ትንቢተ ዳንኤል
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 1ኛ ሩብ ዓመት 2020

ከየካቲት 28 - መጋቢት 4

11ኛ ትምህርት

Mar 07 - Mar 13




ከጦርነት ወደ ድል



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኤፌሶን 6፡-12፣ ዳንኤል 10፣ ዕዝራ 4፡-1-5፣ ኢያሱ 5፡-13-15፣ ራዕይ 1፡-12-18፣ ቆላስያስ 2፡-15፣ ሮሜ 8፡- 37-39


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ”እርሱም፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፥ አትፍራ ሰላም ለአንተ ይሁን በርታ፥ ጽና አለኝ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና። አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ። “ (ዳንኤል 10፡-19)

ዳ ንኤል 10 በዳንኤል 11 እና 12 የሚቀጥለውን የዳንኤልን ራዕይ ማጠቃለያ ያስተዋውቃል። ከመጀመሪያው ይህ ራዕይ ስለ ‹‹ታላቅ ተጋድሎ›› ትኩረት እንደሚያደረግ መረጃ ተሰጥቶናል (ዳንኤል 10፡-1)። ዳንኤል 11 ስለዚህ ጦርነት ዝርዝር መረጃን ሲፈነጥቅ፣ ዳንኤል መንፈሳዊው ጎኑን ሲያሳይ ፣ በምድር የተባባሱ ጦርነቶች ጀርባ የፈለካዊ ክፍል ያለውን የመንፈሳዊ ጦርነትን ያሳያል። ይህን ምዕራፍ ስናጠና፣ ስንጸልይ ሳል ጥልቀት ባለው መልኩ በፈለካዊ ጦርነት ውስጥ እንደምንያዝ እናያለን። ነገር ግን በትግላችን ውስጥ ብቻችንን አይደለንም፣ ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ከሰይጣን ጋር ይዋጋል። የገባንበት የመጨረሻው ጦርነት ከምድራዊ ሐያላት ጋር ሳይሆን ከጨለማው ኃይል ጋር መሆኑን እንመለከታለን።

ከዳንኤል ከብዙ ዘመናት በኋላ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዳስቀመጠው ‹‹መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ›› (ኤፌሶን 6፡- 12) በመጨረሻም በጦርነቱ ያለው ስኬታችን ብቻውን ሰይጣንን በመስቀሉ ላይ ባሸነፈው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያርፋል። የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለመጋቢት 5 ሰንበት ይዘጋጁ።

የካቲት 29
Mar 08

ጾም እና ጸሎት ደግሞ እንደገና


ዳንኤል ለተራዘመውም የለቅሶው ጊዜ ምክንያትን አልዘረዘረም። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ልብን የሚነካ ምልጃ ከባቢሎን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደተመለሱ በነበረው የአይሁድ ሁኔታ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። ዕዝራ 4፡-1-5ን ያንብቡ። አይሁዶች በመመለሳቸው ምን አይነት ተግዳሮት ነበር ያጋጠማቸው?



ከዕዝራ 4፡-1-5 ላይ አይሁዶች መቅደሱን እንደገና ለመገንባት ባደረጉት ጥረት ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠማቸው እናውቃለን። ሰማሪያውያን ወደ ፋርሱ ንጉስ፣ ግንባታቸውን እንዲያቆሙ የተሳሳተ መረጃን ልከዋል። በእንደዚህ ያለ ውድቀት ዳንኤል ለሶስት ሳምንት ያህል እግዚአብሔር በቂሮስ ላይ ተጽዕኖ አድርጎ ስራው እንዲቀጥል ተማጽኗል። እናም ከእግዚአብሔር የጸሎትን መልስ ከመቀበሉ በፊት ዳንኤል ለሶስት ሳምንት በጸሎቱ ገፍቷል። በዚህ ጊዜ ነብዩ ከአመጋገቡ ተቆጥቦ ነበር፣ ከተመረጡ ምግቦች ታቅቦ እና ሰውነቱን ከመቀባትም እንዲሁ ተአቅቦ አድርጎ ነበር። ስለ እራሱ ምቾት እና እፎይታ ሙሉ ለሙሉ ግድ አልነበረውም ፣ ነገር ግን በብዙ ሺ ማይሎች ስለሚርቁት አይሁዶች ጦርነት ነበር በጥልቀት ይጨነቅ የነበረው።

የዳንኤል የጸሎት ሕይወት ስንመለከት በጣም ጠቃሚ የሚሆኑ ነጥቦችን እንማራለን። አንደኛ ፣ በጸሎት፣ ልመናችን ወዲያው ባይመለሰም እንኳን መበርታት/መጽናት አለብን። ሁለተኛ፣ ለሌሎች ለመጸለይ ሰዓትን መመደብ አለብን። ስለ ምልጃ ጸሎት የተለየ ነገር አለ። ‹‹ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው።›› (ኢዮብ 42፡10) የሚለውን አስታውሱ። ሶስተኛ ፣ ጸሎት እግዚአብሔርን እውነተኛ እና መሰረታዊ የሆነን ነገር እንዲያደርግ ያደርገዋል። ስለዚህ ሁልጊዜ ሁሉን አይነት ጸሎቶችን ልንጸልይ ይገባል። ለሸክም በማይቻሉ መከራዎች፣ ትልልቅ ችግሮች እና ስብርብር በሚያደርጉ ተግዳሮቶች ሸክማችንን በጸሎት ለእግዚአብሔር እናምጣ ።

ዳንኤል 10፡-12ን ያንብቡ። ይህ ስለ ጸሎት፣ ስለ እግዚአብሔር ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ የግል ልምምድ ከሚሆን ይልቅ እግዚአብሔርን የሆነ ነገር እንዲሰራ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ በሆነ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያለ ልምምድ እንደሆነ ምንድን ነው የሚያስተምረን?

የካቲት 30
Mar 09

ራዕይ-ስለ ልዑሉ


ዳንኤል 10፡-4-9ን ያንብቡ። በዚህ ስፍራ በዳንኤል ላይ ምን ሆነ?



ዳንኤል ልምምዱን ሲገልጽ፣ እያየ ያለውን የበዛ ውበትን በደንብ ማሰብ እንችላለን። ሰው የሚመስለው (ዳንኤል 10፡-5፣6) ወደ ኋላ ሔደን ስናስብ በሰማዩ ችሎት (ዳንኤል 7፡-13) ላይ የተከሰተውን ‹‹የሰውን ልጅ ›› ይመስለዋል። የለበሰው የበፍታ ልብስ የክህነት ልብስን ይመስላል(ዘለዋውያን 16፡-4)፣ ይህ ደግሞ ይህን ሰው ከሰማያዊ ቤተመቅደስ(ዳንኤል 8) ‹‹የልዑል ቅዱሳን ››ጋራ ያያይዘዋል። እንዲሁ ወርቅም ከካህን ልብስ ጋር እንደ ባለሟልነት መለያ በመሆን ያገለግላል። በመጨረሻ ከዚህ ምስል ደግሞ የሚስበው ብርሃኑ፣ እሳቱ፣ ብሩ፣ እና ሐይለኛው ድምጹ የሚገልጸው ይህ ፍጥረት አምላካዊ ባህሪ እንዳለው ነው።

ይህ ሰው ካህናዊ፣ ንጉሳዊ እና የወታደራዊ ባህሪያትን የተላበሰ ነው። ይህ ምስል ለአጭር ጊዜ እነ ኢያሱ ወደ እያሪኮ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ለኢያሱ ከተገለጸለት አካል ጋራ የሚገርም መመሳሰልን ያሳያል(ኢያሱ 5፡-13፣14)። ኢያሱ በራዕይ የ ‹‹የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ›› ነበር ያየው። በሚገርም ሁኔታ በዕብራይስጡ ‹‹አለቃ›› (ሳር) የሚለው ቃል በዳንኤል 10፡-21 ላይ ሚካኤልን ለመግለጽ የተጠቀመበት ቃል ጋር አንድ አይነት ነው። ነገር ግን በጣም ተቀራራቢ መመሳሰል በዳንኤል እና በኢያሱ ተከስቷል። በዳንኤል 10 ላይ ባለው የዳንኤል ራዕይ ፣ በኢያሱ 5፡-13-15 እና ራዕ 1፡-12-18 መካከል ምን አይነት መመሳሰሎችን እናገኛለን?



እንደ ዳንኤል ከእርሱ ጋር የነበሩት እጅግ ፈሩ፣ እንዲሁም ዳንኤል እራሱ ተዝለፈለፈ እና በመሬት ላይ ወደቀ። የእግዚአብሔር መገለጥ በቀላሉ አደቀቀው። ቢሆንም ግን ምንም ፍርሃት ቢኖርም የዳንኤል ራዕይ እግዚአብሔር የአለምን ታሪክ እንደሚቆጣጠር ያሳየናል። በእርግጥ ራዕዩ እንሚገለጸው፣ እግዚአብሔር የሰብአዊ ዘርን ታሪክ ዋና ዋና ነጥቦችን ከነብዩ ጊዜ ጀምሮ እስከ የእግዚአብሔር መንግስት ምስረታ ድረስ ለዳንኤል እንደሰጠው እናያለን (ዳንኤል 11 እና 12)። በዳንኤል ደግመን ደጋግመን እንደተመለከትነው እግዚአብሔር የአለምን ታሪክ ከተቆጣጠረ በእኛ ግላዊ ሕይወትስ ምን ማድረግ ይችላል?

መጋቢት 01
Mar 10

በመልአኩ መነካት


ዳንኤል 10፡-10-19ን ያንብቡ። መልአኩ ዳንኤልን በነካው ቁጥር ምን ይሆን ነበር?



በመለኮት ብርሃን ነጸብራቅ ምክንያት ነብዩ ዳንኤል ወደቀ። ከዚያም መልአኩ መጣና ነካው እና አጽናናው። ትረካውን ስናነብ መልአኩ ዳንኤልን ሶስት ጊዜ እንደነካው እንመለከታለን። የመጀመሪያው መንካት ነብዩን እንዲቆም እና ከሰማይ የሚመጣውን ማጽናኛ ቃል እንዲሰማ አደረገው። ‹‹እርሱም እንዲህ አለኝ። ዳንኤል ሆይ፥ አትፍራ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።››(ዳንኤል 10፡-12)። የዳንኤል ጸሎት ሰማይን አንቀሳቅሶ ነበር። ለእኛ ይህ እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደሚሰማ ያረጋግጥልናል ይህ ደግሞ በመከራ ጊዜ ታላቅ መጽናኛ ነው።

የሁለተኛ መንካቱ ዳንኤልን እንዲናገር አስቻለው። ነብዩ በጌታ ፊት ቃላቶቹን ማውጣት እና ፍርሃቱን እና ስሜቱን መግለጽ ቻለ። ‹‹እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ በፊቴም ቆሞ የነበረውን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።ይህ የጌታዬ ባሪያ ከዚህ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል? አሁንም ኃይል አጣሁ፥ እስትንፋስም አልቀረልኝም አልሁት። ››(ዳንኤለ 10፡16-17)። ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ መናገር ብቻ አይደለም አንደበታችን እንዲከፈት እና ስለ ስሜታችን ፣ ፍላጎታችን እና ተስፋችን መናገር እንችል ዘንድ ይፈልጋል።

ሶስተኛው መንካት ኃይልን አመጣለት። ዳንኤል ብቁ እንዳልሆነ ሲገነዘብ መልአኩ ነካው እና በእግዚአብሔር ሠላም አጽናናው። ‹‹እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፥ አትፍራ ሰላም ለአንተ ይሁን በርታ፥ ጽና አለኝ። ›› (ዳንኤል 10፡-19)። አስታውሱ መልአኩ ወደ ዳንኤል የተላከው፣ መረጃን እና ማስተዋልን ለመስጠት፣ ለጸሎቱ ምላሽ ነው። በሌላ አባባል፣ በዳንኤል 11 የሚመጣው ራዕይ ስለ እየሩሳሌም ወቅታዊ ሁኔታ የዳንኤልን ሐዘን እና ጸሎት ተከትሎ ዳንኤልን ለማበረታታት ነበር። እግዚአብሔር በእኛ በኩል ሆኖ ሠላም ሊኖረን ይችላል፣ ምንም እንኳን ጥቃትን ብንጋፈጥም። የፍቅር መንካቱ የወደፊቱን በተስፋ እንመለከት ዘንድ ያስችለናል።

“ለእኛ በተለመደው የሕይወት እርምጃ ፣ ምን አልባት ሰማይ በጣም ቅርብ ነው” (ኤለን ጂ. ኋይት ፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 48)። ምን ያህል ጊዜ ነው ሰማይ እና ምድር በቅርበት ስለመተሳሰራቸው የሚያስታውሱት? ይህ እውነታ በአእምሮአችሁ እና በልባችሁ ሁልጊዜ ብትጠብቁት ምን ያህል አኗኗራችሁ የተለየ ይሆናል?

መጋቢት 02
Mar 11

ታላቅ ተጋድሎ


ዳንኤል 10፡-20፣21ን ያንብቡ። በዚህ ለዳንኤል የተገለጸው ምንድን ነው?



ሠማያዊው መልዕክተኛ መጋረጃውን ገለጠ እና ለዳንኤል ከሰብአዊያን ታሪክ ጀርባ የሚካሔደውን የአለማት ጦርነት ገለጸለት። ዳንኤል መጸለይ ሲጀምር፣ በሰማይ እና በምድር መንፈሳዊው ጦርነት ተጀመረ። ሰማያዊ ፍጥረታት ከ ፋርስ ንጉስ ጋር፣ አይሁዳውያን ቤተ መቅደሱን መገንባታቸውን እንዲቀጥሉ ፣ ውጊያን ጀመሩ። ዳንኤል 10ን ከከፈትንበት ጀምሮ የፋርስን ንጉስ ቂሮስን እናውቀዋለን። ቢሆንም ግን የሰው ንጉስ ብቻውን ከሰማይ ፍጥረታት ጋር ሊዋጋ አይችልም። ይህ ከሰብአዊው ንጉስ ጀርባ የመንፈሳዊ ወኪል ቂሮስን በመገፋፋት አይሁዳውያን ቤተ መቅደሱን እንዳይገነቡ እንዲያስቆም እያደረገ እንዳለ ይጠቁማል።

በሕዝቅኤል 28 ላይ ፣ የጢሮስ ንጉስ ሰይጣንን ወክሎ የመናፍስታዊው ኃይል ከከተማዋ ሰብአዊ ንጉስ ጀርባ የሆነበት ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷል። ስለዚህ ሚካኤል ሊዋጋው የመጣው የፋርስ ንጉስ ከኋላው ሳይጣንን እና መላእክቱን ማሰለፉ አያስገርምም። ይህ መቅደሱ በእየሩሳሌም እንዳይገነባ ከነበረው የሰዎች ተቃውሞ መንፈሳዊ ተነጻጻሪነት ነበረው። ዳንኤል 10፡-13ን ያንብቡ። በዚህ የተገለጸው የጦርነት አይነት፣ ምን አይነት ነው?



‹‹ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለውን መልካም ያልሆነ አስተሳሰብ ሠይጣን ለማሳየት በምድር ላይ የነበረውን ኃያል መንግስት፣ የሜዶን እና ፋርስ ንጉስን ለመጠቀም ተጽዕኖውን በቻለው መጠን ሲያደርግ ሳል፣ መላእክት ደግሞ በዳንኤል በኩል በግዞት ስላሉት ሠሩ ። ሰማይ ሁሉ ያተኮረበት ግጭት አንድ ነው። በመልካም እና በክፉ ኃይል መካከል የነበረውን የመጨረሻ ትግል ፣ በነብዩ ዳንኤል በኩል ትንሽ ብልጭታው ተገልጾልናል። ለሶስት ሳምንት ገብርኤል ከጨለማው ኃይል ጋር ታገለ፣ በቂሮስ አእምሮ ውስጥ ተጽዕኖን ለማድረግ ከሚታገለው ኃይል በተጻራሪ ታገለ፣ እናም ሁኔታው ሳይጠናቀቅ ክርስቶስ እራሱ በገብርኤል በኩል መጣ።

‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ ›› በማለት ገብርኤል እራሱ ተናገረ፤ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ›› (ዳንኤል 10፡-13)። በእግዚአብሔር ሕዝብ በኩል ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ ሰማይ አደረገ። በመጨረሻ ድሉ ተገኘ፣ የጠላት ኃይል የቂሮስን ዘመን እና ሰባት አመት ተኩል የገዛው የልጁ ዘመን ተቆጠረ። -›› (ኤል ጂ. ኋይት፣ ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንገስ ገጽ 571፣572)

መጋቢት 03
Mar 12

አሸናፊ አለቃ


ከመጀመሪያው በዳንኤል መጽሐፍ ጎላ ያለው ገጸ ባህሪ ‹‹የሰው ልጅ›› (ዳንኤል 7፡ -13) የተባለው ወይም ‹‹የሠራዊት አለቃ›› (ዳንኤል 8፡-11) ነው። በመጨረሻም ይህ ስም ሚካኤል እንደሆነ ተረዳን (ዳንኤል 10፡-12)፣ ያም ማለት ‹‹ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው ?›› ማለት ነው። እርሱም ከፋርስ ንጉስ ጋር በነበረው ግጭት ገብርኤል ለመርዳት መጣ (ዳንኤል 10፡-13) መልአኩ ይህን የሰማይ አካል ‹‹ ሚካኤል አለቃችሁ ›› (ዳንኤል 10፡-21) ሲል ይጠቅሰዋል። ከ ይሁዳ 9 ላይም እንደምንረዳው ከሰይጣን ጋር ታግሎ ሙሴን ያስነሳው ሚካኤል የመላዕክት አለቃ ነው።

ራዕይ 12፡ -7 ሚካኤል የሰማይን ሰራዊት እንደሚመራ ይገልጻል። ስለዚህ ሚካኤል ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም። የፋርስ መንግስት ዋና አዛዥ እንዳለው ሁሉ፣ ከሰብአዊያን መሪ ኋላ የቆመው የመንፈሳዊው ኃይል እንዲሁ በእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ወደ ውጊያው የገባው እና በዓለም አቀፈዊው ጦርነት በእነርሱ ፋንታ ድል ያደረገው ሚካኤል የሰራዊት አዛዣቸው ሆኖ አለ። ቆላስያስ 2፡15ን ያንብቡ። ኢየሱስ እንዴት ነው ዓለም አቀፈዊውን ጦርነቱን በድል ያጠናቀቀው?



የክፉን ሐይላት ስንጋፈጥ በአሸናፊያችን በኢየሱስ እምነትን መያዝ እንችላለን። አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ሰይጣንን አሸንፎታል። በምድራዊው ሕይወቱ በምድረ በዳ በፈተነው ጊዜ አሸንፎታል፣ ከዲያቢሎስ ኃይላት ጋር ተጋጥሟል እናም ከጨለማው ሐይላት ብዙዎችን ነጻ አውጥቷል። ኢየሱስ ከጴጥሮስ በስተኋላ ሆኖ ወደ ቀራኒዮ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያደናቅፍ በሞከረ ጊዜ አሸንፎታል። ለደቀ መዛሙርት በመጨረሻው ቃሉ ፣ ኢየሱስ በቅርብ ስለሚሆነው ሞቱ ድል እንደሆነ ተናግሯቸዋል፣ በሰይጣን ላይ ወሳኝ በሆነ ድል ተደመደመ። ‹‹ አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።

›› (ዮሐንስ 12፡-31፣ 32) አንዳንድ ጊዜ ዙሪያችንን እንመለከታለን እናም ነገሮች በእውነት መጥፎ ሆነው እናያለን። አመጽ፣ የስብዕና መውረድ፣ ሙስና እና በሽታ በየቦታው ተስፋፍቷል። ከስጋና ከደም ያልሆነ ጠላት በጭካኔ ከሁሉም በኩል የጠቃናል። ነገር ግን ምንም ያህል የምንዋጋው ጦርነት ብርቱ ቢሆን ኢየሱስ ለእኛ ይዋጋልናል፣ እንደ አለቃችን እና በሰማያዊው መቅደስ እንዳለ ካህናችን ይቆምልናል። ሮሜ 8፡-37-39ን ያንብቡ። በክርስቲያናዊ ሕይወታችን የአሸናፊነት ቃል ኪዳናችንን እውነተኛ የህይወት ልምምዳችን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

መጋቢት 04
Mar 13


ተጨማሪ ሐሳብ


‹‹ በቂሮስ አእምሮ ውስጥ ተጽዕኖን ለማድረግ ከሚታገለው ኃይል በተጻራሪ ለሶስት ሳምንት ገብርኤል ከጨለማው ኃይል ጋር ታገለ … በእግዚአብሔር ሕዝብ በኩል ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ ሰማይ አደረገ። የጠላት ኃይል የቂሮስን ዘመን እና ሰባት አመት ተኩል የገዛው የልጁ ዘመን ተቆጠረ። በመጨረሻ ድሉ ተገኘ ›› (ኤል ጅ. ኋይት፣ ፕሮፌትስ ኤንድ ኪንገስ ገጽ 572) ‹‹ በሰማይ ሐያላት ምን አይነት አክብሮት ነበር ለዳንኤል የተሰጠው! ከፍርሃቱ አጽናናው እና ጸሎቱ በሰማይ እንደተሰማ አረጋገጠለት። በዚያ ከልብ በሆነ ልመና ምላሽ ገብርኤል የንጉሱን ልብ ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ ተላከ።

ዳንኤል በጾም እና በጸሎት በነበረበት ሶስት ሳምንት ውስጥ ንጉሱ ይህንን ጥያቄ ሲገፋ ቆዬ ነገር ግን የሰማያዊው አለቃ ፣ የመላእክት አለቃ፣ የዳንኤልን ጸሎት ለመመለስ ወሳኝ ውሳኔን እንዲያደርግ ወደ አስቸጋሪው ንጉስ ልብ ተላከ ››(ኤለን ጂ. ኋይት ዘ ሳንቲፋይድ ላይፍ፣ ገጽ 51)


የመወያያ ጥያቄዎች




1.ይህንን እውነት ለማየት በክርስትና ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ባንሆንም ፣ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስትነታችን የ‹‹ታላቁን ተጋድሎ››አላማ ፣ወይም መላው አለም ገብቶበት ባለው በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ባለው ትግል ሐሳብ ጠንካራ ነብያቶች ነን። እናም እንደምናምነው በእርግጥ ሁሉም ሰው በዚህ ተጋድሎ ውስጥ አለበት። ሌሎች የማያምኑም ሰዎች ሁሉ እንኳን ስለ ገቡበት የሆነ አይነት ትግል ያወራሉ። የእርስዎ የግልዎ ልምምድ ምንድን ነው? በራስዎ ሕይወት እንዴት ነው የሚገለጸው? በትግል ውስጥ ያሉ ሌሎችን ሊረዳ የሚችል ሌላ የተማሩት ምን አለ?

2.ኤፌሶን 6፡-10-18ን ያንብቡ። ጳውሎስ የተጠቀመበትን ግልጽ የሆነ ወታደራዊ ስዕልን አስተውሉ። ለታላቁ ተጋድሎ ምን ‹‹የውጊያ መመሪያ›› ነው በዚህ ስፍራ የተሰጠው?

3.በዳንኤል 10፡-11 ፣ ለሁለተኛ ጊዜ (ዳንኤል 9፡-23) ዳንኤል ‹ሃሙዱት› ወይም ‹‹ የተወደድክ ›› በማለት ተጠራ። ይህ ስለ ቀረበው ግንኙነት ፣ በሰማይ እና በምድር ስላለ ስለ ስሜታዊ መቀራረብም ምን ይነግረናል? ከዘመናዊው አለም ያለማመን እይታ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ትልቅ ልዩነት እንዳለው አስቡ። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ እይታ፣ ዳንኤልን እንደ ማስረጃ ስንወስደው፣ ምን ተስፋን ያቀርብልናል?