የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚተከሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐንስ 21፤ ዮሐንስ 11:9፣ 10፤ዮሐንስ 8:42–44፤ ዮሐንስ 4:46–54፤ 2 ጢሞ. 3:16 ፤ ዮሐንስ 15፡1-11።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም
ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤
እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” (ዮሐ. 5፡39)።
የዮሐንስ ወንጌል ልክ እንደ ማርቆስ ወንጌል፣ በገሊላ በሚሆን መሰባሰብ ይደመደማል።
ይህ የዮሐንስ የመጨረሻ ትምህርት ስለዚያ ስብሰባ የሚናገር ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስን እና
የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደምናውቅ ከሚገልጸው ጭብጥ ጋር ይገናኛል፤ ይህም
በአራተኛው ወንጌል ውስጥ የሚታይ ጽንሰ-ሀሳብ ነው።
ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ከሦስት ዓመታት በላይ ቢቆዩም፣ ኢየሱስ የሚሆነውን
ደጋግሞ ቢነግራቸውም፣ አሁንም ለሥቅለቱና ለትንሣኤው ዝግጅት በጣም ይጎድላቸው ነበር።
እንደ አለመታደል ሆኖ ቃሉን አልተቀበሉትም ነበር። እኛም ተመሳሳይ ስህተት የመሥራት
ችግር ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን፦ ይህም የእግዚአብሔርን ቃል ልንሰማ ወይም ልናነብም
ብንችልም፣ ነገር ግን በቃሉ አለመኖር እና አለመታዘዝ፤ ማለትም ሃሳባችንንና ድርጊታችንን ሊመራ
የሚገባ ብርሃን አድርገን አለመቀበል ማለት ነው። ይህ ምናልባትም በሚያሳዝን ሁኔታ በጣም ብዙ
ክርስቲያኖች ሳያውቁት ያሉበት ሁኔታ ነው።
በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ባለን የመጨረሻ ሳምንት ስለ ኢየሱስ ከማወቅ እንድንሻገር፣
ይልቁንም እሱን በተሻለ እንድናውቀው እንዲሁም በእርሱ እና በቃሉ ውስጥ እንድንኖር ሊረዱን
የሚችሉትን የዚህን ወንጌል ቁልፍ ነጥቦች ጥቂቶቹን እንመለከታለን።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለታኅሣሥ 19 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዮሐንስ 21:1-19ን አንብቡ። ስለ እግዚአብሔር ጸጋ እና ስለ ሰው ትሕትና በተለየ መልኩ ምን ወሳኝ እውነቶች ተገለጡ?
ዮሐንስ 20 የሚያበቃው ለመደምደም ምክንያታዊ አግባብ ባለው በመጽሐፉ ዓላማ
ነው፣ ነገር ግን አንድ ተጨማሪ ምዕራፍ አለ። ምዕራፍ 21 የሚጀምረው ጴጥሮስን ጨምሮ
አንዳንድ ደቀ መዛሙርት ወደ ገሊላ ተመልሰው ሌሊቱን በባህር እንዳሳለፉ በመጠቆም
ነው። አሮጌው ዘመን የተመለሰ፣ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቀድሞው ዓሣ የማጥመድ ሥራቸው
የተመለሱ ይመስላል። ነገር ግን በዚያ ምሽት ምንም ዓሣ አልያዙም ነበር።
በማለዳ በባህር ዳርቻ ላይ የተገኘ አንድ ሚስጥራዊ እንግዳ መረባቸውን በጀልባው
በቀኝ በኩል እንዲጥሉ ነገራቸው። ከዚያም መረቡን ወደ ውስጥ መሳብ እስከማይችሉ ብዙ
ዓሦችን ያዙ። ከኢየሱስ ጋር አገልግሎት ሲጀምሩ የነበረውን ጊዜ ይመስላል (ሉቃስ 5:1-11ን
ተመልከቱ)። ዮሐንስ ኢየሱስን አውቆት ወዲያው ለጴጥሮስ ነገረው፤ እርሱም ዘሎ ወደ ውሃው
ውስጥ ከገባ በኋላ ወደ ባሕሩ ዳርቻ መጣ።
ለጌታው ያለውን ፍቅር በተመለከተ ኢየሱስ ጴጥሮስን ሦስት ጥያቄዎችን ጠየቀው።
ከስቅለቱ በፊት፣ ጴጥሮስ ነፍሱን ስለ ኢየሱስ አሳልፎ እንደሚሰጥ አጥብቆ ተናግሯል (ዮሐንስ
13፡37)። የዚያን ጊዜ ነበር ኢየሱስ ይልቁንም እርሱ ሦስት ጊዜ እንደሚክደው የነገረው (ዮሐንስ
13፡38)። በገሊላ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ጴጥሮስ ራሱን ምሥክር አድርጎ አላቀረበም፤
ከዚህ ይልቅ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ። እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው”
እንጂ (ዮሐንስ 21:17)።
አንዳንዶች ኢየሱስ ጴጥሮስን ሲጠይቅ (ከመጨረሻው ጊዜ በስተቀር) “አጋፔዮ”
(“agapaō”) የሚለውን ግስ እንደተጠቀመ፣ ጴጥሮስ ደግሞ ሁል ጊዜ “ፊሌዮ” (“phileō”)
በሚለው ግሥ ምላሽ ይሰጥ እንደነበር ያስተውላሉ፤ ይህም ልክ እንደ ጓደኛ መውደድን
ይገልጻል። አንድምታው ጴጥሮስ ከፍ ወዳለው የፍቅር ዓይነት አልደረሰም ማለት ነው።
በእርግጥም፣ የጴጥሮስ ምላሽ ራስን ዝቅ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። ጴጥሮስ
የበፊቱን ውድቀቱን በመመልከት፣ በትሕትናና ስለ ራሱ ከልክ በላይ መናገርን ባለመፈለግ
“ዝቅ ያለ ቃል” መጠቀሙ ሳይሆን አይቀርም። ኢየሱስም ያረጋገጠው ይህንን ትህትና ነው፤
ይህም ጴጥሮስን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ነበር። ትህትና አንዱ ትልቅ የአገልግሎት መመዘኛ
እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም፣ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ የትኩረት ማዕከል ኢየሱስ ክርስቶስ
እንጂ ራስ ሊሆን አይችልም።
የጴጥሮስ ተሐድሶ እና በቀደመችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሪነት ሚናው ኢየሱስ
ከሞት መነሳቱን ከሚያሳዩት ጠንካራ ማስረጃዎች አንዱ ነው። ኢየሱስ በሌሎቹ ደቀ መዛሙርት
ፊት ወደ አገልግሎት መልሶት ካልሆነ በስተቀር ጴጥሮስ ከዚያ ሁሉ በኋላ ጎልቶ የወጣበትን
ምክንያት ማስረዳት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።
ጌታን ለማወቅ ለሚፈልግ ሰው ትህትና ቁልፍ የሆነው ለምንድነው? በመስቀሉ
ብርሃን ፊት ማናችንም ብንሆን ልንኮራበት የምንችለው ምን ነገር አለ?
ዮሐንስ 21:20-22ን አንብቡ። ጴጥሮስን ወደ ተሳሳተ ጎዳና የመራው የትኛው ጥያቄ ነው? ኢየሱስ መንገዱን ያቃናው እንዴት ነው?
ኢየሱስ ጴጥሮስን ወደ አገልግሎት መልሶት “ተከተለኝ” ብሎት ነበር። ይህ ማለት
በባሕሩ ዳርቻ ከኢየሱስ ኋላ በአካል ተከትሎ መሄድ ሊሆን ይችላል። ይህም የሆነው ጴጥሮስ
ዘወር ብሎ ዮሐንስ ኢየሱስን ሲከተል ስላየ ነው፤ ከዚያም “ጌታ ሆይ፥ ይህስ እንዴት ይሆናል?”
ብሎ ይጠይቃል (ዮሐንስ 21:21)።
ጴጥሮስን ወደ አገልግሎት ሲመልስ፣ ኢየሱስ የጴጥሮስን አሟሟት ተንብዮ ነበር
(ዮሐንስ 21፡18)። ጴጥሮስ ስለ ዮሐንስ ሞት የማወቅ ጉጉት የነበረው ይመስላል። ኢየሱስ በሌላ
ደቀ መዝሙር ላይ ምን እንደሚደርስበት እንዳይጨነቅ የጴጥሮስን ትኩረት እርሱን ወደ መከተል
ጉዳይ ይመልሳል።
ዮሐንስ 21:23–25ን አንብቡ። ኢየሱስ የተናገረው ነገር በተሳሳተ መንገድ
የተወሰደው እንዴት ነው? ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን አለመግባባት ማስተካከል
የቻለው እንዴት ነው?
ኢየሱስ “እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ፥ ምን አግዶህ? አንተ ተከተለኝ!”
ሲል የተናገረውን ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል (ዮሐንስ 21:22)። ኢየሱስ ዮሐንስ
ከመሞቱ በፊት ተመልሶ ይመጣል ማለት እንደሆነ አስበው ነበር። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እና ዮሐንስ
አርጅቶ ሲሞት (በእርግጥም ደግሞ ሞተ) ኢየሱስ ካልተመለሰ፣ ቀውስ ሊፈጠር ይችል ነበር።
ዮሐንስ ይህን የተሳሳተ አመለካከት ያስተካክለው ጉዳዩ የኢየሱስ ፈቃድ መሆኑን የሚያመለክት
እንደሆነ እንጂ የተተነበየው ወደፊት ስለሚሆነው እንዳልሆነ በማመልከት ነው።
በሌሎች ሰዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ በኢየሱስ ላይ የማተኮር ሃሳብ በቀሪው የሳምንቱ
ትምህርት ውስጥ ትልቅ መሪ ሀሳብ ነው። ኢየሱስ፣ እና ኢየሱስ ብቻ አዳኛችን ነው። ሰዎች
ሊያሳዝኗችሁ ወይም ሊጎዷችሁም ይችላሉ። ከማክሰኞ እስከ ሐሙስ ድረስ ያሉት እውነቶች
የእግዚአብሔርን ቃል የመረዳትን ሀሳብ ያነሳሉ፤ ዓላማውም፣ ምንም እንኳን ሌሎች የሚሰጡን
እርዳታ፣ ምክር፣ እና ምሪት ቢኖርም፣ ዋናው ነገር ብቻውን ጌታችንና መሪያችን ሊሆን
የሚገባውን ኢየሱስን ማወቅ እና መከተል ነው።
እናንተ ከፍ አድርጋችሁ የምትመለከቷቸው ሌሎች ሰዎች ምን ያህል ጊዜ ነው
ያሳዘኗችሁ? ከዚህ ልምድስ ምን ትምህርት ተማራችሁ?
ዮሐንስ 1:4-10፤ ዮሐንስ 3:19-21፤ ዮሐንስ 5:35፤ ዮሐንስ 8:12፤ ዮሐንስ 9:5፤ ዮሐንስ 11:9፣ 10፤ እና ዮሐንስ 12:35ን አንብቡ። እዚህ ላይ ምን ታላቅ ንፅፅር ታያላችሁ? ይህ ንፅፅር እውነትን ለመረዳት መሰረታዊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
ዓለም በጨለማ ውስጥ ነው፤ ብርሃንን ይቃወማል እናም ወደ እውነተኛው የፍጥረት፣
የመገለጥ እና የመቤዠት አምላክ የሚወስደውን መንገድ በራሱ ማግኘት አይችልም።
“ሰብአዊ ፍጡር በራሱ ስለ መለኮት ፈጽሞ ማወቅ አይችልም። ከሰማይ ይልቅ ከፍ
ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ? ኢዮብ
11፡8። ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ነገር ሊገልጽልን የሚችለው የልጅነት መንፈስ ብቻ
ነው። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው… ለእኛ እግዚአብሔር
በመንፈሱ በኩል ገለጠው” (ኤለን ጂ ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 424)።
ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አብን “ተረከው” (ዮሐንስ 1፡18)። የግሪኩ ግስ ex-
ēgéomai ሲሆን ትርጉሙም «መተርጎም» «መግለጽ» «መተረክ» ማለት ነው። ዮሐንስ
ኢየሱስን፣ አምላክን ማወቅ ምን ማለት እንደሆነ የገለጸ የሰማይ መልእክተኛ አድርጎ ያቀርባል።
እግዚአብሔርን በእውነት ማወቅ የምንችለው በኢየሱስ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 8:42-44ን አንብቡ። ኢየሱስ የእስራኤል ሃይማኖታዊ መሪዎች
እምነታቸውን የመሠረቱበትን የተሳሳተ መሠረት የገለጸው እንዴት ነው?
በእውነት ያልቆሙት ከራሳቸው ይናገራሉ። እነሱ የአንድን ጽሑፍ ትርጉም “የሚያዩት”
ከሰው እይታ አንጻር ብቻ ነው። ከዚህ በተቃራኒ፣ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን መሆኑን መቀበል
እና በቃሉ ትርጓሜ እርሱን መከተል አለብን። በአንጻሩ፣ ዲያብሎስ የሚናገረው “ከራሱ” ነው
(ዮሐንስ 8፡44)። ካልተጠነቀቅን እና በእምነት እና ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ካልተገዛን፣
ተመሳሳይ ነገር የማድረግ፣ ማለትም መጽሐፍን በራሳችን ፍላጎት፣ መሻት እና አመለካከት ብቻ
በማንበብ አደጋ ላይ ነን። ይህ ደግሞ ከምንገምተው በላይ ድካማችን የሆነ ነገር ነው።
ምቾት ለሚነሷችሁ እውነቶች መስጠት ከሚገባችሁ ምላሽ በተቃራኒ እንዴት ነው
ምላሽ የምትሰጡት?
“ከላይ” ወይስ “ከታች” የሆነ ሥነ መለኮት ዮሐንስ 4:46-54ን አንብቡ። ባለሥልጣኑን ወደ ኢየሱስ ያመጣው ችግር ምንድን ነው? ከዚህ ጀርባ ያለው ዋናው ጉዳይስ ምን ነበር?
ይህ ሰው የዓለም ብርሃን ወደሆነው ወደ ኢየሱስ መጣ፣ ነገር ግን ኢየሱስ ልጁን
ከፈወሰው ብቻ ለማመን ወስኖ ነበር። የዚህ ሰው ሥነ መለኮት “የታች (ከዓለም) የሆነ” ነው
ልንል እንችላለን። ከዓለም የሆነ ሥነ-መለኮት ለእግዚአብሔር እና ለቃሉ ህጎችንና ደረጃዎችን
ያወጣል። የሰው ሀሳቦች አንካሳና ውስን፣ እንዲሁም እንደየሁኔታዎች ተለዋዋጭ ቢሆኑም ሰዎች
የእግዚአብሔርን ቃል የሚተረጉሙበት የመጨረሻ ሥልጣን ሲሆኑ ይታያል። በዚህ ውስጥ
መውደቅ እንዴት ያለ አደገኛ ወጥመድ ነው!
“ከላይ” የሆነ ሥነ-መለኮት በተቃራኒው በመጀመሪያ በእግዚአብሔር እና በቃሉ
በማመን በእምነት ምላሽ ይሰጣል (ዮሐንስ 4፡48፤ ዮሐንስ 6:14፣ 15፤ 2 ጢሞ. 3፡16)።
መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ለሚቀበሉት የራሱ ተርጓሚ ይሆናል። ከዘመኑ ፍልስፍና ይልቅ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረዳትና ለመተርጎም መመሪያ ነው። የሰዎች
አመለካከት ለእግዚአብሔር ቃል መገዛት እና መታዘዝ አለበት እንጂ በተቃራኒው መሆን
የለበትም።
የኢየሱስን ቃል ማመን ከፈለግን የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል ማመን አለብን
(ዮሐንስ 5፡46፣ 47)። “በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ” (ዮሐ 8:31)።
የእግዚአብሔርን ቃል ከተጠራጠርን ቃሉ በእኛ ውስጥ ሊኖር አይችልም (ዮሐ. 5፡38)።
“የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ
በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል። እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ
የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ” (ዮሐ. 12፡ 48-49)።
የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ብቻውን መረጃን ከማግኘት በላይ ነው።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ማለትም ነው። ይህ ደግሞ ቃሉን ሰምቶ በተግባር ምላሽ
መስጠት ነው። «ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን
ወይም እኔ በራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል” (ዮሐ. 7:17)።
እናም ይህ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት እና ማድረግ ለእርሱ ያለን ፍቅር መግለጫ
ነው። “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን
በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” (ዮሐ. 14:23)
ለኢየሱስ ባለን ፍቅር እና ታዛዥነት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
ለምንድነው የትኛውም አይነት “ታዛዥነት” በፍቅር ላይ ያልተመሰረተ ሲሆን
ሕጋዊያን (የህግ ባሪያ) የመሆን አደጋ ያለበት?
ዮሐንስ 12:32ን አንብቡ። ይህ አስደናቂ መግለጫ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥልጣን የሚገልጸው በምን መንገዶች ነው?
በዚህ የሩብ ዓመት ትምህርት ውስጥ እንደተመለከትነው፣ የዮሐንስ ወንጌል ወደ
ኢየሱስ ይስበናል፣ ነገር ግን ይህ የሚሆነው እግዚአብሔርን ለማወቅ እና ፈቃዱን ለማድረግ
ፈቃደኛ ከሆንን ብቻ ነው። በወንጌሉ ውስጥ፣ ኢየሱስን የሚያገኙት ሰዎች ብርሃኑን ተቀብለው
አድገዋል ወይም ብርሃኑን ንቀው ታውረዋል። ኒቆዲሞስ፣ በጕድጓዱ አጠገብ ያለችው ሴት፣
የንጉሡ ሹም፣ በቤተ ሳይዳ መጠመቂያ ያለው ሰው፣ እንጀራና ዓሣ የተመገቡት አምስት ሺህ
ሰዎች፣ የኢየሱስ ወንድሞች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ዐይነ ሥውር ሆኖ የተወለደው ሰው፣
ማርያምና ማርታ፣ ጲላጦስ፣ እነዚህ ሁሉ ኢየሱስን ካገኙት በኋላ ይዞ ስለመጣው እውነትና
ብርሃን ምርጫ አድርገዋል።
ከታች ከዓለም ያለው ሥነ-መለኮት የሚጀምረው የእግዚአብሔርን መኖር እና ተፈጥሮ
ለመወሰን እና ለመመርመር በሚደረግ የሰዎች ክርክር ነው። የሰዎች አመለካከት፣ ያነከሰ፣
የወደቀ፣ ጭፍን ጥላቻ የተሞላ ሆኖ ሳለ፣ ነገር ግን ከመለኮታዊው፣ ከቅዱሱ፣ ፍጹምና ሁሉን
አዋቂ ከሆነው ሊቀድም ይፈልጋል። ከዚህ ከታች ያለው ሥነ-መለኮት ቀደም ሲል እንዳደረገው
እና ወደፊትም እንደሚያደርገው ሰዎችን ወደ ጥፋት እንደሚመራ የተረጋገጠ ነው (ራእይ
14:1-12ን ተመልከቱ)። መለኮታዊውን ለመተካት የሚፈልግ የሰው ጥበብ፣ የሐሰት አምልኮን
በዓለም ላይ አስገድዶ ሊጭን ይሞክራል።
ዮሐንስ 15:1-11ን አንብቡ። የመንፈሳዊ እድገት እና ጤና ምስጢር ምንድነው?
ሚስጥሩ ከኢየሱስ ጋር ተያይዞ መቆየት ነው። እሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ቃል፣ የሕይወት እንጀራ፣ የዓለም ብርሃን፣ የበጎች በር፣ መልካም እረኛ፣ ትንሣኤና
ሕይወት፣ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት፣ እና እውነተኛው የወይን ግንድ ነው።
የመለኮት አካላት እና እንዲሁም ቃላቸው የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ማግኔቶች
ናቸው። ካልተቃወምን ወደ እነርሱ ይስቡናል። “የእግዚአብሔር ድምፅ በቃሉ እየተናገረን ነው፣
የምንሰማቸውም ብዙ ድምፆች አሉ። ክርስቶስ ግን ይህን ብሏል፦ እነሆ ክርስቶስ በዚህ ወይም
በዚያ አለ ከሚሏችሁ ተጠንቀቁ። ታዲያ እኛ ሁሉንም ነገሮች ወደ ቃሉ ካላመጣን እውነት
በእነርሱ ዘንድ እንደሌለ እንዴት እናውቃለን?” (Ellen G. White, The Advent Re-
view and Sabbath Herald, April 3, 1888)። ስለዚህ የራሳችንን አመለካከት
በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለቀረቡት እውነቶች አሳልፈን መስጠት አለብን።
የእግዚአብሔር አመለካከት ከሰዎች አመለካከት በእጅጉ የተለየ ነው።
እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በቃሉ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ያለውን ዕይታ ለእኛ
ያጋራል። በጨለማ መመላለስ ወይም በቃሉ እንደተገለጠው ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚመጣውን
ብርሃን መቀበል ብንፈልግ ምርጫው የእኛ ነው።
ከዚህ ምርጫ ጋር ሊነጠል የማይችለው ነገር የሰዎች ቤዛ ለሆነው ለእግዚአብሔር
ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ራሳችንን አሳልፈን መስጠታችን ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣
እግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሣኤ የፍቅሩን ጥልቀት ገልጦልናል። ስለ
ኢየሱስም እናውቃለን ምክንያቱም ሕይወቱ፣ ሞቱ እና ትንሳኤው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ
ተመዝግቧልና።
“የእግዚአብሔር መላእክት ያለ ማቋረጥ ከምድር ወደ ሰማይ፣ ከሰማይ ወደ ምድር
ይመላለሳሉ። ክርስቶስ ለተጎሳቆሉትና ለሚሰቃዩት ያደረጋቸው ተአምራት ሁሉ የተከናወኑት
በመላእክት አገልግሎት አማካይነት በእግዚአብሔር ኃይል ነበር። ከእግዚአብሔር የሚላክልን
በረከት ሁሉ የሚመጣው በክርስቶስ አማካይነት በሰማያዊ መልእክተኞች አገልግሎት
በኩል ነው። ሰብአዊነትን በመልበሱ መድኃኒታችን ከአዳም ልጆች ጋር አንድነትን መሰረተ፤
በመለኮታዊነቱም የእግዚአብሔርን ዙፋን ጨብጦአል። ስለዚህ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና
በሰዎች መካከል አገናኝ ድልድይ ነው (ኤለን ጂ ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 129)።
1. በዮሐንስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ታሪኮች ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና
ባሕርይ አብልጦ የሚናገረው የትኛው ነው? ያ ታሪክ ለምን አሳማኝ ሆኖ
እንዳገኛችሁት በሰንበት ትምህርት ጥናት ቡድን ውስጥ አጋሩ።
2. በተጨባጭ ሁኔታ አንድ ሰው እውነትን ፍለጋ እንዴት መሄድ አለበት?
3. ራስን እንደ እውነተኛ ዳኛ አድርጎ መቁጠርን መተው ብዙ ጊዜ ከባድ
የሚሆነው ለምንድን ነው? ይህን ሙሉ በሙሉ ማድረግ እንችላለን ወይንስ
ሰው መሆናችን በተወሰነ ደረጃ ለቅዱሳት መጻሕፍት ያለን ዕይታ ላይ ተጽዕኖ
ያሳድራል? ይህን እውነታ መገንዘብ ያለብን ለምንድን ነው? ትሕትና ጭፍን
ጥላቻን ለጌታ ቃል ስንል እንድንተው የሚረዳን እንዴት ነው?
4. የምዕራቡ ዓለም ክርስትና ታሪክ የእግዚአብሔር ቃል በሰዎች ፖለቲካና
ጭፍን ጥላቻ ሥር ሲወድቅ ምን እንደሚከሰት በሚያሳዩ አስፈሪ ምሳሌዎች
የተሞላ ነው። ከእነዚህ ምሳሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?
የሰው አመለካከቶች መጽሐፍ ቅዱስን “ለመተርጎም” ዋነኛ ማጣሪያ ሲሆኑ
ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ላለንበት ጊዜ ከእነርሱ ምን ትምህርት እናገኛለን?
5. የዮሐንስ ወንጌልን ትልቁን ምሥል በራሳችሁ አባባል አጠቃሉ። ዛሬ ለእኛ
ያለው መካከለኛው መልእክት ምንድን ነው?
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ