መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንተርጉም
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 2ኛ ሩብ ዓመት 2020

ሰኔ 6-12

12ኛ ትምህርት

Jun 13 - Jun 19




ከባድ ጥቅሶችን ለመረዳት መጣር



ሰንበት ከሰዓት

የሚከተሉትን ጥቅሶች ለዚህ ሳምንት ጥናት አንብቡ፦ 2ጢሞ.2፡10-15፤ 1ቆሮ.29፡ 17፤ ያዕ.4፡6-10፤ ሐዋ.17፡11


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “የጌታችንም ትዕግስት መዳናችሁ እንደሆነ ቁጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፡- በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነበረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ። ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻኅፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።” (2ጴጥ.3፡15-26) ።

ስ ለ ጳውሎስ ደብዳቤ በምንወያይ ጊዜ ጴጥሮስ በሌላ ስፍራ ላይ እንደፃፈው “ለማስተዋል የሚያስቸግሩ” አንዳንድ ነገሮች አሉ (2ጴጥ.3፡16) ። እነዚህ ቃላቶች “ባልተማሩ እና ባልጸኑ ሰዎች” በኩል ለገዛ ጥፋታቸው የሚያጣምሙ እና የሚያበላሹ ናቸው። ጴጥሮስ አንዳንድ ጥቅሶች ብቻ እንጂ ሁሉም ጥቅሶች ለመረዳት አዳጋች ናቸው እያለን አይደለም። ይህንን እናውቃለን አይደል? ታማኝ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎች እንግዳና ለመረዳት ከባድ የሆኑ ጥቅሶች አላጋጠማቸውምን? በእርግጥም የሆነ ጊዜ ላይ ሁላችንም እንዲህ አይነት የህይወት ልምምድ ገጥሞናል።

ለዚህም ነው በዚህ ሳምንት የምንመለከተው ነገር ቢኖር ከባድ ጥቅሶችን በስፋት ለማየት ብቻ ሳይሆን ከባድ እንዲሆኑ ያደረጋቸውን ምክንያት እና ከእግዚአብሔር ቃል ላይ እውነትን እንደሚፈልጉ ታማኝ ሰዎች እነዚህን ጥቅሶች በምን መልኩ እንደምናጠና ነው። በስተመጨረሻም አንዳንድ አስቸጋሪ አረፍተ ነገሮች አሁን ባለንበት ሁኔታ ምላሽን ላያገኙ ይችላሉ። በተመሳሳይ ጊዜም በስፋት የተገለፀልን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከባድ ባለመሆናቸው በጣም ጥቂት ከባድ የሆኑ ጥቅሶች ስላሉ በእግዚአብሔር ቃል ስልጣን ላይ ያለንን መተማመን እንዲያዳክሙ መፍቀድ የለብንም። የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንታችሁ ለግንቦት 22 ሰንበት ተዘጋጁ።

ሰኔ 07
Jun 14

ግልጽ ተቃርኖ በጥቅሶች መካከል እንዲኖር የሚያደርጉ ሁነኛ ምክንያቶች


2ጢሞ.2፡10-15ን አንብቡ። ጳውሎስ ጢሞቲዎስን እንዲተጋ ያስጠነቅቀዋል፡ “የእውነትን ቃል በአግባቡ እንዲይዝ” ። ለኛ ወሳኝ የሆነ መልዕክትን እየሰጠን ያለው እንዴት ነው?





የትኛውም ጥልቅ አሳቢ እና ታማኝ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ለመረዳት የሚያዳግቱ ክፍሎች እንዳሉ አይክድም። በትክክልም እነዚህ ከበድ ያሉ ክፍሎች እንዳሉ ይጠበቃል። ሁላችንም ፍጽምና የጎደለንና ውሱን ፍጥረቶች ነን፣ የመለኮታዊው ነገር ይቅርና ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ላይ እንኳን ሙሉ እውቀት ያለው ሰው ለም። ስለዚህ ያልተማረ እና ውሱን የሆነው የሰው ልጅ ወሰን የለሽ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት ሲጥር አንዳንድ ከባድ እና አዳጋች ነገሮች ይገጥሙታል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለመረዳት መቸገራችን በራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ እንዳልሆነ በምንም መልኩ አያረጋግጥልንም።

የመለኮት መገለጥና ምሪት የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያጠፋ ሁሉ እነዚህን ከባድ ክፍሎች የተሳሳቱና እርስ በርስ የሚጣረሱ እንደሆኑ ይናገራል። ምክንያቱም ለእነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የጻፉት መጽሐፍ ስለሆነ ፍጹም ያልሆነና ስህተት የሞላበት ነው። በዚህ አረዳድ የእግዚአብሔር ቃልን አንድነትና ተአማኒነት ከመለኮት ምሪት እንደመጣ የሚገልጸውን ሀሳብ ለመረዳት የሚደረግ ጥረት የለም። መጽሐፍ ቅዱስን ስለ ፍጥረት ጉዳይ (ለምሳሌ) የተጻፈውን የመጀመሪያ ገጾች ላይ በተጻፈው ሃሳብ ጥያቄ ያለው ሰው ወዲያውኑ የተቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም ጥርጣሬ እና አለመተማመን ሊፈጠርበት ይችላል።

በቃሉ የምናገኛቸው አንዳንድ ልዩነቶች ከፊደል ጸሐፊዎች ወይንም ከጽሑፍ ተርጓሚዎች የሚመነጩ ጥቃቅን ግድፈቶች ናቸው። ኤለን ጂ. ኋይት እንደምትገልጽልን፡- “አንዳንዶች በሀዘኔታ እየተመለከቱን “ፊደሉን በሚጽፉ ወይንም የጽሑፉ ትርጉም በሰሩ ሰዎች በኩል አንዳንድ ስህተቶች እንዳልተፈጠሩ ታስባላችሁን?” ይላሉ። ይህ ሊሆን ይችላል፣ ጠባብ የሆነው አዕምሮ ግን ሊሆን ወይንም ሊከሰት ይችላል በሚል የተደናቀፈ ሀሳብ ሚስጥራዊ በሆኑ የምሪት ቃላት ይደናቀፋል። ምክንያቱም ደካማ የሆነው አስተሳሰባቸው ይህንን ከእግዚአብሔር አላማ አንፃር ማየት ስለማይችል ነው። አዎ የትኛውም ሰው ሊቀበለው በሚችለው ግልፅና ቀላል ነገር እንኳን ይደናቀፋል። መለኮትን መረዳት ማለት የእግዚአብሔር ንግግር ግልጽና የተዋበ እንዲሁም ተመራጭ በሆኑ ግብአቶች የተሞላን ሃሳብ መረዳት ነው። በጣም ግልጽ ሆኖ ከተገለጠው እውነት የወጡ ሁሉም ግድፈቶች ለአንድ ነፍስ ችግር ለመፍጠር ወይም የሰዎችን እግሮች እንዲያሰናክሉ ለማድረግ የቀረቡ መንስኤዎች አይደሉም።” – Ellen G. White, selected messages, book 1, p. 16.

መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ በትህትና እና በመሰጠት መንፈስ ማንበባችን ወሳኝ የሆነው ለምንድነው?

ሰኔ 08
Jun 15

ከባድ ጥቅሶችን በታማኝነት እና በጥንቃቄ ለመረዳት መሞከር


ልትረዷቸው የተቸገራችሁባቸው ጥቅሶች ወይም የጥቅስ ስብስቦች ከሌሎች ጥቅሶች ጋር ወይንም ካለው እውነታ ጋር አልጣጣም ብሏችሁ ያውቃል? በአንድም ወይም በሌላ ጊዜ ይህ ችግር አላጋጠመም ብሎ መገመት አዳጋች ነው። ጥያቄው ታዲያ እንዴት ምላሽ ሰጣችሁ ወይንም ደግሞ ወሳኙ ጥያቄ እንዴት አድርጋችሁ መልስ ልታገኙ ትችላላችሁ? የሚል ነው። 1ዜና.29፡17፣ ምሳሌ 2፡7፣ 1ጢሞ.4፡16ን አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ከባድ የሆኑ ጥቅሶችን እንዴት ለመረዳት መጣር እንዳለብን ምን ይነግሩናል?





ታማኞች ስንሆን ብቻ ነው ከበድ ያሉ ጥቅሶች በበቂ ሁኔታ ሊገጥሙን የሚችሉት። ለመረዳት ከባድ የሆኑ ጥቅሶችን አድበስብሰን ወይም እንዲሁ ደብቀን እንዳናልፍ የሚጠብቀን ነገር ቢኖር ታማኝነታችን ነው። ታማኝነት ጥራዝ ነጠቅ ከሆነና በጥልቀት ካልተመረመረ ምላሽ እንድንቆጠብ ያደርገናል። እግዚአብሔር በታማኝነት እና በሀቀኝነት ይደሰታል። ስለዚህ በምናደርገው ድርጊት ሁሉ ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ላይ ሳይቀር ይህንን ባህሪ ለማስረፅ መሞከር አለብን።

ታማኝ የሆኑ ሰዎች ከባድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት ሲሞክሩ የሚያቀርቡት መረጃ ከአውዱ እንዳልወጣ፣ በቋንቋቸው በኩል እውነቱ እንዳልተበረዘ ወይንም ደግሞ ሌሎችን ለማሳመንና ወደ ስህተት እንዳይመሩ ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ከባድ በሆኑ ጥቅሶች ዙርያ የተድበሰበሰ ወይንም በቂ ያልሆነ መልስ ከመስጠት ይልቅ እርግጠኛ የሆነ ምላሽ እስክናገኝ ጊዜ ሰጥቶ መጠበቅ የተሻለ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጊዜ ታማኝ የመሆናችን አዎንታዊ ጎኑ መተማመንን ስለሚገነባልን ነው። መተማመን ደግሞ ጤነኛ ለሆነ የእርስ በርስ ግንኙነቶች አንኳር የሆነ ነገር ነው። ይህ ሰዎችን ያሳምናቸዋል። የማይመስል ምላሽ ከመስጠትና ጥቅሱ ያላለውን እናንተ ግን ማለት የፈለጋችሁትን ነገር ለመናገር ከመሞከር ይልቅ ለጥያቄዎቹ መልስ መስጠት እንዳልቻላችሁ መናገር ወይም ተገቢውን ትንተና መስጠት እንደተቸገራችሁ መግለጽ ይሻላል።

ጠንቃቃ የሆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እውነት በጉጉት ለማወቅ ይፈልጋሉ። በዚህም ውሱን በሆነ እውቀት ወይንም የማይመስል መረጃ ላይ ተመስርቶ የተቻኮለ ድምዳሜ ላይ እንዳይደርሱ በቀጣይነት ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ጠንቃቃ ሰዎች ማንኛውንም ወሳኝ የሆነ እይታ ወይንም ዝርዝር ሃሳብ ቸል ብሎ ከማለፍ የተቆጠቡ ናቸው። በአስተሳሰባቸው ችኩሎች አይደሉም ነገር ግን የቃል ጥናታቸውንና ተዛማጅ መረጃዎችን ለማግኘት በጥልቀትና በትጋት ይሰራሉ። ሙሉ በሙሉ መረዳት ያስቸገርዎ ወይንም ስለ እውነት ካለዎት መረዳት ጋር አልጣጣም ያልዎት ጥቅስ ሲገጥሞት ምን ያደርጋሉ? ምን ቢያደርጉስ ይመረጣል?

ሰኔ 09
Jun 18

ከባድ ጥቅሶችን በትህትና ለመረዳት መሞከር


ያዕ.4፡6-10፤2ዜና. 7፡14 እና ሶፎ.3፡12ን አንብቡ። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያሉትን ከባድ የሆኑ ጥቅሶች ለመረዳት ትህትና ምን ያክል አስፈላጊ ነው?





ብዙ ሰዎች በአንድ ነገር ላይ፣ ከእነርሱ ውጪ በሆነ ነገር ላይ ጥገኛ ስለመሆናቸው በአስደናቂ ሁኔታ ተረድተዋል። የትህትና እይታንም ሰጥቷቸዋል። እነርሱ የሁሉም ነገር መለኪያ እንዳልሆኑ ተረድተዋል። እነዚህ ሰዎች የራሳቸው ሃሳብ ልክ ነው ከማለት ይልቅ ለእውነት ዋጋ ይሰጣሉ። እውነት ደግሞ እነርሱ የፈጠሩት ሳይሆን የሚያገኙት ነገር እንደሆነ ያውቃሉ። ምናልባትም እነዚህ ሰዎች የተረዱት ታላቅ እውነት ቢኖር ስለ እውነት ጥቂቱን ብቻ ማወቃቸውን ነው። እነርሱ የሚያውቁት ጳውሎስ እንደጻፈው “በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ” (1ቆሮ.13፡12) የሚለውን ሀሳብ ነው።

የዚህ ትህትና አስተሳሰብ ጥቅሙ በጣም ብዙ ነው፡- የትህትና ልማድ በሁሉም የእውቀት ዘርፍ የማደግ መሠረት ነው። ይህም ለመማር ፈቃደኛ የሆነ መንፈስን በመፍጠር ነፃነትን ይሰጣል። ይህ ማለት ታዲያ ትሁት የሆኑ ሰዎች በብዛት ይሳሳታሉ ማለት አይደለም ወይም ደግሞ ሁልጊዜ ሃሳባቸውን የሚለውጡና ፅኑ አቋም የሌላቸው ናቸው ማለት አይደለም። ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ብቻ ራሳቸውን የሰጡ ናቸው። የእውቀታቸውን ውሱንነት ስለሚረዱ የዚህ አለም አዋቂ፣ ትምክህተኛ እና ኩራተኞች የሚያደርጉትን ስለቃሉ ያላቸውን እውቀትና መረዳት ለማስፋት አቅሙ አላቸው። “በምሪት፣ በትሁትና፣ በሚጠይቅ አዕምሮ፣ በጽናትን ለማወቅ ቆረጦ፤ ቃሉን በማንበብ ለቀረበ ማንኛውም ሰው ቃሉ የሚናገረውን ማስተዋል ይችላል። መንፈስ ያላረጋገጠውን ቃል በመመርመር የሚመጡ ሁሉ ያለአድሎዎ የሚመረምረው መንፈስ ውጪ ይሆናሉ። ጌታ ግድየለሽ ለሆነ አዕምሮ አይናገርም።

ፈቅደው ሃሳባቸው ለተበከለና አክብሮት ለሌላቸው ሰዎች ምሪቱን አያባክንም። ነገር ግን ፈታኙ ወደራሱ ሃሳብ ለመሳብ የእያንዳንዱን አዕምሮ ያስተምራል ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ሕግ ከንቱ እንዲሆንም ይፈልጋል። “ልባችንን ትሁት አድርገን በቅንነትና በአክብሮት የህይወትን ቃል እንመርምር፡- ትሁት የሆነውና ተፀፅቶ የሚመለስ አዕምሮ ብቻ ነው ብርሃንን ሊያይ የሚችለው” The Advent Review and Sabbath Herald, August 22, 1907. በትህትና እና እርግጠኛ በመሆን መካከል ያለውን ትክክለኛ ሚዛን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? ለምሳሌ ይህንን መጠይቅ እንዴት እንመልሰዋለን? ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ስለ ሰንበት ጉዳይ ትክክለኛ መሆናችሁንና ሌሎች ግን የተሳሳቱ ስለመሆናቸው በምን ሁኔታ እርግጠኛ ትሆናላችሁ?

ሰኔ 10
Jun 19

ቆራጥነትና ታጋሽነት


ገላ.6፡9ን አንብቡ። ለሌሎች መልካም ስናደርግ በጽናት ማድረግ እንዳለብን ጳውሎስ እንደነገረን ሁሉ ከባድ ጥያቄዎችን ለመረዳት ስንሞክርም መያዝ ያለብንም ተመሳሳይ አመለካከት ነው። ችግሮችን ስንፈታ ቆራጥነትና ታጋሽ መሆን አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው ?





ታላቅ የሆነ ስኬት ሁልጊዜ ጥንካሬን ይፈልጋል። በቀላሉ ያገኘነውን ነገር ብዙ ጊዜ ቀላል አድርገን የማየት ነገር አለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸው ከባድ የሆኑ ክፍሎች ጭንቅላታችን እንዲሰራና በቆራጥነት እና በትዕግስት ምላሽ እንድንፈልግ ስለሚያደርገን ጉዳዩ ምን ያክል ወሳኝ እንደሆነ ይገልጽልናል። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ትርጓሜውንና መልዕክቱን የበለጠ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት የጠፋ ጊዜ ሁሉ በመልካም ሁኔታ የጠፋ ጊዜ ነው። ምናልባትም በትጋት የመጽሐፍ ቅዱስን ምላሽ ለረጅም ጊዜ ለማግኘት መጣር በስተመጨረሻ ላይ ለችግሩ ምላሽ ካገኘንለት ጉዳይ ይልቅ ታላቅ በረከት ያለው ነው። ተስፋ ለሚያስቆርጥ ችግር መፍትሄ ማግኘት በራሱ እጅግ የተዋበ ነገር ነውና።

ፈጥነን እነዚህን ከባድ ነገሮች መፍታት አልቻልንም ማለት መፍትሄ የላቸውም ማለት አይደለም። ይህንን የማስረጃ እውነታ የምናይበት መንገድ አስገራሚ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቸጋሪ ክፍል ሲገጥማቸው ትንሽ ሙከራ አድርገው ምላሽ ባጡ ጊዜ ወዲያውኑ ለዚህ ችግር መፍትሄ የለውም ብለው የሚደመድሙ ብዙዎች ናቸው። አንዳንዶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተአማኒነት ላይ ጥያቄን ያነሳሉ። ነገር ግን መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ማየት ተስኖን ሳናውቅ ቀርተን ወይንም ደግሞ የሰው ልጆች ጥበብ ውሱን ሆኖ እንጂ ምናልባት ምላሹ በጣም ቀላል ይሆናል። የአልጄብራን ሂሳብ ትምህርት ገና የጀመረ ሰው ከባድ የሆነን ክፍል ለመስራት ግማሽ ሰአት ቢወስድበትና በከንቱ ቢደክም እርሱ መልሱን ማግኘት ባለመቻሉ መፍትሄ ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም ብሎ ሊናገር ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንም ልክ እንዲሁ ተመሳሳይ ነው።

ምላሽ ለማግኘት ጠንካራ ጥረት እያደረጋችሁ እንኳን አንዳንድ ከባድ የሆኑ ክፍሎች ቢገጥሟችሁም ለጊዜው ተወት አድርጉትና በዚሁ ጊዜ እግዚአብሔር ግልጽ ያደረገላችሁን ነገር ተለማመዱት። አንዳንድ መንፈሳዊ እይታዎች የሚገኙት እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድናደርገው የነገረንን ነገረ ለመከተል ፈቃደኛ ከሆንን በኋላ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠኑ ጽኑ እና ታጋሽ ሁኑ። ትዕግስት በመጨረሻው ጊዜ የአማኞች ባህርይ መገለጫ ነው። (ራዕይ 14፡12ን ተመልከቱ) ። በትጋት እና በትዕግስት አስቸጋሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ከሚያጠኑ ሰዎች ምን እንማራለን? እውነትን ለመመርመር ተስፋ እንዳይቆርጡ ሌሎችን እንዴት አድርገን እናበረታታቸው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከባድ ክፍሎች ሲያጋጥሙን ልንፈራና ልንጠነቀቅ የሚገባን ለምንድው?

ሰኔ 11
Jun 20

ከባድ ክፍሎችን በቃሉ እና በፀሎት ለመረዳት መሞከር


ሐዋ.17፡11፣ ሐዋ.8፡35፣ ሐዋ.15፤150-16ን አንብቡ። ሐዋርያትና የቀደመችው ቤተክርስቲያን አባላት ከባድ ጥያቄዎች ሲገጥሟቸው በእንዴት ያለ መንገድ ተጋፈጡ? አሁንም ቃሉ ራሱን በራሱ መተርጎሙ ምርጡ የመነሻ ሀሳብ ሊሆን የቻለው ለምንድነው?





ለመጽሐፍ ቅዱስ ከባድ የሆኑ ክፍሎች ምርጡ መፍትሄ አሁንም የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ከባድ ክፍሎች ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተነጥሎ በተወሰደ አንድ ጥቅስ ላይ ከመመስረት ይልቅ የበለጠ መረዳት የምንችለው ከሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከምናገኘው ብርሃን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት በርግጥም መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም አለብን። በቃሉ ውስጥ ያለውን እውነት ለመቆፈር መማር ልናደርግ ከሚገቡን ወሳኝ ነገሮች አንዱ ነው።

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን መረዳት ካልቻላችሁ በተመሳሳይ ርዕስ ላይ ከተፃፉ ሌሎች ጥቅሶች ላይ ብርሃናትን ለማግኘት ጣሩ፡፤ እምብዛም ግልጽ ካልሆኑቱ ይልቅ ሁልጊዜ ግልጽ ከሆኑ ክፍሎች የሚፈነጥቀውን ብርሃን እሹ። ግልጽ የሆኑ አረፍተ ነገሮች ላይ ለመረዳት የሚከብዱ ክፍሎችን በማምጣት ግልጹን መልዕክት ልናጨልም ወይም ልናዳፍን አይገባም። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ አጣቃሽ ምንጮችን ወይንም ፍልስፍናዎችን ወይንም ሳይንስን እንደተጨማሪነት ከመጠቀም ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ራሱን በራሱ እንዲፈታልን ልንፈቅድ ይገባናል። እንደምናውቀው ስንንበረከክ ከባድ የሆኑ ነገሮችን አዲስ በሆነ እይታ ማየት እንጀምራለን። በጸሎት ስንቀርብ እያልን ያለነው ነገር ቢኖር ቃሉን ለመፍታትና ለመረዳት የመለኮት እርዳታ ያሻናል ነው። ስንጸልይ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲያንን የመራው ያው መንፈስ ቅዱስ አዕምሮአችንን እንዲያበራልን እየፈለግን ነው ማለት ነው።

ስንጸልይ የውስጥ ሀሳባችን ይከፈታል እናም የምናነበውን ነገር ለምን መረዳት እንደፈለግን ለእግዚአብሔር መንገር ይቻለናል። ስንጸልይ እግዚአብሔር ለቃሉ አይኖቻችን እንዲከፍት እና የእርሱን እውነት ለመከተልና ለመለማመድ የእሺታን መንፈስ እንዲሰጠን እየጠየቅነው ነው። (ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው!) ። ለፀሎታችን ምላሽ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኩል ሲመራን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገለጠው እውነት ጋር አንቃረንም። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲያን ለኛ ከፃፉልን ነገር ጋር በመጣጣም ቃሉን ያረጋግጥልናል። ፀሎት የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ ለመረዳት እና ለመታዘዝ ትክክለኛው የአስተሳሰብ ሁኔታ እንዲኖረን አድርጎ የሚያግዘን እንዴት ነው?

ሰኔ 12
Jun 21


ተጨማሪ ሐሳብ


Read Ellen G. White, ~What to do with doubt?` pp. 105-113 in steps to chirist. Read section 8 in the document` Methods of Bible study` which can be found at http:///www.adventistbiblicalresearch.org/materials/bible-interpretation-hermenutics/methods-bible-study. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ውስን የሆነው የሰው ልጅ ሊረዳቸው የሚከብዱት ብዙ ሚስጥራዊ ነገሮች እና ሙሉ ለሙሉ ለመግለጽ ጥልቅ የሚሆኑብን ነገሮች አሉ። ለዚህም ነው ትሁት የሆነ ልብ እና ከቃሉ ለመማር መጸለይ የሚያስፈልገን። ለቃሉ ታማኝ መሆናችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚነግሩን ሀሳብ ከእኛ መረዳት ጋር እንኳን ተቃራኒ ቢሆኑም ለቃሉ እንፈቀድለታለን። ለቃሉ ታማኝ መሆን ማለት ጥቅሶችን ከመለወጥ ይልቅ አክብሮ ይይዛቸዋል (አዎን፣ አንዳንዶች ጥቅሶችን ራሳቸውን ቀይረዋል) ወይንም ደግሞ ትክክለኛ ትርጉማቸውን ሸሽገዋል።

“የእግዚአብሔር ቃል ያለ አክብሮት እና ያለ ፀሎት ሲከፈት፣ ሃሳቦች እና የፍቅር ስሜቶች በእግዚአብሔር ላይ ካልተተከሉ ወይንም ከፈቃዱ ጋር ካልተጣጣሙ አዕምሮአችን በጥርጣሬ ጭጋግ ይሞላል። እናም ቃሉን ባጠናን ጊዜ ሁሉ የጥርጣሬ ሃሳቦቻችን ያይላሉ። ጠላት ሃሳቦቻችንን ይቆጣጠራል ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር ተርጉመን እንድናይ ሃሳብ ያቀርብልናል። ከቃሉ ጋር ያልሆኑ እና ከእግዚአብሄር ጋር ለመጣጣም ያልፈለጉ ሰዎች ሁሉ የተማሩ ቢሆኑም ቃሉን ሲረዱ ወደ ስህተት ሊመሩ እንደሚችሉ ያሳየናል። ስለዚህ ማብራሪያቸውን ለመረዳት ብለን በእነርሱ ላይ እምነት መጣል አስተማማኝ አይደለም። በጥቅሶች መካከል አለመጣጣም እንዳለ ለማግኘት የሚፈልግ ሰው መንፈሳዊ እይታ የሌለው ሰው ነው። በተበከለ እይታቸው ምክንያት ግልጽ እና ቀላል የሆነን ነገር እንዲጠራጠሩና እንዳያምኑ ይሆናሉ” Ellen G. white, steps to chirst, pp. 110, 111.


የመወያያ ጥያቄዎች




1.በዚህ ሳምንት ከተወያየነው ሀሳብ ውስጥ ቃሉን በትክክል ለመረዳት መሠረት የሚሆነን አስተሳሰብ ምንድነው? ቃሉን የበለጠ ለመረዳት የሚያግዙ ሌሎች ተጨማሪ አመለካከቶችስ ምንድናቸው?

2.መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማብራራት እና ለመረዳት አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮች በመኖራቸው ልንደነቅ የማይገባን ለምንድነው? ተፈጥሮአዊው አለም ራሱ እንኳን ለማስተዋል አዳጋች የሆኑ ስንት ነገሮች አሉት? እስከዚህ ወቅት ድረስ ለምሳሌ ውሃ ሚስጥራዊ በሆኑ ነገሮች ተሞልቶአል።

3.እንደ አድቬንቲስትነታችን የሉቃስ 23፡43ን ጥያቄ እንዴት ብለን ነው የምንመልሰው? (አብዛኛዎቹ የጽሁፍ ትርጉሞች) የሱስ ለዛ ሌባ ያለው በዛችው እለት ከእርሱ ጋር በገነት ትሆናለህ ነው። ለዚህ እውነተኛ ምላሹ ምንድነው? እንዴት ሆኖ ነው ለምሳሌ እንደ ዮሐ.20፡ 17፤ መክ.9፡5 እና 1ቆሮ.15፡16-20 ያሉ ጥቅሶች እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎቻችንን እንድንረዳ ሊያግዙን የሚችሉት?