የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ
ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ማቴ. 10:22፤ ዮሐንስ 6:29፤ ዘዳግም 28:1–14፤ ምሳሌ 3:1–10፤ ሚልክያስ 3:7–11፤ ማቴ. 6:25–33።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡልሃል ያገኙህማል።” (ዘዳግም 28:1፣ 2)።
በ
ሚያስደንቅ ሁኔታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ውል (ቃል ኪዳኖችን)
ፈጽሟል። አብዛኞቹ ቃል ኪዳኞች ሁለቱም አካሎች ማለትም
እግዚአብሔርና ሰብአዊ ፍጡራን የሚፈጽሙት የየራሳቸው ድርሻ
ያላቸው ናቸው። የዚህ የሁለትዮሽ ቃል ኪዳን ምሳሌ ‹‹አንተ ይህን ካደረግክ እኔ
ደግሞ ያን አደርጋለሁ›› ወይም ‹‹እኔ ይህን ካደረግኩ አንተ ያን ታደርጋለህ›› የሚል
ነው።
‹‹አንተ አንዳች ብታደርግም ባታደርግም እኔ ይህን አደርጋለሁ›› የሚል አንድ
ወገን ብቻ ቃል ኪዳን የገባባቸው ያልተለመዱ አጋጣሚዎች አሉ። እግዚአብሔር
ከሰብአዊ ፍጡራን ጋር ከፈጸማቸው ቃል ኪዳኖች ጥቂቶቹ በአንድ ወገን ብቻ
የተፈጸሙ ናቸው። ለምሳሌ፡“እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም
ላይ ዝናቡን ያዘንባልና” (ማቴ. 5:45) የሚለው የዚህ ዓይነት ቃል ኪዳን ነው።
እኛ ብናደርግም ባናደርግም እግዚአብሔር ዝናብንና ፀሐይን ይሰጠናል። የውኃ
ጥፋትን ተከትሎ፣ ከድርጊቶቻችን ጋር ባልተገናኘ መልኩ፣ ለሰብአዊ ዘርና
‹‹በምድር ላይ ላሉት እንስሳት በሙሉ›› ምድርን በሙሉ የሚሸፍን ሌላ የውኃ
ጥፋት እንደማያመጣ እግዚአብሔር ቃል ገባ (ዘፍጥረት 9:9–16ን ይመልከቱ) ።
ደግሞም እንዲህ በማለት ቃል ገባ፡- “በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥
ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም” (ዘፍጥረት 8:22)።
እኛ ከምናደርገው ነገር ጋር ባልተገናኘ መልኩ ወቅቶች ይመጣሉ ይሄዳሉም።
በዚህ ሳምንት በእግዚአብሔርና በልጆቹ መካከል የተፈጸሙ ጥቂት እጅግ ወሳኝ
የሆኑ የሁለትዮሽ ቃል ኪዳኖችን እናጠናለን። በእግዚአብሔር ፀጋ ‹‹ድርሻችንን
መወጣት እንድንችል›› እንጸልይ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለጥር 6 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
የክርስቶስ በቀራኒዮ መሞት ከዚህ በፊት በምድር ላይ ለኖረም ሆነ ወደ ፊት ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ድነትን የሚቻል ነገር አድርጓል። ከወቅቶች ቃል ኪዳን በተቃራኒ ድነት በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም አይደለም--ከድርጊታቸው ጋር ባልተገናኘ መልኩ ለሁሉም የተሰጠ አይደለም። ሁሉም ይድናሉ የሚለው እምነት ‹‹አለም አቀፋዊነት›› (ዩንቨርሳሊዝም) ይባላል። ኢየሱስ ምንም እንኳን ለሰብአዊ ዘር በሙሉ ቢሞትም ብዙ ሕዝብ ወደ ጥፋትና ወደ ዘላለም ሞት በሚወስደው ሰፊው መንገድ ላይ እንደሚሄዱ በግልጽ አስተምሯል (ማቴ. 7:13፣ 14)። ሰዎች በኢየሱስ የሚሰጠውን የድነት ስጦታ እንዴት እንደሚቀበሉ የሚከተሉት ጥቅሶች ምን ይላሉ? 1ኛ ዮሐንስ 5:13 ______________________________________________
ማቴ. 10:22 _________________________________________________
ዮሐንስ 6:29 _________________________________________________
2ኛ ጴጥ. 1:10፣ 11 ____________________________________________
ጳውሎስ የድነት ቃል ኪዳን የሁለትዮሽ ባህርይ እንዳለው አስተዋለ።
በቅርቡ እንደሚገደል ስላወቀ፣ ብዙ ወዳጆቹ ቢተውትም፣ በቃል ኪዳኑ
ውስጥ የራሱን ድርሻ መወጣቱን ውድ ለሆነው ወዳጁ ለጢሞቴዎስ በሙሉ
መተማመን ነገረው። “በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት እንዲሰዋ
ተዘጋጅቻለሁ፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥
ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል
ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥
ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” (2ኛ ጢሞ.
4:6–8).
ጳውሎስ “መልካሙን ገድል ስለተጋደልሁ፣ ሩጫዩንም ስለጨረስሁ፥
ሃይማኖቴንም ስለጠበቅሁ አሁን ተዘጋጅቻለሁ” ይላል። ነገር ግን ድነት በሕግ
ሥራ ሳይሆን በእምነት ብቻ ስለመሆኑ ጳውሎስ ሁልጊዜ ጥርት ያለ መረዳት
ስለነበረው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ወደ ራሱ ሥራዎች ወይም
ስኬቶች እየተመለከተ አይደለም። ጳውሎስ እንዲሰጠው እየጠበቀ ያለው ‹‹የጽድቅ
አክሊል›› በእምነት እንዲሰጠው የጠየቀውና እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ አጥብቆ
የያዘው የኢየሱስ ጽድቅ ነው።
ምንም እንኳን ድነት በእኛ መልካምነት ላይ ያልተመሰረተ ስጦታ
ቢሆንም ስጦታውን በሚቀበሉና በማይቀበሉ ሰዎች መካከል ያለው
ልዩነት ምንድር ነው? ይህን ስጦታ መቀበል ምን እንድናደርግ
ይጠይቀናል?
የዘዳግም መጽሐፍ፣ ከአርባ ዓመታት የምድረ በዳ መቅበዝበዝ በኋላ
ለተወለዱት ሁለተኛ ትውልድ እሥራኤላውያን፣ የሙሴ ስንብት መልእክቶች
በጽሁፍ የተቀመጠ መረጃ ነው። እነዚህ መልእክቶች የተሰጡት ከኢያርኮ
በስተምሥራቅ ባሉት የሞዓብ ሜዳዎች ላይ ነበር። ዘዳግም ‹‹የመታሰቢያ
መጽሐፍ›› ተብሎ መጠረቱ ተገቢ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር ከእሥራኤላውያን ጋር የነበረውን አሰራር
በታማኝነት ይከልሰዋል። ከሲና ተራራ አንስቶ በተስፋይቱ ምድር ጫፍ ላይ
እስካለው እስከ ቃዴስ ባርኔ ያደረጉአቸውን ጉዞዎች፣ አመጻቸውንና የአርባ
ዓመታት የምድረ በዳ መቅበዝበዝን እንደገና ያስታውሳል። አስርቱን ትዕዛዛት፣
የአስራት መስፈርቶችንና ማዕከላዊውን ጎተራ እንደገና ጻፋቸው። ነገር ግን
የዘዳግም መጽሐፍ ግንባር ቀደም ትኩረት እግዚአብሔርን እንዲታዘዙና በረከቱን
እንዲቀበሉ ምክር መስጠት ነው። ሙሴ እግዚአብሔርን የሚስለው ለሕዝቡ
ለመጠንቀቅ ችሎታና ፍላጎት እንዳለው አምላክ ነው።
ዘዳግም 28:1–14ን ያንብቡ። ለሕዝቡ ምን ታላቅ ተስፋ ነው የተሰጠው?
ነገር ግን ተስፋውን ለመቀበል ምን ማድረግ ነበረባቸው?
ሙሴ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ድንቅና ተአምራዊ በረከቶችን ሊሰጣቸው
እንደሚያስብ እንዲረዱ እጅግ ይጓጓል። ‹‹ተግታችሁ ብትሰሙት›› የሚሉት
ቃሎቹ ዘላለማዊ መዳረሻቸው አደጋ ላይ እንዳለ እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል።
እንዴት ያለ የምርጫ ነጻነት እውነታ አስደናቂ መገለጫ ነው። የእርሱ ምርጥ
ሕዝብ፣ ታላላቅ በረከቶችና ታላላቅ ተስፋዎች ተቀባዮች ነበሩ፣ ነገር ግን እነዚያ
በረከቶችና ተስፋዎች በሁኔታዎች የሚወሰኑ ናቸው። ተቀባይነት ማግኘት፣
መወሰድና ሥራ ላይ መዋል አለባቸው።
እግዚአብሔር የጠየቃቸው ማንኛውም ነገር ለመተግበር እጅግ የሚከብድ
አልነበረም። “እኔ ዛሬ የማዝዝህ ይህች ትእዛዝ ከባድ አይደለችም፥ ከአንተም
የራቀች አይደለችም።
ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ
እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል በሰማይ አይደለችም። ሰምተን
እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕሩን ተሻግሮ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው?
እንዳትል ከባሕሩ ማዶ አይደለችም። ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ በአፍህና
በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው” (ዘዳግም 30:11–14፣)።
ከበረከቶቹ ባሻገር ካልታዘዙ ሊመጡባቸው ስለሚችሉ እርግማኖች
ማስጠንቀቂያዎች ነበሩ፤ ያ ማለት ኃጢአታቸውና አመጻቸው ምን መዘዝ
እንደሚያመጣ ማስጠንቀቂያዎች ነበሩ (ዘዳግም 28:15–68)።
እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚነግረንን ነገር ‹‹ተግቶ መስማት›› ማለት
ዛሬ ለእኛ ምን ማለት ነው?
የምሳሌ መጽሐፍ ስለ ጥበብና ስለ ሞኝነት የሚናገረውን ያህል ትክክልና ስህተት ስለሆነው ነገር አይናገርም። አንድ ሰው መጽሐፉን ሲያነበው የጥበብን ጥቅሞችና የሞኝነትን አደጋዎች ይመለከታል። ምሳሌ 3:1–10ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ የተሰጡት እንዴት ያሉ አስደናቂ ተስፋዎች ናቸው? ‹‹ከሀብትህ ሁሉ በኩራት ወይም የመጀመሪያ ፍሬ›› ማለት ምን ማለት ነው?
እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ባለቤት ስለመሆኑ እውቅና ለመስጠትና ለእኛ
የሚያስፈልገንን ሁሉ እንደሚሰጠን ስላለን እምነት ማሳያ እንዲሆን በንብረታችን
አስተዳደር ላይ እርሱን እንድናስቀድም ይጠይቀናል። ከዚህም በላይ እርሱን
የምናስቀድም ከሆነ የቀረውን ነገር እርሱ እንደሚባርክ ይናገራል። ለእኛ ይህን
ማድረግ፣ ማለትም እርሱን ማስቀደም፣ የእምነትና የመታመን ሥራ፣ በሙሉ
ልባችን በጌታ መታመናችንን ማሳየትና በራሳችን ማስተዋል አለመደገፍ ነው
(ብዙ ጊዜ እኛ ማስተዋል የማንችላቸውና ትርጉም ሊሰጡን የማይችሉ ነገሮች
ስለሚከሰቱ ይህ በተለየ ሁኔታ ጠቃሚ ነው)።
በእግዚአብሔርና በእርሱ ፍቅር መታመንን በተመለከተ ከመስቀል ይልቅ ሌላ
ምንም ነገር ሊቀሰቅሰን አይገባም። እያንዳንዳችን በኢየሱስ የተሰጠንን ነገር፣ እንደ
ፈጣሪያችንና (ዮሐ. 1፡1-4) ደጋፊያችን (ራዕይ 5፡9) ብቻ ሳይሆን እንደ አዳኛችንም
(ራዕይ 5፡9) ስንገነዘብ ካለን ነገር ሁሉ የመጀመሪያ ፍሬን ለእግዚአብሔር መመለስ
ልናደርግ ከምንችለው እጅግ አነስተኛው ነገር ነው።
“እግዚአብሔር አሥራት የእርሱ እንደሆነ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ለእርሱ እንዴት
መጠበቅ እንዳለበትም ይነግረናል። ‹‹እግዚአብሔርን በሀብትህ አክብር ከፍሬህም
ሁሉ መጀመሪያ›› ይላል። ይህ ሀብታችንን ለራሳችን ተጠቅመን የቀረውን ለጌታ
እንድናመጣ አያስተምረንም። የእግዚአብሔር ድርሻ መጀመሪያ ይለይ።”—Ellen
G. White, Counsels on Stewardship, p. 81.
እርሱን ብናስቀድም ‹‹ጎተራችን ሞልቶ እንደሚትረፈረፍ›› እግዚአብሔር
ተናግሮአል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው በተዓምር አይደለም፤ ይህ ማለት አንድ
ቀን ስትነቃ ጎተራዎችህና መጥመቂያዎችህ በድንገት ሞልተው ታገኛለህ ማለት
አይደለም።
ይልቁንም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መልካም መጋቢነት፣ በጥንቃቄ ስለማቀድና ገንዘብን
በሀላፊነት ስለማስተዳደር በሚናገሩ መርሆዎች የተሞላ ሲሆን እግዚአብሔር
እንድንተገብረው በሚጠራን ነገር ላይ ታማኝ ሆኖ መገኘት የእኛ ግንባር ቀደም
ሀላፊነት ነው።
ታማኝ ለመሆን እየፈለግን ሳለ ጎተራዎችና መጥመቂያዎች ሙሉ
ባይሆኑም፣ ከባድ የሆነ የገንዘብ ችግር ባለባቸው ጊዜያቶችም ቢሆን፣
በእግዚአብሔርና በተስፋዎቹ መታመንን እንዴት እንማራለን?
በአከፋፈል ልምምድና ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት መካከል የቀረበ መንፈሳዊ ግንኙነት አለ። እሥራኤላውያን እግዚአብሔርን ሲታዘዙና በአስራት ታማኝ ሲሆኑ በለጸጉ። ከዚህ በተቃራኒ ይህንን ባላደረጉ ጊዜ ችግር ገጠማቸው። በመታዘዝ የመበልጸግና ባለመታዘዝ ችግር ውስጥ የመግባት ዑደትን የሚከተሉ ይመስላሉ። እግዚአብሔር በነቢዩ ሚልኪያስ አማካይነት ከሕዝቡ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነትን ለመፈጸም የጠየቀው ከእነዚህ ታማኝነት ካልታየባቸው ጊዜያቶች መካከል በአንዱ ወቅት ነበር። ሚልክያስ 3፡7-11ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉ ተስፋዎችና ግዴታዎች ምንድር ናቸው?
ሕዝቡ ወደ እርሱ ከተመለሱ እርሱም ወደ እነርሱ እንደሚመለስ እግዚአብሔር
ቃል ገብቷል። ወደ እርሱ መመለስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በጠየቁት ጊዜ
‹‹አሥራትንና ሥጦታን መቀማትን አቁሙ›› በማለት በግልጽ ተናግሮአል።
ለመረገማቸው ምክንያቱ ቀማኛነታቸው ነበር። ለእርግማኑ እግዚአብሔር
ያስቀመጠው መፍትሄ ይህ ነው፡- “አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ” (ሚልክያስ
3:10)። ይህንን ካደረጋችሁ “የሰማይን መስኮቶች እከፍትላችኋለሁ፣ በረከትንም
ማስቀመጫ ቦታ እስክታጡ ድረስ አትረፍርፌ አፈስላችኋለሁ”ይላል።
የምናስቀምጥበት ቦታ እስከማይኖረን ድረስ ከተቀበልን ሌሎችን ለመርዳትና
የእግዚአብሔርን ስራ ለማስፋፋት የሚያስችል ትርፍ ነገር አለን ማለት ነው።
“እንዲሞትልህ አንዲያ ልጁን የሰጠው አምላክ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን ፈጽሟል።
በረከቶቹን ይሰጥሃል፣ ለዚያ ምላሽ አስራትና ስጦታ እንድታመጣለት ይሻል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማስዋል የምችልበት ምንም መንገድ የለም ብሎ ለመናገር
ማንም መድፈር አይችልም። አስራትንና ስጦታን በተመለከተ የእግዚአብሔር
ዕቅድ በሚልኪያስ መጽሐፍ ምዕራፍ ሶስት ላይ በግልጽ ተነግሮአል። ሰብአዊ
ወኪሎች ለስምምነቱ እውነተኛ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ይጠራቸዋል።”—Ellen
G. White, Counsels on Stewardship, p. 75.
ከመታዘዝ አዎንታዊ ዑደቶች መካከል አንዱ ተመዝግቦ ያለው፣ መልካም
የነበረው የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሰበት ዘመን ነው። በይሁዳ ትክክለኛ
መነቃቀት ስለነበር ሕዝቡ አስራትንና ስጦታን በታማኝነት ወደ ቤተ መቅደስ ጎተራ
መመለስ ጀምሮ ነበር። እጅግ ብዙ አስራትና ስጦታ ስለመለሱ በቤተ መቅደስ
ውስጥ ተከምሮ ነበር። ሕዝቡ “የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥
የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በኵራት በሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት አብዝተው ባቀረቡ”
ጊዜ ምን እንደሆነ 2ኛ ዜና 31፡5 ይነግረናል።
አስራት መመለስዎ ወይም አለመመለስዎ ስለ ራስዎ መንፈሳዊነትና
ከእግዚአብሔር ጋር ስላለዎ ግንኙነት ምን ይናገራል?
ስለ ኢየሱስ ‹‹ተራው ሕዝብ በደስታ አዳመጡት›› ተብሏል (ማርቆስ 12፡
37)። ክርስቶስን ከተከተሉትና ካዳመጡት ብዙ ሕዝብ መካከል አብዛኞቹ የዚህ
ቡድን አባላት የነበሩ ተራ ሕዝብ ነበሩ። በተራራው አጠገብ ኢየሱስ የመገባቸውና
የተራራውን ስብከት የሰሙት እነዚህ ሰዎች ነበሩ። ኢየሱስ በመሰረታዊነት ግድ
የሚላችሁ የቤተሰቦቻችሁን ፍላጎቶች ማሟላት እንደሆነ አውቃለሁ አላቸው።
በየቀኑ ለሚያስፈልጋችሁ ምግብና መጠጥ፣ እንዲሁም ለሰውነታችሁ ሙቀት
ለሚሰጣችሁና ለሚከላከልላችሁ ልብስ ትጨነቃላችሁ። ነገር ግን እኔ የምሰጣችሁ
ሀሳብ ይህ ነው አላቸው።…
ማቴዎስ 6፡25-33ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ቃል የተገባው ተስፋ ምን
ነበር? እነዚህን ተስፋዎች ለመቀበል ሰዎቹ ምን ማድረግ ነበረባቸው?
እግዚአብሔር የሰጣቸው ብዙዎቹ ተስፋዎች የሁለትዮሽ ቃል ኪዳን ያለባቸው ናቸው። በረከቱን ለመቀበል የራሳችንን ድርሻ መወጣት ያስፈልጋል። ኢሳይያስ 26፡3ን ያንብቡ። የእግዚአብሔርን ሰላም ለማግኘት ምን እንድናደርግ ነው የተጠየቅነው?
1ኛ ዮሐንስ 1፡9ን ያንብቡ። ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኢየሱስ ምን ያደርግልናል?
2ኛ ዜና 7፡14ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ እግዚአብሔር ባቀረበው ሀሳብ ላይ እንዲህ ቢሆን ይህ ይሆናል የሚሉ ሀሳቦች ምንድር ናቸው?
እነዚህና ሌሎች ብዙ ጥቅሶች እግዚአብሔር ሉአላዊ አምላክ ቢሆንም፣
ፈጣሪያችንና ደጋፊያችን ቢሆንም፣ ድነት የፀጋ ስጦታ እንጅ በእኛ መልካም
ሥራ የማይገኝ ቢሆንም፣ በዚህች ምድር ላይ በሚካሄደው በታላቁ ተጋድሎ ላይ
የምንጫወተው ክፍል አለን። የፈቃድና የምርጫ ነጻነትን ቅዱስ ስጦታ በመጠቀም
የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ለመከተልና እግዚአብሔር እንድናደርግ እየጠራን ያለውን
ነገር ለመታዘዝ መምረጥ አለብን። እግዚአብሔር በረከትንና ሕይወትን ቢሰጠንም
በዚያ ፋንታ እርግማንንና ሞትን መምረጥ እንችላለን። እግዚአብሔር ‹‹እንግዲህ
አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ›› ማለቱ አያስደንቅም።
(ዘዳግም 30፡19)።
:- “በዓለም የትኛውም ወቅት ቢሆን የእግዚአብሔር ሕዝብ
በስልታዊ ልግስና (አስራት በመመለስ) እና ስጦታዎችን በመስጠት የእርሱን እቅድ
በደስታና በፈቃደኝነት በፈጸሙ ጊዜ ሁሉ የእርሱን መስፈርቶች በታዘዙበት ልክ
ብልጽግና ልፋታቸውን ሁሉ እንደሚያጅብ የተገበላቸውን ተስፋ ተገንዝበዋል።
እግዚአብሔርን በሀብታቸው በማክበር፣ እርሱ የሰጣቸውን ተስፋ እውቅና
ሲሰጡና ከመስፈርቶቹ ጋር ሲስማሙ ጎተራዎቻቸው ሞልተው ተትረፈረፉ። ነገር
ግን አስራትንና ስጦታን ባለመመለስ እግዚአብሔርን ሲቀሙ ለእርሱ መመለስ
ያለባቸውን ስጦታዎች በገደቡት ልክ እርሱም ለእነርሱ የሚሰጣቸውን በረከቶቹን
ስለገደበ እየዘረፉ ያሉት እርሱን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም እንደሆነ ተገነዘቡ።
”—Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 3, p. 395.
የዳንነው የእግዚአብሔር ፀጋ ስጦታ በሆነው በእምነት ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ
ቅዱስ ግልጽ ያደርጋል። ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት መታዘዛችን ለእርሱ ፀጋ ምላሽ
ነው። ፀጋ በእኛ ስራ አይገኝም (በእኛ ሥራ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ፀጋ አይሆንም
ነበር። ሮሜ 4፡1-4ን ይመልከቱ) ።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የፈጸመውን የሁለትዮሽ ቃል ኪዳን ስንመለከት
በረከቶቻችንንና ሀላፊነቶቻችንን ማየት እንችላለን። እግዚአብሔር ለሚሰጠን
ነገር በምንሰጣቸው ምላሾቻችን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት በማጽናት በከፍተኛ
ደረጃ የራሳችንን መዳረሻ እንወስናለን። መታዘዝ--የፍቅር አገልግሎትና መገዛት-የደቀ መዝሙርነት እውነተኛ ምልክት ነው። ከመታዘዝ ነጻ በመሆን ፈንታ
እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠይቀውን መታዘዝ ተግባራዊ ማድረግ እንድንችል
የሚያደርገን የክርስቶስ ጸጋ ተካፋዮች ያደረገን እምነትና እምነት ብቻ ነው።
1.እያንዳንዱ አድቬንቲስት አስራትን በመመለስ ታማኝ ቢሆን
ኖሮ ቤተ ክርስቲያናችን መልእክቱን ለማሰራጨት የምትፈልገውን
ነገር ሁሉ ለማድረግ ከበቂ በላይ ገንዘብ ይኖራት ነበር ይባላል።
ቤተ ክርስቲያን እንድትፈጽም የተጠራችበትን ነገር ማድረግ
እንድትችል ለመርዳት አስራትንና ስጦታን በተመለከተ እርስዎ
ምን እያደረጉ ነው?
2.ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ምርጫዎቻችንና ሥራዎቻችን
ምን ያህል አስፈላጊ ናቸው የሚለውን አመለካከት ያስቡበት።
አስራትን፣ ጸሎትንና ጥሩ መጋቢነትን በማካተት በሕጋዊነት
ወጥመድ ውስጥ ሳንወድቅ የሥራና የመታዘዝ ጥያቄዎችን በፊታችን
ማቆየት የምንችለው እንዴት ነው?
3.ታማኝ እንኳን ብንሆን አስቸጋሪ ጊዜያቶች ስለሚመጡበት ሁኔታ
ስለሚነሳው ጥያቄ በክፍላችሁ በማክሰኞ ትምህርት መጨረሻ ላይ
ተነጋገሩ። ይህ ሲሆን እንዴት ነው መረዳት የምንችለው? ሲሆንስ
ከተስፋ መቁረጥ የምንጠበቀው እንዴት ነው?