፡ ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 33:12– 14፣ ሩት 1:16–18፣ ዮሐ. 17:21–26፣ ገላ. 3:28፣ ኤፌ. 2:11–22፣ 5:21–6:9።
መታሰቢያ ጥቅስ:-“ይህም፣ አባት ሆይ፤ አንተ በእኔ፣ እኔም በአንተ እንዳለሁ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም አንተ እኔን እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ አነርሱም በእኛ እንዲሆኑ ነው” (ዮሐ. 17፡21)፡፡
ቤ
ተሰባዊ ህይወት ለተለያዩ ሰዎች ልዩ ልዩ የህይወት ጊዜያቶችንና ወቅቶችን
ይወክላል። እናትና አባት በህይወታቸው የመጀመሪያ ልጃቸውን ማግኘታቸው
እስከ ዕድሜ ልክ የሚዘልቀውን መሰረታዊ ለውጥ ይወክላል። ካለመኖር ወደ መኖር
ለመጣውም ጨቅላ እንዲሁ መሰረታዊ ሽግግር ነው። ከዚያም ልጆችም በፊናቸው
በተለያዩ የህይወት ምዕራፎች በማለፍ የወላጆቻቸውን ቤት ለቅቀው የራሳቸውን
ልጆች ይወልዳሉ።
በቤተሰብ ውስጥ እንደ ወላጆች ወይም እንደ ልጆች ሁላችንም ከተመሳሳይ ነገር
ጋር ትግል የምንፈጥር ሲሆን--ትግሉ የቤተሰብን አንድነት ፈታኝ ከሚያደርገው
ኃጢአተኛው ሰብዓዊ ተፈጥሮ ጋር ነው ብሎ ባጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል።
መላው ሰብዓዊ ፍጡር በመስቀል ላይ በየሱስ ክርስቶስ አካል ከእግዚአብሔር ጋር
እርቅ መፍጠሩ እውነት ቢሆንም (ኤፌ. 2፡13-16፣ ቆለ. 1፡21-23) ቤተሰባዊውን
አንድነት በብቸኝነት ህያው ሊያደርግ ከሚችለው የክርስቶስ ጸጋ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር
ራሳችንን ዕለት በዕለት ገጣሚ ማድረግ ከእኛ ይጠበቃል። ይህ የየቀኑ የህይወታችን
ተሞክሮ ሊሆን ይገባል። እንደ መታደል ሆኖ አዎን በክርስቶስ ጸጋ መሆን ይችላል።
ጳውሎስ በክርስቶስ ባሉ ሕዝቦች መሃል ያለውን አንድነት ለመግለጽ ምን ዓይነት ሳያ ይጠቀማል? ክርስቶስ “ሁለት” የነበሩትን “አንድ” ያደረገው እንዴት ነው? ኤፌ. 2:11–22፣ ገላ. 3:28።
በሰዎች መካከል ያለውን የመለያየት ግድግዳ የክርስቶስ መስቀል የማስወገድ ኃይል
አለው። የአይሁድ ቤተ አምልኮ ግድግዳዎች ወንዶችን፣ ሴቶችን እንዲሁም አሕዛብን
ይለዩ ነበር። ጳውሎስ በክርስቶስ ያሉ አይሁዶችና አይሁድ ያልሆኑ አሕዛብ በክርስቶስ
ስላላቸው አንድነት ለመግለጽ የሚጠቀመው ቋንቋ ሕዝቦችን እንዲሁም ወንድ፣
ሴት ሳይል ልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በእኩል የሚፈርጅ ነው። “ዐላማውም
ከሁለቱ አንድን አዲስ ሰው በራሱ ፈጥሮ ሰላምን ለማድረግ ነው” (ኤፌ. 2፡15)።
ይህ ጥንዶች በጋብቻ ያለውን “አንድ ሥጋ” የመሆን አንድነት በእውነት እንዲያውቁ
የሚረዳ እንደ መሆኑ መልካም የምስራች ነው። እንዲሁም ረዘም ላሉ ጊዜያት
ሲቆራቆሱ የኖሩ ቤተሰቦች በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት እርቅ ማውረድ ይችላሉ።
በክርስቶስ ስላለን አንድነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መጥቀስ አንድ ነገር ቢሆንም
በተግባር መኖር ግን ፍጹም ሌላ ነገር ነው። ቃል የተገባልንን አንድ የመሆንን ሕብረት
መለማመድ እንችል ዘንድ ክርስቶስ ምን ዓይነት ተጨባጭ ለውጦችን በህይወታችን
ማምጣት ይችላል? ሮሜ 6:4–7፣ 2ቆሮ. 5:17፣ ኤፌ. 4:24–32።
“አንድ ክብ ቅርጽ ያለውን ኳስ መሳይ ነገር በምናብዎ ይሳሉ። ከክቡ ጫፉ እየተነሱ
ቁልቁል ወደ ክቡ አማካኝ አቅጣጫ የሚያልፉ አያሌ መስመሮች ቢኖሩ፤ መስመሮቹ
ወደ አማካኙ ነጥብ በደረሱ ቁጥር አንደኛው ከሌላኛው እጅግ እንደሚቃረብ ማሰብ
እንችላለን. . .
“ወደ ክርስቶስ በተጠጋን ቁጥር አንዳችን ከሌላችን ጋር የተቀራረብን እንሆናለን”—
Ellen G. White, The Adventist Home, p. 179.
“እነርሱ ለይተው ተገነዘቡት ወይም አልተገነዘቡት. . . አማላጅና አማካይ የሆነው
ክርስቶስ በአባትና በልጅ እንዲሁም በባልና በሚስት መካከል ይቆማል። በእርሱ፣
በቃሉና እርሱን በመከተል ካልሆነ--ከራሳችን ውጪ ቀጥተኛ ግንኙነት መመስረት
አንችልም”—Dietrich Bonhoeffer, The Cost of Discipleship (New York:
The MacMillan Publishing Co., 1979), p. 108.
ቤተሰብዎ ወይም የቤተክርስቲያንዎ ሕብረት ለክቡ ቅርጽ አማካይ
ነጥብ ምን ያህል የቀረበ ነው? ግንኙነቶች መሆን እንዳለባቸው ይሆኑ
ዘንድ ሌላ መቀረቡ የግድ የሆነ ነገር ምንድን ነው?
“እኛ ለእናንተ ፍቅር እዳለን ሁሉ እርስ በርስ ያላችሁን ፍቅርና ለሌሎችም ያላችሁን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ፤ ያትረፍርፍላችሁም” (1ተሰ. 3፡12)። የሱስ “‘እኛ አንድ እንደ ሆንን’” (ዮሐ. 17፡22) ሲል ተከታዮቹም አንድ እንዲሆኑ ወደ አባቱ ጸለየ። ይህን አንድ የመሆን ነገር ለማሳካት በተለይ ፍቅር በሚኖረው ሚና ዙሪያ ትኩረት እያደረጉ እዚህ ላይ የሱስ ምን እያለ እንደነበር ጠቅለል አድርገው ለማቅረብ ይሞክሩ።
የሱስ ይህን ጸሎት ሲጸልይ በተከታዮቹ መካከል ሊኖር የሚገባው አንድነት
በአእምሮው ነበር። ይህን ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ አጋፔ በመባል የሚታወቅ ፍቅር
መለማመድ ለዚህ ሕብረት በእጅጉ ወሳኝ ነው። በዚህ ጸሎትና በሌሎች በሌሎች
የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ጥቅም ላይ የዋለው አጋፔ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች
ያለውን ፍቅር የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነው።
እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር የራሱ
የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ሲሆን (1ዮሐ. 4፡8) የክርስቶስ ተከታዮች መገለጫም ነው
(ዮሐ. 13፡35)። የእግዚአብሔር ፍቅር ለኃጢአተኛው ልብ ተፈጥሮአዊ አይደለም።
ሆኖም የሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአማኙ ውስጥ መኖር ሲጀምር ይህ ፍቅር
በግለሰቡ ህይወት መመንጨት ይጀምራል (ሮሜ 5፡5፣ 8፡9-11)።
“‘ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ’ ” ዮሐ. 15፡12)። እነዚህን
ቃላት የጻፈው ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ በአንድ ወቅት ተወዳጅ ሳይሆን ዕቡይ፣
የሥልጣን ጥመኛ፣ ሞገደኛና ግልፍተኛ ነበር (ማር. 3:17፣ ሉቃ. 9:54-55 በተጨማሪ
Desire of Ages, p. 295 ያንብቡ)። እነዚህ ሁሉ ባህሪያት የሱስ እርሱን ከመውደድ
እንዳልገቱት በኋለኞቹ የሕይወቱ ዘመኑ ማስታወስ ችሎ ነበር። የየሱስ ፍቅር እያደር
ዮሐንስን በመለወጥ ሌሎች በክርስትና ሕብረት ያሉ ወገኖችን መውደድ አስቻለው።
“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን” (1ዮሐ. 4፡19)። “እግዚአብሔር እንዲህ
ከወደደን፤ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል” (1ዮሐ. 4፡11)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ቆሮ. 13፡4-8። “ፍቅር” በተሰኘው ቃል ምትክ
የእርስዎን ስም ለማኖር ይሞክሩ። ሃሳቡን ምን ያህል ገጣሚ ሆኖ
አገኙት? የሱስ በመንፈሱ አማካይነት እነዚህን የፍቅር ጸጋዎች ወደ
ህይወትዎ እንዲያመጣ ይጠይቁት። ወደዚህ የሚመኙትና አስደሳች
የክርስትና ሁኔታ ለመድረስ እንዴት ዓይነት ለውጦችን እንዲያደርጉ
መንፈስ ሊያነሳሳዎና ሊያግዞ ይችላል?
“መታበይና ራስ ወዳድነት ላፍታ ገለል መደረግ ቢችሉ፤ እጅግ አስቸጋሪ የተባሉ
ነገሮች በቀላሉ መወገድ በቻሉ ነበር” —Ellen G. White, Early Writings, p. 119.
እንደ ሰብዓዊነታችን ተፈጥሮአችን በኃጢአት ተበክሎአል። ደግሞም የዚያ ብክለት
ታላቁ ምሳሌ የራስ ወዳድነት እርግማን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ራስ ወዳድነት
መሰረታዊ ተፈጥሮአቸው በሆነውና ሁሉንም ነገር ለእኔ “እኔ፣ እኔ…” ብቻ በሚሉ
ጨቅላ ህፃናት በጉልህ መስተዋሉ ከዚህ ችግር ጋር የተወለድን ያስመስለናል።
በዕድሜ ከፍ ስንል ይህ ባህሪ ብዙም ደስ በማይል መልኩ ራሱን ይገልጣል--በተለይ
በቤት ውስጥ።
በእርግጥ የሱስ የመጣው ይህን ለመለወጥ ነበር (ኤፌ. 4፡24)። እኛ እርሱን መልበስ
እንደምንችልና ከዚህ አጥፊ ባህሪ ቁጥጥር መውጣት እንደምንችል ቃሉ ተስፋ
ይሰጠናል። የእርሱ ህይወት ከራስ ወዳድነት ቁጥጥር ውጪ መኖር ምን ማለት
እንደሆነ አመላካች ፍጹም ምሳሌ ነው። እርሱ እንደ ተመላለሰ በመመላለስ (1ዮሐ.
2፡6) ለራሳችን ብቻ የመኖርን ዝንባሌ ማሸነፍ እንችላለን።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ይመልከቱ። ከእኔነት የጸዳ ህይወት ስለመኖር ምን ይነግሩናል?
ፊልጵ. 2:3–5
1ዮሐ. 3:16–18
ኤለን ጂ. ኋይት በመግቢያው ላይ እንደ ተናገረችው መታበይና ራስ ወዳድነት ለአፍታ
እንኳ ገለል ቢል ብዛት ያላቸው ችግሮች በቅጽበት መወገድ ይችሉ ነበር። መላውን
የቤተሰብ አባላት ጨምሮ በተለይ ወላጆች ይህን ኃጢአት (ምሳ. 16፡6) ለመላው
ዩኒቨርስ አብልጦ ከራስ ወዳድነት የጸዳ ምሳሌ ከሆነው መስቀሉ ግርጌ ሊያኖሩ
ይገባል። ይህ ማለት ያለማቋረጥ ወደ መስቀሉ እየተመላለስን በጸሎት መንበርከክ፣
በእምነት እንባችንን ማፍሰስና መታዘዝ ከሆነ ከማድረግ ወደ ኋላ ማለት የለብንም።
በህይወትዎ ሊገለጽ ከሚችል ማንኛውም ዓይነት ራስ ወዳድ ጉዳይ
ጋር በሚያደርጉት ትግል በመስቀሉ ስር ምን ያህል ጊዜ ያጠፋሉ?
በመስቀሉ ስር በቂ ጊዜ የሚያጠፉ ከሆነ (ማቴ. 7:16) ይህ ጥቅስ
እንዴት ሊረዳዎ ይችላል?
በግንኙነቶች ውስጥ ትሕትናን እና ማገልገልን አስመልክቶ ጳውሎስ የሰጠው ምክረ ሀሳብ ምን ይመስላል--ኤፌ. 5፡21? ይህ አመለካከት ለቤተ ክርስቲያን ኅብረት ምን ዓይነት አስተዋጾ ያለው ይመስሎታል? በቤት ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው--ኤፌ. 5፡22-6፡9?
“ተገዙ” (ኤፌ. 5፡21) በሚል የቀረበው ይህ ቃል በበጎ ፈቃደኝነትና በምርጫ ላይ
ተመርኩዞ ሌላውን ማገልገል የሚል አንደምታ አለው። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ መርኅ
በክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 20:26–28፣ ዮሐ. 13:4-5፣ ፊልጵ. 2:5–8) በመንፈሱ
የተሞሉት ሁሉ ጉልህ መታወቂያ ለመሆን በቃ (ኤፌ. 5፡18)።
“ለክርስቶስ ካላችሁ
አክብሮታዊ ፍርሀት” የተሰኘው አባባል ሰዎች ራሳቸውን በዚህ መልኩ እንዲሰጡ
መነሳሳት ይፈጥራል (ኤፌ. 5፡21)። ከማኀበረሰቡ ጋር በሚኖር መስተጋብር
ራስን አሳልፎ መስጠትና የሰውን ችግር እንደ ራስ ማየት ሥር ነቀል የክርስቲያናዊ
አስተምህሮ ለውጥ ነው። አባባሉ ሁሉም በክርስቶስ አንድ የመሆናቸውን መንፈሳዊ
ሐቅ ለህይወት ይዞ ከማምጣት ውጪ የተለየ ነገር የለውም።
ቤተሰባዊው መርኅ፡ ራስን ለሌሎች የማስገዛት የክርስትና መርኅ የሚገለጽበት
ስፍራ መኖሪያ ቤት ነው። ይህ መርኅ በቤት ውስጥ ውጤታማ መሆን ከቻለ
በቤተ ክርስቲያን አመርቂ ልዩነት ይዞ ይመጣል። ጳውሎስ ራስን በማስገዛት መርኅ
አንደምታዎች ዙሪያ ለመነጋገር በፍጥነት ወደ ቤተሰብ ያመራል።
በኤፌ. 5፡22-6፡9 ሦስት ጥንድ ግንኙነቶች የተዳሰሱ ሲሆን እነዚህም በጣም
የተለመዱ ግን ሚዛናቸውን የሳቱ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ናቸው። ዓላማው አሁን
ያለውን ማኅበረሰባዊ ሥርዓት ለማጠናከር ሳይሆን ፍጹም በተለየው በፈቃደኝነት
ላይ በተመሰረተው የአማኙ ራሱን ለሌላው የመስጠት ተግባር የክርስቶስ እምነት
አካሄድ እንዴት እንደሚሠራ ለማሳየት ነው።
ጳውሎስ በማኅበረሰቡ ውስጥ በቀላሉ ለጉዳት ተጋላጭ በሆኑ ሚስቶች፣ ህፃናትና
ባሮች ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚናገረው ለምን ይመስሎታል? አንዱ ለሌላው ራሱን
ከማስገዛቱ በተያያዘ ገጣሚነት ያላቸውን ሀረጎች ያስፍሩ።
ኤፌ. 5:22
ኤፌ. 6:1
ኤፌ. 6:5
በማኅበረሰቡ ከፍ ያለ ማኅበረሰባዊ ጉልበት ያላቸው ማለትም ባሎች፣ ወላጆች
እንዲሁም ጌቶች ሁሌም የተጠቀሱት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው። እያንዳንዱ
የሕብረተሰብ ክፍል የሚቀበለው መመሪያ ከባህሉ ጋር የሚሄድና የተለመደ አይደለም።
እነዚህ መመሪያዎች የዘመኑን አማኞች ሳያስደንቁ እንዳልቀሩ ይታመናል። በመስቀሉ
ዙሪያ ያለውን መሬት በመደልደል የግንኙነትን እውነተኛ አንድ የመሆን ተሞክሮ
መንገድ መክፈት ችለዋል።
የትዳር ጓደኞች አንዳቸው ለሌላቸው እንክብካቤ ሊያደርጉ በኪዳን አጽንተው
የጀመሩት ጉዞ ውሎ አድሮ የሚኖረው ጽናት የሚለካው በእያንዳንዱ የቤተሰብ
አባላት ቁርጠኝነት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ መጠበቅ ያልቻሉ ተስፋዎችን፣ የታጠፉ
ቃሎችንና ጽናት የጎደላቸውን ቁርጠኝነቶች እየጠቀሰ በምሳሌ ያቀርብልናል።
በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር እርዳታ ለጓደኞቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው
ሊኖራቸው የሚገባውን ቁርጠኝነት ሳያጓድሉ በጽናት ያለፉ አስደሳችና ብዙዎቻችንን
ማነጽ የሚችሉ የተራ ሰዎችን ተሞክሮ በምሳሌ ይዞአል።
የሚከተሉትን ቤተሰቦችና የቁርጠኝነታቸውን ደረጃ ለመመልከት ይሞክሩ።
በአንዳንድ ቤተሰብ ቁርጠኝነት ጥንካሬ ማግኘት የቻለው እንዴት ነበር? በሌሎች
ላይ የታየውን ቁርጠኝነት እንዲበረታታ ያደረገው ነገር ምን ነበር?
በወላጆችና በልጆች መካከል የሚኖር ቁርጠኝነት፡ (ዘፍ. 33:12–14፣ ዘፀ.
2:1–10)
በዘመዳሞች መካከል የሚኖር ቁርጠኝነት (ዘፍ. 37:17–28፡
በቤተሰብ መካከል የሚኖር ቁርጠኝነት፡ (ሩት 1:16–18፣ 2:11-12፣ 20፣ 3:9– 13፣ 4:10-13)
በትዳር ጓደኞች መካከል የሚኖር ቁርጠኝነት፡ (ሆሴ 1:2-3፣ 6፣ 8፣ 3:1–3)
ጋብቻ በመመስረት ወይም ልጅን በጉዲፈቻ በማሳደግ ራሳችንን ለሌላው ሰው
ለመስጠት ቁርጠኞች ስንሆን፤ ለወደፊቱ የተለየ ምርጫ በማድረግና ራሳችንን
በፈቃደኝነት ለዚያ በማስገዛት የሕይወታችንን ክፍል ለአንድ አስፈላጊ ምዕራፍ
እናውላለን። ደንቦች አሉታዊ ባህሪያቸውን እንደ ያዙ ሊቀጥሉ ቢችሉም፤ የጋብቻና
የቤተሰብ ግንኙነቶች ግን ማበብና መፍካት የሚያስችላቸውን ፍቅር ይሻሉ።
የሱስ ቁርጠኝነትን አስመልክቶ የሰጠው ተስፋ (ዕብ. 13፡5) ለእርስዎ
በግል ያለው ትርጉም ምን ይመስላል? እርሱ ለእርስዎ ያለው ቁርጠኝነት-እርስዎ ለእርሱ፣ ለባለቤትዎ፣ ለልጆችዎና ለአማኙ ኅብረት ባሎት
ቁርጠኝነት ላይ ምን ዓይነት ውጤት ይኖረዋል?
፡ Ellen G. White, “A Sacred Circle,” pp. 177–180, in The
Adventist Home; Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 236–238.
ሕብረት--የመጀመሪያው ተግባር፡ “በቤተሰብ ውስጥ ሕብረት መፍጠር
የክርስቲያኖች ተቀዳሚ ተግባር ነው. . .
“የቤተሰብ አባላት በቤት ውስጥ ተግባራቸው አብልጠው ቅርበት በፈጠሩ ቁጥር-አባት፣ እናት፣ ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች ከቤት ውጪ ባላቸው ግንኙነት በላቀ
የሚያንጹና ጠቃሚ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ይሆናሉ።”—Ellen G. White, The Adventist Home, p. 37.
የቤተሰብ ሕብረት ምስጢር፡ “ከክርስቶስ መለየት በቤተሰብ መሃል
እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን መለያየትና ጸብ እንዲፈጠር መንስዔ ይሆናል። ወደ
ክርስቶስ መቅረብ ወደ ወንድም እህቶች መቅረብ ማለት ነው።
በቤተ ክርስቲያን
እና በቤተሰብ እውነተኛ ሕብረት ለማምጣት ምስጢሩ ዲፕሎማሲ ወይም አመራር
ሳይሆን (እነዚህም አስፈላጊ ቢሆኑም) ምስጢሩ ከክርስቶስ ጋር ሕብረት መፍጠር
ነው”—Page 179.
፡
1.በገዛ ማኅበረሰባችሁ ከቤተሰብ ሕብረት በተቃራኒ በሚሠሩ ውጪያዊ
ኃይላት ዙሪያ ተወያዩ። ከእነዚህ ተጽእኖዎች በተቃራኒ እየታገሉ
ለሚገኙ ቤተሰቦች ምን ዓይነት ተጨባጭ መፍትሔ ማቅረብ ይችላሉ?
2.የመፍረስ አደጋ የገጠመው ቤተሰብ ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችሁ አለ?
ካለ፤ እያንዳንዳችሁ ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ልታመጡና ችግሩን
ልትቀርፉ በምትችሉበት ነጥብ ዙሪያ ተወያዩ።
3.ሌላውን በማገልገልና ራስን በማስገዛት ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ተወያዩ።
ጽንሰ ሃሳቡ ከክርስትና ዐውድ አኳያ እንዴት ነው የሚስተዋለው? ይህ
መርኅ የተሳሳተ ግንዛቤ ያገኘውስ እንዴት ነው?
4.በቤተሰብ ውስጥ ከሚመለከቱት ሕብረት ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን
አንድነት የሚበጁና መተግበር የሚችሉ ምን ዓይነት መርኅዎችን
ማግኘት ይችላሉ?