መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንተርጉም
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 2ኛ ሩብ ዓመት 2020

ግንቦት 22-28

10ኛ ትምህርት

May 30 - Jun 05




መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ታሪክ



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ ፡- 1ኛ ሳሙ 17፣ ኢሳ 36፡ 1-3 ፣ ኢሳ 37፡14-38፣ ዳንኤል 1፣ 5፣ ማቴ 26፡57-67፣ ዕብ 11፡1-40


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ›› ( ዘጸ 20፡ 2 (እንዲሁ ዘዳ 5፡6))

መ ጽሐፍ ቅዱስ የተቋቋመው በታሪክ ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታሪክ ቀጥ ባለ አቅጣጫ ፍጹም ከሆነው ጅማሮ፣ እግዚአብሔር ሁሉን ከፈጠረበት ወደ መጨረሻው ግቡ፣ በዳግም ምጻቱ እንደገና ምድርን ወደሚያድስበት የሚሔድ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊ ተፈጥሮ ከሌሎች ሐይማኖታዊ መጽሐፎች የሚለየው አንዱ ባህሪው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ውስጥ በአካል ስራውን የሚሰራውን አምላክ፣ እግዚአብሔርን አለ ከማለት ይጀምራል። ያን ደግሞ ለማረጋገጥ አይሞክርም። በመጀመሪያ ፣ እግዚአብሔር ይናገራል በምድር ላይ ሕይወት ተፈጠረ ( ዘፍጥ 1፡1-31)። አብርሐምን ከከለዳውያን ምድር ጠራው። ሕዝቡን ከግብጻውያን የባርነት ቀንበር አላቀቀ። በእራሱ ጣቶች በጽላት ላይ አስርቱን ትእዛዛት ጻፈ(ዘጸ 31፡ 18)። ነብያትን ላከ። መሳፍንትንም ላከ።

የእርሱ መለኮታዊ ህግ እና የድነትን እቅድ ለሌሎች ህዝቦች እንዲያጋሩ ሰዎችን ጠራ። በመጨረሻ ልጁ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አለም ላከ ይሔ ለዘለአለም ታሪክን ከፈለ። በዚህ ሳምንት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የቀረቡ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸን ታሪክ በማስረጃ ለማረጋገጥ የሚረዱንን የተወሰኑ ቁልፍ ጉዳዮችን እና የከርሰ ምድር የታሪክ ቅርስ ጥናት ማስረጃዎችን እንመለከታለን። የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ ግንቦት 29 ሰንበት በማጥናት ይዘጋጁ።

ግንቦት 23
May 31

ዳዊት ፣ ሰለሞን እና ንጉሳዊ አገዛዙ


በእስራኤል ታሪክ የዳዊት እና የሰለሞን የግዛት ዘመን እንደ ወርቃማ ጊዜ ይወሰዳል። ነገር ግን አንዳንዶች እንደሚሉት ዳዊት እና ሰለሞን ባይኖሩ ኖሮስ? መጽሐፍ ቅዱስ አንደሚለው ግዛታቸው ምን አልባት ሰፊ እና እረጅም ባይሆን ኖሮስ ( አንዳንዶች እንደሚሉት) ? ያለ ዳዊት ዋና ከተማቸው እየሩሳሌምም አትኖርም ነበር(2ኛ ሳሙ 5፡ 6-10)። ያለ ዳዊት በልጁ በሰለሞን የሚገነባ ቤተመቅደስም ባልነበረ(1ኛ ነገስት 8፡ 17-20)። በመጨረሻ በዳዊት የዘር መስመር ነበር መሲህ እንደሚመጣ ቃል የተገባው እና ያለ ዳዊት መጭው መሲህም አይኖርም ነበር (ኤር 23፡ 5፣ 6፣ ራዕ 22፡16)። የእስራኤላውያን ታሪክ አንደገና ሙሉ ለሙሉ መጻፍ ያስፈልገው ነበር። ሆኖም ግን ያ ታሪክ በመጽሐፍ እንደሚነበበው በትክክል ለእስራኤል እና ለቤተክርስቲያን የተለየውን ሚናቸውን እና ተልዕኳቸውን የሰጠ ነው።

1ኛ ሳሙ 17ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ነው ቁርጥ ያለን ድል የሰጣት? ከዚህ ድል ማነው ተጠቃሚ? ድሉ የተካሔደው የት ነው?





በ1ኛ ሳሙ 17፡1-3 ውስጥ ያለው ጦርነት ትክክለኛ መልክአምድራዊ አቀማመጡ ስፍራን ያስታውሉ ። የኪህርበት ኩፋ መገኛ በተራራው ላይ በምዕራፉ እንደተገለጸው እስራኤላውያን ሰፍረው ያሉበት ቦታ ነው። በዚያ በቅርቡ የተደረገ ቁፋሮ እንዳሳየው በጣም ሰፊ የሆነ ምሽግ ፣ የጦር ሰፈር ከተማ ከሳኦል እስከ ዳዊት ጊዜ በነበረው ተራራ ላይ ሆኖ ይታያል። በተመሳሳይ ሰዓት የነበሩ ሁለት በሮችም ወጥተዋል። በጥንቱ እስራኤል ጊዜ አብዛኞቹ ከተሞች በእስራኤል አንድ በር ስለነበራቸው ይህ ነገር ምን አልባት ሸዓራይም ከተማን በማሳየት ይረዳ ይሆናል(1ኛ ሳሙ 17፡52) በእብራይስጥ ሁለት በር ማለት ነው። ይሄ ከሆነ ጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥንታዊ ከተማን አገኘን ማለት ነው። በ 2008 እና 2013 እስካሁን ከተገኙ ሁሉ ጥንታዊ የእብራይስጥን ጽሑፍ የሚወክሉ እንደሆኑ ብዙዎች ያመኑባቸው የተቀረጹ ጹሁፎች ተገኝተዋል።

ሁለተኛው የተቀረጸ ጽሑፍ አስበኣል የሚለውን ስም ጠቅሷል፣ ከሳኦል ልጆች ከአንዱ ስምጋር በትክክል ተመሳሳይ ነው( 1ዜና 9፡39) በ1993 በሰሜናዊው ከተማ በቴል ዳን በተደረገ ቁፋሮ በደማስቆው ንጉስ ሃዛኤል በሐውልት ላይ የተቀረጸ ጽሁፍ ተገኝቷል፣ ‹‹በእስራኤሉ ንጉስ›› እና ‹‹በዳዊት ቤት›› ላይ ስለገኘው ድል ዘግቧል። ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ያለ ተመሳሳይ የዳዊት ሥርዎ- መንግስት ነው፣ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ዳዊት በታሪክ ውስጥ እንደነበረ የሚያስረዳ ተጨማሪ የምድር ውስጥ ቅርስ ማስረጃ ነው። አንዳንዶች እንደሚሉት ንጉስ ዳዊት በእውነት ካልነበረ ፣ ለእኛ እምነት ስለሚኖረው እንደምታ አስቡ ምን ማለት ነው ?

ግንቦት 24
Jun 01

ኢሳያስ፣ሕዝቄል እና ሰናክሬም


ኢሳያስ 36፡1-3፣ እና ኢሳያስ 37፡14-38ን ያንብቡ። በዚህ መግለጫ ይሁዳን በመቃወም የተደረገ የአሶሪያውያን እንቅስቃሴ ነው ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዴት ነው ነጻ ያወጣ?





በ 701 ቅ.ዓ የሰናክሬም እንቅስቃሴ በይሁዳ ላይ ነበር። ይህ መግለጫ በመጽሐፍ ተመዝግቧል። እንዲሁ በተለያያ መንገድ በራሱ በሰናክሬምም ተመዝግቧል። በዚህ ታሪካዊ እና በዋና ከተማዋ ናይንቪ እንደተገኘው በጣም ይኩራራ ነበር ‹‹አርባ ስድስቱ ጠንካራ አጥር የነበራቸው ከተሞቹን (ሕዝቅያስ) እና ለቁጥር የታከቱ በጎረቤቶቻቸው ዙሪያ የነበሩ ትንንሽ ከተሞች ከብቤ ድል አድረጌአቸዋለሁ ›› በናይንቬህ የሰናክሬም ቤተመንግስት የይሁዳን ከተማ ለቺሽን ማሸነፉን ተከትሎ ባደረገው ግብዣ የቤተመንገስቱን ማዕከለኛ ክፍል ግድግዳ ከበባውን እና ከተማዋን በጦርነት ድል መንሳቱን በሚያሳይ እና በሚያሳርፍ መልኩ ሸፍኖት ነበር።

በቅርብ ጊዜ በ ላቺሽ በተደረገ ቁፋሮ በሰናክሬም ከተቃጠለች በኋላ በተከማዋ ፍርስራሽ ተከማችቶ ተገኝቷል ። ነገር ግን እየሩሳሌም በተአምራዊ መንገድ ተርፋለች። ሰናክሬም በዚህ ብቻ ሊኩራራ ይችላል ‹‹ የይሁዳውን ሕዝቅያስን በጎጆዋ እንዳለች ወፍ በከተማው ውስጥ ዘግቼዋለሁ›› ሊል ይችላል። እየሩሳሌምን እንዳጠፋ የሚገልጽ ነገር የለም ፣ እናም ደግሞ በባርነት የተወሰዱ ምርኮኞችም እንደነበሩ አይገልጽም። እውነት ነው እየሩሳሌም ተከባለች ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንሚለው የጌታ መላእክት እየሩሳሌምን ነጻ እንዳወጧት እና ከበባው ለአንድ ቀን ያህል ብቻ ነበር። ኢሳያስ አስቀድሞ እንደተናገረው ‹‹ ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል። ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም። በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፥ ወደዚችም ከተማ አይመጣም ይላል እግዚአብሔር፦ ስለ እኔም ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ። ›› (ኢሳ 37፡ 33-35) ።

በሚያስገርም መልኩ ላቺሽ ብቻ ነበረች በ ናይኒህ፣ በሲሪያውያን ዋና ከተማ በዝና ትታይ የነበረው። እየሩሳሌም በቤተመንግስቱ ግድግዳ ላይ አልተገኘችም። ሰናክሬም ሊኩራራ የሚችለው ላቺሽን ስላሸነፈ ብቻ ነው። በ ሰማዩ አምላክ እና በሶሮያውያን አማልዕክት መካካል የነበረው ትእይንት እግዚአብሔር ሕዝቡን ነጻ በማውጣት ታየ። የሶርያውያንን የቁጣ ስራ ተመለከተ የሕዝቅያስን ጸሎት ሰማ። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ይሰራል። በዚህ ሰዓት እና ስፍራ እስራኤልን በተአምራዊ መንገድ ነጻ ያወጣ እግዚአብሔርን ፣ ዛሬ እርስዎ የሚጸልዩለት ፣ የሚታመኑበት እና የሚተማመኑበት እሱው እራሱ መሆኑን እንዴት ነው ሊያስተውስ የሚችሉት?

ግንቦት 25
Jun 02

ዳንኤል ፣ ናቡከደነፆር እና ባቢሎን


በሐምሌ 2007 አንድ ተመራማሪ ከቬይና ዩኒቨርስቲ የባቢሎን ንጉስ የነበረው ናቡከደነጾርን አንድ በዲንጋይ ላይ የተቀረጸ ጽሑፍ ሲያገኝ በብርቲሽ ሙዚየም በአንድ ፕሮጅክት ላይ ይሰራ ነበር ። በጽላቱ ላይ ‹‹ ናቡርሳርሳኬም ›› የሚልን ስም ያገኛል በኤርሚያስ 39፡3 ላይ በግልጽ የተጠቀሰ የባቢሎናውያን ስም ነበር። ናቡሳርሳኬም ከብዙ ሰዎች ከንጉሶች እና ከባለስልጣናት አንዱ ነው፣ ምስጋና ለከርሰምድር ቅርስ ተመራማሪዎች እንጂ ባገኙት ጥናት መሰረት በዳንኤል እና በናቡከደነጾር ዘመን የነበረ ሰው ነበር።

ዳንኤል 1 እና 5ን ያንብቡ። በታሪክ ውስጥ ቀደም ሲል የነበረው የዳንኤል ውሳኔ እንዴት ነበር የእግዚአብሔር ድርጊት፣ እንደ አገልጋዩ እና እንደ ነብይ ተጠቅሞ በሚሊዮን ሰዎች ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ ካደረገበት ሁኔታ ጋራ የሔደው?





ዳንኤል ለእግዚአብሔር በሚበላው እና በሚጸልየው ታማኝ ሆኖ ጸንቶ ለመቆም‹‹በልቡ አሰበ ››(ዳን 1፡8)። ይህ መልካም ልምድ ቀደም ብሎ በነበረው ልምምድ የተቀረጸ ሲሆን ለረዥሙ ሕይወቱ ጥንካሬን የሚሰጠው ዘዬው ሆነ። ውጤቱም ንጹህ አስተሳሰብ፣ ጥበብ፣ እና ከላይ የሚመጣው ማስተዋል ነበር። ይሔ ደግሞ በናቡከደነጾር እና በቤልሻጽር ዘንድም የታወቀ ሆነ ። ስለዚህም በግዛቱ ውስጥ ወደ ከፍተኛው ቦታ ከፍ አለ። ነገር ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊው ከንጉስ ናቡከደነጾር ጋር ያደረገው ንግግር ነበር(ዳን 4፡ 34-37)።

ናቡከደነጾር የ ናቦፖላዛር ልጅ ነበር። በአንድ ላይ በጣም የከበረች ከተማን ገንብተዋል፣ ከጥንት ከተሞች ሁሉ የበለጠች ነበረች(ዳን 4፡30)። የባቢሎን ከተማ በጣም ሰፊና ትልቅ ነበረች፣ ከ 300 በላይ ቤተመቅደሶች፣ በጣም የሚያምር ቤተመንግስት እና ባለ 12 ጫማ እና 22 ጫማ ስፋት ባላቸው ግንቦች የታጠረች ከተማ ነበረች። ግንቦቹ ስምንት ዋና ዋና በሮች አሏቸው፣ ሁሉም የተሰየሙት በባቢሎናውያን አማልዕክት ነው። በጣም የታወቀው ደግሞ የኢሻታር በር ነው፣ በጀርመኖች ተቆፍሮ የተገኘ እና በፔርጋሞም ሙዚየም በርሊን ውስጥ ይገኛል። በዳንኤል 7፡4፣ ባቢሎን ክንፎች ባለው አንበሳ ተገልጻለች። ወደ ኢሻታር የሚወስደው መንገድ ወደ 120 የሚሆኑ የአንበሶች ምስል ያለበት ነበረ።

በሰው ላይ የተከመረ በጣም ትልቅ አንበሳ ምስል በቁፋሮው ጊዜ ተገኝቷል እናም በከተማዋ ቆሞ ይገኛል። እነዚህ ሁሉ የሚመሰክሩት አንበሳ ታላቂቱን ባቢሎንን ለመወከል ተገቢ እና ትክክል እንደሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ እና ትንቢታዊ መልዕክት እንዲህ ተረጋግጧል። ዳንኤል 1፡8 እንደሚናገረው ዳንኤል ‹‹ በልቡ አሰበ ›› ይላል። ምን ማለት ነው? ምን ነገሮች አሉ ‹በልባችሁ ልታስቡ› የሚገባ፣ ማድረግ ስላለባችሁ እና ስለሌለባችሁ?

ግንቦት 26
Jun 03

ታሪካዊው ኢየሱስ


ማቴዎስ 26፡57-67፣ ዮሐ 11፡45-53፣ እና ዮሐንስ 18፡29-31ን ያንብቡ። ቀያፋ ማነው እናም በክርስቶስ ሞት ላይ የነበረው ሚና ምንድን ነው? ጴንጤናዊው ጲላጦስ ማነው እናም ካህናት ያሰቡት ነገር ግቡን እንዲመታ ውሳኔው ምን ያህል አስፈላጊ ነበር?





ቀያፋ የካህናት አለቃ እና የኢየሱስን ሞት ፈልጎ ሐሳቡን አዘጋጅቶ ሴራውን የጎነጎነ ነው።በሮማውያን ቦታ ሆኖ ይጽፍ በነበረው በአይሁድ ታሪክ አዋቂው በጆሴፉስ አማካኝነት ቀያፋ መኖሩ በታሪክ ተመዝግቧል። ‹‹እርሱ ከከፍተኛ ካህናት ውስጥ ያለውን ሳይፐስም ይባል የነበረውን ዮሴፍን ከመከልከሉ በተጨማሪ፣ ከፍተኞቹ ካህናት ውስጥ እና የቀደመው ሊቀካህ የነበረውን የአናናስ ልጅ የሆነውን ዮናታንን እርሱን እንዲተካ ሾመው ›› ይላል። (Josephus Complete Works (Grand Rapids, MI: Kregel Publications, 1969), book 18, chapter 4, p. 381.)

በ 1990 አንድ የቤተሰብ መቃብር በደቡብ እየሩሳሌም 12 የአጥንት ሳጥኖችን ይዞ ተገኝቷል። ሳንቲሞቹ እና ሸክላዎቹ ከመቃብሩ ቦታ የተገኙት ወደ መጀመሪያው ምዕተ አመት አጋማሽ ያሳያሉ፣ ከክርስቶስ ሞት በኋላ። በጣም ያጌጠው የአጥንት ሳጥን እና በውስጡ ብዙ አጥንቶችን የያዘው ሳጥን ላይ የተጻፈው ‹‹ ዮሴፍ የቀያፋ ልጅ ›› ይላል በርካታ ተመራማሪዎች እንዳመኑት ይሄ መቃብር እና የአጥንት ሳጥን ሊቀ ካህን የነበረው እና ለኢየሱስ ሞት ምክንያት የሆነው የቀያፋ እንደሆነ ነው። በ1961 የተቀረጸ ጽሁፍ የጴጤናዊውን ጲላጦስን፣ በጢብሮስ ግዛት ስር የይሁዳ ገዥ የነበረው ሰው ስም የያዘ ደንጋይ በ ቂሳሪያ ማሪቲማ ቲአትር ተገኝቷል። ስለዚህ በእነዚህ ሁለት መረጃዎች በክርስቶስ ሞት ዙሪያ አንዳንድ ወሳኝ የነበሩ ታዋቂ ሰዎች በታሪክ ውስጥ ተረጋግጠዋል።

የማያምኑ ተመራማሪዎችም በሁለተኛው ምዕተ አመት ስለ ኢየሱስ የናዝሬቱ ተናግረዋል። ታሲቶስ ፣ የሮም ታሪክ ተመራማሪ ነው፣ ስለ ክርስቶስ በጤብሮስ አገዛዝ ጊዜ በጴንጤናዊው ጲላጦስ እንደተገደለ እና በቀደምት ክርስቲያኖችም ላይ ስደት እንዳመጣ ጠቅሶ ጽፏል። ወጣቱ የመሪም ገዥ ፒሊኒይ ከክርስቶስ ሞት በኋላ በ 112-113 ለገዥው ትራጃነ፣ ክርስቲያኖችን እንዴት ሊይዛቸው እንሚገባ ጽፏል። ሲገልጻቸውም በሆነ ቀን ይገናኛሉ ብርሐን ከመሆኑ በፊት ይሰባሰባሉ ፣ ልክ ለአማልእክት እንሚደረግ ይዘምራሉ ሲል ገልጧቸዋል።

እነዚህ የከርሰ ምድር ቅርስ ጥናቶች እና ታሪካዊ ማስረጃዎች ተጨማሪ እና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አውታር ውጭ የሆኑ ስለ ክርስቶስ፣ ከሞቱ በኋላ ለ 50 አመታት ይመለክ እንነበር፣ መኖሩን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ማሳረጃዎች ናቸው። ወንጌላት እራሳቸው የመጀመሪያዎቹ ማስረጃዎች /ምንጭ ናቸው። እናም ስለ ኢየሱስ እና ስለ ሕይወቱ ለመማር በጥንቃቄ ልናጠናቸው ይገባል። አምነታችንን የሚደግፉ የከርሰ ምድር ቅርስ ጥናት ማስረጃዎች መልካም እና የሚረዱ ቢሆኑም እንኳ ለምንድን ነው እምነታችንን በእነዚህ ነገሮች ላይ ጥገኛ ማድረግ የማይገባን?

ግንቦት 27
Jun 04

እምነት እና ታሪክ


ባዶ በሆነ ሁኔታ አንኖርም። ምርጫችን በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ላይ ተጽእኖ አለው። በተመሳሳይ መንገድ የጥንት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሕይወት ከእራሳቸው ውጭ ወደፊት በሌሎችም ላይ ከፍትኛ ተጽእኖ ነበረው። ዕብራውያን 11 ‹‹የእምነት ምዕራፍ ›› በመባል ይታወቃል፣ እጥር ብሎ የጥንት የእምነት አርበኞች ተጽዕኖን ያሳየናል። ዕብራውያን 11፡ 1-40ን ያንብቡ። የእነዚህን የጥንት ጀግኖች ህይወታቸውን በማጥናት ምን ልንማር እንችላለን? ሔኖክ



ኖህ



አብርሐም



ሳራ



ዮሴፍ



ሙሴ



ረዓብ



ሳምሶን



እምነት በቀላሉ በአንድ ነገር ወይም በአንድ ሰው ላይ ማመን አይደለም፣ ለሚያምኑት ነገር አጸፋዊ ምላሽ በመስጠት የሚተገበር ነው።የሚሰራው እምነተ ነው ፣ እንደ ጽድቅ የሚቆጠረው ይህ ነው።ታሪክን የሚቀይሩ የእነዚያ እምነቶች ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ድርጊቶች እያንዳንዳቸው በእግዚአብሔር ቃል ላይ መታመንን ይጠይቃሉ። ከልምምድ እና ከምክንያት በላይ በእግዚአብሔር ቃል ላይ በመታመን ኖህ መርከቧን ሲገነባ በእምነት እየሰራ ነበር፣። ምክንያቱም ዘንቦ አያውቅም ፣ ልምምድም የለም እንዲሁ የውሃ ጥፋት ይመጣል የሚለውም በፍጹም ስሜት አይሰጥም። ነገር ግን ኖህ እግዚአብሔርን ታዘዘ ፣ የሰው ዘርም ተረፈ። አብራም ኋላ አብርሐም ተባለ፣ ኡርን ትቶ ወደ ደቡብ ሞሶፖታሚያ ሔደ፣ በወቅቱ በጣም የተወሳሰበ ከተማ ነበረ ነገር ግን እግዚአብሔር ወዴት እንሚወስደው ሳያውቅ ወጣ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መንቀሳቀስን መረጠ።

ሙሴ በወቅቱ ትልቋ ሐገር/ግዛት በነበረችው በግብጽ ላይ ገዥ ከመሆን ይልቅ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለመምራት የበጎች እረኛ መሆንን መረጠ። ከሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ የጠራውን የሐያሉን ድምጽ ታመነ። ረዓብ የእግዚአብሔርን ነጻ የማውጣት ዘገባ እንደሰማች ለመታመን ወሰነች ፣ ሁለቱን ሰላዮች ደበቀቻቸው እናም የኢየሱስ የዘር ሐረግ ውስጥ ገባች። ውሳኔያችን ለቁጥር የሚታክቱ ሰዎች ላይ፣ በትውላደችን እና ከዚያም አልፎ በሚመጣው ትውልድ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳለው የምናውቀው ጥቂቱን ነው! ምን አይነት ወሳኝ የሆነ ውሳኔ በፊትዎ አለ? የሚያደርጉትን ነገር እንዴት ነው የሚመርጡ እና ለምንስ?

ግንቦት 28
Jun 05


ተጨማሪ ሐሳብ


የኤለን ጂ ኋይትን “David and Goliath,” ገጽ. 643–648; in Patriarchs and Prophets; “Hezekiah,” ገጽ. 331–339; “Deliverance from Assyria,” ገጽ. 349–366 in Prophets and Kings; section 4.k., in “Methods of Bible Study,” የሚለው በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል http://www.adventistbiblicalresearch.org/materials/ bible-interpretation-hermeneutics/methods-bible-study. ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ሰፊ እና ምሪትን በመስጠት ተወዳዳሪ የሌለው፣ የሰው ልጅ ያለው ታሪክ ነው። ከዘለአለማዊው እውነት ምንጭ የተቀዳ እና የመለኮት እጆች በዘመናት መካካል ቅድስናውን ጠብቀውለት ያለ መጽሐፍ ነው። ያለፈውን በጣም እሩቁን ሰዎች በጥናት ገብተው ሊደርሱ የሚሹትን ያበራል ። እነሆ የምድር መሰረት የጸና እነ ወደ ሰማይ የተዘረጋን ሐይልን የምናገኘው በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው ። የዘራችንን ታሪክ ልናገኝ የምንችለው በዚህ ብቻ ነው ፣ በሰበአዊ አግባባ ከሌለው ጥላቻ ወይም ሰበአዊ ኩራት የጸዳ ነው። ›› (ኤለን ጂ ኋይት፣ ስነ-ትምህርት ገጽ 173 ) ‹‹የእግዚአብሔር ማስተዋል እና ቃሉ ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ባለው ያርፋል።

መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ሐሳብ በሳይንስ አይፈተንም። እነዚህ ሐሳቦች ግን ወደ ማይሳሳተው መለኪያ ዘንድ ያመጣል። የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንደሆነ ያውቃል እናም እውነት ደግሞ ከእራሱ ጋር በፍጹም አይጋጭም። በእግዚአብሔር ከተገለጠው እውነት ጋር የሚጋጭ ሳይንስ ተብሎ በተጠራው አስተምህሮ ያለ ማንኛውም ነገር ባዶ የሰዎች የግምት ሥራ ነው። (“To the really wise, scientific research opens vast fields of thought and information.”—Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 8, p. 325.)


የመወያያ ጥያቄዎች




1.በረቡዕ ጥናታችን መጨረሻ ላይ የተነሳውን ጥያቄ እንደገና ያስታውሱ። አዎ፣ የከርሰ ምድር ቅርስ ጥናትን የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ለማረጋገጥ እንደ ማስረጃ ስናገኝ ጥሩ ነው ። ነገር ግን የተገኙ የከርሰ ምድር ቅርስ ጥናት ማስረጃዎች ሲተነተኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጋር ሲጋጩስ ምንድን ነው የሚሆነው? በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃልነቱ መታመን እንዳለብን ይሔ ሊነግረን የሚገባው ምንድን ነው? ከየትኛውም የከርሰ ምድር ቅርስ ጥናት ወይም የሰው ሳይንስ ይልቅ ልንታመነው እንደሚገባ ሊነግረን የሚችለው ምንድን ነው?

2.ስለ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ያስቡ፣ ባላፈው ጊዜአቶች የተፈጸሙትንም እንኳን ቢሆን አሁን ዛሬ ካላችሁበት ጊዜ ላይ እንደተፈጸሙ ልናይም እንችላለን። ለምሳሌ ስለ ዳንኤል 2 እና 7 ላይ ስላሉት መንግስታት አስቡ። በታሪክ ውስጥ ከተፈጸሙት ከእነዚህ ትንቢቶች አንዴት መማር እንችላለን፣ እንዲሁም ገና ወደፊት በሚመጡት ትንቢቶች ላይ ደግሞ በጌታ ለመታምን እንዴት እንችላለን ?