የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 1ኛ ሩብ ዓመት 2019

ከየካቲት 9–15

8ኛ ትምህርት

Feb 16 – Feb 22




ሰይጣን -- የተሸነፈ ጠላት



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ራእ. 12፣ ዘፍ. 3:15፣ ኢሳ. 14:12–15፣ ዳን. 7:23–25፣ 2ተሰ. 2:8–12፣ ራእ. 13:13-14፣ 19:20፡፡


መታሰቢያ ጥቅስ :-“‘እነርሱም በበጉ ደም፣ በምስክርነታቸውም ቃል፣ ድል ነሱት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ ለነፍሳቸው አልሳሱም’ ” (ራእ. 12፡11)፡፡

የ መጽሐፉ የመጨረሻው ዘመን መልእክት ክፍል ራእ. ምዕ. 12 ላይ ይጀምራል። የመጀመሪያው አጋማሽ፤ በጥላቻ በተሞላው ዓለም ቤተ ክርስቲያን በዘመናት የገጠማትን መንፈሳዊ ትግል ሲገልጽ፤ ሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአትና ዘላለማዊ መንግሥት የሚያመሩ ክስተቶች ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የምዕ 12 ዓላማ ከዓለም ታሪክ የመጨረሻ ቀውስ በስተጀርባ ያለውን ብርቱ ገጽታ ቁልጭ አድርጎ ማሳየት ነው፡፡ የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች በክርስቶስና በሰይጣን መካከል እየተካሄደ ያለ ሥነ ፈለካዊ ተቃርኖ አካል መሆኑን ይነግረናል፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሔር እና የሕዝቦቹ ዋንኛ ጠላት ተደርጎ በራእይ መጽሐፍ መቅረቡን እናያለን፡፡ ይህ መልአክ ምናባዊ ሳይሆን በእርግጥ ያለ እና በዩኒቨርስ ለሚፈጠር ማንኛውም ክፉ ተግባርም ሆነ ዐመጻ ስውር አንቀሳቃሽ ሞተር ነው፡፡ ሰይጣን ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ላይ ስኬት ለማግኘት የሚያስችለው የመጨረሻ ዕድል ውጊያውን ማሸነፍ ብቻ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ሙሉ ትኩረቱ ለዚያ ክስተት መዘጋጀቱ ላይ ነው፡፡

በምዕ. 12 የቀረበው ራእይ ፋይዳ ሰይጣን በእርግጥ የተሸነፈ ጠላት መሆኑን በበቂ ማረጋገጫ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ማበርከት ነው፡፡ ክርስቶስ በምድራዊ አገልግሎቱ፣ በመስቀል ላይ እንዲሁም በትንሳዔው ሰይጣንን እንዳሸነፈ፤ በመጨረሻም እንዲሁ ድል ይነሳዋል፡፡ ስለዚህ በመጨረሻው ዘመን ለሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ብቸኛው ተስፋ የሚገኘው በክርስቶስ ነው፡፡

የካቲት 10
Feb 08

ሴቲቱ እና ዘንዶው


ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 12፡1-4፡፡ ዮሐንስ ሁለት ታላላቅና አስደናቂ ተምሳሌታዊ ምልክቶችን በራእይ የተመለከተ ሲሆን አንደኛው ምጥ የያዛት ነፍሰጡር ሴት ነበረች። ለመሆኑ ይህች ሴት ማን ናት? ጥቅሶቹ ምን ያስተምሩናል?



በመጽሐፍ ቅዱስ ሴት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተምሳሌት ናት (2ቆሮ. 11፡2)፡፡ ንጽህት ሴት ታማኝ የሆኑትን አማኞች ስትወክል በተቃራኒው ያለችው አመንዝራዋ ደግሞ ክህደት የፈጸሙትን ትወክላለች፡፡ በራእ. 12 የቀረበችው ሴት መሲህ ወደ ዓለም የወጣባትና (ራእ. 12፡1-5) ከመስቀሉ አስቀድሞ የነበረችው የብሉይ ኪዳኗ እስራኤል ተምሳሌት ናት፡፡ ከቁ. 13-17 ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ትወክላለች፡፡ ይህች ሴት ፀሐይን ለብሳና በጨረቃ ላይ በጽናት ቆማ ተስላለች፡፡ ፀሐይ የክርስቶስን ክብር (ማቴ. 17፡2፣ ራእ. 1፡16) እና ሕዝቦቹን ትወክላለች (ማቴ. 13፡43)፡፡ ጨረቃ እንደ ፀሐይ ነጸብራቅነቷ ወደ ብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃል ትንቢቶች ታመላክታለች፡፡

ዮሐንስ በራእይ ያየው ቀጣዩ ተምሳሌታዊ ምልክት ቀይ ዘንዶ ነበር፡፡ ዘንዶው የቀደመው እባብ (ራእ. 12፡9) ይኸውም ዲያብሎስና እና ሰይጣን ነው፡፡ ጅራቱ የከዋክብትን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር እንደ ጣላቸው ጥቅሱ ይናገራል፡ ፡ ጅራት የማታለልና የማጭበርበር ዓይነተኛ ተምሳሌት ነው (ኢሳ. 9፡14-15፣ ራእ. 9፡10)፡፡ በሰማይ ከነበረው የከበረ ማዕረግ ቁልቁል የተምዘገዘገው ሰይጣን (ኢሳ. 14፡12-15) ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸውን የሰማይ መላእክት ለክፉ ዓላማው እያባበለ አታልሎ እርኩስ መናፍስት አደረጋቸው (2ጴጥ. 2፡4፣ ይሁዳ 6)፡፡ እነዚህ እርኩሳን መናፍስት በመልካምና በክፉ መካከል ብርቱ ተቃርኖ በነገሠበት የዩኒቨርስ ዘመን እግዚአብሔርን እና የማዳን ሥራውን የሚቃወሙ ተባባሪ ኃይሎች ሆነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 12፡1-5፡፡ ዘንዶው “የጥንቱ እባብ” (ራእ. 12፡9) በሚል ተጠቅሶአል፡፡ በዘፍ. 3፡15 እና የሴቲቱን ዘር ለማጥፋት አጥብቆ በሚተጋው በጥንቱ እባብ ገጽታ መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት አለ?



ሰይጣን ገና ከመጀመሪያው የሚወለደውን ልጅ ይኸውም መሲሁን ለማጥፋት እየተጠባበቀ ነበር፡፡ ረጅሙ የትዕይንቱ አካል በውልብታ ቀርቦአል፡ በመጨረሻ መሲህ ተወለደ፣ ዘንዶው ሊያጠፋው ሳይችል ቀረ፤ ልጁም “ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ” (ራእ. 12፡5)፡፡ በራእ. 12፡11 መሰረት-የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሕይወታቸው ሰይጣንን ድል መንሳት የቻሉት እንዴት ነበር? የሱስ በሰይጣን ላይ ያገኘው ድል እርስዎ ከኃጢአት ጋር ለሚያደርጉት መንፈሳዊ ግብግብ መጽናናት ሊሆንዎ የሚገባው እንዴት ነው?

የካቲት 11
Feb 08

የሰይጣን ለዘላለም ከሰማይ መባረር


በሰማይ ተካሂዶ ስለነበረው ጦርነት የሚናገሩትን እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ራእ. 12፡7-9፡፡ ለመሆኑ ሰይጣንን ከሰማይ ያስባረረው የዚያ ጦርነት ተፈጥሮ ምን ነበር?



ሰይጣን በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ዐመጻ ባደረገ በታላቁ ተቃርኖ መጀመሪያ ከሰማይ ተባረረ፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዙፋን ገልብጦ “ራሴንም እንደ ልዑል አደርጋለሁ” (ኢሳ. 14፡12-15) የሚል ክፉ ምኞት ተጸናውቶት ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ግልጽ ዐመፃ ለማድረግ ቢሞክርም ሽንፈት ገጥሞት የኋላ ኋላ ወደ ምድር ተጣለ፡ ፡ ሰይጣን የመጀመሪያዎቹን ሰብዓዊ ጥንዶች አስቶ የዚህን ዓለም ገዢነት ሥልጣን ያለ አግባብ ከእጁ አስገባ (ሉቃ. 4፡6)፡፡ በመሆኑም በዚህ ዓለም ገዢነቱ (ዮሐ. 12፡31) የምድር ተወካይ ሆኖ በሰማይ ጉባዔ ላይ መገኘት ቻለ (ኢዮ. 1፡6-12)፡፡ ሆኖም ሰይጣን ከሰማይ ከተባረረ አንስቶ እርሱና የወደቁት መላእክቶቹ የመጨረሻ ቅጣታቸውን እስኪቀበሉ የዚህ ምድር ግዞተኞች ተደረጉ (2ጴጥ. 2፡4፣ ይሁዳ 6)፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ--እነሆ የሱስ ጠፍቶ የነበረውን ሰብዓዊ ዘር በሞቱ ዋጀ። የሰይጣንም እውነተኛ ጸባይ በመላው ዩኒቨርስ ፊት ይፋ ሆነ፡፡ “ሰይጣን ማሳቻ ጭምብሉ ተገልጦ እውነተኛ ማንነቱ መውጣቱን ተመለከተ፡፡ የአገዛዝ ባህሪው ባልወደቁት መላእክትና በዩኒቨርስ ፊት ፍንትው ብሎ ታየ፡፡ ሰይጣን ያለ አንዳች መሸፋፈን ገዳይነቱን ገልጦ አሳይቶ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ ደም በማፍሰስ ራሱን ከሰማያዊ አካላት አዘኔታና ርኅራኄ ውጪ አደረገ፡፡ ከዚህ በኋላ ለሥራው ገደብ እንዲበጅ ተደረገ፡፡”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 761. አሁን መላው ሰማያዊ አካላት በተካተቱበት በዩኒቨርስ ፊት የምድር ገዢነት ሥልጣን ወደ የሱስ ተዛወረና የእርሱ ሕጋዊ የምድር ገዢነት ታወጀ (ኤፌ. 1፡20-22፣ 1ጴጥ. 3፡22)፡፡ ሰይጣንና አጋሮቹ ተጠራርገው ከሰማይ የተባረሩት በዚህ ወቅት ነበር፡፡ የሱስ ይህን ሁኔታ እንዲህ ሲል አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፡ “‘ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህም ዓለም ገዥ አሁን ወደ ውጭ ይጣላል’ ” (ዮሐ. 12:31)፡፡

ይህ ፍርድ በሰይጣን ላይ ከተሰጠ በኋላ “ ‘የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልና መንግሥት፣ የእርሱ ያክርስቶስ ሥልጣንም መጥቶአል’ ” (ራእ. 12:10)፡፡ “ጥቂት ዘመን ብቻ እንደቀረው” (ራእ. 12፡12) የሚያውቀው ሰይጣን፤ ያ ቀን እስኪመጣ በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን ሕዝቦች የሚጎዳበት ኃይል ውሱን ተደርጎበታል፡፡ ምንም እንኳ የቀረው ጊዜ “ጥቂት” ቢሆንም፤ በእያንዳንዷ ሽርፍራፊ ሰከንድ በሰዎች ላይ ሕመምና ሥቃይ በምድር ደግሞ ጥፋትና ውድመት እያደረሰ ይገኛል፡፡ ራሳችንን ከሰይጣን ስለምንከላከልበት ብቸኛ መንገድ ራእ. 12፡11 ምን ያስተምረናል?

የካቲት 12
Feb 08

የምድር ውጊያ


ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 12፡13-14፡፡ ሰይጣን ከሰማይ ከታገደ በኋላ በ1,260 ትንቢታዊ ቀናት ቤተ ክርስቲያንን መዋጋቱን ገፍቶበት ነበር፡፡ በእነዚያ ጊዜያቶች ውስጥ እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው አግባብ ምን ይመስላል?



“ክርስቶስ ሕይወቱን ሰጥቶ የሠራው ታላቅ ሥራ፤ በሰማይ የወንድሞች ከሳሽ የነበረው ሰይጣን ወደ ምድር እንዲጣል አስቻለ፡፡ ምንም እንኳ ሰይጣን በማያባራ ተቃውሞው ቢገፋበትም፤ ሰብዓዊውን ዘር የመታደጉ የደኅንነት እቅድ እነሆ እንደቀጠለ ይገኛል… ይህን ያላግባብ የወሰደውን ግዛት በስተ መጨረሻ በኃይል እንደሚነጠቅ የሚያውቀው ሰይጣን፤ እግዚአብሔር በአምሳሉ በፈጠረው ሰብዓዊ ዘር ላይ የተቻለውን ውድመት ለማድረስ ቆርጦ ተነስቶአል፡፡

ክርስቶስ ለሰብዓዊው ዘር ያሳየው ይቅር ባይነት፣ ፍቅርና አዘኔታ ስላበገነው፤ ሰብዓዊው ፍጡር ለዘላለም ጠፍቶ የሚቀርበትን እያንዳንዱን የረቀቀ ማታለያ ዘዴ ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡ ሰይጣን በተስፋ አስቆራጭ አዙሪት መውደቁ፤ አውዳሚ አካሄዱን ከቀድሞ በበለጠ ጉልበት እንዲቀጥልበት አድርጎታል፡፡”—Ellen G. White, The Spirit of Prophecy, vol. 3, pp. 194, 195. ክርስቶስ በምድር አጥብቆ የሚወዳትና የዐይኑ ማረፊያ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ሰይጣን በቁጣና በንዴት ጦዞ በተቃራኒ መሥራቱን መቀጠሉ አያከራክርም። ይህም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ዳግም ምጽአት በምትጠባበቅበት በትንቢታዊው 1,260 ቀናት የበረሓ ቆይታዋ መለኮታዊውን ከለላ ታገኛለች፡፡ ሰይጣን ስደት የሚያደርስበት ዘመን--1,260 ቀናት እና “ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ” በሚል በራእ. 12--ለሁለት ጊዜ ተጠቅሶአል፡፡ ሁለቱም በመረጃ አስደግፈው የሚናገሩት በዳን. 7፡23-25 የተጠቀሰው ትንሹ ቀንድ ተግባራቱን የሚያከናውንባቸውን ዘመናት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ተምሳሌታዊ ቀመር አንድ ትንቢታዊ ቀን ከአንድ ዓመት ጋር እኩል ነው፡፡ በታሪክ ከዚህ ትንቢታዊ አቀራረብ ጋር በእጅጉ ስምሙ ሆኖ የምናገኘው ከ538 ዓ.ም. እስከ 1798 ዓ.ም. ያለው ጊዜ ነው፡፡ የሮም ጳጳሳዊ ሥርዓት በምዕራቡ ዓለም ላይ ተንሰራፍቶ በጭቆና ይገዛ በነበረበት ወቅት የፈረንሳይ አብዮት ፍንዳታ መከሰት ብርቱ ጉዳት አደረሰበት። ጉዳቱ እስኪጠግለት፤ ለጊዜውም ቢሆን፤ የነበረውን ኃይል ሙሉ ለሙሉ አጣ፡፡ በበረሓ የነበረችው ሴት ትንቢት ድምዳሜ ላይ ሰይጣን በድጋሚ ኃይሉን አስተባብሮ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ጥቃት ይሰነዝራል፡፡ ዘንዶው ሴቲቱን ለማጥፋት እንደ ወንዝ ያለ ውሃ ወይም ጎርፍ ከአፉ ይተፋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግሞ እንደ ቀረበው ጎርፍ ስደትን ያመላክታል (ኢሳ. 59፡19)። በዚህ ወቅት ለሴቲቱ ሰላማዊ የሆነችው ምድር ውሃውን መጥጣ ትታደጋትና ምቹ ሁናቴ ትፈጥርላታለች፡፡

እዚህ ላይ ስደቱ እንዴት ለ1,260 ቀናት እንደ ቆየ አሰብ ያድርጉ። በእኛ ግንዛቤ ረጅም ዘመን የሚያስቆጥር የሚመስል እንደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ያለውን ክስተት ለማስተዋል ምን ያህል ውሱን እንደሆን ይህ ምን ሊነግረን ይችላል?

የካቲት 13
Feb 08

በትሩፋኖች ላይ የተከፈተ ውጊያ


ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 12፡17፡፡ ሰይጣን በመጨረሻ የሚዋጋው ከማን ጋር ነው?



አብላጫው የምድር ሕዝብ ክህደት በፈጸመበት ሁናቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው የቆሙ ወገኖች--የተቀሩት ወይም ትሩፋን በሚል ተጠቅሰዋል (1ነገሥ. 19፡ 18፣ ራእ. 2፡24)፡፡ በምድር ፍጻሜ ላይ አብዛኛው ሕዝብ በሰይጣን በኩል የሚቆም ቢሆንም፤ ነገር ግን ለክርስቶስ ታማኝ ሆነው በመጽናት የሰይጣንን ቁጣ የሚጋፈጡ ሕዝቦችም ይኖራሉ፡፡

በራእ. 12፡17 የተገለጹት ትሩፋን ሁለቱ መለያ ባህሪያት ምንድን ናቸው? አንድ ሰው የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ትሩፋን ነኝ ብሎ ለመቀበል የሚያስችለው አሳማኝ ሁናቴ ምንድን ነው?



የመጨረሻው ዘመን ትሩፋን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ይጠብቃሉ፡፡ ለመጨረሻው ዘመን ውዝግብ ዋንኛ መንስዔ የዐሥርቱ ትእዛዛት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ተራ ቁጥሮች እንደሚሆኑ ራእ. 13 ያሳየናል፡፡ የመጀመሪያዎቹ አራት ትእዛዞች ቁልፍ አካል አምልኮ ነው፡፡ የመጨረሻው አስጨናቂ ጊዜ ዐበይት ርዕሰ ጉዳይ ሊመለክ የሚገባው ማን ነው? የሚል ይሆናል፡፡ የዓለም ሕዝቦች የአውሬውን ምስል ለማምለክ ሲመርጡ የእግዚአብሔር ትሩፋት ግን ፈጣሪን ያመልካሉ (ራእ. 14፡7)፡፡ አራተኛው ትእዛዝ ከሌሎቹ በተለየ እግዚአብሔር ፈጣሪያችን መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህ ደግሞ በመጨረሻው ቀውስ ወቅት ዋንኛና አስፈላጊ ሚና ይጫወታል ብለን የማመናችን አንዱ መንስዔ ነው፡፡

የመጨረሻው ጊዜ ትሩፋን ሁለተኛ ባህሪ “የኢየሱስን ምስክር የያዙ” መሆናቸው (ራእ. 19፡10) ሲሆን፤ ይህም በዚያው ቁጥር ላይ “የትንቢት መንፈስ” በሚል ሀረግ ተገልጾአል፡፡ “የትንቢት መንፈስ” የተሰኘው አገላለጽ ዮሐንስ በኖረበት ዘመን-የትንቢት ስጦታ የሚል አንደምታ አለው፡፡ ይህ ሀረግ የሱስ በዮሐንስ በኩል እንዳደረገው (ራእ. 2) በተመሳሳይ በትንቢት ስጦታ አማካይነትም የራሱን ምስክርነት እንደሚሰጥ ይጠቅሳል፡፡

ሰይጣን ሊያስታቸውና ሊያጠፋቸው ማንኛውንም ጥረት በሚያደርግበት በእነዚያ አስቸጋሪ የመጨረሻ ጊዜያቶች የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሚመሩበት የትንቢት ስጦታ በመካከላቸው እንደሚገለጥ የራእይ መጽሐፍ ያሳየናል፡፡ እኛ እንደ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተጠባባቂነታችን በኤለን ጂ. ኋይት አገልግሎትና ጽሑፎች አማካይነት ስጦታው እንደ ተሰጠን እናምናለን፡፡ በ“ትንቢት መንፈስ” በኩል ስለ ተሰጡን ጥልቅ ማስተዋልና መገለጦች ምን ይላሉ? ስጦታው በየግላችን እንዲሁም እንደ ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት የውዴታ ግዴታ አስቀምጦብናል?

የካቲት 14
Feb 08

የሰይጣን የመጨረሻ ስልት


ሰይጣን የውግያ የስልቱን ለውጦ የዓለምን ሕዝቦች ከመዳፉ ለማስገባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ታማኞቹን የክርስቶስ ተከታዮች ሳይቀር የማሳት ሙከራ እንደሚያደርግ ራእ. 12፡17 ያመለክታል፡፡ ሰይጣን ማስገደድንና ማሳደድን ተቀዳሚ ስልቱ አድርጎ አምላካዊውን የደኅንነት ሥራ ለመግታት መሞከሩን የዘመናት የክርስትና ታሪኮች በዋቢነት ይነግሩናል፡፡ ይህ ስልት የፈለገውን ስኬት እንዳላስገኘለት ታሪክ ያሳየናል፡ ፡ ሆኖም በመጨረሻው ዘመን ትሩፋን ላይ የመጨረሻውን ጥቃት ለመሰንዘር በሚያደርገው ዝግጅት በማስገደድ ስልቱ ላይ መጠነ ሰፊ ማታለያ ዘዴ ያክልበታል፡፡ የሚያስት በሚል ጥቅም ላይ የዋለው ቃል የታሪክን ዐውድ በሚያስቃኘን ክፍል (ራእ. 4-11) አለመጠቀሱ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሆኖም ሰይጣን ለመጨረሻው ውጊያ በሚያደርገው ዝግጅት በንቃት የተሞሉ እንቅስቃሴዎቹን ለመግለጽ ቃሉ በቋሚነት ጥቅም ላይ መዋሉን እንመለከታለን (ራእ. 12-20)፡፡

የሰይጣንን የመጨረሻውን ዘመን እንቅስቃሴ ገላጭ የሆነው የሚያስት በሚል የቀረበው ቃል በራእ. 12፡9 ይጀምርና ራእ. 20፡7-10 ይደመደማል፡፡ ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ተሰ. 2፡8-12፣ ራእ. 13፡13-14፣ 19፡20፡፡ የመጨረሻው ዘመን ማሳቻ ተፈጥሮ ምን ይመስላል?



ሰይጣን በዓለም ያሉ የእግዚአብሔርን ታማኞችን ለማሸነፍ በሚያደርገው ሙከራ መጠነ ሰፊ እውነት መሳይ ሽንገላዎችን እንደሚለቅ ራእ. 13-20 ያሳየናል፡፡ በራእ. 13 ዘንዶውና ሁለቱ ተባባሪ ኃይላት ማለትም ከባሕር የወጣው አውሬ (ራእ. 13፡1-10) እና ከምድር የወጣው አውሬ (ራእ. 13፡11-18) የሦስትዮሽ ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ የሰይጣን የሦስትዮሽ ቅንጅታዊ አመራር ከአምላካዊው ሥላሴ በተቃራኒ የተዋቀረ ነው (ራእ. 1፡4-6)፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ምድር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወምና ሕዝቦችን አስቶ በመጨረሻው ቀውስ ወቅት ፊታቸውን ከእግዚአብሔር እንዲመልሱና ከሰይጣን ጋር እንዲቆሙ የማድረግ ሥራ የሚሠሩት እነዚህ በሦስት አካል የተዋቀሩ ሰይጣናዊ ኃይላት፤ በተቀረው የመጽሐፉ ክፍል እንዳይነጣጠሉ ሆነው ቀርበዋል (ራእ. 16፡13-14፣ 19፡20፣ 20፡10)፡፡ በመጨረሻው ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው የማሳቻ ዘዴ እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚማልል የራእይ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡

በመጨረሻው ዘመን አብልጦ የሚሠራውን አሳች ተፈጥሮ የያዘውን የሰይጣን እንቅስቃሴ ለይቶ ለመገንዘብ ብሎም ለመቋቋም ጥበብ ያለው አእምሮ እንዲሁም መንፈሳዊ ዐይኖች ሊኖሩ የግድ እንደሆን የራእይ መጽሐፍ ከአንዴም ሁለቴ ጥሪ አቅርቦአል (ራእ. 13፡18፣ 17፡9)፡፡ በዚህ ስፍራ የቀረበው ጥበብ ምን ዓይነት ነው? ይህን ጥበብ እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያዕ. 1፡5 ምን ይለናል?

የካቲት 15
Feb 08


ተጨማሪ ሀሳብ


Read Ellen G. White, “Snares of Satan,” pp. 518–530, in The Great Controversy. የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች በክርስቶስና በሰይጣን ኃይላት መካከል የሚደረገው ታላቁ ተቃርኖ አካል መሆናቸውን ለእግዚአብሔር ሕዝቦች መንገር--ከሁሉ የቀደመው የራእ. 12 ዓላማ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ዛሬ እየተጋፈጡ ስለሚገኙት አስቸጋሪ ሁናቴ የሚናገረው አምላካዊ ቃል--በቅርቡ ደግሞ በላቀ ተሞክሮ ያለፈና በቁጣ የነደደ ጠላት አሰፍስፎ እንደሚጠብቃቸው ያስጠነቀቅቃል፡፡ ጳውሎስ በመጨረሻው ዘመን ስለሚደረጉ የሰይጣን እንቅስቃሴዎች እንዲህ ይላል፡ “ይህም በሐሰተኛ ታምራት በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፤ እንዲሁም ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለ መውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል” (2ተሰ. 2፡9-10)፡፡

የራእይ መጽሐፍ የወደፊቱን ጉዳይ በዋዛ እንዳንመለከትና በእግዚአብሔር ላይ ለመታመን ቅድሚያ እንድንሰጥ አጥብቆ ያስጠነቅቀናል፡፡ በሌላ በኩል ምንም እንኳ ሰይጣን ብርቱና በከፍተኛ ተሞክሮ ያለፈ ጠላት ቢሆንም ክርስቶስን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እንደሌለው የራእይ መጽሐፍ ያረጋግጥልናል (ራእ. 12፡8)፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ተስፋ የተመሰረተው ሰይጣንንና ዲያብሎሳዊ ኃይላትን ድል በነሳው በክርስቶስ ላይ ነው፡፡ ጌታ ሁል ጊዜ ከታማኝ ተከታዮቹ ጋር እንደሚሆን ጽኑ የተስፋ ቃል ሰጥቶናል “‘እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ” (ማቴ. 28፡20)፡፡


የመወያያ ጥያቄዎች




1.እንደ ዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂ እንደምናሟላ አድርገን ራሳችንን መብትና ጥቅም--ብሎም ኃላፊነት መብትና ጥቅም ለግል መዳናችን ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? ሕዝብ የመጨረሻዎቹን ትሩፋን ባህሪ እንመለከታለን፡፡ እንዴት ያለ ልዩ ነው! (ሉቃ. 12፡48)፡፡ ይህን ልዩ እንደ ዋስትና ላለመውሰድ ጥንቃቄ

2.“ብዙውን ጊዜ ሰብሰብ ብለን ስለ ሰይጣን ኃይል ስናወራ እንስተዋላለን። ሰይጣን ኃይል ያለው ፍጡር መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ነገር ግን ክፉውን ከሰማይ ስለ ወረወረው አዳኜን ኃያሉን አምላክ አመሰግናለሁ። ስለዚህ ጠላታችን ማውራታችን፣ መጸለያችንና ማሰባችን አስተሳሰባችን ላይ እየገዘፈ የሚሄድ ማንነት እያገኘ እንዲሄድ ያስችለዋል። ለመሆኑ ስለ የሱስ የማንጨዋወተው ለምንድን ነው? ስለ ኃያልነቱም ሆነ ስለ ፍቅሩ የማናሰላስለው ለምንድን ነው? የባላንጣችንን ኃይል አግዝፈን በመመልከታችን ሰይጣን በእጅጉ ደስተኛ ነው፡፡ በየሱስ እየተመሰጥን እርሱን አጥብቀን ስንይዝ ወደ አምላካዊው አምሳል እየተለወጥን እንመጣለን፡፡”—Ellen G. White, Advent Review and Sabbath Herald, March 19, 1889. ለመሆኑ ክርስቲያኖች የሰይጣንን ኃይል የሚያገዝፉት እንዴት ነው? በሌላ በኩል ስለ ሰይጣን ኃይል ሳይሆን ነገር ግን ከነአካቴው መኖሩን መካድ ምን ዓይነት አደጋ አለው?