ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘዳግም 32፡ 45-47፣ ዘፍጥረት 49፡8-12፣ ኢሳያስ 53፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ 15፡ 51-55 እና ሮሜ 12፡2
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። ›› (መዝሙር 119፡105)
መ
ጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፎችን መያዙ፣ በ40 ጸሐፊዎች በሶስት አህጉራት
ውስጥ (ኢስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ) በ 1500 አመታት ውስጥ መጻፉ
የተለየ ያደርገዋል። ቅዱስ እና ሐይማኖታዊ የሆነ እሱን የሚመስል ሌላ መጽሐፍ
የለም። አያስደንቅም! ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ከ24600 በላይ የሆኑ የአዲስ ኪዳን ጽሑፎች ከ ክርስቶስ በኋላ ባሉት አራት ክፍለ
ዘመናት ሊገኙ ችለዋል። ከ ፕላቶ ትክክለኛ ጽሑፎች ሰባት አሉ፣ ከሔሮዱቱስ
ስምንት ፣ እና ከ256 የሚበልጡ ተርፈው የተገኙ ቅጅዎች ደግሞ ከሖሜር አሉ።
ስለዚህ ስለ አዲስ ኪዳን ጠንካራ ፣ የተሳሰረ እና የተረጋገጠ ሐይለኛ መረጃ አለን።
መጽሐፍ ቅዱስ የታወቀ የመጀመሪያው የተተረጎመ መጽሐፍ ነው። በምዕራብ
ማተሚያ ቤቶች የታተመ የመጀመሪው መጽሐፍ ነው። ዛሬ በምድራችን 95 በመቶ
በሚሆነው ሕዝብ ዘንድ የተነበበ እና በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በሰፊው የተሰራጨ
መጽሐፍ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በይዘቱ እና በመልዕክቱም የተለየ ነው፣ ትኩረቱም በታሪክ ውስጥ
እግዚአብሔር ባለው የማዳን እንቅስቃሴ ላይ ነው። ያም ታሪክ የእግዚአብሔርን
ዕቅድ እና ዘለአለማዊውን መንግስት አስቀድሞ እንደመናገሩ ከትንቢት ጋራ የተሳሰረ
ነው። የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ነው፣ ምክንያቱም መጽሐፍቱ የተጻፉበት ያው
መንፈስ (2ኛ ጢሞ 3፡16) አሁን ላሉ አማኞች ቃሉን ሲያጠኑ ሳለ ወደ እውነት ሁሉ
እንዲመራቸው የተሰፋን ቃል ተሰጥቷል (ዮሐ 14፡ 16፣ 17 ፣ ዮሐ 15፡26፣ ዮሐ 16፡
13)።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ መጋቢት 26 ሰንበት በማጥናት ይዘጋጁ።
በሰዎች ንግግር መካከል በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ቃላቶች ብዙ ጊዜ በመጨረሻ የሚነገሩት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ መጽሐፎች ጸሐፊ የሆነው ሙሴ፣ ከመሞቱ በፊት ለሕዝቡ መዝሙርን ዘምሮላቸው ነበር( ዘዳ 31፡ 30-32፣ 43)። ዘዳግም 32፡45-47ን ያንብቡ። ወደ ተስፋይቱ ምድር ዕብራውያኑ ሊገቡ በተቃረቡ ጊዜ ሙሴ በሕይወታቸው ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል እና ሀይሉን እንዴት ነበር የገለጸው?
ከሙሴ የመጨረሻ ንግግር ቃላቶች ውስጥ ጠንካራ የሆነ ልባዊ ምክር ነበረ።
በእርሱ አማካኝነት እግዚአብሔር በተናገራቸው ቃል ላይ ልባቸውን በማሳረፍ፣
ሙሴ ለሕዝቡ አበክሮ ማስተላለፍ የፈለገው ትኩረታቸው በእግዚአብሔር እና
በፈቃዱ ላይ እንዲሆን ነው። እነዚህን ቃላቶች ለልጆቻቸው በማስተማር እያንዳንዱ
ትውልድ የእግዚአብሔርን የድነት ቃልኪዳን እንዲያስተላልፍም ነበር። አስተውሉ
የትኞቹንም ቃላቶች እንዲመርጡ እና እንዲወስዱ ሳይሆን ነገር ግን እንዲያደርጉ
ወይም እንዲጠብቁ ‹‹ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን
እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።›› (ዘዳግም
32፡46) ነው።
በምድር ታሪክ መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር ለቃሉ ታማኝ የሆኑ ህዝቦች ይኖሩታል።
ማለትም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ እና የኢየሱስ እምነት ያላቸው ማለት
ነው። እነዚህ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ታማኞች ናቸው ።የሚያስረግጠው
በምድር ላይ ስለሚኖር የተድላ ህይወት ብቻ አይደለም ነገር ግን ኢየሱስ ባዘጋጀልን
ቤት ውስጥ ስላለው ዘለዘአለማዊ መዳረሻ ነው።
ዮሐንስ 1፡1-5፣ 14፣ ዮሐንስ 16፡6ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ እና ስለ
ዘለአለማዊ ሕይወት ምንድን ነው የሚያስተምሩን? ቃል ስጋ ሆነ የሚለው ቃል
ከመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ እና በመንፈስ መነሳሳት ጋራ የሚያገናኘው ምንድን ነው?
ኢየሱስ የሁሉም ቃል ትኩረት እና አላማ ነው። የእርሱ ስጋ ለብሶ እንደ መሲህ
መምጣት የብሉይ ኪዳን ቃል ፍጻሜን ያሳያል። ምክንያቱም ኖረ፣ ሞተ እናም
እንደገና በህይወት ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ከዚያም
በበለጠ በአዲስ ሁኔታ ስለሚመጣው የዘለአለም ሕይወት ላለው ታላቅ የተስፋ
ቃልም ማረጋገጫ ነው።
ዘዳግም 32፡47 እንደገና ያንብቡ። የእግዚአብሔርን ቃል የመታዘዝ
እውነት ከንቱ ‹‹ለእናንተ ከንቱ አይደለምና›› እንዳልሆነ ለእራስዎ
እንዴት ነው የተለማመዱት? ለምንድን ነው በእግዚአብሔር ማመን እና
ቃሉን መታዘዝ በፍጹም ከንቱ የማይሆነው?
የጸሐፊዎቹ ልዩ ልዩ መሆን፣ የነበሩበት ስፍራ እና ዳራቸው እግዚአብሔር በታሪክ መካካል ግንኙነት እያደረገ እና መልዕክቱን ለህዝቡ በማድረስ ሲሰራ፣ መልዕክቱን ተቀባዮቹ የባህል ብዝሀነት እንዳላቸው መጠን እንደሆነ በጣም ተለየ ምስክርነትን ይሰጣል። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች እና ስለ ማንነታቸው ምን ይነግሩናል? (ዘጸዘት 2፡10፣ አሞጽ 7፡14፣ ኤርሚያስ 11-6፣ ዳንኤል 6፣1-5፣ ማቴዎስ 9፡9፣ ፊሊጵስዩስ 3፡ 3-6፣ ራዕይ 1፡9)።
መጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ዳራ ባላቸው በርካታ ሰዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ የተጻፈ
ነው። አንዳንዶቹ በቤተ-መንግስት ሆነው ሲጽፉ፣ ሌሎች ደግሞ በእስር ቤት ፣
በስደት እና አንዳንዶች ደግሞ በሚስዩናዊ ጉዞ ወንጌልን እያሰራጩ ባሉበት ሁኔታ
ጽፈዋል። እነዚህ ሰዎች የተለያየ ትምህርት እና ስራ ነበራቸው። አንዳንዶች እንደ
ሙሴ ያሉ ንጉስ ለመሆን የተወሰነላቸው ወይም እንደ ዳንኤል ደግሞ በከፍተኛ
ስፍራ ላይ እንዲያገለግሉ የተመረጡ ነበሩ። ሌሎች ደግሞ በቀላሉ እረኞች ነበሩ።
የተወሰኑት በጣም ወጣት ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ሽማግሌዎች ነበሩ። ከእነዚህ
ልዩነቶች ሁሉ ይልቅ አንድ የጋራ የሆነ ነገር ነበራቸው፣ የትም እና በምንም አይነት
ሁኔታ ውስጥ ቢኖሩም በእግዚአብሔር የተጠሩ እና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው
መልዕክቱን ለህዝቡ የጻፉ ነበሩ።
እንዲሁ አንዳንድ ጸሐፊዎች ከትበው ላስቀሯቸው ኩነቶች የአይን ምስክርም ነበሩ።
ሌሎች ደግሞ ጥንቃቄ የተሞላበት የግል ምርምር አድርገዋል ወይም በጥንቃቄ፣ ያሉ
ዶሴዎችን ተጠቅመዋል (ኢያሱ 10፡ 13፣ ሉቃስ 1፡ 1-3)። ነገር ግን ሁሉም የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍሎች በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተነድተው የተጻፉ ናቸው( 2ኛ ጢሞ
3፡16)። ይህ ነበር ለጳውሎስ ‹‹በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ
ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።››(ሮሜ 15፡
4) ለማለት ምክንያት የሆነው። የሰብአዊን ዘር ቋንቋን የፈጠረው እግዚአብሔር
የተመረጡ ሰዎችን በአስተማማኝ እና ተአማኒነት ባለው ሁኔታ በመንፈስ የተነዱትን
ሐሳብ እንዲጽፉ አስቻላቸው።
‹‹እግዚአብሔር ለአለም እውነትን ለማድረስ ሰብአዊ በሆኑ ወኪሎቹ ፣ እራሱ
በእራሱ ፣ በመንፈሱ አማካኝነት፣ ብቁ በሆኑ ሰዎች ስራውን እንዲሰሩ በማስቻል እና
በማድረስ ሲደሰት ነበር ። የሚናገሩትን እና የሚጽፉትን እንዲመርጡ አእምሮዎችን
ይመራል ። የከበረው ነገር በምድራዊ እቃ ውስጥ ያድራል ነገር ግን የሆነው ሁሉ
ቢሆን ጉዳዩ ከሰማይ ነው ›› Ellen G. White, 4 Selected Messages, book 1,
p. 26.
ስለዚህ የተለያዩ በርካታ ጸሐፊዎች በተለያዩ እና በበርካታ አውዶች
ውስጥ ቢሆኑም አንኳ እግዚአብሔር በሁሉም ውስጥ ተገልጿል። ይህ
አስገራሚ እውነት እንዴት ነው የእግዚአብሔር ቃል ትክክለኛነትን
እንድናረጋግጥ የሚረዳን?
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ሐይማኖታዊ ስራዎች የተለየ ነው፣ ምክንያቱም ወደ 30 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ የተዋቀረው ከትንቢቶች እና ከትንቢታዊ ጽሑፎች ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ንጽረተ-አለም የትንቢቶች ስብስብ እና በሰዓታቸው መፈጸም በታሪክ መካከል ለሚሰራው እና ለነብያቱ ለሚገልጸው እግዚአብሔር ማዕከላዊ ነው (አሞጽ 3፡7)። መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው ቃል ብቻ አይደለም ወይም ታሪካዊ ቃልም አይደለም - ትንቢታዊ ቃል ነው። የሚከተሉት ጥቅሶች እንዴት ነው ስለሚመጣው መሲህ ዝረዝሩን የገለጡት? ዘፍ 49፡ 8-12
መዝ 22፡12-18
ኢሳ 53፡3-7
ዳን 9፡ 2- 27
ሚኪ 5፡ 2
ሚል 3፡ 1
ዘካ 9፡ 9
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ቢያንስ ቀጥተኛ የሆኑ 65 ትንቢቶች ስለ መሲህ አሉ ፣
ታይፖሎጂን ከጨመርን ከዚህ ይበልጣሉ ( ታይፖሎጂ ማለት ስለ ብሉይ ኪዳን
ልማዶች የሚያጠና ነው። ለምሳሌ ስለ መስዋዕቶች እና ስለ ኢየሱስ ትንንሽ
ትንቢቶች)። እነዚህ ትንቢቶች ዝርዝር ከሆኑ ትንቢቶች ጋርም ለምሳሌ ‹‹በትረ
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥››(ዘፍ 49፡10) የተያያዙ ናቸው። ያም እሱ በይሁዳ
በቤተልሔም ይወለዳል (ሚክ 5፡2)። ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ ››፣ ተገረፈ፣
በሐሰት ተወነጀለ ነገር ግን እራሱን ለመከላከል አፉን አልከፈተም(ኢሳ 53፡ 3-7)።
እጆቹን እና እግሮቹን ቸነከሩ። እናም ልብሶቹን ተከፋፈሉ (መዝ 22፡12-18)።
እነዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች በእንደዚህ አይነት ሁኔታ በትክክል በኢየሱስ
በሕይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው መፈጸማቸው በመለኮታዊው መንፈስ ሰዎች
ተነድተው እና መገለጥን አግኝተው እንደጻፏቸው ያረጋግጣል። እንዲሁ ኢየሱስ
ማን እንደሆነ እና ሌሎች ማን እንደሆነ እንዳሉት ሁሉ ይጠቅሳል። ኢየሱስ ሞቱን
እና ትንሳኤውን በመተንበይ የጥንት ነብያትን ትንቢት ተከትሏል (ሉቃ 9፡21፣ 22 ፣
ማቴ 17፡22፣23)፣ የኢየሩሳሌም ውድቀት(ማቴ 24፡1፣2)፣ እና ዳግም ምጻቱ(ዩሐ
14፡ 1-3)። ስለዚህ ስጋ መልበሱ፣ ሞቱ እና ትንሳኤው በመጽሐፍ ቅዱስ ተተንብዩአል
እናም መፈጸማቸው አስተማማኝነቱን ያረጋግጣል።
በኢየሱስ እና ለእኛ በመሞቱ ስላለው እምነትዎ ሊያስቧቸው
የሚችሏቸው ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? በሰንበት ጥናት ክፍልዎ
ያጋሯቸው፣ እናም በክፍል ውስጥ ጥያቄዎን ያንሱ፤ ለምንድን ነው
ማስረጃዎቹ በጣም የሚያስገድዱት?
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ቅዱስ መጻሕፍት ጋር ሲስተያይ በጣም ይለያል ምክንያቱም
በታሪክ ውስጥ የተመሰረተ ነው። ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ የሰብአዊ ዘር
የፍልስፍና ሐሳብ ብቻ አይደለም (ልክ እንደ ኮነፊሸስ ወይም ቡዳኸ) ነገር ግን በታሪክ
ውስጥ ወደ ተቀመጠለት ግልጽ ግብ የሚሔድን የእግዚአብሔርን አንቅስቃሴ መዝግቦ
የያዘ ነው። የመጽሐፈ ቅዱስ ግቦቹ 1) የመሲህ መምጣት ቃል ኪዳን 2) የኢየሰሱ
ዳግም ምጻት ናቸው። ከጥንታዊ ግብጽ እስከ ዘመናዊው የምስራቅ ሐይማኖቶች
ባሉ የሳይክሊክ አመለካከት በተቃራኒ ይህ እርምጃ ለ አይሁድ -ክርስቲያኖች እምነት
የተለየ ነበር።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3-5፣ 51-55፣ ሮሜ 8፡11 ፣ እና 1ኛ ተሰሎ 4፡
14ን ያንብቡ። ስለ ታሪካዊው የክርስቶስ የትንሳኤ እውነት ብቻ ሳይሆን
ነገር ግን በግል ይህ ምን ማለት እንደሆነ እነዚህ ጥቅሶች ምንድን ነው
የሚያስተምሩን?
የአራቱ ወንጌላት እና የጳውሎስ ምስክርነት ኢየሱስ እንደሞተ ፣ እንደተቀበረ እና
በአካል እንደተነሳ ብሎም ለተለያዩ የሰው ዘሮች እንደታየ ይመሰክራሉ። ይህ
በመቃብር ስፍራ ባስቀመጡት እና ኋላ መቃብሩ ባዶ ሆኖ ባዩት የአይን ምስክሮች
ተረጋግጧል። ምስክሮች ኢየሱስን ነክተውታል፣ እርሱም ከእነርሱ ጋር ተመግቧል።
መግደላዊት ማርያም፣ ማርያም(የኢየሱስ እናት)፣ ሌሎች ሴቶችም ከሞት የተነሳውን
ኢየሱስን ተመልክተውታል። ደቀመዛሙርት በኤማሁስ መንገድ ላይ አናግረውታል።
ኢየሱስ ለታላቁ የወንጌል ተልዕኮም ተገልጦላቸው ነበር። ጳውሎስ ያን ሲጽፍ የቃሉ
ምስክሮች ያን እምቢ ቢሉ የእኛ ስበከት እና እምነት ‹ከንቱ› (1ኛ ቆሮ 15፡ 14) ይሆናል
ይላል። ሌሎች ትርጉሞች ‹‹ ባዶ እና የተወገደ›› ወይም ‹‹ ጥቅም የለሽ›› ይሉታል።
ደቀመዛሙርት ሲያስቀምጡት ‹‹ እውነት ነው ጌታ ተነስቷል ›› (ሉቃስ 24፡ 34)
ይላሉ። የግሪኩ ቃል ኦንቶስ የሚለው የሚያመላክተው በእርግጥ የተከናወነን
ነገር ነው። ሲተረጎምም ‹‹በእውነት››፣ ‹‹በእርግጥ ›› የሚል ነው። ደቀመዛሙርቱ
ሲያረጋግጡ ‹‹ በእርግጥም ጌታ ተነስቷል ›› በማለት ነው።
ክርስቶስም ከሞቱት ልክ እንደ ‹‹የመጀመሪያ ፍሬ ›› ተመስሏል (1ኛ ቆሮ 15፡ 20)።
የክርስቶስ በግልጽ ከሙታን መነሳት እና ዛሬም መኖር ታሪካዊው እውነታ ሲመጣ
ጻድቃን እንደሚነሱም አንዱ ማረጋገጫ ነው። ሁሉም ጻድቃን ‹‹ እንዲሁ ሁሉ
በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና ›› (1 ቆሮንቶስ 15፡23) ይላል። በዚህ ላይ ያለው
አገላለጽ የፍጥረትን ድርጊት መፃኢ በሆነ መልኩ ያመላክታል ‹‹ የክርስቶስ የሆነ ሁሉ
›› ወይም ለእርሱ ታማኝ በመሆን ያሉ ሁሉ በዳግም ምጻቱ ይነሳሉ (1ኛ ቆሮ 15፡52)
‹‹ በመጨረሻ መለከት ሲሰማ ›› (1ኛ ቆሮ 15፡52)
2ኛ ነገስት 22፡3-20 ን ያንብቡ። ንጉስ ኢዮስያስ ልብሱን እንዲቀድ ያደረገው ምን ምክንያት ነው? የሕጉ መጽሐፍ መገኘት እርሱን ብቻ ሳይሆነ ነገር ግን አጠቃላይ ይሁዳን የቀየረው እንዴት ነው?
ከክርስስ ልደት በፊት በ 621 ፣ ኢዮስያስ 25 አመቱ ያህል ነበር፣ ሊቀ ካህኑ ኬልቅያስ
‹‹ የሕጉን መጽሐፍ ›› አገኘ። ምን አልባት የመጀመሪያቹ አምስቱ መጽሐፍት ወይም
በትክክል የ ዘዳግም መጽሐፍ ነበር። በአባቱ የንግስና ዘመን በ አሞን እና በጣም
የተረገመው አያቱ ምናሴ፣ ይህ ጥቅል የጠፋው በአል ሲመለክ በነበረበት ጊዜ (አሸራህ)
፣ ‹‹የሰማይ ሠራዊት ›› ባሉበት ( 2ኛ ነገስት 21፡3-9) መሃል ነበር፣ ። ኢዮስያስ
የቃልኪዳኑን ሁኔታዎች በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ በመሰዊያው እራሱን አዋረደ፣ እርሱ
እና ሕዝቡ እውነተኛውን አምላክ ከማመን ምን ያህል እንደራቁ ተገነዘበ። እርሱም
በምድሩ ሁሉ ወዲውኑ ተሃድሶን ጀመረ። የማምለኪያ ስፍራዎችንም አፈራረሰ፣
የጣኦት ምስሎችን አፈራረሰ።
እርሱ ሲጨርስ ፣ በይሁዳ ሁሉ ለአምልኮ አንድ ስፍራ
ብቻ ቀረ፣ ያም በእየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ነበር። የእግዚአብሔርን
ቃል ማግኘታቸው ወደ ጸና እምነት፣ ንስሃ እና የሚለውጠው ሐይል መራቸው። ይህ
ለውጥ የጀመረው በኢዮስያስ ሲሆን በመጨረሻ ወደ ተቀረው ይሁዳ ተሰራጨ።
መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ነው ሕይወታችንን የሚለውጥ ሐይል እንዳለው
የሚያረጋግጥልን እና ወደ ድነት የሚወስደውን መንገድ የሚያሳየን?
ዮሐንስ 16፡13 ፣ ዮሐንስ 17፡17፣ ዕብ 4፡12፣ እና ሮሜ 12፡2።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሐይል ከጠንካራ ምስክርነቶች ውስጥ አንዱ የተለወጡ
የግለሰቦች ሕይወት ነው። የሰዎችን ሐጢያት የሚቆርጠው እና ትክክለኛው ሰብአዊ
ባህሪን የሚገልጽ እና አዳኝ እንደሚያስፈልገን የሚያሳየን ቃሉ ነው ።
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ በተለያዩ ታሪኮች የተዋቀረ፣ በትንቢቶች እና ሕይወትን
በሚለውጥ ሐይል የተሞላ ልዩ መጽሐፍ ሊተረጎም የሚችለው እንዲሁ በተለየ
መንገድ ነው። እንደሌሎች መጽሐፎች ሊተረጎም አይችልም፣ ሕያው የሆነው
የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ወደ እውነት ሁሉ››(ዮሐንስ 16፡13) የሚመራን መንፈስ ቅዱስን
እንደሚልክ የተስፋን ቃል በሰጠን እና ሕያው በሆነው በክርስቶስ ብርሐን ሊስተዋል
ይገባል።
እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ የእግዚአብሔርን እውነት እንደሚገልጽ
እንዲተረጎም ደግሞ የእራሱ የሆን ውስጣዊ መርሆች ሊኖሩት ይገባል። እነዚህ
መርሆች ሊገኙ የሚችሉት ጸሐፊዎቹ መጽሐፍ ቅዱስን እራሱን እንዲተረጉም
እንዴት እንደተጠቀሙበት እና እንደተመሩበት በማጥናት ነው።
ከኤለን ጂ ኋይት ጽሑፎች በታላቁ ተጋድሎ መጽሐፍ ውስጥ ‹‹
“The Scriptures a Safeguard,” ገጽ. 593–602››፣ በዘመናት ምኞት መጽሐፍ
ውስጥ “Let Not Your Heart Be Troubled,” ገጽ. 662–680 ያሉትን ሐሳቦች
ያንብቡ፡
‹‹በቃሉ ውስጥ ለሰዎች ድነት አስፈላጊ የሆነውን እውቀት አስቀምጠዋል።
ቅዱሳን መጽሐፍት ሐይል እንዳላቸው፣ እንደ ማይሳሳቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ
የተገለጠባቸው አድርገን ልንቀበል ይገባል። የባህሪ መለኪያ ፣ የስነ-መለኮታዊ
አስተምህሮ ገላጭ እና የተሞክሮ ሁሉ መፈተኛ መለኪያ ናቸው ›› (ኤልንጅ ኋይት፣
ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 9)
ብዙዎች የእግዚአብሔርን ቃል ከፍ ለማድረግ እና በእርሱ ባለ ታማኝነታቸው ላይ
ለመጽናት ሕይወታቸውን እስከመስጠት ደርሰዋል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል በደም
በተጨማለቀው የሜሬ ግዛት ዘመን የካቶሊኮችን ተጽዕኖ በመቃወም አንዱ እንግሊዝ
ውስጥ የአንድ አካባቢ አስተዳዳሪ ሚኒስተር የሆነው ዶ/ር ሮላንድ ቴይለር ነበር።
ከቤተክርስቲያን ከተባረረ በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በነበረው ቅርበት ካፌዙበት
በኋላ በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ዊንችስተር ቢሾፕ እና የእንግሊዝ አስተዳዳሪ ለሆነው
አመለከተ፣ ነገር ግን ወደ እስር ቤት ወረወረው እንዲያውም ልዩ ከክትትልም
እንዲደረግበት አደረገ። ልክ በ 1555 ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናገረ
‹‹ ‹ መልካም ሰዎች! ያስተማርኳችሁ ሌላ ምንም አይደለም ነገር ግን ከእግዚአብሔር
ቅዱስ ቃል እና ከተባረከው የእግዚአብሔር መጽሐፍ፣ ከመጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ
ያገኘኋቸውን ትምህርቶች ነው። ዛሬ በዚህ የመጣሁት ይህን በደሜ ላትም ነው› ››
(”—John Foxe, The New Foxe’s Book of Martyrs, rewritten and updated
by Harold J. Chadwick (North Brunswick, NJ: Bridge-Logos Publishers,
1997), p. 193.) በማለት ተናግሮ ተሰዋ። ዶ/ር ቴይለር ሊቃጠልበት ያለው እሳት
ሲቀጣጠል እና ሕይወቱን እስኪያጣ ድረስ መዝሙር 51ን ሲደጋግም ተደምጧል።
1.በምን መንገድ ነው ትንቢቶች መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ መሆኑን
የሚያረጋግጡት? እነዚህ የተፈጸሙ ትንቢቶች እምነታችንን ሊያጠናክሩ
የሚችሉት እንዴት ነው ?
2.በማክሰኞው ክፍል መጨረሻ ላይ ካለው ጥያቄ አንጻር የኢየሱስ
መሲህነት ማስረጃ በጣም ሐይለኛ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው?
3.ኢየሱስ እና ሐዋሪያት የማይናወጥ እምነትን በቅዱሳት ጽሑፎች
ላይ በመተማመን መለኮታዊ ስልጣን እንዳላቸው አሳይተዋል። ለምሳሌ
ኢየሱስ ምን ያል ጊዜ ነበር የብሉይ ኪዳንን መጽሐፍት የጠቀሰው
እና ቃልህ ይፈጸም ዘንድ(ብዙ ጊዜ ከእራሱ አንጻር ) ይገባል ያለው?
(ለምሳሌ ማቴ 26፡54፣ 56 ፣ ማር 14፡49፣ ሉቃ 4፡21፣ ዮሐ
13፡18፣ ዮሐ 17፡ 12 ን ይመልከቱ)። ስለዚህ ኢየሱስ እራሱ እንኳ
መጽሐፍ ቅዱስን (በእርሱ ጊዜ ብሉይ ኪዳንን ማለት ነው) በትኩረት
ከወሰደ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ በተለይ ደግሞ ከትንቢቶች
መፈጸም ጋር በተያያዘ የእኛ አመለካከት ምን ሊሆን ይገባል?