ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ማቴ 4፡1-11፣ ማቴ 22፡3740፣ ሉቃ 24፡13-35፣ 44፣45 ፣ ሉቃ 4፡ 25-27፣ ሐዋ 4፡ 24-26
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ›› (ማቴ 4፡ 4)
በ
ሚያሳዝን ሁኔታ በዚህ ድህረ-ዘመናዊ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በሰፊው እየተተረጎመ
ያለው አተረጓጎሙን እና ስልጣኑን ጥያቄ ውስጥ ባስገቡ የፈላስፋዎች መነጽር
ስር ነው። በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ በብዛት የሰው ልጅ ገና ባላደገበት በጥንት ጊዜ
የነበረ አስተሳሰብ፣ በዚህ ዘመን ያለውን አለም ለማስተዋል በማይችልበት ሁኔታ ላይ
ያለ አስተሳሰብ እንደሆነ ይታያል። በተመሳሳይ ጊዜ መንፈሳዊ ነገሮቹ ተረስተዋል
ወይም ከምስሉ ተወግደዋል፣ መጽሐፍ ቅዱስን እግዚአብሔር ሰብአዊን ፍጥረት
ያየበት ከመሆን ይልቅ ሰው እግዚአብሔርን ወዳየበት ዶሴነት ተቀይሯል። እናም
ውጤቱ በዳርዊን አስተሳሰብ እና ዘመናዊ ፍልስፍና ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት
እንደማይረባ ተወስዷል።
ቢሆንም ግን ይህን አቋም እኛ ሙሉ በሙሉ አንቀበልም። ከዚህ ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ
በመነዳት ሁሉንም ጽሑፍ ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርት ብሉይ ኪዳንን ፣ በዚያን ጊዜ
የነበራቸው ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስን ማለት ነው ፣ የተረዱበትን መንገድ በማጥናት
መመልከት እንችላለን። እንዴት ነበር የተገለጹትን ሰዎች፣ ቦታዎች እና ኩነቶች
ያገናኙት? ግምቶቻቸው እና ለመተርጎም የተጠቀሙባቸው ተጓዳኝ መንገዶች ምን
ነበሩ? የተሳሳተ መረዳት ካላቸው እና ግምታቸው ወደ የእግዚአብሔር ቃል ክህደት
እና ጥርጣሬ ከሚወስዱን ሰዎች ይልቅ የእነዚህን (የኢየሱስን እና የሐዋሪያትን)
መንገድ እና መረዳት እንከተል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሚያዚያ 10 ሰንበት አጥንተው ይዘጋጁ።
በመጥምቁ ዮሐንስ የተደረገው የኢየሱስ ጥምቀት ለአዳኙ አገልግሎት መጀመሪያ መለያ ነበር፣ ያን ተከትሎ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ምድረበዳ ሔደ፣ ደካማ በሆነው የሰብአዊ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በሠይጣን ተፈተነ። ማቴዎስ 4፡1-11ን ያንብቡ። በምድረበዳ የሰይጣንን ፈተና ኢየሱስ እንዴት ነበር የተቋቋመው? ከዚህ ላይ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ልንማር የሚገባን ምንድን ነው ?
በምግብ ፍላጎት ሲፈተን ኢየሱስ ‹‹ ‹እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ
በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ››
በማለት ነበር የመለሰው። ኢየሱስ ወደ ኋላ ሔዶ ሕያውን ቃል ፣ የመጨረሻውን
እና ምንጩን ጠቀሰ። በዚህ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን ስልጣን አረጋገጠ። በአለም
መንግስታት እና በክብራቸው ኢየሱስ በተፈተነ ጊዜ ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ
ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና ። ››
(ማቴ 4፡10፣ ሉቃ 4፡8 ) በማለት መለሰ።
እዚህ ላይ ትክክለኛው አምልኮ ትኩረቱ
እግዚአብሔር ላይ እንጂ በሌላ ነገር ላይ እንዳልሆነ አስታወሰን፣ እናም ለቃሉ እራስን
መስጠት እውነተኛው አምልኮ ነው። በመጨረሻ ፣ በሚታይ ፍቅር ላይ እና በመዳፈር
ላይ በነበረው ፈተና ኢየሱስ ሲመልስ ‹‹ ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው
ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው። ›› (ማቴ 4፡7 እና ሉቃ 4፡12)።
በሁሉም ፈተናዎች ኢየሱስ ሲመልስ ‹‹ ተጽፏል ›› ከሚል ቃል ጋር ነበር። ያም
ከሰይጣን ጥቃት እና ፈተና ጋር ለመጋፈጥ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቃል በቀጥታ
ነበር የሔደው፣ ወደ ሌላ አልነበረም። ይህ ለሁላችን በጣም ሐይለኛ ትምህርት
ሊሆነን ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የመጨረሻው እና
ብቸኛው መመዘኛ እና የእምነታችን መሰረት ሊሆን ይገባል።
አዎ! ለባላጋራው ጥቃት መመከቻ ኢየሱስ የተጠቀመው መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ
እና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነበር። ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው፣ ነገር ግን ሰይጣንን
በተቋቋመበት ጊዜ እራሱን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ቃል ሰጠ።
አማራጭ አልነበረም፣ በጣም የተራቀቀ፣ ውስብስብ ክርክር አልነበረም ፣ የግል የሆነ
የጥላቻ የቃላት ልውውጥ አልነበረም። ከዚያ ይልቅ በጣም ቀላል ነገር ግን ቆይታው
መሰረት ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ነበር ። ለክርስቶስ መጽሐፍ ቅዱስ ታላቅ
ስልጣን እና ታላቅ ሐይል አለው። በዚህ መንገድ አገልግሎቱ በተረጋገጠ መሰረት
ተጀመረ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ተአማኒነት ላይ መገንባቱን ቀጠለ።
እንዴት ነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ መመካት እና እራስን መስጠትን
መማር የምንችለው?
ማቴዎስ 5፡-17-20ን፣ እና ማቴዎስ 23፡2፣3 ን ያንብቡ። በዚህ አውድ ስር ኢየሱስ እያለ ያለው ምንድን ነው?
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ያስተማራቸው የእግዚአብሔርን ቃል እና ሕጉን እንዲከተሉ ነው። በእርሱ ዘንድ የቅዱሳት መጽሐፍትን ስልጣን ወይም አስፈላጊነት ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት በፍጹም ምንም አይነት ፍንጭ አልነበረም። በተጻራሪው ያለምንም ማቋረት በተከታታይ እንደ የመለኮት ስልጣን ምንጭ ይጠቅሰው ነበር። እናም ለሰዱቃውያን እንዲህ አላቸው ‹‹ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ። ›› (ማቴ 22፡29)። ለኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት፣ እና አስተምህሮቱን ብቻውን ማወቅ አስፈላጊ የሆነውን እውነትን ለማወቅ በቂ አልነበረም። ማቴዎስ 22፡37-40 ለሙሴ ሕግ ኢየሱስ ስላለው እይታ/አመለካከት ምንድን ነው የሚነግረን?
ለህግ አዋቂው በተናገረው በዚህ ቃል ኢየሱስ ከ1500 አመታት በፊት ለሙሴ
የተሰጡትን አስርቱን ትእዛዛት አጠቃለላቸው። እዚህ ላይ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን
ሕግ ላይ ትኩረት እንዳደረገ እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከፍ እንዳደረገው ልንገነዘብ
ይገባል። በርካታ ክርስቲያኖች እዚህ ላይ ልክ አዲስ ትእዛዝ እንደተሰጠ በማሰብ
የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ ። እናም የብሉይ ኪዳን ሕግ አሁን በአዲስ የአዲስ
ኪዳን ወንጌል እንደተተካ ያስባሉ። ነገር ግን እውነታው ኢየሱስ ያስተማረው
ትምህርት የተመሰረተው በብሉይ ኪዳን ሕግ ላይ ነው። ክርስቶስ ሕጉን በሙላት
ከገለጠ እና ግልጽ ካደረገ በኋላ ‹‹ ‹ በእነዚህ ሁለት ሕግጋት › ›› (አስርቱን ትእዛዛት
አጠር አድርጎ የመጀመሪያዎቹ አራቱ በሰው እና በመለኮት ግንኙነት ላይ ሲያተኩሩ
ቀጣዮቹ ስድስቱ ደግሞ በሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ያተኩራሉ) ›› ‹በእነዚህ
በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።›(ማቴ 22፡40) ። በዚህ መንገድ
ኢየሱስ እንዲሁ ሁሉንም የብሉይ ኪዳን ከፍ አደረገ ‹‹ ሕግ እና ነብያትን›› ባለ ጊዜ
ይህ በአጭሩ ሕግን፣ ነብያትን እና ጽሑፎችን መጠቆሙ ነበር ወይም ሁሉንም ፣
ሶስቱን ፣ የብሉይ ኪዳን ክፍሎችን ማለት ነው።
‹‹ እርሱ (ክርስቶስ) ወደ ቅዱሳት መጽሐፍት ሲያመላክት በስልጣናቸው አጠያያቂ
እንዳልሆኑ አድርጎ ነው እናም እኛም እንደዚህ ልንደርግ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ
ልክ ሊወሰን የማይችለው እግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ሊወሰድ ይገባል። የሁሉም
ግጭቶች መጨረሻ እና ለእምነቶች ሁሉ መሰረት እንደሆነ መቅረብ አለበት። ›› (Ellen G. White, Christ’s Object Lessons, pp. 39, 40)
ምንአልባት ካላ ምን አይነት ተወዳዳሪ የስልጣን ምንጭ (ቤተሰብ፣
ፍልስፍና እና ባህል) ነው እራስዎን ለእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰጡ
የሚጻረርዎት?
ሉቃስ 24፡ 13-35፣ 44፣45ን ያንብቡ። ለደቀመዛሙርት የወንጌልን መልዕክት ለማስተማር ኢየሱስ እንዴት ነበር መጽሐፍ ቅዱስን የተጠቀመው?
ከክርስቶስ ሞት በኋላ ተከታዮቹ ግራ ተጋቡ፣ ተጠራጠሩም። እንዴት ነው ይህ
ሊሆን የቻለው? ምንስ ማለት ነበር? በሉቃስ መጽሐፍ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ኢየሱስ
ሁለት ጊዜ ሲገለጥላቸው እናያለን፣ መጀመሪያ ለኤማሁስ መንገደኞች ለሁለቱ፣ እና
ኋላ ደግሞ ለሌሎች። በሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች ኢየሱስ እንዴት የብሉይ ኪዳን
ትንቢቶች እንደተፈጸሙ ገለጸላቸው። ‹‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ
በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። ›› (ሉቃ 24፡ 27)።
በድጋሚ በሉቃስ 24፡44፣45 እንዲህ አለ ‹‹እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ
ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ
የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። ›› ከዚያም ኢየሱስ ‹‹ በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን
ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤››።
በሉቃስ 24፡27 ያለውን በቀጥታ የጠቀሰውን ‹‹ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ
እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። ›› ይህ በ ሉቃስ 24፡ 44 ላይ
ያለውን እንደገና በሁለተኛው ክፍል ትኩረት ሲሰጥ ነው ‹‹ በሙሴ ሕግና በነቢያት
በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ
ቃሌ ይህ ነው አላቸው። ››። ይህ በግልጽ የሚፈጥረው ኢየሱስ ቃል ስጋ የሆነው
(ዮሐ 1፡1-3፣ 14)፣ ከመቶ አመታት በፊት አስቀድሞ የተነገረው እንዴት እንደተፈጸመ
በመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ላይ ሲተማመን ያሳያል። በአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ
ነገር ኢየሱስ ሐዋሪያትን በምሳሌ እያስተማራቸው ነበር። የወንጌልን መልዕክት
ለማሰራጨት ወደፊት ሲሔዱ ሳለ እነሱም እራሳቸው ሁሉንም ቅዱሳት መጽሐፍት
ወደ ማስተዋል እና ሐይልን ወደ መቀበል ሲመጡ እና ያን ደግሞ በአለም ውስጥ
ወዳሉ አዳዲስ ተለዋጮች/ነፍሳት ማተዋል እና መረዳትን ሲያመጡ ነበር።
ተመልከቱ በማቴዎስ 28፡ 18-20 ላይ እንዲሁ ኢየሱሰ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረውን
(ዛሬም የምንጠቀመው) ‹‹ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። ›› ነገር ግን
ያ ስልጣን በአባቱ እና በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ላይ የተተከለ ነበር ‹‹ እንግዲህ
ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ደቀ
መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ
ጋር ነኝ።›› ነበር ያላቸው። ከዚያ ቁልፍ የሆነው ክፍል ይመጣል ‹‹ ያዘዝኋችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ›› ኢየሱስ ምን ነበር ያስተማራቸው እና
ያዘዛቸው። ትምህርቱ የተመሰረተው በሁሉም ቅዱሳት መጽሐፍት ላይ ነበር።
በመጣበት ቃል ፣ በትንቢታዊ ስልጣን ላይ ነበር እናም እራሱን ለአባቱ በሰጠበት
በቅዱሳት መጽሐፍት የተተነበዩ የትንቢቶች ፍጻሜ ነበር።
ኢየሱስ ቅዱሳት መጽሐፍትን ከተቀበለ፣ ለምንድን ነው እኛም
ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ያለብን? እንደገና የቅዱሳት መጽሐፍትን
ስልጣን መቀበል እንዳለብን እንዴት ነው መማር የምንችል (ምንም
እንኳን ሁሉም ዛሬ አስፈላጊ እና የሚተገበር ባይሆን እንኳ)? በሰንበት
ቀን መልስዎን ወደ የውይይት ክፍልዎ ይዘው ይምጡ።
ኢየሱስ ያስተማረው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው እግዚአብሔር ከሚናገረው ጋር
ተመሳሳይ እንደሆነ እና መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ነው። ምንጩ
የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነው እናም ስለዚህ ለየትኛውም የህይወት ገጽ የመጨረሻ
ስልጣን አለው። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ፈቃዱን ለሰብአዊ ዘር በመጽሐፍ
ቅዱስ በመግለጽ ሲሰራ ነበር።
ለምሳሌ በማቴዎስ 19፡ 4፣ 5 ኢየሱስ በሙሴ የተጻፈን ጥቅስ ሲጠቅስ ነበር። ነገር
ግን ኢየሱስ ይህን ጥቅስ ወሰደና እንዲህ አለ ‹‹ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ
በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን
ይተዋል፥›› ‹‹መጽሐፍ ይላል ›› ከማለት ይልቅ ኢየሱስ ‹‹ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና
ሴት አደረጋቸው፥ አለም ›› የፈጣሪን ቃል የዘፍጥረት ተራኪ እንደጻፈው። በእርግጥ
እግዚአብሔር የተወሰደው የእዚህ አባባል ደራሲ እንደሆነ ነው ፣ ምንም እንኳን
በሙሴ ቢጻፍ።
የሚከተለውን ምንባብ ያንብቡ። ኢየሱስ እንዴት ነበር የመጽሐፍ
ቅዱስን ታሪካዊ ሰዎችን እና ኩነቶችን የተረዳው?
ማቴ 12፡3፣4
ማር 10፡ 6-8
ሉቃ 4፡ 25-27
ሉቃ 11፡51
ማቴ 24፡ 39
ኢየሱስ በዘላቂነት የብሉይ ኪዳን ሰዎችን ፣ ቦታዎችን እና ኩነቶችን እንደ ታሪካዊ
እውነታ ይወስዳቸው ነበር። ዘፍጥረት 1ን እና 2ን ጠቅሷል፣ አቤልን በዘፍጥረት
4 ላይ ፣ ዳዊት የቤተመቅደሱን ሕብስት መብላቱን እና ኤልያስን ከሌሎች ታሪካዊ
ሰዎች ጋር ጠቅሷል። በተደጋጋሚ ስለ የጥንት ነብያት ስቃይ ተናግሯል (ማቴ 5፡
12፣ ማቴ 13፡57፣ ማቴ 23፡ 34-36፣ ማር 6፡4)። በማስጠንቀቂያ መልዕክቱ
ኢየሱስ ስለ ኖህ ቀናት አብራርቷል። ‹‹ በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ
ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ
ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ
መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ›› (ማቴ 24፡ 38፣39) ። በዚህ ታሪካዊ ኩነት፣
ታላቅ የእግዚአብሔር የፍርድ ድርጊት፣ ኢየሱስ የጠቀሰው እያንዳንዱ ጠቃሚ ነገር
አለው።
ኢየሱስ እራሱ እነዚህን ታሪካዊ ሰዎች እንደ እውነት የጠቀሰበት
ምክንያት ዛሬ ብዙ ሰዎች ንስሃ የገቡ ክርስቲያኖችም እንኳን ሳይቀሩ
መኖራቸውን ይጠራጠራሉ፣
እናም እዚህ ላይ ስላለ ስለ ሰይጣን
የማታላል ሐይል የሚለው ምንድን ነው? ለምንድን ነው በዚህ የማታለያ
መረብ ውስጥ ልንወድቅ የማይገባን?
የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች መጽሐፍ ቅዱስን ያቀረቡበት መንገድ ልክ ኢየሱስ ባቀረበበት አይነት ነው። ስለ መለኮታዊ አስተምህሮ፣ ሞራል እና የትንቢቶች መፈጸምን በተመለከተ ብሉይ ኪዳን ለእነርሱ ስልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነበረ። እነዚህ ሰዎች የተናገሩት ወይም በስልጣኑም ወይም ስለየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እውነተኛነት ጥያቄ ያነሱበትን ምንም፣ የትም አናገኝም። እነዚህ ከታች ያሉ ክፍሎች/መልዕክቶች ሐዋሪያት እንዴት የእግዚአብሔርን ቃል ስልጣን እንዳስተዋሉ ምን ያስተምሩናል? ሐዋ 4፡ 24-26
ሐዋ 13፡ 32-36
ሮሜ 9፡17
ገላ 3፡8
አስተውሉ! በእነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ቅዱሳት መጽሐፍት እና የእግዚአብሔር
ድምጽ እንዴት እንደተመሳሰሉ። በሐዋሪያት ሥራ 4 በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት
በፊት ሐዋሪያት ስለ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ መፈታት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ
ነበር። በምስጋናቸው ውስጥ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን እንደ
ፈጣሪ እውቅና ሲሰጡ እና በባሪያው በዳዊት በኩል እንደተናገረ ድምጻቸውን ከፍ
አድረገው ተናግረዋል። ያ ማለት የዳዊት ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነበር ማለት ነው።
በ ሐዋሪያት ሥራ 13፡ 32-36፣ ዳዊት በሐዋሪያው ጳውሎስ ተጠቅሷል። ነገር ግን
ቃሎቹ የእግዚአብሔር ባህሪ ነበራቸው ቁጥር 32 እንዲህ ይላል ‹‹እኛም ለአባቶች
የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤ ››
ጳውሎስ በሮሜ 9፡17 እግዚአብሔርን አንደ ባለቤት ሲጠቀምበት ‹‹መጽሐፍ ››
የሚልን አባባል ተጠቅሟል ። ‹‹ መጽሐፍ ፈርዖን›› ሲል በእርግጥ ‹‹እግዚአብሔር
ለፈርዖን እንዳለው›› ብሎም ሊያስቀመጥ ይችል ነበር። በገላቲያ 3፡8 ‹‹መጽሐፍ››
ለሚለው አባባል ባለቤት ሆኖ ‹‹እግዚአብሔር››ተቀምጧል፣ ይህ ምን ያህል
እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር ቃል ቅርበት እንዳላቸው ያሳያል።
በእርግጥ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በተመሳሳይ መልኩ በብሉይ ኪዳን ላይ ሲያርፉ
ልክ እንደ የእግዚአብሔር ቃል አድርገው ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቅሶች አሉ
በአዲስ ኪዳን እንደ የእግዚአብሔር ቃል የተጠቀሱ። አንድ ምሁር 2688 ግልጽ የሆኑ
ማጣቀሻዎችን ዝርዝር አውጥቷል። 400 ከ ኢሳያስ መጽሐፍ፣ 370 ከ መዝሙረ
ዳዊት፣ 220 ከዘጸአት ወዘተ። አንዱ ደግሞ በእነዚህ ላይ በተዘዋዋሪ የተጠቀሱን፣
መልዕክቶችን እና ጭብጦችን ቢያነሳ ዝርዝሩ ከዚህም በላይ ይሆናል።
መጽሐፍቱ
በብሉይ ኪዳን ማጣቀሻዎች የተሟሉ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምሩት ‹‹
››ተጽፏል›› በሚል ሐረግ ነው። (ማቴ 2፡5፣ ማር 1፡2፣ 7፡6፣ ሉቃ 2፡23፣ 3፡4፣
ሮሜ 3፡4፣8፡36፣ 9፡33፣ 1ኛ ቆሮ 1፡19፣ ገላ 4፡27፣ 1ኛ ጴጥ 1፡16)። እነዚህ ሁሉ
የሚያረጋግጡት በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ለኢየሱስ አስተምህሮ መሰረት እና
ሐዋሪያትም የሚያርፉባቸው እንደሆኑ ነው።
በመጽሐፍት ላይ ያለውን ስልጣን ዝቅ አድርገን እንድናይ የሚያደርጉ
የትኛውም አይነት ሐሳቦች
አደገኛ እንደሆኑ እነዚህ ምሳሌዎች
ሊያስተምሩን የሚገባው ምንድን ነው?
ከኤለን ጂ ኋይት “As a Child,” ገጽ 68-74 እና ‹‹ ፈተና ››
የሚለውን ከዘመናት ምኞት ገጽ 114- 123 ላይ ያንብቡ።
‹‹ ሰዎች እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ፣ ከእግዚአብሔርም እንኳን ይልቅ
ብልሆች አድርገው ይወስዳሉ። በማይንቀሳቀሰው መሰረት ላይ እግሮቻቸውን
ከመመስረት ይልቅ እና ሁሉንም ወደ እግዚአብሔር ቃል መመዘኛ ከማምጣት ይልቅ
ያን ቃል በእራሳቸው መመዘኛ፣ በሳይንስ እና በተፈጥሮ ሊመዝኑ ይፈልጋሉ እናም
ከሳይንሳዊ ሐሳባቸው ጋር የማይሔድ ከመሰላቸው ማንም ሊገባው እንደማይችል
በመቁጠር ያስወግዱታል›› (Ellen G. 13 White, Signs of the Times, March
27, 1884, p. 1.)
‹‹ በቃሉ እንደተገለጠው ከጥበብ እና አላማ ጋር ጥሩ እውቅና፣ ጠንካራ ህሊና
ያላቸው ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ይሆናሉ እናም ከታላቁ አስተማሪ ጋር ውጤታማ
ሰራተኞች ይሆናሉ… ክርስቶስ ለህዝቡ የእውነትን ቃል ሰጥቷል እናም ለአለም ሁሉ
በማሳወቅ ሁሉም የየእራሱን እንዲያደርግ ተጠርቷል… ከእውነት ወይም ከቃሉ ውጭ
የሚሆን ቅድስና የለም እናም ያ በሁሉም ዘንድ ሊስተዋል የሚገባ ምን ያህል አስፈላጊ
ነው! ›› (Ellen G. White, Fundamentals of Christian Education, p. 432.)
1.ኢየሱስ ፣ የወንጌል ጸሐፊዎች እና ጳውሎስ የብሉይ ኪዳን
መጽሐፍትን እንደ እግዚአብሔር ቃል ካዩ፣ ዛሬ በዘመናዊው አለም
ያሉ መጽሐፍትን አንባቢዎች እንደሳቱት ባለ ሐሳብ ዙሪያ መውደቅ
እንደሌለብን፣ ይህ ምንድን ነው ሊስተምረን የሚገባው?
2.ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪ ምሁራን በክህደት የት
እንደሔዱ ለማሳየት ከዚህ ቀጥሎ ጥቂት ነገሮችን ለምሳሌ ብዙ
ዘመናዊ ምሁራን የካዷቸውን እውነቶችን እናንሳ። ቀጥተኛ የ6 ቀናት
ፍጥረት ታሪክን ክደዋል፣ ከዚህ ይልቅ የቢሊዮን አመታት አፈጣጠርን
የዝግመተ ለውጥን በፋንታው ተቀብለዋል። አለማቀፋዊውን የውሃ
ጥፋት ክደዋል አንዳንዶች ደግሞ የአብርሐምን መኖር ክደዋል።
ጥቂቶች ደግሞ የእስራኤልን ከግብጽ መውጣት ክደዋል። አንዳንዶች
የኢየሱስን ተአምራቶች ከሞት በአካል መነሳቱን ጭምር ክደዋል።
አንዳንዶች መጭውን ጊዜ የሚተነብዩትን ትንቢቶች ነብያት መጭውን
ጊዜ የተናገሩበትን አንዳንድ ጊዜ መቶ አመታት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ
አንድ ሺ አመታትን በማለት ነው ክደዋል፣ ይህ ድምዳሜ ምን ሰዎች
በመጽሐፍት ስልጣን ላይ እና ባለቤት ላይ መጠራጠር ሲጀምሩ ምን
ሊሆን እንደሚችል ምን ይነግረናል ? እንዲሁ እንደዚህ አይነት ሰዎችን
ለመርዳት እና ወደ ተጠራንበት መረዳት እንዲመጡ እና አውነትን
እንዲረዱ የሚያደርጉ መንገዶች ምን አይነት ናቸው?
3.በማክሰኞ ጥናት ክፍል መጨረሻ ላይ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ላይ
ሁሉ መጽሐፍት ዛሬ እንኳን ለመተግበር አስፈላጊ እንኳን ባይሆኑም
በመንፈስ እንደተነዱ እንዴት ነው የምናስታውለው?