ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ዳን.2፡27-45፤ ዮሐ.14፡29፤ ዘሁ.14፡34፤ ዳን.7፡1-25፤ ዳን.8፡14፤ 1ቆሮ.10፡1-13።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “እርሱም፡ እስከ ሁለት ሺ ሶስት መቶ ማታና ጠዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።” (ዳን.8፡14) ።
የ
መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ለማንነታችንና ለተልዕኮአችን በጣም አስፈላጊ
ነው። ትንቢት ከውስጥና ከውጪ ሆነን የእግዚአብሔርን ቃል ትክክለኝነት
የምናረጋግጥበትን ዘዴ ይሰጠናል። የሱስ እንዲህ አለ “ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ
አሁን አስቀድሞ ሳይሆን ነግሬአችኋለሁ።” (ዮሐ.14፡29 ዮሐ.13፡19ንም ተመልከቱ)።
ታዲያ ወሳኙ ጥያቄ፡ ትንቢቱ በርግጥም ሲፈጸም እንድናውቅ በትክክል ትንቢቱን
እንዴት መተርጎም ይገባናል?
በተሃድሶ ወቅት የተሃድሶ መሪዎች የተከተሉት ዘዴ ታሪክን መሠረት ያደረገ
ነው። ይህ ዘዴ ደግሞ የዳንኤልና የዮሐንስ ራዕይ ለትንቢት ፍቻቸው ቁልፍ ሆኖ
አገልግሏቸዋል። ታሪክን መሠረት ያደረገ ዘዴ ትንቢትን የሚያየው በቀጣይነት እያደገ
በመሄድ የታሪኩ ፍጻሜ ድረስ እንደሚደርስ፤ ካለፈው ታሪክ መነሻነት ይጀምርና
በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት እንደሚደመደም ነው።
በዚህ ሳምንት ታሪካዊ የመመዘኛ ዘዴን መሠረት ላደረገ የትንቢት ፍቺ
ምሶሶ የሆኑ ነጥቦችን እናጠናለን። “በታሪክ የምናየው የትንቢቶች መፈፀምን፣ በታላቁ
የተሃድሶ ንቅናቄ ጊዜ የእግዚአብሔርን የጥበቃ ሥራ ማጥናት እና በመጨረሻው
የታላቁ ተጋድሎ ግጭት ህዝቦች የሚያደርጉትን የዘመቻ ክስተቶች እድገት
እንድናስተውል ያደርገናል።” – Ellen G. White, Testimonies for the church,
Vol. 8, P. 307.
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለግንቦት 15 ሰንበት ይዘጋጁ።
ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ትንቢትን ለማጥናት የሚጠቀሙበት መሰረታዊ ዘዴ ታሪካዊ የመመዘኛ ዘዴ ይባላል። ሳይቆራረጥ መስመሩን ተከትሎ ሲፈስ ያየነው ያለፈው፣ የአሁኑኑና የወደፊቱ አንኳር የሆኑ ትንቢቶች ናቸው። በትምህርት ቤት ታሪክን ከምናጠናው ጋር ተመሳሳይነት አለው። እንዲህ የምናደርግበት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እነዚህን ትንቢቶች የሚፈታልን በዚህ መንገድ ስለሆነ ነው። ዳን.2፡27-45ን አንብቡ። የትኛው የህልም ክፍል ነው በታሪክ ውስጥ ያለውን ቀጣይና ያልተቆራረጠ የስልጣናት ቅደም ተከተል የሚያሳየን? መፅሐፍ ቅዱስ ራሱ የመጨረሻውን ትንቢት እንዴት መፍታት እንዳለብን የሚያሳየን በምን መንገድ ነው?
የወርቁ ራስ የናቡከደነጾር መንግስት መሆኑን ልብ በሉ። ስለዚህ ዳንኤል ባቢሎንን
የመጀመሪያው መንግስት እንደሆነ አሳወቀ (ዳን.2፡38)። ከዛም ዳንኤል እንዲህ
አለ “ከአንተም በኋላ ከአንተም የሚያንስ ሌላ መንግስት ይነሣል፤ ከዚያም በኋላ
በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሌላ ሶስተኛ የናስ መንግስት ይነሣል።” (ዳን.2፡39)። ከዛም
አራተኛው ይቀጥላል (ዳን.2፡40)። ልክ ግዙፍ ከሆነው አካል ከራሱ አንስቶ እስከ
ጣቶቹ ድረስ በተለያዩ መንግስታት እንደተወከለ ሁሉ በምስሉ ላይ የምናየውም
ያለምንም የጊዜ ክፍተት አንዱ አንዱን እየተከታተለ መጣ ። ጊዜና ታሪክ የተያያዙ
እንደሆኑ ሁሉ እነርሱም አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር የተያያዙ ናቸው።
በዳንኤል 7 እና 8 ላይ ደግሞ በምስሉ ፈንታ የተለያዩ አውሬዎች ምሳሌ
ሆነው ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ተመሳሳይ የሆነ ትምህርትን ያብራራልናል። 4 በቅደም
ተከተላቸው ሳይቆራረጡ የሚመጡ ምድራዊ ነገስታት ቀርበውልናል (ሶስቱ ደግሞ
ዳንኤል 8 ላይ ተጠቅሰዋል)። ከጥንት የታሪክ መነሻቸውን አድርገው እስካሁን እና
እስከ ወደፊቱ የሚዘልቁ ሲሆን ክርስቶስ ሲመለስ ግን እግዚአብሔር ዘላለማዊ
መንግስቱን ያኔ ያቋቁማል።
ስለዚህ የዳንኤል 2፤ ዳንኤል 7 እና 8 ላይ የተሰጡት ተከታታይ ህልሞች
ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እስከዛሬ የያዙት ይህ የታሪክ መሰረት የፕሮቴስታንት
ታሪክ አዋቂዎች ትንቢትን እንዲተረጉሙ መሠረት ጥሎላቸዋል።
ዮሐ. 14፡29 አንብቡ። ትንቢት እንዴት ተደርጎ ተግባራዊ ሊሆን
እንደሚችል የሱስ የተናገረበት መንገድ ምን እገዛ ያደርግልናል?
በባቢሎን ጊዜ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያላገኙትን የታሪክ ሁኔታ ግልጽ
ሆኖልን ለምንኖር ለኛ ዛሬ ላይ ያለው ጠቀሜታ ምን ያክል ነው?
ታሪክን የምንመዝንበትና ትርጓሜ የምንሰጥበት አንዱና ቁልፉ መንገድ የአመት-ቀን መርህ ነው። አያሌ ሊቃውንት በምዕተ ዓመታት ውስጥ የዳንኤልና ራእይ የጊዜ ትንቢትን ለመፍታት ይህንን መርህ ነበር የተጠቀሙት። ይህንን መርህ ያገኙት ከብዙ ወሳኝ የሆኑ ጥቅሶች ላይ እና ከትንቢቶቹ ከራሳቸው አውዳዊ ንባብ ነው። ዘዳ.14፡34 እና ህዝ.4፡6ን አንብቡ። በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር የአመት-ቀን መርህን በምን መልኩ ገለጸልን?
እነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የአመት-ቀን መርህን ሃሳብ በግልጽ መመልከት
እንችላለን። ለምሳሌ እንደ ዳን.7፡25 እና ዳን.8፡14 እንዲሁም ራዕይ 11፡2-3፤ ራዕይ
12፡6፣ 14 እና ራዕይ 13፡5 ያሉ አንዳንድ የጊዜ ትንቢቶች ላይ ይህንን መርህ በምን
መንገድ ማረጋገጥ እንችላለን?
በዳንኤል እና ራዕይ ትንቢቶች የአመት-ቀን መርሃችንን የሚደግፉ ሶስት
ሌሎች ግብአቶች አሉ፡- የተምሳሌቶች፤ ረጅም የጊዜ ርዝመቶች እና እንግዳ የሆኑ
ገለፃዎች
በቅድሚያ የአውሬዎቹና የቀንዶቹ ባህርያት መንግስታትን የወከሉበት ተምሳሌታዊ
አቀራረብ የሚነግረን ነገር ቢኖር የጊዜ ትንታኔዎቹም ሊስተዋሉ የሚችሉት
በተምሳሌታዊ አቀራረብ ሲሆን ነው። አውሬዎቹና ቀንዶቹ እንዲሁ ቃል በቃል ብቻ
የምንወስዳቸው አይደሉም። ሌላ ነገርን በተምሳሌትነት የሚገልጹ ናቸው። ስለዚህ
የተቀሩት ትንቢቶች በተምሳሌታዊ አገላለፅ እንዲሁ ቃል በቃል በሚወሰድ ፍቺ
ካልቀረቡልን ታዲያ ለምንድነው የጊዜን ትንቢት ብቻ ቃል በቃል የምንወስደው?
ምላሻችን የሚሆነው በርግጥም አይደለም የሚል ነው።
በመቀጠልም ከትንቢት ያገኘና ብዙዎቹ ክስተቶች መንግስታቶች የሚሸፍኑት ጊዜ
ብዙ ምዕተ ዓመታትን ሲሆን የጊዜ ትንቢትን እንዲሁ ቃል በቃል ብንወስድ ኖሮ ግን
ይህ ሊሆን አይችልም። አንድ ጊዜ የአመት-ቀን መርህን ተግባራዊ ስናደርግ ጊዜያቶቹ
በትክክልና በአስደናቂ ሁኔታ ከክስተቶቹ ጋር እኩል ይገጣጠማሉ። ነገር ግን የትንቢት
ጊዜዎቹን እንዲሁ ቃል በቃል ወስደን ብንተረጉማቸው ይህንን ማግኘት አንችልም።
በስተመጨረሻም እንግዳ በሆነ አቀራረብ ለየት ብሎ የጊዜ ርዝመት
ተተንትኖ የተቀመጠልን ተምሳሌታዊ በሆነ አፈታት ነው። በሌላ አገለለፅ በነዚህ
ትንቢቶች ውስጥ ጊዜ የተጠቀሰበት መንገድ (ለምሳሌ 2300 ማታ እና ጠዋት
በዳን.8፡14 ላይ) እንዲሁ በተለመደ መንገድ ያለውን የጊዜ ሁኔታ የሚያሳይ ሳይሆን
ተምሳሌታዊ መሆናቸውን ይነግረናል።
በዳን.9፡24-27 ላይ የምናገኘው ሰባውን ሱባኤ ተመልከቱ “ኢየሩሳሌምን
ለመጠገንና ለመስራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ዓለቃው እስከ መሲሁ
ድረስ” የሚለውን ስናነብ (ዳን.9፡25) ቃል በቃል ስንወስደው 69 ሳምንታት ናቸው
ወይንስ አንድ ዓመት ከ4 ወራት ከአንድ ሳምንት ብቻ የጊዜ ሁኔታ ነው? በዚህ
መንገድ የምናስተውል ከሆነ ትንቢት ትርጉም የለውም። ትርጉም አለው እንዴ?
የመፅሐፍ ቅዱስ መርህ የሆነውን አመት-ቀን መርህን 70 ሳምንታት
ስንፈታው 490 አመታት ሲሆኑስ ምን ይከሰታል?
ለብዙ ምዕተ ዓመታት የፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ መሪዎች በዳን.7 እና በዳን.8 ላይ የሚገኘው የትንሹ ቀንድ ሃይል የሮም ቤተክርስቲያን መሆኑን ለይተው አውቀዋል። ለምን? ዳን.7፡1-25 እና 8፡1-13ን አንብቡ። በሁለቱም ምዕራፎች ውስጥ የምናገኘው የትንሹ ቀንድ ተመሳሳይ ባህሪ ምንድነው? እንዴትስ ለይተን እናውቀዋለን?
በዳን.7 እና 8 ላይ የተጠቀሱ ሰባት የጋራ ባህሪያቶች እነዚህ ናቸው (1)
ሁለቱም ቀንድ ብለው ነው የገለጹት (2) ሁለቱም ላይ አሳዳጅ ሀይል ሆነው ቀርበዋል
(ዳን.7፡21፣ 25፤ 8፡10፣ 24)። (3) ሁለቱም ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉና
በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል የሚናገሩ ናቸው (ዳን.7፡8፣ 20፣ 25፤ 8፡10፣
11፣ 25)። (4) ሁለቱም ላይ ትኩረታቸው የእግዚአብሔር ህዝቦች ናቸው (ዳን.7፡
25፤ 8፡24)። (5) ሁለቱም ምዕራፎች ላይ ተግባሮቻቸው ተብራርቶ የተገለፀው
በትንቢታዊ ጊዜ ነው (ዳን.7፡25፤ 8፡13-14)። (6) ሁለቱም ምእራፎች ላይ እስከ
መጨረሻው ጊዜ ድረስ ቆይተዋል (ዳን.7፡25-26፤ 8፡17-19) እና (7) ሁለቱም ላይ
ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ሀይል ጠፉ (ዳን.7፡11፣ 26፤ 8፡25)።
ታሪክ እንደሚያስረዳው የመጀመሪያው መንግስት ባቢሎን ነው (ዳን.2፡38)፣
ሁለተኛው ደግሞ ሜዶንና ፋርስ (ዳን.8፡20)፣ ሶስተኛው ግሪክ (ዳን.8፡21)። ከነዚህ
መንግስታት በኋላ ሮም እንደ መጣች ታሪክ በማያጠራጥር መንገድ ያስረግጥልናል።
ዳንኤል 2 ላይ ሮምን የወከለው ብረት እኩሉ ብረት እኩሉ ሸክላ ሆኖ
እስከተቀላቀለው የእግሩ ክፍል ድረስ ይዘልቃል። ያም እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ
ነው። ዳንኤል 7 ላይ የምናገኘው ትንሹ ቀንድ ከአራተኛው አውሬ ጋር የመጣ ነገር
ግን የዚህ አራተኛ አውሬ አካል ሆኖ የቀጠለ ነው።
ከሮም ዘንድ ወጥቶ ለ1260 አመታት የፖለቲካና ሃይማኖታዊ ተፅዕኖውን
ያሳረፈው የትኛው ሀይል ነው? (ዳን.7፡25ን ተመልከቱ ከታሪክ እና ትንቢት ጋር
ገጣሚ የሆነ አንድ ሀይል ቢኖር ጳጳሳዊው ሮም ነው። ጳጳሳዊው ሮም ወደ ስልጣን
የመጣው ከአውሮፓውያን አስር ባርቤሪያ ነገድ መሪዎች ውስጥ ሶስቱን ከነቃቀለ
በኋላ ነው (ዳን 7፤24)። ጳጳሱ “ከቀደሙት ሁሉ ይለያል” (ዳን.7፡24)።
ከሌሎች
ነገዶች ለየት የሚያደርገው ነገር ተገልጾልናል። ጳጳሳዊው ሮም “በልኡሉም ላይ
የስድብን ቃል ይናገራል” (ዳን 7፤25)። እናም “እስከ ሰራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን
ታላቅ አደረገ” (ዳን.8፡11)። የክርስቶስን ስልጣን ነጥቆ ጳጳሱ በርሱ ቦታ ለመተካት
ጣረ። ጳጳሳዊው ስርአት የስደትን ትንቢትም ፈጽሟል “እስከ ሰማይ ሰራዊት ድረስ
ከፍ አለ” (ዳን.7፡25) ብዙዎችንም “ወደ ምድር ጣለ” (ዳን.8፡10)። ይህ የሆነው
ፕሮቴስታንቶች ባመጡት የተሃድሶ ንቅናቄ ምክንያት ሲታረዱ ነው”። ጳጳሱ
“ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል” (ዳን.7፡25)። ይህን የሚያደርገውም
ሁለተኛውን ትዕዛዝ በማስወገድና 4ተኛውን ትዕዛዝ ሰንበትን ወደ እሁድ ቀን
በመቀየር ነው።
ዳንኤል 2፣ 7 እና 8 ላይ እንደምናገኘው ከግሪክ በኋላ
እስከመጨረሻው ዘመን ድረስ የሚቆይ አንድ ሀይል ተነሳ ይለናል።
አሁን ጳጳሳዊ በሆነ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም ከሮም ውጪ ይህ ሃይል
ማን ሊሆን ይችላል? ከፖለቲካ አንፃር ትክክል እንዳልሆነ ተደርጎ
ቢያስቡም ወቅታዊ እውነትን ያዘለውን የሶስቱን መላዕክት መልዕክት
መማር ወሳኝ የሆነው ለምንድነው?
በዚህ ሳምንት የምናጠናው የትንቢት ማብራሪያ ከተሃድሶ ንቅናቄ አንስቶ ለነበሩ የፕሮቴስታንት ታሪክ አጥኚዎች አድካሚ ሆኖባቸው ነበር። ነገር ግን በ1800 አጥቢያ ላይ እስከነበረው የሚለራይትስ እንቅስቃሴ ድረስ የ2300 ቀናትና የፍርድ ምርመራ ጉዳይ በትኩረትና በጥንቃቄ አልተጠናም ነበር። የሚከተለውን መረጃ ተመልከቱ ዳንኤል 7 ዳንኤል 8 ባቢሎን (አንበሳ) ------ሜዶና ፋርስ (ድብ) ሜዶና ፋርስ (አውራ በግ) ግሪክ (ነብር) ግሪክ (አውራ ፍየል) አረማዊ ሮም (አራተኛው አውሬ) አረማዊ ሮም (ወደ ጎን የሰፋው ቀንድ) ጳጳሳዊው ሮም (ትንሹ ቀንድ) ጳጳሳዊው ሮም (ወደ ላይ ከፍ ያለው ቀንድ) ዳን.7፤9-14፤ 8፡14፣ 26ን አንብቡ። በዚህ ጥቅስ ላይ እንደምናገኘው በሰማይ ምን እየተከናወነ ነው?
ጳጳሱ በጄኔራል ባርተር ተይዞ በመታሰር የመካከለኛው ጊዜ ስደት በ1798
ላይ ካበቃ በኋላ (ራዕይ 13፡13)፤ዳንኤል 7 እና 8 ላይ ስለ ፍርድ ይነግረናል። በሰማይ
ፍርድ እንደሚካሄድ “ፍርድም ሆነ” (ዳን.7፡10) እናም “የሰው ልጅ የሚመስል
ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ” (ዳን.7፡13)። ይህ
የፍርድ ትእይንት ከ1798 በኋላ ከየሱስ ዳግም ምፅዓት በፊት የሚሆን ነው።
ዳንኤል 7 ላይ የምናገኘው የፍርድ ትዕይንት ዳንኤል 8፡14 ላይ ካለው
የቤተ መቅደሱ መንፃት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። ሁለቱም ክፍሎች የሚናገሩት
ተመሳሳይ ስለሆነ ነገር ነው። በዳንኤል 8፡14 መሰረት “የቤተ መቅደሱ መንፃት
ጊዜ የመንፃት ቀን የሆኑትን 2300 ማታና ጠዋትን ወይንም ቀናትን ይገልጽልናል።
በአመት-ቀን መርህ መሰረት እነዚህ ቀናት 2300 አመታትን ይወክላሉ።
የ2300 አመታት ጅማሮ መነሻው የሚገኘው ዳንኤል 9፡24 ላይ ሲሆን የሰባ ሱባኤ
(490 አመታት) ትንቢት በዚህ ራዕይ ውስጥ ተቀጥሯል።
በርግጥም ብዙ ሊቃውንት በትክክል የዳንኤል 8:14ቱን የ2300 ቀናት
(አመታት) ትንቢትንና የዳንኤል 9:24-27 የሰባው ሱባኤ ትንቢትን የአንድ ትንቢት
ሁለት ክፍል አድርገው ነው የሚያዩት። ስለ ሰባ ሱባኤው የምናገኘው ቀጣይ ቁጥር
የሚገኘው ዳንኤል 9:25 ላይ ሲሆን የዚህን የጊዜ መጨረሻ ይነግረናል “ኢየሩሳሌምን
መጠገንና መስራት ትዕዛዙ ከወጣበት ጀምሮ” ። የዚህ ክስተት ጊዜም ”በንጉሱ
በአርጤክስስ በሰባተኛው አመት“ (ዕዝራ 7:7) ወይም 475 ከ.ክ.ል.በፊት ላይ ነው።
ከዚህ ተነስተን ወደፊት 2300 አመታትን ስንቆጥር 1844 ላይ እንደርሳለን። ይህም
ከ 1798 ብዙም ሳይርቅ ከክርስቶስ ዳግም ምፃት በፊት የሚሆን ነው። ይህ ወቅት
የሱስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የማማለድ ስራውን የጀመረበትና የሰማያዊው ቤተ
መቅደስ የነፃበት ጊዜ ነው።
በአርብ ቀን ላይ የሚገኘውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ።
እንደሚተረጉምው የጥናት ዘዴ(typology) ሆኖ ሲቀርብ
በትንቢት ውስጥ ባለው ራዕይ በዳንኤልና ራዕይ መጽሐፍ የምናገኛቸው
ተምሳሌታዊ ነገሮች አንድ የመጨረሻ ፍጻሜ ነው ያላቸው። ለምሳሌ አውራው ፍየል
የተባለው ግሪክ፣ አንድ መንግስት ነው (ዳን.8፡21)። ጥቅሱ ራሱ ግልፅ አድርጎ በስም
ገልጾልናል! እንዴት ታዲያ የበለጠ ግልጽ አይሆንልን?
ይህ የትምህርት ጥናት ክፍል ትኩረት ያደረገው በአንድ የተለየ ሰው፣
ክስተቶች፤ ወይንም በታሪክ እውነታ ውስጥ በብሉይ ኪዳን ስለምናገኛቸው ነገሮች
ደግሞም ወደፊት ስለሚጠብቁን ታላላቅ እውነቶች ነው። ይህንን ዘዴ እንደ የንግግር
መፍቻነት የሱስ በአዲስ ኪዳን ደራሲያን ጽሁፍ ውስጥ እንዲሁም ብሉይ ኪዳን
ውስጥም ሲጠቀሙበት ይታያል። ይህ እንዲህ ነው ወይም አይደለም ብለን ለማወቅ
የምንችለው በመንፈስ ተነድተን ቃሉን የጻፉ ደራሲያን ለይተው ሲያስቀምጡልን
ብቻ ነው።
1ቆሮንቶስ 10፡1-13ን አንብቡ። ምን አይነት የታሪክ ክስተትን ጠቅሶ
ነው ጳውሎስ የቆሮንቶስን ቤተክርስቲያን የገሰፀው? ይህ ሁኔታ ከኛ
ጋር እንዴት ይዛመዳል?
ጳውሎስ በዘፀአት ጊዜ ወደነበረው የታሪክ ሁኔታ በመመለስ ጥንታዊ ዕብራውያን በምድረበዳ ያሳለፉትን ልምድ በመጥቀስ ይህንን ሃሳብ አጠነከረ። በዚህ መንገድ ጳውሎስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንዲጽፍ መርቶታል “ይህ ምሳሌ ሆነልን” (1ቆሮ.10፡6)፤ በመጨረሻ ዘመን የምንኖር መንፈሳዊ እስራኤሎች በፈተና እንድንጸናም ያስጠነቅቀናል። ከታች ያሉትን ጥቅሶች አንብቡ እና የሱስ እና የብሉይ ኪዳን ደራሲያን የገለፁትን የተለየ ክስተት ፃፉ። ማቴ.12፡40
ዮሐ.19፡36
ዮሐ.3፡14፣ 15
ሮሜ.5፡14
ዮሐ.1፡29
በእያንዳንዱ ጉዳይ ውስጥ የሱስ እና የአዲስ ኪዳን ደራሲያን
እንደጠቀሱልን ታሪኮች እንድንሆን ወይንም እንዳንሆን በሚል ሃሳብ
መተርጎማቸው የትንቢትን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳየናል። በዚህ
መንገድ የታሪክ እውነታ ፍፃሜን ያመለክቱናል።
እንደ ድነት እቅድ መግለጫ ያገለግል የነበረውን የምድራዊ ቤተ
መቅደስ አገልግሎት እስቲ አስቡ። በጣም ወሳኝ ስለሆነው የቤተ
መቅደስ መልዕክት ይህ ትምህርት ዛሬ ላይ ምን ያስተምረናል?
Read Clifford Goldstein, 1844 made simple (Boise, FR:
Pacific Press, 1988) as one place, of many, to find more material on the
2300 day prophecy. See also 1844 made simple org.
ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ አጥኑ
ዳንኤል 7
ዳንኤል 8
ባቢሎን (አንበሳ)
ሜዶና ፋርስ (ድብ)
ሜዶና ፋርስ (አውራው በግ)
ግሪክ (ነብር)
ግሪክ (አውራው ፍየል)
አረማዊ ሮም (አራተኛው አውሬ)
አረማዊ ሮም (ወደ ጎን የሰፋው ቀንድ)
ጳጳሳዊ ሮም (ትንሹ ቀንድ)
ጳጳሳዊ ሮም (ወደላይ ከፍ ያለው ቀንድ)
ፍርድ በሰማይ
የሰማዩ ቤተ መቅደስ መንፃት
በዳንኤል 7 የምናገኘው የፍርድ ትዕይንት ወሳኝ ነው። የሆነውም ከ1260
የስደት አመታት በኋላ ነው (ዳን.7፡25)። በዳንኤል 8፡14 ካለው የቤተ መቅደሱ
መንፃት ጋር ተመሳሳይ ነው። በሰማይ ያለው የፍርድ ትዕይንት በሚያሳዝን ሁኔታ
በወደቀው ምድራችን መጨረሻ ላይ ወደሚመሰረተው ወደ እግዚአብሔር መንግስት
ይመራናል። እዚህ ላይ በዳንኤል 8፡14 ለተጠቀሰው ሃሳብ ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ
ማስረጃዎችን እናገኛለን።
1.መለስ በሉና ዳንኤል 2ን ከልሱ። ታሪክን መሠረት ያደረገ ዘዴ እዚህ
ጋ እንዴት እንደተገለፀ ተመልከቱ፡ የተያያዙ የዓለም መንግስታት
በቅደም ተከተላቸው ከጥንት ጀምሮ ከተነሱ በኋላ በእግዚአብሔር
ዘላለማዊ መንግስት መመስረት ይጠናቀቃል። እግዚአብሔር እነዚህን
ትንቢቶች እንድንፈታ ቁልፉን ሰጥቶናል። በአሁኑ ሰአት በክርስቲያኑ
አለም ውስጥ በጣም ጥቂቶች ታሪክን መሠረት ያደረገ ዘዴን በመተርጎም
የሚጠቀሙ ቢኖሩም ይህ ምን ይነግረናል? ይህ እውነታ ከአድቬንቲስት
መልዕክት ጋር የተያያዙትን ጉዳዮች በዚህ ወቅት ለአለም ለመናገር
እንዴት አድርጎ ያግዘናል?
2.የዳንኤል 8፡24ን 2300 የትንቢት ጊዜያት ምን ያህል አስተዋላችሁት?
ካላስተዋላችሁት ከውይይት ክፍልዎ ጋር ለመካፈል እንድትችሉ ለምን
ለመማር ጥቂት ጊዜ አትወስዱም? በትንቢት የመሰረት እውነት ላይ
በጽኑ መመስረታችን ሊያስደንቅዎ ይችላል።
3.ዳንኤል 7፡18፣ 21፣ 22፣ 25፣ 27ን አንብቡ። ቅዱሳን ላይ ምን
እንደሚደርስ አስተውሉ። የትንሹ ቀንድ ሐይል ምን ያደርጋቸዋል?
ጌታስ በተቃራኒው ምን ያደርጋል? ፍርድን በተመለከተ ለቅዱሳን
ያላቸው መልካም ዜና ምንድነው? በስተመጨረሻ ፍርዱ ምን
ያመጣላቸዋል?