
፡ ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 3:1–15፣ 2ቆሮ. 4:6፣ ሉቃ. 1:26–38፣ ማቴ. 1:18–24፣ ኤፌ. 4:15፣ 1ዮሐ. 3:18፣ ዘዳ. 6።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው” (ምሳ. 1፡8)፡፡
እ
ንደ ሰብዓዊ ፍጡርነታችን እኛ ሁሌም ተማሪዎች ነን። ደግሞስ፤ ሕይወት በራሷ
ትምህርት ቤት ናት ይባል የለ?
“ከጥንት ዘመን ጀምሮ ለእግዚአብሔር ታማኝ የነበሩ እስራኤላውያን ስለ ወጣቶች
ትምህርት ብዙ ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር። በሕግጋቱ እንደ ተገለጸውበተለይምና
በእስራኤልምታሪክ እንደታየው ሁሉ ልጆች ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ስለ እርሱ
ደግነትና ታላቅነት እንዲማሩ አምላክ መመሪያ ሰጥቶ ነበር። መዝሙር ጸሎትና
በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተመሠረቱ ትምህርቶች ለታዳጊ አእምሮ እንደሚስማሙ
ሆነው ይቀርቡ ነበር። የእግዚአብሔር ሕግ የአምላክ ባሕርይ መግለጫ እንደሆነና
የሕግንም መርሆዎች በልቦናቸው ሲቀበሉ በአእምሮአቸውና በልቦናቸው
የእግዚአብር ምሳሌ እንደሚቀረጽባቸው ወላጆች ለልጆቻቸው የማስተማር ኃላፊነት
ነበረባቸው። አብዛኛው ትምህርት ይሰጥ የነበረው በቃል ነበር። ሆኖም ወጣቶች
የዕብራይስጥ ጽሑፎችን ንባብ ይማሩ ነበር። እንዲሁም የብሉይ ኪዳን ጥቅል
ብራናዎች መማሪያቸው ነበሩ።” (የዘመናት ምኞት ገጽ 53።)
በአመዛኙ የሰብዓዊው ፍጡር ታሪክ፤ ትምህርት መቅሰሚያ ስፍራ ቤት ነው--በተለይ
በመጀመሪያዎቹ ዓመታት። ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በቤት ውስጥ ስለሚቀሰም
ትምህርት ምን ይላል? ቤተሰባችን የቱንም ዓይነት ሁኔታ ላይ ሊገኝ ቢችል እንኳ
ለራሳችን ልንወስድ የምንችላቸው መርኅዎች ምንድን ናቸው?
ምንም እንኳ በእነዚያ የቀደሙ የሰብዓዊ ፍጡራን ቀናት ታሪኮች፤ ከቤተሰብ የተገኙት
የትምህርት ትሩፋት የነበራቸውን መአዛ የሚገልጹ ዝርዝር ሀሳቦችን መጽሐፍ ቅዱስ
ባያቀርብልንም--ቤተሰባዊው ትምህርት ቤተሰባዊውን መዋቅር ተከትሎ ለመጀመሩ
ግን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
“በኤደን የተመሰረተው ሥርዓተ ትምህርት ቤተሰብን ያማከለ ነበር። አዳም
‘የእግዚአብሔር ልጅ’ (ሉቃ. 3፡38) ነበር። የልዑል ልጆች መመሪያዎችን የሚቀበሉት
ከገዛ አባታቸው ነበር። ይህ የእነርሱ ቤተሰብ--እውነተኛ የቤተሰባዊ ትምህርት ቤት
ዐውድ ነበረው።”—Ellen G. White, Education, p. 33.
በዚያን ወቅት ይሰጥ ስለነበረው ትምህርት በትክክል ባናውቅም፤ እጹብ ድንቅና
አስገራሚ ስለሆነው የፍጥረት ሥራ እና የኃጢአትን መግባት ተከትሎ ስለ ወጣው
የደህንነት እቅድ ሊሆን እንደሚችል ግን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
የሚከተሉት ጥቅሶች አዳምና ሔዋን ለልጆቻቸው ያካፈሏው ትምህርቶች
አካል ሊሆኑ የሚችሉበት ምክንያቱ ምንድን ነው? ከጥቅሶቹ ምን
እንማራለን? ዘፍ. 1–2፣ 3:1–15፣ 2ቆሮ. 4:6፣ ሉቃ. 10:27፣ ገላ.
3:11፣ ራእ. 22:12።
“በዓለም የመጀመሪዎቹ ቀናት ላይ የተቋቋመው ሥርዓተ ትምህርት ከዚያ ቀጥሎ
ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለሰብዓዊው ፍጡር በምሳሌነት እንዲያገለግል ሆኖ
የተቀረጸ ነበር። መርኅዎቹን እንዲያንጸባርቅ ሆኖ የተነደፈው ይህ ሥርዓተ ትምህርት
የመጀመሪዎቹ ወላጆቻችን መኖሪያ በነበረው የኤደን አትክልት ስፍራ ተቋቋመ።”—
Ellen G. White, Education, p. 20.
ክርስቲያናዊው ሥነ ትምህርት--ነገረ መለኮት፣ ሥነ አምልኮ፣ ስለ አምላካዊው
መመሪያዎች ምንነት፣ ስለ አማኞች ኅብረት፣ ወንጌልን ስለ ማሰራጨት እና
አገልግሎት ስለ መስጠት--ቤተሰብንና አባላቱን ለማስተማር የሚደረግ ቁርጠኝነት
ነው። ቤት--ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና የተስፋ ቃል ለቤተሰብ አባላት አገልግሎት
የሚሰጥበት መድረክ ነው። ህፃናት--የሱስን እንደ ጌታቸው፣ አዳኛቸውና ወዳጃቸው
የሚተዋወቁበትና መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ቃል የከበረ ዋጋ የሚሰጥበት
ስፍራ ነው። ቤተሰብ ከሰማያዊው አባታችን ጋር የሚኖረን ጤናማ ግንኙነት ምን
ሊመስል እንደሚችል በምሳሌነት የምንመለከትበት ዓይነተኛ ተቋም ነው።
ቃየን እና አቤል መሥዋዕቶቻቸውን ይዘው በእግዚአብሔር ፊት ቀረቡ (ዘፍ.
4፡1-4)። ወንድማማቾቹ መሥዋዕት የማቅረብን ትርጉምና አስፈላጊነት ከደኅንነት
እቅድ ዐውድ ከወላጆቻቸው ለመማራቸው እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ሆኖም
መልካም ትምህርት ሁሌም ተስፋ የተደረገውን ውጤት ይዞ ሊመጣ እንደማይችል
ከታሪኩ መመልከት ይቻላል።
የቤትዎ ሁኔታ የቱንም ዓይነት ገጽታ ሊይዝ ቢችል እንኳ፤ የእውነት
አስተምህሮ የሚቀርብበትና በተጨባጭ የሚኖርበት ስፍራ ይሆን ዘንድ
ምን ዓይነት ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ የሱስ የልጅነት ጊዜ የሚሰጠን ዝርዝር በጣም አነስተኛ በመሆኑ፤ ከእነዚያ ዓመታት አብዛኞቹ ምስጢራዊና የተሰወሩ ናቸው። ሆኖም ምድራዊ ወላጆቹ ስለነበሩት ማርያምና ዮሴፍ የተሰጡን ግንዛቤዎችና ስለ እነርሱ የምንማራቸው ነገሮች ስለ የሱስ ልጅነትና የቀደሙ ትምህርቶች ማብራሪያ እንድናገኝ ይረዱናል። ጥቅሶቹ ስለ ማርያምና ዮሴፍ ምን ያስተምሩናል? የሱስ በወላጆቹ ስለ መማሩ ግንዛቤ የሚሰጡን እንዴት ነው? ሉቃ. 1:26–38
ሉቃ. 1:46–55
ማቴ.1:18–24
ማርያምና ዮሴፍ ታማኝ አይሁዶች እንደነበሩና አምላካዊውን ሕጎችና ትእዛዞች
በመጠበቅ ለመኖር የሚሹ ወገኖች እንደነበሩ በጥቅሶቹ መመልከት እንችላለን።
ጌታ ወደ እነርሱ መጥቶ በእነርሱ ስለሚሆነው ነገር ሲነግራቸው፤ የተባሉትን ሁሉ
በታማኝነት ፈጸሙ።
“ሕጻኑ የሱስ በምኩራብ ትምህርት ቤቶች አልተማረም። የመጀመሪያ ሰብአዊ
መምህሩ እናቱ ነበረች። ከአንደበትዋና ከነቢያት ጥቅል መጻሕፍት ስለ ሰማያዊ
ነገር ተማረ። በሙሴ በኩል እርሱ ራሱ ለእስራኤል ልጆች የተናገራቸውን ቃላት
በእናቱ ጭን ላይ ተቀምጦ ተማራቸው። ከሕፃንነት ወደ ጎልማሳነት እያደገ ሲመጣም
የምሑራኑን ትምህርት ቤቶች አልፈለጋቸውም። መምህሩ እግዚአብሔር ሰለ ነበር
ከእነዚህ ዓይነት ትምህርት ቤቶች የሚገኘውን ትምህርት አልፈለገውም” (የዘመናት
ምኞት፡ ገጽ54።)
ማርያምና ዮሴፍ ለልጃቸው መልካምና ታማኝ መምህራን መሆናቸው ባያጠራጥርም፤
ስለ ልጃቸው ያላስተዋሏቸው ብዙ ነገሮች እንደ ነበሩ በሉቃ. 2፡41-50 የቀረበው
ታሪክ ይገልጽልናል። ለዚህ ምክንያቱ የሱስ ከጌታ ብቻ ያገኘው ወይም ጌታ ብቻ
ያካፈለው ዕውቀትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ስለነበር ነው።
ከላይ የቀረበውን የኤለን ኋይት ጽሑፍ ደግመው ይመልከቱ። የሱስ
የተናገራቸውን ቃላት ከእናቱ እግር ስር ቁጭ ብሎ ስለ መማሩ-እርሷ በዚህ ስፍራ ከጻፈችው መልእክት አኳያ እንዴት ልንመለከተው
እንችላለን? ይህ--እጅግ አስደናቂ ስለሆነው አምላካዊ ፍቅር ምን
ይነግረናል? የወደቅንና ኃጢአተኛ ፍጡራን የሆንነው እኛ--ለዚህ
እንዴት ያለ ምለሽ መስጠት ይኖርብናል?
በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ ሥነ ትምህርት ተጨባጭ ተግባቦት ወይም የግንኙነት
አካል ተብሎ መወሰድ ይችላል። ዕውቀት፣ ጥበብ፣ መረጃ እና ተጨባጭ እውነታዎችን
አጭቆ የያዘው መምህር ይህን ያለውን የከበረ ነገር ለተማሪዎቹ ያጋራል። ማንኛውም
በዕውቀት የበለጸገ ሰው የተሸከመውን ዕውቀት ለሌሎች ማጋራት ይጠበቅበታል።
በመማር ማስተማር ሂደት ይህን ማድረግ ካልቻለ--የማወቁ መልካምነት ምኑ ላይ
ነው?
በሌላ በኩል መልካም የማስተማር ክህሎት ግንኙነት የመፍጠር ችሎታ ብቻ
ሳይሆን፤ ለአጠቃላዩ ሂደት ወሳኝ የሆነውን ግንኙነት መገንባት መቻል ጭምር ነው።
“እውነተኛ መምህር ለተማሪዎቹ መልካም ስጦታ የመሆኑን ያህል እጅግ የከበሩ
ጥቂት ነገሮችን ለተማሪዎቹ ማካፈል ይችላል። ጎልማሶችን፣ ወጣቶችንና ህፃናትን
ቀርበን ስሜታቸውን መካፈል ስንችል አብልጠን እናስተውላቸዋለን። እነዚህን
ወገኖች አብልጠን ለመጥቀም ልናስተውላቸው የግድ ይሆናል።”—Ellen G.
White, Education, p. 212.
በሌላ አነጋገር መልካም የሆነው የማስተማሪያ መንገድ የተማሪውን ስሜት እና
ግላዊ የአረዳድ ችሎታ ጭምር አካቶ ይሠራል። አጠቃላዩን ትምህርት ቤት እንደ
አንድ ቤተሰብ ከመመልከት አኳያ ይህ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በተማሪና መምህር
መሃል መልካም የግንኙነት መስመር የግድ መገንባት ይኖርበታል።
ቀረቤታዎች የሚፈጠሩትና የሚጎለብቱት ዓይነተኛ የግንኙነት መስመር በመዘርጋት
ነው። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ወይም በጸሎት ከእግዚአብሔር
ጋር ግንኙነት መፍጠር ካልቻሉ የመቀጨጭና የመጨንገፍ አደጋ ይገጥማቸዋል።
ቤተሰብ በአምላካዊው ጸጋ እና በክርስቶስ ዕውቀት ማደግ አለበት ካልን፤ መለኮታዊ
ምሪት ሊኖረው የግድ ይሆናል።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። ጠንካራ ቤተሰባዊ ግንኙነቶችን
(ወይም ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት) እንዴት መመስረት እንዳለብን
አስመልክቶ ከጥቅሶቹ ምን መማር እንችላለን? መዝ. 37:7–9፣ ምሳ.
10:31-32፣ ምሳ. 27:17፣ ኤፌ. 4:15፣ 1ዮሐ. 3:18፣ ቲቶ 3:12፣ ያዕ. 4:11።
ተገቢና ትክክል የሆነውን የግንኙነት ዘር ጊዜ ወስዶ መዝራት የቤተሰብ አባላት
ከክርስቶስ ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማስቻል ብቻ ሳይሆን፤ በራሱ በቤተሰቡ
መሃል ያለው የእርስበርስ ግንኙነት እንዲጎለብትም ያስችላል። ልጅዎ ወደ ጉርምስና
ዕድሜ ብሎም ለአካለ መጠን ሲደርስ ደስታ የሚያመጡ አዳዲስ የግንኙነት
መስመሮችን ይከፍታል። ምናልባት ልጅ ባይኖሮት እንኳ በእነዚህ ጥቅሶች የሚገኙ
መርኅዎች ለሁሉም ዓይነት የግንኙነት ዘርፍ ጠቃሚ ውጤት ያስገኙሎታል።
በእጅጉ አስፈላጊው--የምንናገረው ነገር ሳይሆን የአነጋገራችን ሁኔታ
ስለ መሆኑ አሰብ ያድርጉ። የተናገሩት ነገር ትክክል ቢሆንም፤ ነገር
ግን ጉዳዩን ያቀረቡበት መንገድ አጉል ተጽእኖ ካሳደረበት አጋጣሚ
ምን ተምረዋል?
“አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቆጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና
ተግሳጽ አሳድጓቸው” (ኤፌ. 6፡4)።
“ጠባየ ምልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቁ እጅግ ትበልጣለች” (ምሳ. 31፡
10)።
ወላጆች ታላቅ ኃላፊነት አለባቸው። አባት የቤተሰብ ራስ ሲሆን ቤተሰብ ደግሞ ለቤተ
ክርስቲያን፣ ለትምህርት ቤት እና ለሕብረተሰቡ እንክብካቤ የሚያደርግና ዕድገት
የሚያመጣ አካል ነው። አባት ደካማ፣ ኃላፊነት የማይሰማውና ብቃት የጎደለው
ከሆነ--ቤተሰብ፣ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ማኅበረሰቡ ይህን ተከትሎ የሚመጣው
መዘዝ ተጋሪ ይሆናሉ። አባቶች የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን “ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣
ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት” (ገላ. 5፡22-23)
ለማሳየት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
እናቶችም እንዲሁ በሕብረተሰቡ መሃል የሚጫወቱት እጅግ አስፈላጊ ሚና አለ።
የልጆቻቸውን ባህሪያት እና የቤታቸውን ስሜትና አመል በማረቅ ረገድ ታላቅ ተጽእኖ
ማሳደር ይችላሉ። አባቶች ከእናቶች ጋር በጋራ በመሆን ልጆቻቸውን ለማስተማርና
ለማሰልጠን የሚቻላቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ወላጆች ከሚከተሉት ጥቅሶች ምን መማር ይችላሉ? ኢፌ. 5:2223፣ 25- 26፣ 1ቆሮ. 11:3; 2፣ 6:14; ሮሜ 13:13-14፣ 2ጴጥ.
1:5–7፣ ፊልጵ. 4:8.
ክርስቲያን ወላጆች በመጽሐፍ ቅዱስ የቀረበውን ክርስቶስ በባህሪያቸው የማሳየት ሥነ
ምግባራዊ ግዴታ አለባቸው። ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት በጋብቻ
ትስስር ተምሳሌት ቀርቦአል። ወላጆች የመሪነት ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ
ሲያፈገፍጉ ወይም አምባገነን ሲሆኑ፤ ለገዛ ልጆቻቸውም ሆነ ለዓለም የሚያቀርቡት
ሐሰተኛውን የክርስቶስ ምስል ይሆናል። ሁሉም ክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸውን
በትጋት እንዲያስተምሩ እግዚአብሔር ያዛል (ዘዳ. 6፡7)። ወላጆች ልጆቻቸው
ጌታን በፍጹም ልባቸው እንዲወዱ የማስተማር ኃላፊነት አለባቸው። ልጆች ፈሪሐ
እግዚአብሔር እንዲያድርባቸው፣ ሙሉ ለሙሉ በፍቅር ላይ የተመሰረተ አምልኮ
እንዲያደርጉና ራሳቸውን ለእርሱ መስጠት እንዲማሩ ሊታገዙ ይገባል። ወላጆች ጌታ
ለሕዝቡ አድርጓቸው የነበሩ ታላላቅ ነገሮችን ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ የሚያዙ
ግልጽ መመሪያዎችን እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች ሰጥቶ እንደ ነበር በዘዳግ. 6፡
7 ተወስቶ እናገኛለን። የቀደሙት የእግዚአብሔር ሕዝቦች የቱንም ዓይነት ታላላቅ
ታሪኮች ለልጆቻቸው ሊነግሩ ቢችሉም፤ እኛ ከክርስቶስ መስቀል በኋላ የምንኖር
ወገኖች ግን ከእነዚያ ከቀደሙት የተሻለ የምንነግራቸው እንዳለ እናምናለን።
በመሆኑም እኛ የምንሰጠው የፈውስ ሥራ ወይም ሥልጠና አምላካዊውን እውነት
በልጆቻችን ላይ በማፍሰስ ከክርስቶስ ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ማዘጋጀት
ሲሆን፤ ይህ በባህሪው የማያቋርጥ ሂደት ነው።
በስተመጨረሻ--ቅዱስ የሆነው የመምረጥ ነፃነት ለእያንዳንዳችን መሰጠቱን
ልብ ማለት ተገቢ ነው። ውሎ አድሮ ልጆች አድገው ለአካለ መጠን ከደረሱ በኋላ
በእግዚአብሔር ፊት መልስ የሚጡት እነሱ ራሳቸው ይሆናሉ።
የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸው አስቀድሞ ጌታ እንዴት
በአስደናቂ መንገድ እንደመራቸው በተደጋጋሚ ለሕዝቡ ያወሳው ሙሴ፤ ይህን
ያደረገላቸውን ነገር እንዳይረሱ ደጋግሞ አስጠንቅቋቸው ነበር። የኦሪት ዘዳግም
መጽሐፍ የሙሴ የመጨረሻው ፈቃድና ኪዳን እንደ ነበር በብዙ መልኩ መመልከት
ይቻላል። መጽሐፉ በሺህ ከሚቆጠሩ ዓመታት አስቀድሞ የተጻፈ እንደመሆኑ
ባህልንና የኑሮ ዘይቤን አስመልክቶ ከማንኛውም የዛሬው የዕለት ከዕለት ህይወት
ፍጹም የተለየ ቢሆንም፤ መርኅዎቹ ግን እነሆ ለእኛም ይሠራሉ።
ዘዳ. 6 ያንብቡ። ክርስቲያናዊውን የትምህርት መርኅዎች አስመልክቶ ከዚህ
ምዕራፍ ምን መማር እንችላለን? እንደው ለልጆቻችን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እኛ
ስለ እግዚአብሔርና ስለ ታላቁ የደኅንነት ሥራው የምናውቀውን ያህል ለማያውቁ
ለምናስተምራቸው ትምህርቶች ማዕከላዊ ሊሆኑ የሚገባቸው ነገሮች ምንድን
ናቸው? በተጨማሪ ከጥቅሶቹ ምን ዓይነት ማስጠንቀቂያዎች እናገኛለን?
እግዚአብሔር በመካከላቸው ሆኖ ይሠራው የነበረው አስደናቂ ሥራ ሁሉም
ለልጆቻቸው ሊያስተምሩት የሚገባና እያንዳንዱን ቤተሰብ ማዕከል ያደረገ እጅግ
ዋንኛ ተግባር ነበር። እንዲሁም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ነገሮች ሁሉ እንዳይረሱ
የተሰጠው ማስጠንቀቂያ እጅግ ግልጽ ሆኖ የቀረበ ነበር። ወላጆች መጽሐፍ ቅዱሳዊው
አስተምህሮ ከልጆቻቸው ህይወት ጋር ውህደት እንዲፈጥር የሚያስችለውን
ተቀዳሚና ዐበይት ሚና ይጫወቱ ከተባለ፤ በልጆቻቸው ላይ የሚያውሉት በቂ
ዕውቀትና ጊዜ እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩ የገዛ ሕይወታቸውን የማደራጀትና
የማዘጋጀት ኃላፊነት አለባቸው።
“የህፃኑ የመጀመሪያ መምህርት እናት ናት። ጨቅላው በቀላሉ ለማንኛውም ነገር
ተጠቂና ተጋላጭ በሆነባቸው--ደግሞም በፍጥነት በሚያድግባቸው በእነዚያ የቀደሙ
ቀናት ትምህርት የሚቀስምባቸው ዕድሎች ሁሉ በከፍተኛ ሁኔታ የሚወድቁት
በእናቲቱ ላይ ነው።”—Ellen G. White, Education, p. 275.
ይህ፤ ወላጆች ስለ አምላካዊው ፍቅርና የተስፋ ቃል ለልጆቻቸው አገልግሎት
የሚሰጡበት ወቀሳኝ ወቅት ነው። የእግዚአብሔርን ጥበብና ተስፋ ለልጅዎ
ለማስተማር የሚያስችል ጊዜ በግልዎ በመመደብ በቤተሰብዎ ላይ እስከ መጪዎቹ
ትውልዶች የሚዘልቅ አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ።
“ለልጆችህ አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣
ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር” (ዘዳ. 6፡7)። የመልእክቱ
ጭብጥ ምንድን ነው? ሁሌም ቢሆን ጌታ በተጨባጭ ያስቀመጠልንን
ነገር ልጆቻችን እንዲያስቀድሙ መንገር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ራሳችን
ማድረጋችን ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ አስመልክቶ ከጥቅሱ ምን
እንማራለን?
Read Ellen G. White, “Preparation,” pp. 275–282 in
Education; “Cooperation,” pp. 283–286 in Education; “Discipline,” pp.
287–297 in Education.
“ልጅ ለቀደሙት ብሎም ለቀጣዮቹ ዓመታት የሚወስዳቸው ሥልጠናዎች ኃላፊነት
በአባቶች እና በእናቶች ጫንቃ ላይ የሚያርፍ እንደመሆኑ--አፋጣኝ፣ ጥንቃቄ
የተሞላበትና ጥብቅ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ባልና ሚስት እባት እና
እናት ለመሆን የሚያስችላቸውን ኃላፊነት ከመውሰዳቸው አስቀድሞ ከአካላዊ
ዕድገት ሕግጋት ጋር ሊተዋወቁ ይገባል… የሥነ አእምሮ ዕድገት ብሎም የሥነ ምግባር
አስተምህሮ ሕግጋትን ማስተዋል ይኖርባቸዋል።”—Ellen G. White, Education,
p. 276.
“የትብብር ሥራ በራሳቸው--በእናት እና አባት አማካይነት በቤት ውስጥ ህይወት
ሊጀምር ይገባል። ወላጆች ልጆቻቸውን በማሰልጠን ረገድ የጋራ ኃላፊነት ያለባቸው
ሲሆን፤ ይህ በአንድነት የሚተገብሩት የዘወትር ጥረት ሊሆን ይገባል። እርስ በርስ
መደጋገፍ የሚያስችላቸውን እርዳታ ከእርሱ እየሻቱ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር
የሚያስገዙ ይሁኑ። ይህን ሥልጠና የሚሰጡ ወላጆች መምህሩን የሚተቹ ዓይነት
ሆነው አይገኙም። ይልቁንም የልጆቻቸው ፍላጎት እና ትምህርት ቤቱ ከሚጠይቀው
ቅን ምልከታ አኳያ--የሚቻለውን ያህል በማካፈል ኃላፊነታቸውን እንደተወጡ ሆኖ
ይሰማቸዋል።”—Ellen G. White, Education, p. 283.
1.ልጆች ኖሩን ወይም አልኖሩን የሁላችንም ህልውና በቤተሰባዊ ዘውግ እና የእርስ
በርስ ቁርኝት የተሳሰረ ነው። እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢም ሆነ በሌላ ስፍራ ከሌሎች
ጋር መስተጋብር በመፍጠር ወይም ከዚያም አለፍ ብሎ ለመመስከር ሊረዳዎ የሚችል
ምን ዓይነት ትምህርት ከዚህ ሣምንት ጥናት ማግኘት ችለዋል?
2.ሥነ ትምህርትን እንደ መልካም ነገር የመመልከት ዝንባሌ አለን (ደግሞስ ሥነ
ትምህርትን ማን ሊቃወም ይችላል?)። ነገር ግን ይህ ሁሌም እንደ ተጠበቀው ይሆናል?
ሥነ ትምህርት አሉታዊ ወደ ሆነ ሁናቴ እንዲቀለበስና አስከፊ ውጤት እንዲከተል
መንስኤ የሆኑ ምን ዓይነት ምሳሌዎች ይኖራሉ? ሥነ ትምህርትን መልካም መሣሪያ
ማድረግ እንችል ዘንድ ከእነዚህ አሉታዊ ምሳሌዎች ምን መማር እንችላለን?
3.በረቡዕ ጥናታችን እንደተጠቀሰው ሁላችንም ቅዱሱን የመምረጥ ነፃነት
ተሰጥቶናል። ልጆች ውሎ አድሮ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ብሎም ወደ ጉልምስና
ሲያመሩ፤ በልጅነት ዕድሜአቸው ስለ እግዚአብሔር አምላክ የተማሯቸውን
ትምህርቶች በገዛ ምርጫቸው ያጸናሉ። እኛ ሁላችንም ወላጆች ሆንን ወይም
ማንኛውም ለሌሎች ምስክር ለመሆንና ወንጌልን ለማስተማር ምኞት ያለው ሁሉ፤
ወሳኝ የሆነውን ይህን የመምረጥ ነፃነት እውነታ ሁሌም በአእምሮው መያዝ የለበት
ይሆን?