ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ ፡- ዮሐ 1፡1-3፣ ዘፍ 1፡3-5፣ ዘጸ 20፡8-11፣ ራዕይ 14፡7፣ ማቴ 19፡ 3-6፣ ሮሜ 5፡12ን ያንብቡ።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ›› (ዮሐ 1፡1-4)
የ
መጀመሪያዎቹ የዘፍጥረት ምዕራፎች ለቀሪዎቹ መጽሐፍት መሰረት ናቸው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ዋና ትምህርቶች ወይም የስነ-መለኮት ትምህርቶች ምንጫቸው
ከእነዚህ ምዕራፎች ነው። በዚህ ስፍራ የእግዚአብሔርን ስሉስነት እንደ አባት፣ ልጅ
(ዮሐ 1፡1-3፣ ዕብ 1፡1፣2) እና መንፈስ ቅዱስ(ዘፍ 1፡2) አለምን እና በውስጧ ያሉትን፣
በመጨረሻም በሰውን በመፍጠር በተደመደመ ጊዜ ታየ(ዘፍ 1፡ 26-28)። ዘፍጥረት
እንዲሁ ሰንበትን (ዘፍ 2፡ 1-3)፣ የክፉን ምንጭ (ዘፍ 3)፣ መሲህን እና የድነት እቅድን
(ዘፍ 3፡15)፣ አለምአቀፋዊውን አለምን የሸፈነውን የውሃ ጥፋት(ዘፍ 6-9፣ )፣ ቃል ኪዳን
(ዘፍ 1፡28፣ 2፡2፣3 ፣ 15-17፣ 9፡ 9-17፣ ዘፍ 15)፣ ቋንቋዎች እና የሰዎች መደበላለቅ (ዘፍ
10፣11)፣ እና ከፍጥረት እስከ አብርሃም ድረስ ያለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የዘር ግንድ ቅደም
ተከተልን አውታር አቅርቦ (ዘፍ 5 እና 11) አስተዋውቆል።
በመጨረሻ እግዚአብሔር
የተናገራቸውን ቃላት ሐይል (ዘፍ 1፡3፣ 2ኛ ጢሞ 3፡16፣ ዮሐ 17፡17)፣ የሰብአዊ ዘር
ተፈጥሮ (ዘፍ 1፡26-28)፣ የእግዚአብሔር ባህሪ(ማቴ 10፡ 29፣30) ፣ በወንድ እና በሴት
ያለ ትዳር (ዘፍ 1፡27፣ 28፣ ዘፍ 2፡18፣ 21-25) ፣ የምድር እና በውስጧ ያሉትን ሐብት
ዙሪያ ያለን መጋቢነት (ዘፍ 1፡26፣ 2፡15፣19) ፣ እና ቃል የተገባው የአዲስ ፍጥረት ተስፋ
(ኢሳ 65፡17፣ 66፡22፣ ራዕ 21፡1) ሁሉም የተመሰረቱት የዚህ ሳምንት እና የሚቀጠለው
ሳምንት ጥናታችን በሚሆኑ በእነዚህ የመጀመሪያ ምዕራፎች ላይ ነው።
የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ ግንቦት 15 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ዘፍ 1፡1ን ያንብቡ። ምን አይነት የጠለቀ እውነት ነው በዚህ ላይ የተገለጠው?
መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ላቅ ባለ እና ጠለቅ ባሉ ቃላቶች ይጀምራል፣ ቀላል የሆኑ
ቃላት ነገር ግን በጥንቃቄ ሲያጠኗቸው ሊለካ የማይችል ጥልቀት አላቸው። በእርግጥ
በፍልስፍና ትልቁ ጥያቄ በማንነታችን ዙሪያ ያለው ነው። ለምንድን ነው እዚህ ያለነው
እናም እንዴት እዚህ መጣን የሚሉት በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር ላይ
ተመልሰዋል።
እግዚአብሔር ቀደም ሲል ግልጽ በሆነ ጊዜ ስለፈጠረን አሁን አለን። ከምንም ነገር
አልወጣንም ወይም አንዲሁ በአጋጣሚ ፣ ያለምንም አላማ እና ባልታቀደ አቅጣጫ
አሁን ዘመናዊው ሳይንስ ባስቀመጠው ሳይንሳዊ ቀመር እንደሚያስተምረው ባለ መንገድ
ወደ መኖር አልመጣንም። የዳርዊናውያን ዝግመተ ለውጥ ከቅዱሳት መጽሐፍት ጋር
በየትኛውም አቅጣጫ ይጻረራል። እናም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለማቀራረብ አንዳንዶች
የሚደርጉት ሙከራ ክርስቲያኖችን ቂል ያስመስላቸዋል።
በጊዜ ውስጥ ግልጽ በሆነ ሰዓት ላይ በእግዚአብሔር ተፈጥረናል። ‹‹ በመጀመሪያ
›› የሚለው ቃል ከዚያ በፊት እግዚአብሔር እንደነበረ አመላካች ነው። ያ ማለት
እግዚአብሔር ጊዜ ከመፈጠሩ እና በየቀኑ ዙር ‹‹ ማታ እና ጠዋት ›› ከመባሉ በፊት ፣
አለም ከጸሐይ እና ከጨረቃ ጋራ ባላት ግንኙነት መለያ ከመቀመጡ እና በወራት እና
በአመታት ከመገለጹም በፊት ነበረ ማለት ነው። ይሔ ፍጹም የሆነ ጅማሮ በሌሎች
መጽሐፍት ክፍልም ያስተጋባል ይደገፋልም ። እንዲሁም ያለማቋረጥ ተፈጥሮን እና
የእግዚአብሔርን ፈጠራዊ የስራን መንገድ ያረጋግጣል(ዮሐ 1፡1-3)።
ዮሐንስ 1፡ 1-3 እና ዕብራውያን 1፡ 1፣2ን ያንብቡ። የፍጥረት ወኪል
ማነው? በመስቀል ላይ መሞቱ ምን ማለት እንደሆነ ያስቡበት።
መጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት ወኪል ኢየሱስ እንደሆነ ያስተምራል። መጽሐፍ ቅዱስ
‹‹ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ›› (ዮሐ 1፡3)
ይላል። በኢየሱስ ‹‹ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ›› (ዕብ 1፡1፣2) ይላል። ሁሉም
ነገር ምንጫቸውን ከኢየሱስ ከመጀመሪያው ስላገኙ በመጨረሻም የጀመረውን
እንደሚጨርስ ተስፋ አለን። ምክንያቱም አርሱ ‹‹አልፋና ኦሜጋ ነው›› ‹‹ የመጀመሪያው
እና የመጨረሻው›› (ራዕይ 1፡8 ራዕ 22፡13)።
በእግዚአብሔር መፈጠርን ማወቅ ምን አይነት ልዩነትን ያመጣል?
አስቡት ይህንን የማታምኑ ቢሆን። እንዴት ነበር እራስዎን እና ሌሎችን
የሚመለከቱት እናም ለምን?
በቅርብ አመታት የፍጥረትን ሳምንት በቀጥታ መመልከት፣ እንደ ዘይቤአዊ አነጋገር፣ እንደ ምሳሌ ወይም እንደ አፈታሪክ መመልከት የተለመደ ሆኗል። ይሄ ደግሞ በጣም በረዥም አመታት ጊዜ ውስጥ ህይወት በምድር ላይ ማደግ እንደጀመረ የሚገምተውን የዝግመተ ለውጥን ጽንሰ ሐሳብ አስነስቷል። በዚህ ርዕስ ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው የሚያስተምረው? በዘፍጥረት 1 ላይ ያሉት የፍጥረት ‹ቀናት› ምሳሌያዊ ቀናት ሳይሆኑ ቃል በቃል በመውሰድ የማይስተዋሉት ለምንድን ነው? ዘፍ 1፡3-5 እና ዘጸአት 20፡8-11ን ያንብቡ። በዚህ አገባብ ውስጥ ‹ቀን› የሚለውን ቃል እንዴት ነው የተጠቀመው?
የእብራይስጡ ቃል ዮም ወይም ‹ቀን › በፍጥረት ትረካ ውስጥ ሁሉ ያለማቋረጥ
የተጠቀመው በቀጥታ(ቃል በቃል) አንድ በአንድ ላሉ ቀናት ነው። በዘፍጥረት
የፍጥረት ትረካው ውስጥ ያሉት ቀናት አንድ በአንድ ካሉ ቀናት፣ እኛ ዛሬ
ከምናውቃቸው ቀናቶች ውጭ እንደተጠቀመ የሚጠቁም አንድም ነገር የለም።
በእርግጥ አንዳንድ ምሁራን ቀናቶቹ ቀጥተኛ ቀናት አይደሉም ብለው የሚያምኑ
አሉ። የሆነው ሆኖ የጸሐፊው ፍላጎት ቀጥተኛ ቀናትን ለመግለጽ እንደሆነ ግን
ያውቃሉ/ ያምናሉ።
በጣም የሚገርም ነው! እግዚአብሔር እራሱ ይህን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የጊዜን
መለያ አድርጎ የሰየመው እራሱ እግዚአብሔር ነው(ዘፍ 1፡5)። ዮም ወይም ቀን
በሐረግ ሲተረጎም ‹‹ ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን። ›› (ዘፍ 1፡ 5፣8 ወዘተ) ።
አባባሉን የተጠቀመው ለነጠላ ነው ለብዙ ቁጥር አይደለም ያም ማለት ለአንድ ቀን
ነው።
ስለዚህ ሰባቱ የፍጥረት ቀናት አንደ ሙሉ የጊዜ መለኪያ ይስተዋላሉ በተራ ቁጥር
ጀምረው፣ ‹ ኢቻድ› (‹አንድ›)፣ በመደበኛ ቁጥሮች ይከተላሉ (ሁለት፣ ሶስተ፣
አራት፣ ወዘተ)። ይህ አካሔድ የቀናቶች ተከታታይነትን ይጠቁማል፣ በሰባተኛው
ቀን ያልቃል። እነዚህን አባባሎች ሲጠቀም ወይም በትረካው ውስጥ በቀናቶቹ
መካከል ምንም አይነት ክፍተት አልነበረም። ሰባቱ የፍጥረት ቀናት በእርግጥም ዛሬ
የተከለሉት ሰባቱ ቀናት ናቸው።
እንዲሁ በቀጥታ ያለው የቀናቶቹ አፈጣጠር ያለምንም ጥርጥር የሚያሳምነው
እግዚአብሔር በእራሱ ጣቶች አራተኛውን ትእዛዝ ሲጽፍ ነው፣ የሰባቱ ቀናት
መሰረት ሰንበት የሚያርፈው ተራውን ጠብቆ በቀጥታ ባሉት የፍጥረት ሰባት ቀናት
ወይም የፍጥረት ሳምንት ላይ ነው።
የዘፍጥረት ፍጥረት በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ያለ ፍጥረትም አይደለም። በክርስቶስ
ዳግም ምጻት ጊዜም እግዚአብሔር ሟችን ወደ ማይሞት በሚለውጥበት ጊዜ
የእንደገና ፍጥረት አለ። ‹‹ የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን
እንለወጣለን፤ ››(1ኛ ቆሮ 15፡ 52) ይላል።
እግዚአብሔር በ እንደገና የመፍጠር ጊዜ በቅጽበት ይህን ማድረግ
ከቻለ የቴስቲክ ዝግመተ ለውጥ እንደሚያስተምረው ለምንድን ነው
በመጀመሪያው ፍጥረት ጊዜ ቢሊዮን አመታትን የሚወስድበት?
በዘመናችን ሰባተኛው ቀን ሰንበት በማያምነው ማህበረሰብ እና በሐይማኖታዊው ማህበረሰብ ዘንድ በከባድ ጥቃት ስር ነው። ይህን ሐቅ በአለም አቀፍ ዙሪያ ባሉ ኮርፖሬሽኖች የስራ የጊዜ ሰሌዳ ማየት ይቻላል፣ በብዙ አውሮፓ ሀገራት ሰኞን ልክ እንደ የስራ መጀመሪያ ቀን እሁድን ደግሞ እንደ ሰባተኛ ቀን ለማድረግ ተሞክሯል። እናም በቅርቡ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በጳጳሱ በተጻፈ ደብዳቤ ሰባተኛውን ቀን ሰንበት ‹‹ የአይሁድ ሰንበት ሲሉ ጠርተውታል ›› እናም አለም የአለምን ሙቀት ለመቀነስ የእረፍትን ቀን እንዲፈልግ ጥሪ አድርገዋል። (Pope Francis, Laudato Si’, Vatican City: Vatican Press, 2015, pp. 172, 173)። ዘፍጥረት 2፡ 1-3፣ ዘጸአት 20፡8-11፣ ማርቆስ 2፡ 27ን እና ራዕይ 14፡7ን ያንብቡ። ከአራተኛው ትእዛዝ ጋር የተያያዘው የፍጥረት ሳምንት እንዴት ይስተዋላል? ይህ ደግሞ ከሶስቱ መላዕክት መልዕክት ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ‹‹እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ
በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። ›› (ዘፍ 2፡2)። በፍጥረት የሚያምኑ
ብዙዎች ብዙ ስራ በስድስተኛው ቀን ላይ እንደተሰራ ብቻ ትኩረት ይሰጣሉ። ነገር ግን
እግዚአብሔር ስራውን በስደስተኛው ቀን እንዳልጨረሰ ለመገንዘብ ቸል ይላሉ። ስራው
የተጠናቀቀው ሰንበትን በፈጠረ ጊዜ ነው። ለዚህ ነው ኢየሱስ እንዲህ ያለው ‹‹ደግሞ።
ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤ ›› (ማር 2፡27)።
ኢየሱስ ይህንን ቃል በስልጣን ሲናገር ሳል እርሱ እራሱ እንደ ዘለአለማዊ ምልክት እና
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያተመበት ምልክት አድርጎ ስለሰራው
ወይም ስለፈጠረው ነው። ሰንበት ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሰብአዊ ፍጥረት
ሁሉ ነው።
የዘፍጥረት መጽሐፍ ኢየሱስ ሰንበትን ከፈጠረ በኋላ ያደረጋቸውን ሶስት ነገሮች
ይጠቅሳል። መጀመሪያ፣ ‹‹አረፈ›› (ዘፍ 2፡2) ከእኛ ጋር ለማረፍ ያለውን ፍላጎት
በመግለጽ መለኮታዊ ተምሳሌቱን ሰጠን። ሁለተኛ፣ ሰባተኛውን ቀን ‹‹ባረከው›› (ዘፍ 2፡
3)። በፍጥረት ትረካ ውስጥ እንስሳት ተባርከዋል(ዘፍ 1፡22)፣ እናም አዳም እና ሔዋን
ተባርከዋል(ዘፍ 1፡28) ነገር ግን በቀጥታ የተባረከ ብቸኛ ቀን ሰባተኛው ቀን ብቻ ነበር።
ሶስተኛ፣ እግዚአብሔር ‹‹ ቀደሰው›› (ዘፍ 2፡3) ወይም ‹ ቅዱስ አደረገው ›።፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላ ቀን እንደዚህ አይነት መለየትን አላገኘም። እነዚህ ሶስት
ድርጊቶች ለአራተኛው ትእዛዝ ተደግመዋል። እግዚአብሔር በእራሱ ጣቶች በጻፈው እና
ወደ ፍጥረት በማመላከት ፍጥረት የሰንበት መሰረት እንደሆነ አሳይቷል (ዘጸ 20፡ 11)።
በራዕይ 14፡7 እና በዘጸ 20፡11 ላይ የሰንበት ትእዛዝ ፈጣሪን ለማምለክ
እንደ መሰረት በቀጥታ ተጠቅሷል። ይህ ቀጥተኛ ግንኙነት ከሰንበት እና
ከመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ጋር ምንድን ነው የሚያያዘው?
ያለፉት አስርት አመታት ማህበረሰቦች እና መንግስታት ትዳርን የተረጎሙበት መንገድ አስገራሚ ለውጥ ለማድረጉ ምስክሮች ናቸው። በጣም በርካታ ሕዝቦች የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አጽድቀዋል፣ ቀደም ሲል የነበሩ እና የቤተሰብን መዋቅር ማዕከላዊ ሆነው ይዘው ይጠብቁ የነበሩ የአንድ ወንድ እና አንድ ሴት ህጎችን ቀይረዋል። ይህ በብዙ አቅጣጫ ተደርጎ የማያውቅ ለውጥ ነው እናም በትዳር ተቋም ላይ፣ በቤተክርስቲያን እና በመንግስታት መካካል ባለ ግንኙነት ላይ እንዲሁም በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጠቀሰው የትዳር እና የቤተሰብ ቅድስና ላይ ጥያቄን አስነስቷል። ዘፍጥረት 1፡26-28 እና ዘፍጥረት 2፡18፣ 21-24ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ትዳርን በተመለከተ ስለ የእግዚአብሔር ሐሳብ ምን ያስተምሩናል?
በስድስተኛው ቀን እግዚአብሔር በፍጥረት ጫፍ ላይ ደረሰ ፣ ሰውን ፈጠረ። በጣም
አስደሳች ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር በብዙነት ተጠራ በዘፍጥረት 1፡26 ‹‹
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ›› አለ። ሁሉ
የስላሴ አካላት እርስ በእርሳቸው ፍቅር በተሞላው ህብረት መለኮታዊውን የሰውን
እርስ በእርስ ግንኙነት ያለበትን ትዳርን በዚህች ምድር ላይ መሰረቱ።
‹‹እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት
አድርጎ ፈጠራቸው። ›› (ዘፍ 1፡27) ። አዳምም እንዲህ ሲል አወጀ ‹‹ ይህች አጥንት
ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ›› (ዘፍ
2፡23)። እናም አዳም ‹‹ሴት ›› ሲል ስምን አወጣላት። ትዳር ‹‹ ስለዚህ ሰው አባቱንና
እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ›› (ዘፍ 2፡24)
የሚለውን ይጠይቃል።
ይህ ግንኙነት የሚፈጸመው እራሳቸውም ከአባታቸው እና ከእናታቸው በመጡ በአንድ
ወንድ እና በአንድ ሴት መካካል እንደሆነ መጽሐፍት በግልጽ ያስቀምጣሉ። ይህ
ጽንሰ ሐሳብ ወደፊት በምድራዊ አባት እና እናታቸው ይብራራል። ‹‹እግዚአብሔርም
ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም
የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
››(ዘፍ 1፡28)። በተቃራኒ ጾታ መካካል በሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ካልሆነ በስተቀር
ይህ ነገር ሊሟላ አይችልም።
በማቴዎስ 19፡ 3-6 ያለውን የኢየሱስን ቃላት ያንብቡ። ስለ ትዳር
ንጽህና እና ተፈጥሮ የሚያስተምረን ምንድን ነው? በኢየሱስ ቃላት
አንጻር ለሰብአዊያን እና ሐጢያተኛ ለሆነው ሁሉ ያለውን የእግዚአብሔር
ፍቅር በፍጹም ሳንረሳ እንዴት ነው ጠንካራ እና በእምነት የተሞላ አቋም
በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የትዳር መርሆች ላይ ሊኖረን የሚገባው?
መጽሐፍ ቅዱስ በፍጥረት፣ በውድቀት፣ በመሲሁ የመምጣት ተስፋ እና የመጨረሻ ድነት መካከል የማይቆራረጥ ግንኙነትን ያቀርባል። እነዚህ ዋና ዋና ኩነቶች ለሰብአዊያን የድነት ታሪክ መሰረት ሆነዋል። ዘፍጥረት 1፡31፣ ዘፍጥረት 2፡15-17፣ እና ዘፍጥረት 3፡1-7ን ያንብቡ። በእግዚአብሔር እንከን አልባ ፍጥረት ላይ ምንድነው የሆነው?
እግዚአብሔር ፍጥረቱን ‹‹ መልካም ነበር ›› (ዘፍ 1፡31) ሲል አውጇል። ‹‹ ፍጥረት አሁን
ተጠናቋል … ኤደን በምድር ላይ ፈክታለች። አዳም እና ሔዋን የህይወትን ዛፍ ያለማንም
ከልካይ ያገኙ ነበር። የሐጢያት ድንኳን ወይም የሞት ጥላ ደህና በሆነው ፍጥረት ላይ
አልነበረም ››(ኤለን ጅ ኋይት አበው እና ነብያት ገጽ 47)። እግዚአብሔር አዳምን እና
ሔዋንን ከተከለከለችው ዛፍ እንዳይበሉ ነገር ግን ከበሉ በእርግጠኝነት ሞትን እንደሚሞቱ
አስጠንቅቋቸው ነበር(ዘፍ 2፡ 15-17)። እባብ ንግግርን የጀመረው በጥያቄ ነበር፣ እናም
እግዚአብሔር ካለው ጋር በፍጹም የማይሔድ ነበር ፣ ‹‹ ‹በእርግጥ አትሞቱም › ››(ዘፍ 3፡
4 )። ሰይጣን ለሔዋን ታላቅ እውቀት እንደምታገኝ እና እግዚአብሔርን እንደምትመስል
ቃል ገባላት፣ እናም በእርግጥ እርሷም አመነችው።
ጳውሎስ እንዴት አድርጎ ነው በዘፍጥረት 2፡15 -17 ላይ ያለውን
የእግዚአብሔርን ቃል ያረጋገጠው? ሮሜ 5፡12ን እና ሮሜ 6፡23ን
ያንብቡ እነዚህ አስተምህሮዎች ከ ቴስቲክ(ፈጣሪ እንዳለ የሚያምኑ)
ዝግመተ ለውጥ ጋር እንዴት ነው የሚገናኘው?
በመጽሐፍት የኋለኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የቀደመውን የመጽሐፍ ቅዱስ
ቃላት እና ተጨማሪ እይታዎችን እንደጨመሩ ማየት እንችላለን። በሮሜ 5-8 ጳውሎስ
ስለ ሐጢያት እና ስለ ድነት ውበት ጽፏል ‹‹ ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው
ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው
ሁሉ ደረሰ፤›› (ሮሜ 5፡12) ። ነገር ግን የዝግመተ ለውጥ አቀራረብ ሞት ከሰብአዊነት
በፊት ለሚሊዮን አመታት እንደነበረ ነው። ይህ ሐሳብ ሐጢያትን በተመለከተ ባለው
በመጽሐፍ ቅዱሳዊው አስተምህሮ ላይ፣ በክርስቶስ የመስቀል ላይ የምትክ ሞት፣ እና
በድነት እቅድ ላይ ጠንከር ያለ ተጽዕኖ አለው።
ሞት ከሐጢያት ጋር ካልተገናኘ የሐጢያት
ዋጋ ሞት አይደለም (ሮሜ 6፡23)፣ እናም ክርስቶስ ለሐጢያታችን የሚሞትበት ምንም
ምክንያት የለውም ማለት ነው። ስለዚህ ፍጥረት፣ ውድቀት እና መስቀሉ መውጫ
በሌለው ግንኙነት የተሳሰሩ ናቸው። የመጀመሪያው አዳም ከመጨረሻው አዳም ጋር
ተያይዟል(1ኛ ቆሮ 15፡45፣47)። በዳርዊናውያን ዝግመተ ለውጥ ማመን ምንም እንኳን
አንዳንድ የእግዚአብሔራዊ ሐሳቦች በሒደቱ ውስጥ ቢኖሩም የክርስትናን ዋና መሰረት
የሚንድ ነው።
የኤለን ጂ ኋይት ን ‹‹ The Creation ››ገጽ 44-51፣ ‹‹ The Literal
Week ›› ገጽ 111-116 በ አበው እና ነብያት ላይ ያንብቡ።
‹‹ ጥቅል መረጃዎች ፣ በማወዳደር ላይ የተመሰረቱ፣ ቃል በቃል ፣ ቋንቋዎች እና ሌሎችም
ከግምት ገብተው ባለበት ደረጃ ተገናኝቶ፣ ወደ አንድ ድምዳሜ ይመራል ያም በዘፍጥረት
1 መሰረት ዮም፣ ‹ቀን› ቃል በቃል 24 ሰዓት ማለት ነው። ››
‹‹ የዘፍጥረት 1 ጸሐፊ የበለጠ ጠቅለል ያለ እና ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ ቃል በቃል
‹ቀን › የሚለውን ከመምረጥ ሌላ መንገድ ማዘጋጀት አልቻለም›› Gerhard F. Hasel,
“The ‘Days’ of Creation in Genesis 1: Literal ‘Days’ or Figurative “Periods/
Epochs’ of Time?” Origins 21/1 [1994], pp. 30, 31.)
‹‹ ታላላቅ አእምሮዎች በእግዚአብሔር ቃል ካልተመሩ በሳይንስ እና በራዕይ መካከል
ያለውን ግንኙነት ለማጥናት የሚደርጉት ሙከራ ግራ የሚያጋባ ይሆናል ። ፈጣሪ እና
ሥራው ከእነርሱ መረዳት በላይ ነው፣ እናም በተፈጥሮ ሕግ ሊብራራ ስለማይችል
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በእጅጉ የማያስተማምን ተደርጎ ይነገራል›› (Ellen G. White,
Testimonies for the 4 Church, vol. 8, p. 258.)
1.ከላይ ያለውን የኤለን ጂ ኋይትን ንግግር ይመልከቱ። ምን ያህል ጊዜ
ነው ያኔ እርሷ የጻፈችውን ዛሬ ተመሳሳዩን የምናየው? ሐይማኖተኝነታቸውን
በግልጽ ያወጁ ክርስቲያኖችም እንኳን ሳይንስ የእኔ ነው ባለው ነገር ፊት
ሲሆኑ በመጽሐፍ ቅደሱ ከተገለጠው በላይ አድረገው ይወስዱታል፣ ያም
ማለት አንደጻፈችው መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታሪክ ‹ የማያስተማምን ይሆናል›
ማለት ነው ።
2.ለምንድን ነው የቴስቲክን ዝግመተ ለውጥ ሐሳብ ይዞ ፣ መጽሐፍ ቅዱስን
በትክክል መውሰድ የማይቻለው?
የቴስቲክ ዝግመተ ለውጥን አራማጅ
የሆኑ ግን ክርስቲያን ነኝ የሚሉ ሰዎች ካሉ ለምን መስቀሉን ጳውሎስ
በጻፈው (ሮሜ 5ን ይመልከቱ) አንጻር /ብርሃን በአዳም ውድቀት እና ሞት
እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል መሃከል ስላለው ትስስር እንዲያብራሩ
አይጠይቋቸውም? ምን አይነት ማብራሪያ ነው የሚሰጡት?
3. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ራዕይ/መገለጥ ከሆነ የአማኞች እምነት
እና አይኖቻቸው ለታላቁ እውነታ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ለተገለጠው የተከፈቱ
መሆን የለባቸውም? ዳርቻ በሌለው አምላክ ለተገለጡት ለመጽሐፍ ቅዱስ
እውነታዎች አእምሮአቸው የተከፈቱ ከሆነ እንዴት ነው ክርስቲያኖች
‹‹አእምሮአቸው ዝግ ነው ›› የሚባሉት? በእርግጥ ከክርስቲያን ንጽረተአለም ይልቅ የ ኤቴስቲክ እና ቁሳዊ አመለካከቶች የአለም ዕይታ የበለጠ
ጠባብ ነው።
4.አማኞች ለእግዚአብሔር ቃል ታማኞች ሆነው ከጸኑ እንዴት ነው ጾታዊ
ማንነት ትግል ውስጥ ያሉትን ልናገለግላቸው የምንችል?
ምንአልባት
እንዳመነዘረችው ሴት አይነት ሰዎችም እና የሐጢያት በደል ያለባቸውም ቢሆን
እንኳን ለምንድን ነው ዲንጋይን ከሚወረውሩት እንዳንሆን የሚያስፈልገው?