ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ማር. 5:22– 24፣ 35–43፣ 1ጴጥ. 5:6-7፣ ዘፍ. 37:17–28፣ ሉቃ. 16:13፣ ሮሜ 6:16፣ 1ቆሮ. 15:26።
መታሰቢያ ጥቅስ:- “ከዚህም በላይ ለእርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋር ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጉድለት እቆጥረዋለሁ፤ ለእርሱ ስል ሁሉን አጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጉድፍ እቆጥራለሁ” (ፊልጵ. 3፡8)፡፡
አ
ዳምና ሔዋን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ፍሬ በበሉበት ቅጽበት በዓይነቱ
የመጀመሪያ የሆነውን ይኸውም የንጽሕናን እጦት ተለማመዱ። ይህ የንጽሕና
እጦት በራስ ወዳድነት፣ በውዝግብ፣ በማመኻኘት፣ በሌላው ላይ የበላይ የመሆንና
የመቆጣጠር ምኞት ተተካ።
አዳምና ሔዋን ከውድቀት በኋላ እርቃናቸውን የሚሸፍኑበት የእንስሳ ቆዳ
በተሰጣቸው ጊዜ ለመጀመሪያው ህይወት መጥፋት ምስክር ሆኑ። እነዚህ ሰዎች
እንደገና እጃቸውን ዘርግተው ከህይወት ዛፍ ፍሬ በመብላት ለዘላለም የሚኖሩ
ፍጡራን እንዳይሆኑ ወደ ህይወት ዛፍ ከመድረስ ታገዱ፣ ፍጹም የሆነውን የኤደን
መኖሪያቸውን አጡ፣ ከዓመታት በኋላ ልጃቸውን አቤል በገዛ ወንድሙ ቃየን እጅ
እንዲያጡ ሆኑ። በመጨረሻ ከባልና ሚስቱ መሃል አንዳቸው በሞት ቀደሙ። ውሎ
አድሮ የቀረውም ተከተለ። በዚህም በአንድ ውሳኔ የተነሳ እነሆ እጅግ ብዙ እጦት
ደረሰ።
እርግጥ ነው ሁላችንም የእጦትን እውነታና ሥቃይ ጠንቅቀን እንረዳለን። እጦት
በቤተሰብ አባል ላይ ሲደርስ ሐዘናችን መሪር ይሆናል። እጦት በተለያየ መልክና ቅርጽ
ክፉኛ እየደቆሰን ከመሆኑ አኳያ በቤተሰባችን መሃል የቀረበ ትስስር መመስረታችን
ሊያስገርም አይችልም።
በቤተሰባዊው ህይወት ዙሪያ የምናደርገውን ምልከታ በመቀጠል በዚህ ሣምንት
ከተለያዩ የእጦት ወቅቶች ዐውድ ምልከታ ለማድረግ እንሞክራለን።
ከሕይወት ዛፍ በኋላ በሺ የሚቆጠሩ ዓመታት ቢያልፉም በተለይ ከጤናችን አኳያ
ስናስበው የቅርብ ክስተት እንደሆነ ይሰማናል። አንድ ሰው በአሳዛኝ ሁኔታ በለጋ
ዕድሜው ካልተቀጠፈ በቀር ውሎ አድሮ ሁላችንም የጤና መቃወስ እውነታን
መጋፈጣችን አይቀሬ ነው።
የጤና መቃወስ አስቸጋሪ የሆነውን ያህል ህመም ራሳችንን ሳይሆን ከቤተሰባችን
በአንዱ ላይ ሲደርስ ምን ያህል የበለጠ ያውካል? በታማሚ ልጆቻቸው ጭንቀት
የወደቁ አያሌ ወላጆች “ምናለ የልጄን ህመም ለእኔ ባረገው!” ሲሉ ይደመጣሉ።
እንዳለመታደል ሆኖ ይህ ምርጫ ለእኛ አልተሰጠንም
።
ጥቅሶቹ በጋራ የያዟቸው ሀሳቦች ምንድን ናቸው? ማር. 5:22–24፣ 35–43፣ ማቴ.
15:22–28፣ ሉቃ. 4:38-39፣ ዮሐ. 4:46–54።
አንዱ የቤተሰብ አባል ለሌላኛው የቤተሰቡ አባል ፈውስ የሱስን ሲማጸን በእነዚህና
በሌሎች ብዛት ያላቸው ስፍራዎች እንመለከታለን።
በወደቀው ዓለም በመኖራችን የሥቃይ ሰለባ መሆናችንን ለማስተዋል አንቸገርም።
ኃጢአት ወደ ዓለም በገባ ጊዜ አብሮ የመጣው ሞት ብቻ ሳይሆን ህመምና በሽታ
ጭምር ነው። ጽኑ ወይም ጊዜያዊ ህመም ሲደርስብን መረበሽ፣ መበሳጨት፣ ተስፋ
መቁረጥ ወይም ይባስ ብሎ እንደ ዳዊት “አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?” (መዝ. 22፡1) ብለን ጥያቄያችንንና
ንዴታችንን ብሎም የውስጥ ህመማችንን ወደ እርሱ እናሰማለን።
ሞት በመጨረሻ በየሱስ ዳግም ምጽአት እስኪሸነፍ ህመምና ሥቃይ ምስጢር
ሆኖ ይቆያል። በመሃል ከአምላካዊው ቃል እጅግ አስፈላጊ እውነቶችን እየነቀስን
መውሰድ እንችላለን። ኢዮብ በቃላት መገለጽ በማይችል ብርቱ ህመም ውስጥ ባለፈ
ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ ግንኙነት መፍጠር ችሎ ነበር፤ “ጆሮዬ ስላንተ ሰምታ
ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ” (ኢዮ. 42፡5)።
ጳውሎስ አንድ ሥር የሰደደ ህመም
እንደ ነበረበት ይታወቃል። ሐዋርያው ይህን ህመም የተቋቋመበት መንገድ ሥቃይ
ሌሎችን ለማጽናናት ብርታት ሊሆነን እንደሚችል ይነግረናል። በጉዳት ላሉ ወገኖች
እንድንራራና ይበልጥ ውጤታማ አገልግሎት እንድንሰጥ ያስችለናል (2ቆሮ. 1፡3-5)።
ይህ የሚሆነው እስርስር አድርጎ እንዳያስቀምጠን የማንፈቅድለት ከሆነ ነው።
እኛ ራሳችን ላይ ወይም በቤተሰባችን አባል ላይ ህመም ቢደርስ
በየትኛው አምላካዊ የተስፋ ቃል ላይ መተማመን እንችላለን? እንዲህ
ዓይነቱ ሁኔታ ሲከሰት የጌታችን የየሱስ ክርስቶስን የመስቀል ላይ
ሥቃይ ማሰብ በእጅጉ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? በቤተሰባችን
የህመም ችግር ቢደርስም በመስቀል ላይ የዋለው ጌታ እውነተኛና ጽኑ
ስለ ሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ያስተምረናል?
እኛ ሁላችን ለሚያምኑን የማንታመን ጉድለት ያለብን ኃጢአተኛ ፍጡሮች ነን።
ለመሆኑ የክህደት ሰለባ ያልሆነ ማን አለ? ሰውን እንዳመኑት ማግኘት ከባድ የመሆኑን
ያህል እኛ ራሳችን በሌላው ላይ ክህደት ስንፈጽም ወይም በቤተሰባችን አባል ክህደት
ሲፈጸምብን--ነገሩ የከፋ ይሆናል።
አንዳንዴ ስናምነው ካልታመነው ግለሰብ ጋር ያለን ግንኙነት እንደ ቀድሞው
እንዲቀጥል ያን ያህል መሥዋዕትነት የምንከፍልለት ዓይነት ሆኖ ሳናገኘው ስንቀር-ቁረጥልኝ ሆዴ ልንል እንችላለን። ነገር ግን ችግሩ የተፈጠረው በቤተሰብ አባላት
ማለትም በባልና ሚስት መካከል ከሆነ ግን በእርግጥ ቀላል ላይሆን ይችላል። አንዱ
የትዳር ዓላማ--ቃል ሲታጠፍ ግንኙነቱን እንዴት ዳግም መገንባት እንደሚገባ
ትምህርት ማግኘት ነው ተብሎ ይታመናል።
መታመን በግንኙነት መሃል ድርድር ውስጥ ሲገባ ወደ ቀድሞው ንጽህና መፈወስና
መመለስ የሚችለው እንዴት ነው? 1ጴጥ. 5:6-7፣ 1ዮሐ. 4:18፣ ያዕ. 5:16፣ ማቴ.
6:14-15።
የተሰበረውን ግንኙነት መልሶ መገንባትን፤ ለረጅም የእግር ጉዞ ከሚደረግ እያንዳንዱ
እርምጃ አኳያ መውሰድ እንችላለን። በደሉ የቱንም ዓይነት ይሁን ወይም በዳዩ
ማንም ሊሆን ቢችል ጉዞው የተጎዳውን በቅን ልብ በማሰብና እውነቱን በመናዘዝ
ይጀምራል።
በዝሙት መውደቅ የቅሬታው መንስዔ ከሆነ ክህደት የፈጸመው አካል ስህተቱን
ሲናዘዝ ፈውስ ይጀምራል። እውነቱን ከፍጹም ግልጽነት ጋር መናዘዝ የፈውሱ
ሂደት አካል ሊሆን ይገባል። እንደ ተሰወረ ሊቀር የሚችል ምንም ነገር ባለመኖሩ
ነገሩ በታወቀ ጊዜ (ደግሞም ይታወቃል) ዳግመኛ በተመሰረተው መታመን ላይ ውሃ
ይቸልሳል። መታመን ለሁለተኛ ጊዜ ሲጣስ ፈውስ ለማግኘት ከመጀመሪያው ይልቅ
ከባድ ይሆናል።
መታመንን ወደ ቀድሞው ለመመለስ ጊዜና ትዕግሥት ይጠይቃል። የተፈጸመው
ጥፋት ከባድ በሆነ ቁጥር መልሶ ለመጠገን ያንኑ ያህል ጊዜ ይወስዳል። ጉዳዩ አንዳንዴ
ሁለት እርምጃ ወደ ፊት--ሦስት እርምጃ ወደ ኋላ ዓይነት ገጽታ ሊኖረው እንደሚችል
ይቀበሉ። ነገ ብሩህ ሆኖ ታይቶት ሲያበቃ በማግስቱ ግን ብሩህነቱ ጠፍቶቦት ራስዎን
ከዚያ መሰወር እንዳለቦት ይሰማዎታል። ሆኖም ብዙዎች የተሰበረውን ግንኙነት
ጠግነው ይበልጥ የተቀራረቡበትን፣ እርካታና ደስታ ያገኙበትን ጥልቅ የትዳር
ህይወት መመስረት ችለዋል።
ከጋብቻ ውጪ ልጅ እስከ መውለድ በተደረሰበት ሁኔታ ትዳርን
ለመፈወስ ምን ዓይነት መርኅዎች ጥቅም ላይ መዋል ይችላሉ? ይቅርታ
እስካለ ድረስ ግለሰቡን ማመን የሚቻልበት ሁኔታ… ይኖራል ወይስ
ያለቀለት ጉዳይ ነው?
በቤተሰብ መሃል መታመን እንዲጎድል ከሚያደርግ ሌላው ምክንያት አንዱ ጠብ
ወይም ብጥብጥ ነው። ሁኔታውን ለማመን የሚብድ ቢሆንም በማኅበረሰብ ውስጥ
ብቸኛው ከፍተኛ ጠብ አጫሪነት የሚስተዋልበት ስፍራ ቤት መሆኑን ጥናቶች
ያመለክታሉ። ቤተሰባዊ ጸብ ክርስቲያኖችን ጨምሮ ሁሉንም ይነካል። ጠብ
አጫሪነት ወይም ጠብ ማጫር አንዱ የቤተሰብ አባል በሌላኛው ላይ ወይም ከአንድ
በላይ የሆኑ አባላት በአንዱ ላይ--የቃል፣ አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
መፈጸም ሊሆን ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል ሳይቀር የተከሰቱ ቤተሰብ ነክ
የጸብ ታሪኮችን አካትቶአል። እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ ምን ዓይነት ሀሳብና ስሜት
ሊመጣብዎ ይችላል? ታሪኮቹ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል እንዲሆኑ የተፈለገበት
ምክንያት ምን ይመስሎታል?
ዘፍ. 37:17–28
2ሳሙ. 13:1–22
2ነገሥ. 16:3፣ 17:17፣ 21:6
በሌሎች ላይ ጥቃት የሚፈጽም ባህሪ ሰዎችን በጉልበትና በበላይነት ለመቆጣጠር
ከሚኖር ግላዊ ምርጫ ይመነጫል። ከዚህ ውጪ በመጠጥ ኃይል፣ በጭንቀት
ብዛት፣ በፍትዎት ምኞት፣ ንዴትን በተሻለ ለመቆጣጠር በሚደረግ መሻት ወይም
ማንኛውም ዓይነት የጉዳዩ ሰለባ ባህሪ እንደ ምክንያት መቆጠር አይችልም። ጥቃት
ፈጻሚዎች ፍቅርን ለመጠምዘዝና ለማዛባት ቢሞክሩም ነገር ግን “ፍቅር ክፉ
አያደርግም” (ሮሜ 13፡10)።
የባለሙያ እርዳታ በጥቃት ፈጻሚው ባህሪ ላይ ለውጥ
የሚመጣበትን መንገድ ማመቻቸት ቢችልም፤ ነገር ግን ይህ መሆን የሚችለው ግለሰቡ
በሚስተዋልበት ባህሪ ዙሪያ ኃላፊነት ሲወስድና ይህ እርዳታ እንደሚያስፈልገው
ፍላጎት ሲያሳይ ነው። ራሳቸውን ለአምላካዊው መገኘት ክፍት ለሚያደርጉ--ጉዳት
ፈጻሚዎች ከዚህ ተግባራቸው እንዲመለሱ፣ ለአጉል ዝንባሌአቸውና ባህሪያቸው
ንስሐ እንዲገቡ፣ በተቻለ በማንኛውም መልኩ ወደ ንጽሕና እንዲመለሱ እና ሌሎችን
መውደድ የሚያስችላቸውንና ልቦቻቸውን የሚፈውሰው የአምላካዊ ፍቅር--አጋፔ
በውስጣቸው አንዲሰርጽ--እርሱ እንደ ኃይሉ መጠን በሙላት መሥራት ይቻለዋል
(ኤፌ. 3፡20)።
ራስዎን በአሰቃቂ ገጠመኝ ሰለባ በሆነ ሰው ቦታ ለማስቀመጥ ይሞክሩ።
እንዴት ዓይነቶቹን የተቀባይነት፣ የማጽናኛና የተስፋ ቃላት መስማት
ይፈልጋሉ? ከጉዳት ፈጻሚው ጋር እንዴት በተሻለ መኖር እንደሚቻል
ምክረ ሀሳብ ከመለገስ ይልቅ ጥንቃቄና እንክብካቤ ያልተለየው
ተቀባይነት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ስንት ሚልዮን ወይም ቢልዮን ሰዎች ከሱስ ጋር እየታገሉ እንደሆነ የሚያውቀው
እግዚአብሔር ብቻ ነው። ምንም እንኳ ሳይንቲስቶች ከፍ ያለ ጉጉትና ምኞት
የሚገኝበትን የአንጎላችንን ክፍል ማየት ቢችሉም የዚህ መንስኤ ላይ ግን እስከ ዛሬ
አልደረሱም።
እነዚህ ከሱስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ክፍሎች የሚገኙበትን ስፍራ ማግኘት ማለት
እኛን ከሱስ ነፃ ማድረግ አለመሆኑ ብዙም መሳጭ ዜና አይደለም።
ሱሰኛው ሳይሆን ነገር ግን ሱስ ወይም መጥፎ ልማድ ለማንም ቢሆን ከባድ
ነገር ነው። ከቤተሰብ አባላት አንደኛው ሊወጣ ካልቻለው ሱስ ቁጥጥር ስር
ሲውል የቤተሰብ አባላት ማለትም--ወላጆች፣ ባልና ሚስት፣ ልጆች ሁሉም ክፉኛ
መሠቃየታቸው አይቀሬ ነው።
አደንዛዥ ዕጽ፣ የሚያሰክር መጠጥ፣ ሲጃራ ወይም ሱረት፣ የወሲብ ድርጊቶችን
የሚያሳዩ መጻሕፍትና ፊልሞች፣ ዝሙት እንዲሁም ምግብ ሳይቀር--ሱስ ወደ መሆን
የሚለወጥ ልማዳዊውና እያደገ የሚሄድ ተፈጥሮ አላቸው። እነዚህ ነገሮች ጉዳት
እያደረሱብዎ መሆኑን እያወቁም እንኳ ሊያቆሟቸው አይችሉም። እርስዎ የመምረጥ
ነጻነት ባለቤት ቢሆኑም ሱስ አምጪ ለሆነው ነገር ምርኮኛ ከሆኑ የዚያ ባሪያ እንጂ
የነፃነትዎ ባለቤት አለመሆንዎን ልብ ይሏል። ጴጥሮስ በቀላሉ በሚስተዋል አገላለጽ
ስለ ሱስ እንዲህ ይላል “እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነፃ
ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነውና”
(2ጴጥ. 2፡19)።
ሰዎችን ወደ ሱስ መውሰድ የሚችሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? ሉቃ. 16፡13፣ ሮሜ 6፡
16፣ ያዕ. 1፡13-15፣ 1ዮሐ. 2፡16።
ኃጢአት እና ሱስ የግድ ተመሳሳይ ነገሮች መሆን የለባቸውም። ኃጢአት ብዙውን
ጊዜ ወደ ሱሰ ሊለወጥ የሚችልበት ሁኔታ ሊከሰት ቢችልም፤ አንድ ሰው ሱሰኛ
ያልሆነበትን ኃጢአት ሊሠራ ይችላል። ኃጢአት ወደ ሱስነት ከመለወጡ አስቀድሞ
የእግዚአብሔር ኃይል ቢያቆመው እጅግ የተሻለ ከመሆኑ አኳያ አዲስ ልብ መቀበል
ለኃጢአትና ለሱስ ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ ይሆናል፡ “የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት
ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል” (ገላ. 5፡24)። በተጨማሪ ጳውሎስ
ለክርስቶስ መኖር እንችል ዘንድ ለዚያ ሱሰኛ ከሚያደርግ ኃጢአተኛ ተፈጥሮ
መሞት ምን ማለት እንደሆነ ለሮማውያኑ እንዲህ ይገልጻል “ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በሐሳባችሁ አትመቻቹለት”
(ሮሜ 13፡14)።
በራሳችን ይድረስ ወይም በቤተሰብ አባሎቻችን--ከሱስ ጋር የሚደረግን
ብርቱ ትግል የማያውቅ ማን አለ? ሰዎች--ምናልባት ክርስቲያኖችን
ጨምሮ በዚህ ዙሪያ ግንዛቤና የባለሙያ ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው እገዛዎን
እንዴት መስጠት ይችላሉ?
እንደ ሰብዓዊ ፍጡርነታችን የሞትን እውነታ እናውቃለን። ስለ ሞት እናነባለን፣ እናያለን፣ ራሳችንም ብንሆን ከሞት አፋፍ ልንተርፍ እንችላለን። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ቆሮ. 15፡26። ሞት የተገለጸበት መንገድ ምን ይመስላል? ለምን በዚህ መልኩ ተገለጸ?
የሚወደውን በሞት የተነጠቀ ሰው የሞትን ብርቱ ጠላትነት ለራሱ አይረዳውምን?
በጌታ ዐ ያንቀላፉ ሁሉ የመቃብር ቆይታቸው ሳይታወቃቸው ለዘላለም ህያው ሆነው
ሊኖሩ ይነሳሉ። “ሞት ለአማኙ ተራ ጉዳይ ነው… ለክርስቲያን ሞት ጸጥታና ጽልመት
የሚስተናገድበት የእንቅልፍ ወቅት ነው።
ህይወት በእግዚአብሔር ውስጥ በክርስቶስ
ይሸሸጋል “‘ህይወታችን የሆነው ክርስቶስ ዳግም ሲገለጥ እኛም ከእርሱ ጋር በክብር
እንገለጣለን’”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 787.
የሞትን ሥቃይና ሐዘን በተጨባጭ የሚያውቀው በሕይወት ያለው የሟች ጓደኛ
ወይም የቤተሰብ አባል እንጂ የሞተው አይደለም። በእርግጥ ሐዘን ተፈጥሮአዊ
እንደመሆኑ የቅርባቸውን ሰው በሞት የተነጠቁ የሚሰጡት የተለመደ ምላሽ ነው።
ምንም እንኳ የሁሉም ሰው የሐዘን ሂደት ተመሳሳይ ባይሆንም ነገር ግን ባጠቃላይ
ብዙዎች በዛ ባሉ ክብደት ያላቸው ምዕራፎች ያልፋሉ። አንድ ሰው በሞት አፋፍ ላይ
መሆኑን እያወቅንና እንደማይተርፍ እየገባን፤ በመጀመሪያ--በሞቱ ከፍተኛ ድንጋጤ
ይሰማናል፣ የሆነውን ለማመንም እንቸገራለን። ድንጋጤ፤ ሐዘንተኛው በደረሰበት
እጦት ስሜቱ ሳይታሰብ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን የሚጠበቅበት መንገድ ሲሆን፤
ከሁለት እስከ ሦስት ወራት አብሮ ሊዘልቅ ይችላል። በተጨማሪ በተለመዱት የዕለት
ከዕለት ተግባራት ሳይቀር በሞት ስለ ተለየው ሰው ዘወትር ማሰብና ማውራት
የተለመደ ነው። ይህ ሁናቴ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
የሚወደውን በሞት የተነጠቀው ግለሰብ ቀስ በቀስ እውነታውን ወደ መቀበል
እስኪደርስ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትና ድባቴ ያልተለየው የሐዘን ደረጃዎች ውስጥ
ያልፋል። እነዚህ የሐዘን ደረጃዎች በግለሰቡ ላይ የተለያዩ ስሜቶች እንዲፈጠሩ
ስለሚያደርጉ--ቁጠኛ፣ ብስጩ፣ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማው፣ ሐዘንተኛነትና
ስጉነት ይፈራረቁበታል።
አንድ ሰው የሚወደውን በሞት ሲነጠቅ የሚከሰተው
የሐዘንተኝነት ስሜት ዓላማ በውስጡ ያለውን ህመም ወይም ያጣውን ሰው
ትውስታዎች በሙሉ ጠራርጎ ማስወገድ አይደለም። ወደ መጨረሻዎቹ የማገገሚያ
ደረጃዎች ሲደረስ ግለሰቡ በየቀኑ እንቅስቃሴው ነገሮችን እንደገና የመጀመርና
የመታደስ ፍላጎት እያደረበት በመምጣት ዕለት በዕለት መደበኛ እንቅስቃሴ ውስጥ
መግባት ይጀምራል።
ከሚከተሉት ጥቅሶች ምን ዓይነት አጽናኝ ሀሳቦች ያገኛሉ? ሮሜ.
8:31–39፣ ራእ. 21:4፣ 1ቆሮ. 15:52–57።
፡ ብዙዎች በሱስ ምክንያት ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል።
የምኞታቸው ባሮች በመሆን ገንዘባቸውን፣ ሥራቸውን፣ ጤናቸውንና ነፃነታቸውን
አጥተዋል። ነገር ግን እነሆ የሱስ በኃጢአታችንና በክፉ ምኞታችን ላይ ነፃነት ሊሰጠን
መጣ “‘ እንግዲህ ወልድ ነፃ ካወጣችሁ፣ በእውነት ነጻ ትሆናላችሁ’ ” (ዮሐ. 8:36)።
በተጨማሪ የሱስ ዘወትር እንደማይለየን ቃል ስለገባልን (ማቴ. 28፡20፣ ኢሳ. 43፡2)
በዚህ ውጊያ ብቻችንን አንዘምትም። በእርግጥ ውጊያው የጌታ መሆኑን ለአፍታም
መዘንጋት የለብንም (1ሳሙ. 17፡47)።
ድል እንደሚቀናንም የተስፋ ቃል ሰጥቶናል
(1ጴጥ. 1፡3-9)። ዛሬ በየትኛውም አደገኛ ሱስ ላይ አሸናፊ በሚያደርጎት የድል ጎዳና
ላይ መራመድ በመጀመር የተመኙት ነፃነት ባለቤት መሆን ይችላሉ። በእርግጥ
እንዲህ ሲባል ከፊትዎ ብርቱ ትግል፤ ከዚያም አልፎ መውደቅ ሊኖር አይችልም
ማለት አይደለም። ጌታ ሁሌም በእርስዎ ተስፋ የማይቆርጥ አምላክ መሆኑ መልካም
የምሥራች ነው። ከዚህ በተጨማሪ የባለሙያ እርዳታ መፈለግ በራሱ ምንም ችግር
የለውም። የጤና እክል ሲገጥሞ ጌታ በሕክምና ባለሙያዎች አማካይነት በጎነቱን
ሊገልጽልዎ እንደሚችል ሁሉ፤ ከሱስ ጋር ለተያያዘም ችግር በተመሳሳይ የሥነ ልቡና
የሕክምና ባለሙያዎችን ተጠቅሞ ሊፈውሶ ይችላል።
“አስቸጋሪ ሁኔታዎችና መከራ ሲከብበን እኛን ለማዳን ኃያል የሆነውን አምላክ
እርዳታ በልበ ሙሉነት እየተጠባበቅን ፈጥነን ወደ እርሱ ልንሸሸግ ይገባል። ልንቀበል
የምንችለውን አምላካዊ በረከት ከመጠየቅ ወደ ኋላ አንበል። ጸሎት ማድረግ
ኃላፊነታችን ቢሆንም፤ ምስጋና ከማቅረብ ችላ እንል ይሆን? የአያሌ በረከቶች
ባለቤት ላደረገን አምላክ አብልጠን ምስጋና ማቅረብ የለብንምን? አመስጋኝነትን
ማልማት ብሎም መንከባከብ ከእኛ ይጠበቃል።
በሐዘንና መከራ ውስጥ ለማለፍ
ብንገደድ እንኳ ዘወትር ስለ አምላካዊው በጎነት ልናሰላስል፣ ምህረቱን ልንቆጥርና
ቅዱስ ስሙን ልናወድስ ይገባል።”—Ellen G. White, Selected Messages, book
2, p. 268.
፡
1.አመኔታ በጎደለበት ሁናቴ የተሰበረውን ግንኙነት በመጠገኑ ረገድ
ይቅር ባይነት ምን ዓይነት ፋይዳ ይኖረዋል? ማቴ. 6:12–15፣ 18:2122። “ፍቅር… በደልን አይቆጥርም” (1ቆሮ. 13፡5)።
2.በሐዘንና መከራ ውስጥ ስናልፍ ስለ እግዚአብሔር ምህረት
ማሰላሰላችንና ደጋግመን ማውራታችን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው?
3.ከማንኛውም ዓይነት እጦት ጋር እየታገሉ ለሚገኙ ወገኖች
ቤተክርስቲያናዊው ቤተሰብ ባጠቃላይ እገዛ ሊያደርግ የሚችልባቸው
ተጨባጭ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?