኖሩን በመላው የመጽሐፍ
ቅዱስ ገጾች ተጠቅሶ እንመለከታለን፡፡ ምድራዊው የቤተ መቅደስ አገልግሎት
የደኅንነትን እቅድና የየሱስን ሰማያዊ ክኅነት አገልግሎት በጨረፍታ የምናይበት ነው፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዕብ. 8:6፣ 9:11-12፣ 23-28፣ 1ዮሐ. 1:9-2:2፡፡ ጥቅሶቹ ስለ የሱስ
የክኅነት አገልግሎት ምን ያስተምሩናል?
ሰማያዊው ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ አንስቶ ስለ ደኅንነታችን
የካኅንነት አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኝበት ስፍራ ነው (ዕብ. 7፡25)፡፡ “እንግዲህ
ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው
ዙፋን በእምነት እንቅረብ” (ዕብ. 4፡16)፡፡
በምድራዊው የመገናኛ ድንኳን ካኅኑ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሁለት ክፍሎች
ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው ዕለታዊውን አገልግሎት የሚሰጥበት ቀዳሚው ቅዱስ ክፍል
ሲሆን ሁለተኛው በዓመት አንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥበት ቅድስተ ቅዱሳን ነበር፡፡
በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ምዕራፍ ስለ ተከፈሉት ስለ እነዚህ የየሱስ ሰማያዊ
አገልግሎቶች ይገልጻል፡፡ የተቀደሰው የየሱስ ሰማያዊ አገልግሎት--ማማለድን፣
ይቅርታን፣ እርቅንና ወደ ቀድሞው ንጽሕና መመለስን አካቶአል፡፡ ንስሐ የሚገቡ
ኃጢአተኞች በየሱስ አማላጅነት በቀላሉ ወደ አብ መቅረብ ይችላሉ (1ዮሐ. 2፡1)፡
፡ የሱስ ከ1844 አንስቶ በሰማያዊው ቅድስተ ቅዱሳን እየሰጠ የሚገኘው አገልግሎት
በዓመት አንድ ጊዜ በሥርየት ቀን ይደረግ ከነበረው የፍርድና ማንጻት ገጽታዎች ጋር
የተሳሰረ ነው (ዘሌዋ. 16)፡፡ ደግሞም የቤተ መቅደሱ የማንጻት አገልግሎት በፈሰሰው
የየሱስ ደም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በክርስቶስ መልካም ተግባራት የኃጢአት
መገኛ መወገድንና በአምላካዊው መንግሥት ሥር ከሚተዳደረው ዩኒቨርስ ጋር
የሚፈጠረውን ፍጹም እርቅና ስምምነት ያሳየው በዚህ ዕለት የተፈጸመው የሥርየት
ተግባር በመጨረሻ የሚመጣውን አስቀድሞ ያመላከተ ነበር፡፡ የዚህ የባለ ሁለት ገጽታ
ኃይማኖታዊ አስተምህሮ አገልግሎት አጠቃላዩን የደኅንነት ዕቅድ በማስተዋሉ ረገድ
በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአድቬንቲስት አስተዋጾ ነው፡፡
ሌላው ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የሚያምኑትና ጠብቀው የያዙት የመጽሐፍ ቅዱስ
አስተምህሮ ሰባተኛ ቀን ሰንበት ነው፡፡ ሰንበት በአማኞች መሃል አንድነትና ኅብረት
የሚያመጣ ቁልፍ ኃይማኖታዊ አስተምህሮ ነው፡፡ በክርስትናው ዓለም ከጥቂቶች
በቀር በብቸኝነት ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ እንከተላለን፡፡
ሰንበት ከፍጥረት ጊዜ አንስቶ እግዚአብሔር ለሰብዓዊው ፍጡር የሰጠው ስጦታ ነው
(ዘፍ. 2፡1-3)፡፡ በፍጥረት መጨረሻ በዕለቱ ገቢራዊ በሆኑ ሦስት መለኮታዊ ድርጊቶች
ሰንበት ተቋቋመ፡ (1) እግዚአብሔር በሰንበት ዐረፈ (2) ቀኑን ባረከው (3) ቀደሰው፡
፡ እነዚህ ሦስት ድርጊቶች ሰብዓዊው ዘር ሰማያዊውን ሐቅ በምድር እንዲለማመድና
የእግዚአብሔርን የስድስት ቀን የፍጥረት ሥራ እውነት አጽንቶ እንዲይዝ በማስቻል
ሰንበትን የተለየ አምላካዊ ስጦታ አድርገው አቋቋሙ፡፡ ሰንበት እግዚአብሔር ሕዝቦቹን
በተለየ ሁናቴ የሚገናኝበት ዕለት ነው፡፡
በመቀጠል የቀረቡ ጥቅሶቹ ሰንበት ለሰብዓዊው ፍጡር ስላለው ትርጉም ምን
ያስተምሩናል? ዘፀ. 20:8-11፣ ዘዳ. 5:12-15፣ ሕዝ. 20:12-20፡፡
ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የየሱስን ምሳሌ ለመከተል ባለን ጽኑ ምኞት (ሉቃ. 4፡16)
ሰባተኛውን ቀን ሰንበት እናከብራለን፡፡ የሱስ በሰንበት ቀን የነበረው ተሳትፎ ዕለቱን
የእረፍትና የአምልኮ አድርጎ ማጽደቁን ያመለክታል፡፡ ክርስቶስ ሰንበትን ከማክበርና
በዕለቱ ደስ ከመሰኘት የሚመጡ አካላዊና መንፈሳዊ ፈውሶችን ወርድና ስፋት
ለማስተማር ሲል አንዳንድ ታምራቶችን በሰንበት ቀን ያደርግ ነበር (ሉቃ. 13፡10-17)፡፡
የሱስ ሰንበትን አለመሻሩን ያስተዋሉ ሐዋርያትና የቀደሙ ክርስቲያኖችም በተመሳሳይ
ዕለቱን ይጠብቁና አምልኮ ያደርጉ ነበር (ሐዋ. 13:14፣ 42፣ 44፣ 16:13፣ 17:2፣ 18:4).
ሌላው ውብ የሰንበት ገጽታ ከኃጢአት ነፃ የመሆናችን ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ሰንበት
እግዚአብሔር እስራኤላውያን ሕዝቦቹን ከግብፅ ባርነት ወደ ተስፋይቱ ከነዓን ዕረፍት
ያስገባበት አዳኝነቱን የሚያስታውሱበት ዕለት ነው (ዘዳ. 5፡12-15)፡፡ ምንም እንኳ
እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ይፈጽሙ በነበረው አለመታዘዝና ጣኦት አምልኮ ጠንቅ
ሙሉ ለሙሉ ወደ ተስፋው ምድር ባይገቡም እርሱ ግን ዛሬም “የሰንበት ዕረፍት
ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል” (ዕብ. 4፡9) ሲል ይነግረናል፡፡ ወደዚያ
ዕረፍት ለመግባት የሚመኙ ሁሉ የሱስ በሚሰጠው ደኅንነት በሚገኝ እምነት ሊገቡ
ይችላሉ፡፡ ለኃጢአታችን ይቅርታ ለማግኘትና የዘላለማዊ ሕይወት ባለቤት ለመሆን
የምንመካው በሥራችን ሳይሆን በዚሁ በእርሱ መልካም ሥራ ብቻ ከመሆኑ አኳያ
በሰንበት ማረፍ ይህን በክርስቶስ የማረፍ መንፈሳዊ ተምሳሌት ይዞአል (ዕብ. 4፡10፣
ማቴ. 11፡28-30)፡፡
ክርስቶስ ለሕዝቡ የሚመኘውን አንድነትና ኅብረት በተጨባጭ እንዲለማመዱ
ሰንበት የረዳዎት እንዴት ነው?
በፍጥረት ወቅት “እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤
በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ” (ዘፍ. 2፡
7)፡፡ ይህ ሰው የተፈጠረበት ታሪከ እግዚአብሔር የሕይወት ምንጭ መሆኑን ያሳያል፡
፡ ለመሆኑ ሕያውነት ወይም አለመሞት የዚህ ሕይወት ውስጠ ባህሪያዊ ገጽታ ነው?
እግዚአብሔር ብቻ ሕያው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል (1ጢሞቴ. 6፡16)፡፡
ሕያውነት ሰብዓዊው ፍጡር ሲወለድ በስጦታ አልተሰጠውም፡፡ ሰብዓዊው ፍጡር
ከእግዚአብሔር በተቃራኒ ሟች ነው፡፡ አምላካዊው ቃል “ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ
እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ” (ያዕ. 4፡14) በማለት ሰብዓዊውን ሕይወት ይገልጸዋል፡
፡ ሰው በሚሞት ጊዜ ፍጹም ራሱን በማያውቅበት ጥልቅ የእንቅልፍ ሁናቴ ውስጥ
ይወድቃል (መክ. 9:5-6፣ 10፣ መዝ. 146:4፣ መዝ. 115:17፣ ዮሐ. 11:11-15)፡፡
ምንም እንኳ ሰብዓዊው ፍጡር ሟች እና ለሞት የሚዳረግ ሆኖ ወደዚህ ምድር
ቢመጣም፤ ነገር ግን የሱስ ክርስቶስን የሕያውነት ምንጭ አድርጎ የሚያስቀምጠው
መጽሐፍ ቅዱስ በእርሱ የማዳን ኃይል ለሚያምኑ ሁሉ የሕያውነትን ተስፋ እንደሚሰጥ
ይነግረናል፡፡ “የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም
ሕይወት ነው” (ሮሜ 6፡23)፡፡ “አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት
ሕይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሃን ባወጣው በመድኃኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ
መምጣት ተገልጦአል” (2ጢሞቴ. 1፡10)፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ
ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ. 3፡16)፡፡ ሰው ለዘላለም ሞቶ እንደማይቀር ይኸው
አምላካዊ ተስፋ ያረጋግጥልናል፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ቆሮ. 15፡51-54፣ 1ተሰ. 4፡13-18፡፡ ጥቅሶቹ ከሞት በኋላ ሕይወት
ስለመኖሩና ሕያውነት ለሰብዓዊው ፍጡር ስለመሰጠቱ ምን ይነግሩናል?
እግዚአብሔር ሕያውነትን ለሕዝቡ የሚሰጠው ወዲያው እንደሞቱ ሳይሆን ነገር
ግን የመጨረሻው የመለከት ድምፅ በሚሰማበት በዚያ የትንሣኤ ጠኋት መሆኑን
ይነግረናል፡፡ አማኞች የሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው እንደ ተቀበሉ
የዘላለማዊውን ሕይወት ተስፋ ያገኙ ሲሆን ነገር ግን የሕያውነት ባለቤት የሚሆኑት
በትንሣኤ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች እንደ ሞቱ ነፍሳቸው ወደ ሰማይ ይሄዳል ስለሚባለው
ጽንሰ ሃሳብ አዲስ ኪዳን የሚያውቀው አንዳች ነገር የለም፡፡ በአዲስ ኪዳንም ሆነ
በብሉይ ኪዳን የማይገኘው ይህ የባዕድ አምልኮ አስተምህሮ ወደ ኋላ እስከ ጥንቱ
የግሪክ ፍልስፍና የሚዘልቅ ታሪክ አለው፡፡
ሞትን የም ናስተውልበት መንገድ የዳግም ም ጽአቱን ተስፋ አብልጠን እንድናደንቅ
የሚረዳን እንዴት ነው? ይህ እምነታችን እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት
አንድነታችንን ይበልጥ የሚያጠናክረው እንዴት ነው?
፡ Ellen G. White, “The Foundations, Pillars, and Landmarks,”
pp. 28-32, in Counsels to Writers and Editors. Read the article “Doctrines, Importance of,” pp. 778, 779, in The Ellen G. White Encyclopedia.
እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን ከአንዳንድ የክርስትና ድርጅቶች ጋር በአንድ
የምንጋራቸው መሰረታዊ ኃይማኖታዊ አስተምህሮዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መሃል አንዱና
ዋንኛው በእኛ ምትክ በሞተውና ሥርየት ባመጣልን የሱስ ብቻ በማመን የሚገኝ
ደኅንነት ወይም ጽድቅ በእምነት ነው፡፡ የጽድቃችን መሰረት የገዛ መልካም ሥራችን
ሳይሆን ነገር ግን ለእኛ በማይገባ የጸጋ ስጦታው በእምነት በተቆጠረልን የክርስቶስ
ጽድቅ ስለ መዳናችን እኛም ሆንን ሌሎች ክርስቲያኖች እናምናለን፡፡ “ለክርስቶስ
የተገባው ለእኛ ይሆን ዘንድ፤ እነሆ በአመጻችን ምክንያት በእኛ ላይ ሊደርስ ይገባ
የነበረው ሁሉ በእርሱ ላይ ደረሰ፡፡ ምንም ጥፋት ሳይኖርበት በእኛ ኃጢአት ተኮነነ፡፡
እኛም የማይገባንን በእርሱ ቅድስና ተዋጀን፡፡ የእርሱን ሕይወት እንቀበል ዘንድ ለእኛ
ይገባ የነበረውን የሞት ሥቃይ ተቀበለ፡፡”—The Desire of Ages, p. 25. ከእነዚህ
እምነቶች የሚወጡ የአኗኗር ዘይቤና የሕይወት ስልቶቻችን በክርስትናው ዓለም ልዩ
ያደርጉናል፡፡ ደግሞም እንዲህ መሆን ከሌለበት ታዲያ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት
መኖራችን ለምን አስፈለገ? ለየሱስ ያለን ፍቅርና የምናውጀው አስተምህሮ እርስ በርስ
የሚያስተሳስረን ጠንካራ ገመድ ሊሆን ይገባል፡፡
1.
በክርስቶስ ይቅር ለመባላችንና ለመጽደቃችን የምንሰጠው አድናቆት
ለክርስትና ኅብረታችን እንዲሁም ከማኅበረሰባችን ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መሰረት
የሚሆነው እንዴት ነው?
2.
ኃይማኖታዊ አስተምህሮአችን ከቤተ ክርስቲያን አንድነት አኳያ ምን ያህል
አስፈላጊ እንደሆነ ያስቡ፡፡ በአንድ ላይ ከምንጋራቸው ኃይማኖታዊ አስተምህሮዎች
ሌላ እነዚህን ከተለያዩ ብሔሮች፣ ኃይማኖቶች፣ የፖለቲካ አመለካከቶችና ባህላዊ
ዳራዎች የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች በአንድ ላይ ያሰባሰበው ምንድን ነው?
ከተልዕኮና ከመልእክት አኳያ ሳይሆን ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ኃይማኖታዊ
አስተምህሮ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይህ ምን ይነግረናል?
3.
“ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት” የተሰኘው ስማችን ሁለት ወሳኝ አስተምህሮዎችን
ይጠቁማል--ሰባተኛ ቀን ሰንበት እና ዳግም ምጽአት፡፡ አንደኛው የስማችን
ክፍል ፍጥረትን ሲያመላክት ሌላው መዋጀትን ያሳያል፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሁለት
አስተምህሮዎች ባላቸው ዝምድና እንደ ሕዝብ ማንነታችንን በጥቂት ቃላት የሚገልጹት
እንዴት ነው?
ማጠቃለያ፡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ከሌሎች የክርስትና ተቋማት ጋር
የሚጋሯቸው ብዙ ኃይማኖታዊ አስተምህሮዎች እንዳሉ ሁሉ የሌሉም አሉ፡፡ እነዚህን
አስተምህሮዎች እንደ ቤተ ክርስቲያን ከልዩ ማንነታችን አኳያ ጠቅለል አድርገን
ስንወስድ በየሱስ የአንድነታችን መሰረት ናቸው፡፡