ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። ዳንኤል 8፣ ዳንኤል 2፡-38፣ ዘፍጥርት 11፡4፣ ዘለዋውያን 16፣ ዕብራውያን 9፡23-28
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- ”እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።“( ዳንኤል 8፡-14)
በ
ዳንኤል 8 ላይ ያለው ራዕይ ለነብዩ የተሰጠው በ 548/547 ዓ፣ም ነው:: እናም
ዳንኤል 7 ላይ ለተሰጠው ፍርድ ወሳኝ ማብራሪያ ይሰጣል። እንደ ዳንኤል 2 እና
7 ሳይሆን የዳንኤል 8 ራዕይ ባቢሎንን ይተው እና የሚጀምረው ከ ሜዶ ፋርስ ነው፣
ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ባቢሎን እያሽቆለቆለ እና ፋርሳውያን ባቢሎንን በመተካት
እና ቀጣዩ የአለም ኃያል መንግስት እየሆኑ ነበር። የዳንኤል 8 ራዕይ ከ ዳንኤል 7 ራዕይ
ጋር ይስተያያል። ቋንቋው እና ምስሎቹ በዳንኤል 8 ላይ ተቀይረዋል፣ ምክንያቱም
ከሰማያዊው የስርዬት ቀን ጋር ተያይዞ ስለ ቤተ- መቅደሱ መንጻት ቀጥተኛ ትኩረትን
ይሰጣል። ስለዚህ የዳንኤል 8 የተለየ ትኩረት አስተዋጽኦ የሚያርፈው የሰማያዊው
ቤተ-መቅደስ ላይ ነው።
ዳንኤለ 7 ግን የሚያሳየው የሰማዩን ትዕይንት እና የሰው ልጅ
መንግስትን ሲቀበል ሲሆን፣ ዳንኤል 8 ደግሞ የሰማያዊው ቤተ-መቅደስን መንጻት
ያሳያል። እናም በእነዚህ ሁለት ምዕራፎች ያለው ንጽጽር የሚጠቁመው የሰማያዊው
ቤተ-መቅደስ መንጻት በዳንኤል 8፣ ከ ዳንኤል 7 የፍርድ ትዕይንት ጋር ነው።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ የካቲት 06 ሰንበት በማጥናት ይዘጋጁ።
ዳንኤል 8ን ያንብቡ። ይህ ራዕይ አጠቃላይ ስለ ምንድን ነው የሚናገረው በዳንኤል 2 እና 7 ካየነው ጋራ እንዴት ነው የሚስተያየው?
ልክ በዳንኤል 2 እና 7 ላይ እንደተሰጠው፣ በዚህ ደግሞ ምንም እንኳን በተለየ
ምስል ቢሆንም የአለም መንግስት መነሳትን እና መውደቅን በተመለከተ ሌላ ራዕይ
ተሰጥቷል። ይህ ምስልን መጠቀም በቀጥታ ከእግዚአብሔር መቅደስ ጋራ ይገናኛል።
በዚህ ላይ ከስርዓት ቀን የመቅደሱ ስርዓት፣ በጥንቱ እስራኤል ጊዜ የነበረው የመንጻት
ስርዓት ጋራ በተያያዘ ምክንያት የአውራ በግ እና የፍየልን ምስል ተጠቅሟል። በቤተመቅደሱ አገልግሎት አውራ በግ እና ፍየል ለመስዋዕት አገልግሎት ይውላሉ። ነገር
ግን ሁለቱ አንድ ላይ የተጠቀሱት በስርየት ቀን ብቻ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ
እንስሶች በዚህ የተጠቀሱት የስርዓትን ቀን፣ የራዕዩ ዋና ትኩረት ነው፣ አስከትሎ
በደንብ ታስቦበት ነው ።
ራዕይው ሲገለጥ ፣ ዳንኤል ያየው አውራው በግ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጎሽም
ነው። ወደ ምዕራብ ፣ ሰሜን እና ደቡብ አቅጣጫ (ዳንኤል 8፡-4)። እነዚህ የሶስትዮሽ
እንቅስቃሴዎች የሚጠቁሙት የዚህ ኃይልን መስፋፋት ነው። ‹‹አውራውም በግ
ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ አራዊትም ሁሉ
ይቋቋሙት ዘንድ አልቻሉም፥ ከእጁም የሚያድን አልነበረም እንደ ፈቃዱም አደረገ፥
ራሱንም ታላቅ አደረገ።›› ( ዳንኤል 8፡-4)። መልአኩ እንደገለጸው፣ ባለ ሁለት ቀንዱ
አውራ በግ የሚወክለው የሜዶን እና የፋርስን መንግስት ነው (ዳንኤለ 8፡-20) ፣
ሶስቱ አቅጣጫዎች በቀጥታ የሚያሳዩት የዚህ አለም አቀፋዊ ኃይል ሶስት ድሎችን
ነው።
በመቀጠል፣ አንድ ፍየል ከትልቅ ቀንድ ጋር ብቅ ይላል፣ የሚወክለውም በታላቁ
እስክንድር ይመራ የነበረውን የግሪክን መንግስት ነው (ዳንኤል 8፡-21)። ፍየሉ
‹‹ ምድርን ሳይነካ ›› ተንቀሳቀሰ የሚለው፣ የሚያሳየው እንቅስቃሴው ፈጣን
እንደሆነ ነው (ዳንኤል 8፡-5)። ይህ በዳንኤል 7 ላይ በክንፎች የተመሰለው
ምሳሌ የሚያመላክተው የእስክንድርን ፈጣን ድሎች ነው። ነገር ግን ፣ ትንቢቱ
እንደሚያሳየው ፍየሉ ጠንካራ እየሆነ ሲሔድ ቀንዱ ይሰበራል (ዳንኤል 8፡-8)። እና
ለአራት ቀንዶች ቦታን ይለቃል፣ አቅጣጫ ጠቋሚውን ወደ አራትዮሽ ይወስደዋል።
ይህ እስክንድር ባቢሎን ላይ በ 323ቅ.ዓ በ33 አመቱ በሞተ እና መንግስቱ ለአራቱ
ጀነራሎቹ በተከፋፈለ ጊዜ ተፈጽሟል።
ከዳንኤል 2፡38 እና ዳንኤል 8፡-20፣ 21 በራዕይው ከተጠቀሱት አራት መንግስታት
ሶስቱ ስማቸው ተገልጾልናል። ይህ አስገራሚ እውነት የዚህን ትንቢት ፍች
ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዴት ነው የሚረዳን?
ዳንኤል 8፡-8-12ን በጥንቃቄ ያንብቡ። ወደ የት አቅጣጫ ነው ይህ ትንሽ ቀንድ የተንቀሳቀሰው፣ እናም ይህን ማስተዋል ለምንድነው አስፈላጊ የሚሆነው?
አራት ቀንዶች ወደ ሰማይ አራቱ ነፋሳት ከተበተኑ በኋላ ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል
ከአንዱ አንድ ትንሽ ቀንድ ወጣ ይላል። እዚህ ላይ ጥያቄው ይህ ቀንድ ወይም ኃይል፣
ከአራቱ መካከል ከአንዱ ቀንድ የመጣው፣ ትላንት እንደተመለከትነው የሚወክለው
አራቱን የእስክንድርን ጀነራሎች ነው ወይንስ ከአራቱ ነፋሳት አንዱን የሚወክል
ነው። ይህ ክፍል ከተጻፈበት የመጀመሪያው ቅጅ ላይ ባለው የሰዋሰው አቀማመጥ
ይህ ቀንድ የመጣው ከአራቱ ከአንዱ የሰማይ ነፋሳት ነው።
ይህ ኃይል ከግሪክ
መንግስት እና ከአራቱ አፈንጋጮች በኋላ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጋራ መግባባት ይህ
ቀንድ ሮም ነው ማለት ይቻላል፣ መጀመሪያ አረመኔያዊው ኋለም ጳጳሳዊው። ‹‹ ይህ
ትንሽ ቀንድ የሚወክለው ሮምን በሁለም ምዕራፍ ፣ በአረመኔያዊው እና በጳጳሳዊው
ነው። ዳንኤል መጀመሪያ ያየው አረመኔያዊውን ምዕራፍ ነው፣ መንግስታዊ ጊዜ ፣
የአይሁድን ሕዝብና ክርስቲኖችን ሲያስፈራራ የነበረበት። ከዚያ ደግሞ የጳጳሳዊው
ምዕራፍ ክፍል እኛ እስካለንበት የቀጠለው እና ገና ወደፊትም የሚቀጥለውን ምዕራፍ
ነው ያየው። ›› ( የሰቨንዝ ደይ አድቬንቲስት ባይብል ኮሜንተሪ፣ ቅጽ 4፣ ገጽ 841)
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ትንሹ ቀንድ መጀመሪያ ያደረገው እንቅስቃሴ አግድም
ነበር ‹‹ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ
ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።›› (ዳንኤል 8፡-9)። እነዚህ
ሶስት አቅጣጫዎች የሚያርፉት በሶስት ዋና ዋና የአረመኔያዊው ሮም ግዛት ውስጥ
ነው።
ትንሹ ቀንድ የራዕዩ ዋና ተዋናይ ሲሆን ወደላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ዘርዘር
ያለ ትኩረትን መሳብ ይጀምራል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ትንሹ ቀንድ ከዳንኤል 7
ጋር በሚቀራብ መልኩ ይሔዳል፣ የሚከተሉት ማነጻጸሪያዎች እንሚያሳዩት፡- (1)
ሁለቱም ቀንዶች ሲጀምሩ ትንሽ ናቸው(ዳንኤል 7፡-8፣ ዳንኤል 8፡-9 )። (2)
ኋላ ላይ ሁለቱም ታላቅ ሆነዋል (ዳንኤል 7፡-20፣ ዳንኤል 8፡-9 )። (3) ሁለቱም
የመግደል ሐይል አላቸው(ዳንኤል 7፡-21፣ 25፣ ዳን ኤል 8፡-10፣24 )። (4) ሁለቱም
እራሳቸውን ከፍ ክፍ የሚያደርጉ እና ትዕቢተኞች ናቸው(ዳንኤል 7፡-8፣ 20፣
25፣ ዳንኤል 8፡-10፣ 11፣ 25)። (5) ሁለቱም ኢላማቸው የእግዚአብሔር ሕዝቦች
ናቸው(ዳንኤል 7፡-25፣ ዳንኤል 8፡-24)። (6) ሁለቱም ከእንቅስቃሴያቸው ጋር
ተያይዞ በትንቢታዊ ጊዜ የተከለሉ ናቸው (ዳንኤል 7፡-25፣ ዳንኤል 8፡-13፣14)።
(7) ሁለቱም እስከ መጨረሻው ዘመን ድረስ ይዘልቃሉ( ዳንኤለ 7፡-25፣ 26፣
ዳንኤል 8፡:-17፣19)። (8) ሁለቱም በአምላካዊ ኃይል ይጠፋሉ (ዳንኤል 7፡-11፣26፣
ዳንኤል 8፡25)። በመጨረሻ በዳንኤል 7 ላይ ያለው ትንሽ ቀንድ ጳጳሱን በመወከሉ
ምክንያት በዳንኤል 8 ላይ ያለው ትንሽ ቀንድ ወደ ላይ ከሚያደርገው መስፋፋት
ጋር ተያይዞ አንድ አይነት ሐይልን መወከል አለባቸው። ስለዚህ እንደ ዳንኤል 2 እና
7 የመጨረሻው ዋና ኃይል ሮም ነው፣ በአረመኔያዊው እና በጳጳሳዊው ምዕራፉ ሮም
ነው።
ዳንኤል 8፡-10-12ን ያንብቡ። ትንሹ ቀንድ ምን አይነት እንቅስቃሴን ነው በዚህ የሚያሳየው?
በዳንኤል 8፡-10፣ ትንሹ ቀንድ ፣ በመንፈሳዊ ደረጃ፣ የባቢሎንን ግንብ ገንቢዎችን
(ዘፍጥረት 11፡-4) ጥረት ለማባዛት/ከፍ ለማድረግ ይሞክራል። በብሉይ ኪዳን
‹‹ሠራዊት›› እና ‹‹ከዋክብት›› የሚለው ስያሜ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ነው።:
እስራኤል የጌታ ሠራዊት ተብሎ ተሰይሟል( ዘጸአት 12፡-41) ። ዳንኤልም እንዲሁ
የእግዚአብሔር ታማኞች ልክ እንደ ከዋክብት እንደሚያበሩ አይቷል( ዳንኤል 12፡
-3)። ይህ በቀጥታ በሰማይ አካል ላይ የተደረገ ጥቃት አይደለም ቢሆንም ግን
የእግዚአብሔር ሕዝብ ፣ ሐገራቸው በሰማይ የሆነ(ፊሊጵስዩስ 3፡-20) ሰዎች ግድያ
ነው። በአረመኔያዊ ንጉሶች ሺዎች ክርስቲያኖች ቢገደሉም ፣ በዚህ ላይ ትኩረቱ ግን
የትንሹ ቀንድ የወደላይ እንቅስቃሴው ነው። ስለዚህ የትንቢቱ የመጨረሻ ፍጻሜ
የሚያያዘው ከጳጳሳዊው ሮም እና ለአመታት ከፈጸመው ግድያው ጋር ነው።
እንዲሁ ዳንኤል 8፡-11 የሚያወራው ስለ ‹‹መስፍን / የሠራዊት አለቃ››፣ በሌላ ስፍራ
ደግሞ ‹‹እስከ አለቃው መሲህ ›› (ዳንኤል 9፡-25) ፣ ‹‹ከአለቃችሁ ከሚካኤል ››(ዳንኤል
10፡- 21)፣ ‹‹ሚካኤል›› ታላቁ ‹‹አለቃ›› (ዳንኤል 12፡-1) በማለት ይጠቅሰዋል። ሌላ
ማንም ሳይሆን የዚህ አገላለጽ ተጠቃሽ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ
ቀደም ብሎ የተጠቀሰው የ ‹‹ሠራዊት›› አለቃ እና በሰማይ ደግሞ ሊቀ ካህናችን
ነው። ስለዚህ ጳጳሱ እና እርሱ የሚወክለው የሐይማኖት ስርዓት በማደናገር እና
የኢየሱስንም የክህነት ሚና ለመተካት ይሞክራል።
በዳንኤል 8፡-11 ፣ ‹‹የየዕለቱ መስዋዕት›› የሚለው በምድራዊ ቤተመቅደስ የተለያዩ እና
የማይቋረጡ ስርዓቶች ፣ የመስዋዕት እና የምልጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ፣ ጋር የተያያዘ
ነው። በእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ ሐጢያተኞች ይቅር የሚባሉ እና ሐጢያቶች
በመቅደሱ መፍትሔ የሚያገኙበት ነው። ይህ ምድራዊ ስርዓት የሚወክለው
የክርስቶስን ሰማያዊ አገልግሎት ነው። ስለዚህ ትንቢት እንደሚተነብየው ጳጳሳዊው
ስርዓት የክርስቶስን አማላጅነት ወደ ምድራዊ ካህናት አማላጅነት ቀየረው።
በእንደዚህ አይነት ተመሳሳይ አምልኮ ፣ ትንሹ ቀንድ የክርስቶስን የምልጃ አገልግሎት
በመውሰድ፣ ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ የክርስቶስን የመቅደስ ቦታ ናደ።
‹‹ሠራዊቱም ከኃጢአት የተነሣ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ተሰጠው እርሱም እውነትን
ወደ ምድሩ ጣለ፥ አደረገም ተከናወነም።››( ዳንአል 8፡-12)። ኢየሱስ ስለ እራሱ
ሲናገር እውነት እንደሆነ ተናገረ(ዮሐ 14፡-6) ፣ የእግዚአብሔር ቃልም እውነት
እንደሆነ ጠቆመ ( ዮሐንስ 17፡17)። በተጻራሪ፣ ጳጳሱ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ህዝቡ
ቋንቋ እንዳይተረጎም ከለከለ። የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በቤተክርስቲያን ስልጣን
ስር እንዲሆን እና ባህል ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ጎን ለጎን እንደ ዋና የእምነት
መመሪያ ሆኖ እንዲቀመጥ አደረገ።
ይህ ጥናት፣ ከሰብአዊ ባህል/ልማድ ይልቅ ድንቅ እና አስፈላጊ ስለሆነው
የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት፣ ምንድን ነው ሊነግረን የሚገባው?
ዳንኤል 8፡-14ን ያንብቡ። ምንድነው በዚህ የተከሰተው?
ከቀንዱ አውዳሚ ጥቃት በኋላ፣ ቤተ-መቅደሱ እንደሚነጻ ማስታወቂያው ተነገረ።
ይህንን መልዕክት ለማስተዋል፣ በአእምሯችን በዳንኤል 8፡-14 ላይ የተጠቀሰው
የቤተ-መቅደሱ መንጻት በዳንኤል 7፡-9-14 ከታየው የፍርድ ትዕይንት ጋር
እንደሚሔድ ልንይዝ ይገባል። እና ይህ ፍርድ የተካሄደው በሰማይ በመሆኑ
ምክንያት ቤተ መቅደሱም የሚገኘው እንዲሁ በሰማይ ነው ማለት ነው። ስለዚህ
ዳንኤል 7 ከፍትህ አንጻር ፣ በሰብአውያን ጉዳይ ውስጥ እና ከእርሱ ጋር በተያያዘ
እግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት እንዳሳየ ፣ ዳንኤል 8 ደግሞ ተመሳሳዩን ኩነት ከቤተመቅደሱ አንጻር ያሳያል።
ምድራዊው ቤተ-መቅደስ የተቀረጸው ልክ የሰማዩን ቤተ-መቅደስ መስሎ ነው።
እናም የድነትን ዕቅድ ሰፊውን ቅርጽ ለማሳየት ያገለግላል። በየቀኑ ሐጢያተኞች
መስዋዕታቸውን ይዘው ይመጣሉ፣ ሰዎቹ የተናዘዙትን ሐጢያት ይቅር ሲባሉ ያለው
ስሜት ሐጢያቱ ወደ ቤተ መቅደሱ ይተላለፋል የሚል ነው። በዚህም ምክንያት ቤተ
መቅደሱ ይቆሽሻል ። ስለዚህም በላዩ ላይ ያለውን ሐጢያት ለማንጻት በየጊዜው
የመንጻት ሒደት እንዲደረግለት ያስፈልገዋል። ያም ደግሞ የመንጻት ቀን ይባላል።
እናም የሚከናወነው በአመት አንድ ጊዜ ነው(ዘሌዋውያን 16ን ይመልከቱ)።
ለምንድን ነው የሰማያዊው ቤተ መቅደስ መንጻት የሚያስፈልገው? በቀጥታ
ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል ሐጢያታቸውን የሚናዘዙት ሰዎች ሐጢያት ወደ
ሰማያዊው መቅደስ ስለተላለፈ ነው ልንል እንችላለን። ልክ ሐጢያታቸውን የተናዘዙ
እስራኤላውያን ሐጢያታቸው ወደ ምድራዊው ቤተ መቅደስ እንደሚተላፍ ሁሉ
ማለት ነው። በምድራዊው የስርየት ቀን ብዙ ሐጢያተኞች መቆም የሚችሉት በጣም
በርካታ እንስሳትን፣ የወደፊቱን የኢየሱስን መታረድ በማመላከት፣ በመሰዋት ነበር።
እናም ልክ በምድራዊው ቤተ መቅደስ በስርየት ቀን ቤተ መቅደሱ ሲነጻ እንደዚያ
እንደሚሆነው በሰማዩ ታዲያ ምን ያህል ይሆን የሚሰዋው? የክርስቶስ ደም ብቻ ነው
ወደ ፍርድ ይዞን የሚሔደው። በዳንኤል 8፡-14 የተጠቀሰው የቤተ-መቅደሱ መንጻት
በምድር የሚደረገው አገልግሎት ሰማያዊ አምሳያ ነው። መሰረታዊ መልዕክቱ ፣ እንደ
ሐጢያተኛ ሐጢያታችን ይቅር ይባል ዘንድ እና በፍርድ ፊት መቆም እንችል ዘንድ
የመሲሁ ደም ያስፈልገናል።
ዕብራውያን 9፡-23-28ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ፣ ስለ እኛ ሲባል
በተሰዋው በኢየሱስ ስላገኘነው ደህንነት፣ ምንድንው የሚገልጽልን?
ዳንኤል 8፡-13ን ያንብቡ። እዚህ ላይ የተጠየቀው ጥያቄ ምንድን ነው? እንዴትስ ነው በቀጣዩ ቁጥር ላይ ያለውን መልስ እንድናስተውል የሚረዳን?
የ2300 ማታ እና ጠዋት የተመደበው ጊዜ ምንድን ነው ?
አንደኛ፣ ዳንኤል አውራውን በግ እና ፍየሉን ካየ በኋላ፣ የትንሹ ቀንድ ድርጊት
እና በእርሱ የመጣው ጥፋት ይቀጥላል፣ ራዕዩም በ ዳንኤል 8፡-13 ወዳለው ጥያቄ
ይቀየራል። ይህ ጥያቄ ታዲያ በቆይታው ላይ ሳይሆን ፣ በተለይ በትንቢታዊው ጊዜ
መጨረሻ ላይ በሚከሰተው ነገር ላይ ያተኩራል። በተጨማሪ እንደዚህ አይነት ጊዜ
በትንሹ ቀንድ የእንቅስቃሴ ጊዜ ብቻ አይወሰንም፣ ምክንያቱም ራዕዩ የሚለው
አገላለጽ ከ አውራው በግ እስከ ትንሹ ቀንድ ድረስ ያለውን ሁሉንም ያጠቃልላል።
ስለዚህ ይሄ በጣም እረዥምና ትክክለኛ ታሪካዊ ዘመንን ይይዛል። ለጥያቄው ‹‹ራዕዩ
እስከመቼ ይሆናል ›› (አውራው በግ ፣ ሜዶንና ፋርስ፣ ፍየል፣ ግሪክ፣ እና ትንሹ
ቀንድ እና የእርሱ ድርጊት፣ ሮም አረመኔአዊው እና ጳጳሳዊው)፣ ሌላው ሰማያዊ
ፍጡር መለሰ ‹‹እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው ከዚያም በኋላ
መቅደሱ ይነጻል አለኝ። ›› ( ዳንኤል 8፡-14) ። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ይህ
ጊዜ በጣም እረዥም ነው ምክንያቱም የሚጀምረው በሜዶን እና ፋርስ መንግስት
ሆኖ እስከ ግሪክ መንግስት፣ አረመኔአዊው እና ጳጳሳዊው ሮም ጊዜ ይዘልቃል።
ታሪክን መሰረት አርገው ትንቢትን እንደሚተነትኑ (አንደኛ ትምህርት ይመልከቱ
) ይህ ትንቢታዊ ጊዜ አንድ አመት - አንድ ቀን በሚለው መርህ መሰረት መሰላት
ይኖርበታል፣ ያም ማለት 2300 ማታ እና ጠዋት ማለት 2300አመታት እንደማለት
ነው። አለበለዚያ 2300 ቀናት ማለት ከስድስት ወራት ጊዜ እምብዛም አይበልጥ፣ይህ
ሊሆን የማይችል ፣ ለዚያ ራዕይ ኩነቶች ሁሉ በጣም አጭር ጊዜ ነው። ስለዚህ
የአንድ አመት - አንድ ቀን መርህ መተግበር አለበት።
ዳንኤል 8 የዚህን ጊዜ መጀመሪያ እንድናሰላ ምንም አይነት መረጃን አይሰጠንም፣
በእርግጥ መጨረሻውን ያስቀምጣል። ነገር ግን ዳንኤል 9 ወሳኝ የሆነውን መረጃ
ይሰጣል (ቀጣዩን ትምህርት ይመልከቱ)
የ2300 አመት ትንቢት በመጽሐፍ ቅዱስ እረዥሙን አመት ይይዛል፣
አስቡበት 2300 አመታት። በጣም እረዥም ጊዜ፣ በተለይ አሁን
እኛ ከምንኖረው አድሜ ጋር ስናነጻጽረው። ይህ ንጽጽር እንዴት ነው
ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ትዕግስት እና ስለ መጨረሻው ጊዜ ባለን
የእራሳችን ግምት እንታገስ ዘንድ ትምህርት የሚሆነን?
ከዚህ በታች እስካሁን በዳንኤል 2፣7 ፣8 ያየናቸውን
መንግስታት በቅደም ተከተል በስዕላዊ መግለጫ አጠር ተደርጎ ቀርቧል። ይህ ስለ
ቤተመቅደሱ መንጻት ምንድን ነው የሚነግረን?
ዳንኤል 2
ዳንአል 7
ዳንኤል 8
ባቢሎን
ሜዶንና ፋርስ
ባቢሎን
ሜዶንና ፋርስ
------ሜዶንና ፋርስ
ግሪክ
አረመኔአዊው ሮም
ጳጳሳዊው ሮም
------
ግሪክ
አረመኔአዊው ሮም
ጳጳሳዊው ሮም
ፍርድ በሰማይ
ግሪክ
አረመኔአዊው ሮም
ጳጳሳዊው ሮም
የቤተ-መቅደሱ
መንጻት
ዳግም ምጻት(ድንጋይ ዳግም ምጻት(ጻድቃን ዳግም ምጻት (ጥፋት
እጅ ሳይነካት)
መንግስትን ይወርሳሉ) ያለ እጅ)
በዚህ ማየት እንደምንችለው፣ በምዕራፎቹ መካከል ተመሳሳይነት አለ። የተገለጹት
ሕዝቦች ብቻ አይደለም ተመሳሳይነት ያላቸው፣ በዳንኤል 7 ላይ ያለው የፍርድ ትዕይንት
ከ1260አመታት(538ቅ.ዓ-1798ዓ.ም) በኋላ በጳጳሳዊው ሮም፣ በቀጥታ ከ ቤተ-መቅደሱ
መንጻት ፣ እንዲሁም በዳንኤል 8 ላይ ከሮም በኋላ የተነሳው፣ የጋራ ተመሳይነት አለው።
በአጭሩ ይህ በዳንኤል 7 ላይ ያለው ፍርድ ወደ አለም መጨረሻ የሚመራው ፍርድ ፣
በዳንኤል 8 ላይ ካለው የቤተ-መቅደሱ መንጻት ጋር አንድ አይነት ነው። እዚህ ላይ የተሰጡን
ሁለት የተለያዩ ትዕይንቶች ግን አንድ አይነት ነገሮች፣ እና ሁለቱም የተከሰቱት በትንሹ ቀንድ
ሐይል በተዘጋጀው የ1260አመታት ግድያ በኋላ ነው።
1.ከላይ ያለው ስዕላዊ መግለጫ፣ የቤተ መቅደሱ መንጻት፣ በዳንኤል 7
ካለው ፍርድ ጋር አንድ አይነት ነው። የእግዚአብሔር የመጨረሻ መንግስት
ከመመስረቷ በፊት ከ 1260አመታት የትንሹ ቀንድ ትንቢት በኋላ የሆነ ሰአት
ላይ መከሰት እንዳለበት እንዴት ነው የሚያሳየን?
2.የዳንኤል 8 ትንቢት ታሪክን ልክ እንደ ሐይለኛ እና በክፉ የተሞላ አድርጎ
ያቀርበዋል። ሁለቱ እንሰሳዎች፣ የአለም ሁለት መንግስታትን እንደሚወክሉ
፣ እርስ በእርሳቸው ይጣላሉ (ዳንኤል 8፡-8-12)። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ
የዚህችን አለም የስቃይ እውነታለመሸፋን እና ለማለፍ ምንም ሙከራ
አላደረገም ። ይህ በእግዚአብሔር መታመንን እንድንማር እንዴት ነው
የሚረዳን እና በዙሪያችን ካለው ክፉ ይልቅ የእርሱን መልካምነት እንድናይ
እንዴት ነው የሚረዳን?