ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሐዋ. 2:42–47፣ 4:32–37፣ ማቴ. 25:38-40፣ ሐዋ. 9:36፣ 2ቆሮ. 8:7–15፣ ሮሜ 12፣ ያዕ. 2:1–9፡፡
መታሰቢያ ጥቅስ:-“በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹህና ነውር የሌለበት ኃይማኖት ይህ ነው፤ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳትና ከዓለም ርኩሰት ራስን መጠበቅ ነው” (ያዕ. 1፡27)፡፡
ታ
ላቁ ተልዕኮ በመባል የሚታወቀው በማቴ. 28፡18-20 የምናገኘው መልእክት
ቢያንስ በክርስቲያኖች ዘንድ በጉልህ ይታወቃል፡፡ ጥቅሱ የተልዕኮአችን
መገለጫ በመሆን አዘውትሮ ከማገልገሉ በተጨማሪ ለማንኛውም ዓይነት የወንጌል
እንቅስቃሴና የሥራ እቅዶች በአነሳሽነት ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው በእነዚህ ጥቅሶች
መነሳሳት ያገኙ ክርስቲያኖች ወንጌልን ለማሰራጨት በመላው የምድር ክፍል
ተንቀሳቅሰዋል፣ ይህን ተከትሎ አልፎ አልፎ ከፍተኛ ዋጋ እስከ መክፈልም ደርሰዋል።
የሱስ ታላቁን ተልዕኮ ሲሰጥ ምን ብሎ ነበር? ሕዝቦችን ደቀ መዝሙር ስለ
ማድረግ፣ ስለ ማጥመቅ እና ስለ ማስተማር ከነገራቸው በኋላ “ያዘዝኋችሁንም
ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው” (ማቴ. 28፡20) አላቸው፡፡ ቀደም ብለን እንደ
ተመለከትነው የሱስ ከሰጠን ትእዛዛት መካከል አብዛኛው ችግረኞችን፣ ጉዳት
የደረሰባቸውንና እራሳቸውን መርዳት የማይችሉትን ከመጎብኘትና ከመርዳት ጋር
ቁርኝት አለው፡፡ እነዚህ ለየሱስ የመጀመሪያ ደቀ መዝሙሮች የተሰጡ መመሪያዎች
ከዚያ ቀደም ተሰምተው ወይም ታይተው የማይታወቁ አለመሆናቸውን መዘንጋት
የለብንም፡፡ ይልቁንም የሱስ አስቀድሞውኑ ከእነርሱ ጋር የመሰረተው ተልዕኮ ቀጣይ
አካል ነው፡፡ እንዲህ ያለው የየሱስ አስተምህሮ--የታላቁ ተልዕኮ አካል በመሆን
በአዲሷ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ህይወት ውስጥ በግልጽ መታየት ይችላል፡፡
ከየሱስ ዕርገትና ከመንፈስ ቅዱስ መውረድ በኋላ በአንድ የተሰባሰቡት አማኞች
በፈጣን ዕድገት የመሰረቷት ይህች የቀደመች ቤተ ክርስቲያን--ከየሱስ ተከታዮች
መሃል በዓይነቱ አዲስ በሆነ ማኅበረሰብ እና በቀደሙት ደቀ መዛሙርት ትመራ
ነበር፡፡ ሆኖም ይህ አዲስ ማኅበረሰብ እንዲሁ በራሱ የተቋቋመ ሳይሆን በየሱስ
አስተምህሮዎችና አገልግሎት እንዲሁም ረጅም ዘመን ባስቆጠሩ የዕብራውያን
ቅዱሳት መጻሕፍትና ነቢያቶች ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሐዋ. 2፡42-47፣ 4፡32-37፡፡ ስለ ቀደመችው ቤተ ክርስቲያን
ማኅበረሰብ በቀረቡት በእነዚህ መግለጫዎች ምን ዓይነት ቁልፍ መሰረታዊ ነገሮች
ይመለከታሉ?
እስራኤላውያን አምላካዊን ንድፍ የተከተለውን ሐቀኛና በቸርነት የተሞላ
ማኅበረሰብ ለመመስረት ያስችላቸው የነበረውን ህይወት በሙላት ሳይኖሩ ያለፉ
ቢመስሉም፤ የቀደመችው ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ግን “‘በመካከልህ ደኻ
አይኖርም’” (ዘዳ. 15፡4) በሚል የተሰጠውን መመሪያ በጽሞና ተቀብላ ሥራ ላይ
አውላ ነበር፡፡ እምነታቸው በተግባር ይገለጥ ከነበረባቸው መንገዶች አንዱ ቁሳዊ
ሀብታቸውን በጋራ የመጠቀም ማኅበራዊ አኗኗራቸው ነበር፡፡ መሬታቸውን ሳይቀር
እየሸጡ ገንዘቡን (ሐዋ. 4፡34-5፡2) ለአማኝ ወገኖቻቸው ችግር መቅረፊያና በዘላቂ
ማቋቋሚያ ያውሉት ነበር፡፡ ደግሞም ገና በሚገባ ካልጠናው ማኅበረሰብ ውጪ ወደ
ነበሩ ሰዎች ለመድረስ ጭምር--በተለይ በፈውስ አገልግሎት (ሐዋ. 3፡1-11፣ 5፡12-16)
በረከት ለመሆን ይሠሩ ነበር፡፡
ሆኖም ይህ ማኅበረሰብ ማንኛውም ነገር ፍጹም በሆነ ለዛና መዋሃድ ይሠራበት
የነበረ፣ እንከን ዐልባውና ምናባዊው utopian society አልነበረም፡፡ የአማኞች ቁጥር
እያደገ በሄደ ቁጥር እነዚህን ሐብቶች በማስተዳደሩ ዙሪያ ውጥረቶች እየጨመሩ
መጡ--በተለይ በየዕለቱ ይከናወን የነበረው ምግብ የማደል አሠራር ላይ መበለቶች
ችላ ተብለዋል በሚል (ሐዋ. 6፡1)፡፡ የቡድኑ የበላይ ኃላፊዎች የነበሩት ደቀ መዛሙርት
ሙሉ ትኩረታቸውን ማድረግ የፈለጉት ወንጌል በመስበክ አገልግሎት ላይ ነበር፡፡
ስለዚህ በመሀላቸው ለተፈጠረ ችግር መፍትሔ የሚሆን አንድ ግብረሃይል ለማቋቋም
ወሰኑ፡፡
ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ተጨባጭ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ
የሚሠራ ሰባት አባላት ያሉት አንድ ዘርፍ ተቋቋመ፡፡ ይህ ዘርፍ ምናልባት በቤተ
ክርስቲያን አገልግሎት ከሚሰጡ የተለያዩ ዘርፎች ቀዳሚውን እውቅና ያገኘው
ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪ ተግባራዊ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን ህይወትና
ምስክርነት ያለውን አስፈላጊነትን ያሳየ ነበር፡፡ “በሙሴ እና በዳዊት ዘመን በሕዝቡ
መሃል የነበሩ መሪዎችን ይመሩ የነበሩ ተመሳሳይ የቅድስናና የፍትሕ መርኅዎች፤
ወንጌልን እንድትሰብክ ኃላፊነት የተሰጣትንና አዲስ የተቋቋመችውን የእግዚአብሔር
ቤተ ክርስቲያንም እንዲሁ መምራት ነበረበት፡፡”—Ellen G. White, The Acts of
the Apostles, p. 95.
የዚያ የቀደመ ማኅበረሰብ ሁኔታ ምን ይመስል እንደ ነበር በዐይነ
ህሊናዎ ለመመልከት ይሞክሩ፡፡ እኛ ዛሬ እነዚያን መርኅዎች ማንጸባረቅ
የምንችለው እንዴት ነው?
የሱስ “ ‘ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ
ምስክሮቼ ትሆናላችሁ’ ” (ሐዋ. 1፡8) ሲል አስቀድሞ እንደተነበየው ቤተ ክርስቲያን
እያደች መሄድ ጀመረች፤ አዳዲስ አማኞችም እምነቱንና የየሱስን አገልግሎት መቀበል
ጀመሩ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዶርቃ አንዷ ነበረች፡፡ በኢዮጴ ትኖር የነበረችው
ዶርቃ--ጣቢታ በመባልም እንዲሁ ትታወቅ ነበር፡፡ የየሱስን መመሪያ ከልብ ተቀብላ
ትተገብር የነበረችው ዶርቃ የታረዙትን ስታለብስ ለራሱ ለየሱስ እንዳደረገች ይሰማት
ነበር (ማቴ. 25፡38፣ 40)፡፡
የዶርቃን አገልግሎት አስመልክቶ በሐዋ. 9፡36 የቀረበውን መግለጫ ያንብቡ።
የእርስዎ ህይወትና አገልግሎት ከዚህ ይዞታና አቀራረብ በተመሳሳይ እንዴት
ይገለጻል? እርስዎ እንዴት ቢገለጹ ይመርጣሉ?
ዶርቃ እንደ “ደቀ መዝሙር” (ሐዋ. 9፡36) የተገለጠችበት አገልግሎት፣ ታማኝነት፣
ጉልበትና በሌሎች ላይ የነበራት ትኩረት ከመኖሪያ ከተማዋ ባሻገር እንድትታወቅ
አስችሏት ነበር፡፡
ጴጥሮስ ለኢዮጴ ቅርብ በነበረው በልዳ አማኞችን እየጎበኘ መሆኑ ሲሰማ፤ የኢዮጴ
ሰዎች ፈጥኖ እንዲመጣ መልእክት ላኩበት (ሐዋ. 9፡37-41)፡፡ ጴጥሮስ በዚያ እንደ
ደረሰ ለድኾች እርዳታ ታደርግ የነበረችውና ያለ ጊዜዋ የሞተችው ዶርቃ ድጋፍ
ያደረገችላቸውን ብዙ ሰዎች አገኘ፡፡ ዶርቃ የሠራቻቸውን ልብሶች ለጴጥሮስ ያሳዩ
የነበሩት መበለቶች እንዴት ለምስኪን ደራሽና ርኅሩኅ ሴት እንደነበረች አስመልክቶ
ብዙ ታሪኮች ሳይነግሩት እንዳልቀረ ይታመናል፡፡
ጴጥሮስ ለዶርቃ ከጸለየ በኋላ እግዚአብሔር እስትንፋሷን መመለሱ፤ ብዙዎች
ስለ ሌሎች በጎ ቀን ከሌት ደፋ ቀና ቢሉም እንኳ ህይወት ሁሌም በአስተማማኝ
ለመቀጠሏ ዋስትና አለመኖሩን ያሳያል፡፡ ለነገሩ ዶርቃ እንኳ መጀመሪያ ታማ
ነበር፡፡ ከዚያም ያው አይቀሬው ሞት መጣ፡፡ ነገር ግን ከቀደሙት ዲያቆናት
አንዱ የነበረውና የቤተ ክርስቲያን መበለቶችን እንዲያገለግል ኃላፊነት የተሰጠው
እስጢፋኖስ የመጀመሪያው ሰማዕት ለመሆን በቃ (ሐዋ. 7፡54-60)፡፡ የአገልግሎት
ህይወት ሁሌም አልጋ በአልጋ አይደለም--አባጣ ጎርባጣም እንጂ!
በዶርቃ ህይወትና ሞት የተለየ እውቅና የተቸራቸው ሁለት ነገሮች ማለትም-አምላካዊው ፍቅር እና ኃያልነት በኢዮጴ ሕዝቦች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደ
ነበራቸው መመልከት ይቻላል፡ “ይህም ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም
በጌታ አመኑ” (ሐዋ. 9፡42)፡፡
መቼም ማለፍ አይቀርምና እርስዎም አንድ ቀን ቢያልፉ፤ በጎነትዎና
አስተዋጾዎ እንደ ዶርቃ የብዙዎችን ልብ የሚሰብርና እንዲታወሱ የሚያደርግ
ይሆን? የመልካም አገልግሎት ቅርስ ትተን ማለፍ የምንችለው እንዴት ነው?
ዶርቃ የልብስ ስፌትና የሽመና ሙያ እንደ ነበራት ሁሉ እርስዎስ ሌሎችን
የሚያገለግሉበት ምን ዓይነት ሙያ አሎት?
ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታን ከተቀበለና ከተለወጠ በኋላ ወንጌልን ለአሕዛቡ
ዓለም የማድረስ ተልዕኮ ወሰደ፡፡ እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠው ስኬት ከአይሁድ
ማንነት ወደ ክርስትና በመጡትና በአዳዲሶቹ አሕዛብ ተከታዮች መካከል ባለው
ግንኙነት ዙሪያ ታላቅ ጥያቄ አስነሳ፡፡ በዚህ አንገብባቢ ርዕሰ ነጥብ ላይ ውይይት
አድርጎ ውስብስቦቹን ጥያቄዎች በአምላካዊው ምሪት ለመፍታት፤ የአይሁድና
አሕዛብ ክርስቲያኖች ጉባኤ በየሩሳሌም ተጠራ፡፡ ጉባኤውም ሆነ በጉባኤው የተገኙ
ውጤቶች በሐዋ. ምዕ. 15 ቀርበዋል፡፡
ጳውሎስ ስለዚህ ጉባዔ ያዘጋጀው ሪፖርት በገላ. 2 የሚገኝ ሲሆን፤ ከየሩሳሌም ጉባኤ
ከተቀበላቸው ትእዛዞች መሠረታዊ ከሆኑት መካከል ለቀጣይ የአሕዛብ አገልግሎቱ
አንድ ሌላ አስፈላጊ ነጥብ ያክላል፡ “አጥብቀው ዐደራ ያሉን ድኾችን ማሰባችንን
እንዳናቋርጥ ብቻ ነው፤ እኔም ይሄንኑ ለማድረግ ጉጉቴ ነበር” (ገላ. 2፡10)፡፡
ጳውሎስ በአጠቃላይ አገልግሎቱ በዚህ ነጥብ ላይ ትኩረት ማድረጉን ገፋበት (ሐዋ.
20፡35)፡፡ ጳውሎስ በየሩሳሌም ከነበረችው የቀደመች ቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ፤
ሁሉንም አማኞች ለማቀፍ በሚያስችል መልኩ የክርስትናው ማኅበረሰብ ራእይ
እየተስፋፋ እንዲሄድ አደረገ፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ቆሮ. 8፡7-15፡፡ ጳውሎስ ወንጌልን በለጋስነት ከመስጠት ጋር
የሚያስተሳስርበት መንገድ ምን ይመስላል?
አማኞች በልግስና እንዲሰጡና በአስቸጋሪ ሁናቴ ውስጥ ይገኙ ለነበሩ አማኝ ወንድም
እህቶቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለማነሳሳት ጳውሎስ በተጨማሪ ሁለት የብሉይ
ኪዳን ጥቅሶችን ጥቅም ላይ ሲያውል ይስተዋላል፡፡ እስራኤላውያን በምድረ በዳ
ጉዞአቸው እግዚአብሔር በልግስና ያወረደላቸውን መና ሐዋርያው የመስጠትና
የማካፈል ምሳሌ አድርጎ ለመላው የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ያቀርባል (2ቆሮ. 8፡
15)፡፡ በተጨማሪ “በተነ፤ ለድኾችም ሰጠ፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል” (2ቆሮ. 9፡
9) ሲል ከመዝሙረ ዳዊት 112፡9 ይጠቅሳል፡፡
ጳውሎስ አንባቢዎቹ በመስጠት ዙሪያ ልዩ ትኩረት ያደርጉ ዘንድ አጥብቆ
አሳስቧቸዋል፡፡ አማኞች ከገቢያቸው ላይ የተወሰነውን ለይተው ካስቀመጡና
እርሱ ወይም ቲቶ ጉባኤያቸውን በሚጎበኙበት ወቅት ይህ ስጦታ ተዘጋጅቶ
ቢጠብቃቸው፤ በየሩሳሌም ለነበሩ አማኝ ችግርተኞች ለማድረስ ቀላል ይሆናል፡፡
ሐዋርያው በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ሌሎቹን
ለማነሳሳት ይሞክራል፡ “የክርስቶስን ወንጌል ተቀብላችሁ ስለ ታዘዛችሁና ለእነርሱም
ሆነ ለሌሎች ስላሳያችሁት ልግስና ሰዎች ተፈትኖ ስላለፈው አገልግሎታችሁ
እግዚአብሔርን ያከብራሉ” (2ቆሮ. 9፡13)፡፡
በፊታችን ለሚቀርብ እያንዳንዱ የበጎ አድራጎት ጥያቄ ምላሽ መስጠት
የማንችል ሲሆን፤ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን አንገብጋቢ ጉዳይ
መለየት የምንችለው እንዴት ነው?
ጳውሎስ ለሮም ሰዎች የላከው ደብዳቤ ማለትም የሮሜ መጽሐፍ--በክርስቶስ
ሞት የተገኘውን የደኅንነት በእምነት ኃይማኖታዊ አስተምህሮ በጥልቀት የገለጸበት
ሥራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከዐሥራ አንደኛው ምዕራፍ በኋላ ግን የትኩረት
አቅጣጫ ወይም የአጽንኦት ለውጥ ያደርጋል፡፡ በየሱስና በወንጌል ታሪክ እንደ
ተገለጸው ሐዋርያው በአምላካዊው ጸጋና ፍቅር ላይ የተመሰረተ ህይወት ስለ መኖርና
ስለ መዋደድ ተግባራዊ ምሪት ይሰጣል፡ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን
ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ
በእግዚአብሔር ርኅርኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት
አምልኮአችሁ ነው” (ሮሜ 12፡1)፡፡ በሌላ አነጋገር፤ እግዚአብሔር በየሱስ ካደረገልን
ነገር አኳያ ልንኖር የሚገባው እንዲህ ነው--እያለን ነው፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሮሜ ምዕ. 12፡፡ በዚህ ምዕራፍ ስለ ፍቅርና ለሌሎች ጥንቃቄ
ስለማድረግ--በተለይ በዕጦት ስለሚገኙ ችግርተኞች የቀረቡትን መመሪያዎች በሚገባ
ለመመልከት ይሞክሩ።
ሮሜ 12--ጳውሎስ ይበልጥ ዘርዘር ያለ ትኩረት ለሚያደርግባቸውና አብዛኞቹ
ሌሎች ደብዳቤዎቹ ለዳሰሳቸው ርዕሰ ነጥቦች እንደ ማጠቃለያ ሊያገለግል ይችላል።
ሌሎችን ማገልገል፣ ማበረታታትና በለጋስነት መስጠትን ጨምሮ (ቁ. 3-8) የቤተ
ክርስቲያን አካል ስለሆኑ ልዩ ልዩ ኃላፊነቶችና ስጦታዎች ይናገራል፡፡ ሆኖም እነዚህ
ነገሮች እንደው በደምሳሳው ሳይሆን በትጋት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በፍቅር ሥራ
ላይ ሊውሉ ይገባል (ቁ. 9-11)፡፡
ይህ ዓይነቱ ህይወት ምን ማለት እንደሆነ ጳውሎስ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ይናገራል።
አማኞች በአስቸጋሪ ሁናቴና በስደት ለሚገኙ--ትዕግሥተኞች፣ በእጦት ያለውን
የሚንከባከቡ፣ በተቻላቸው ክፉን በመልካም የሚያሸንፉ እንጂ በክፉ የማይሸነፉ
የሰላም መልእክተኞች ይሆኑ ዘንድ ሐዋርያው ጥሪ ያቀርባል (ሮሜ 12፡20)፡፡
ይህ ምዕራፍ እንደ አዲስ ሰው የመኖርን ፍቺ እንዲሁም እግዚአብሔርን በግልና
በጋራ ስለ ማገልገል በቂ ሀሳብ ይሰጣል፡፡ የሱስ በመስቀል ላይ ሞቱና የዘላለማዊ
ህይወት ተስፋ በመስጠት ለእነርሱ ስላደረገላቸው ነገሮች በምላሹ--ህይወታቸው፣
ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮችና ድርጊቶቻቸው ሊለወጡ እንደሚገባ ሐዋርያው
ለአዳዲሶቹ የየሱስ ተከታዮች ነግሮአቸው ነበር፡፡ እነዚህ በጭቆና እና በጨካኝ
ማኅበረሰብ ውስጥ መኖር ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቀው የሚያወቁ፤ በሮም
መንግሥት ስር የሚኖሩ ሕዝቦች--ከቀድሞው በተለየ አኳኋን እንዲኖሩ ሐዋርያው
ያስተምራቸዋል፡ “በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ”
(ሮሜ 12፡2)፡፡
ዛሬ እንደ የሱስ ተከታይነትዎ ከመኖርና ሌሎችን ከመውደድ
ሊያስተጓጉልዎ የሚችሉና ሊታገሏቸው የሚገቡ ማኅበረሰባዊ
አመለካከቶችና ልምዶች ምንድን ናቸው?
የቀደመው የክርስትና ወግ እንደሚጠቁመው ከሆነ የየሩሳሌም ጉባኤ ሊቀመንበር
የነበረው የየሱስ ወንድም ያዕቆብ (ሐዋ. 15፣ ገላ. 1 እና 2) በየሩሳሌም የነበረችው
የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያንም መሪ ነበር፡፡ ይህ ሐዋርያ በያዕቆብ መጽሐፍ
ደራሲነትም እንዲሁ ይታወቃል፡፡
ልጅን በእርሱ መጠሪያ ስም መጥራት በዘመኑ እጅግ የተለመደ ነበር፡፡ ያዕቆብ
ለሌሎች ችግር መፍትሔ ቅድሚያ የሚሰጥና ለተረሱ ወይም ዝቅ ተደርገው ይታዩ
ለነበሩ አብልጦ የሚጠነቀቅ ብልህ መሪ ነበር፡፡ ይህ “የአዲስ ኪዳኑ መጽሐፈ ምሳሌ”
በሚል የተገለጸና በእርሱ መጠሪያ ስም የሚታወቅ መጽሐፍ፤ የእግዚአብሔር
ተከታዮች በቅድስና እና በጥበብ መመላለስ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
“ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ”
(ያዕ. 1፡22) ብሎ ክርስቲያን መሪዎችን ለማስታወስ ጉጉ የነበረው የያዕቆብ መጽሐፍ
ደራሲ፤ በእግዚአብሔር ዐይን ንጹህና ዘላቂ በሆነው፣ ፋይዳ ያለው ኃይማኖት
ይኸውም--ማሕበረሰቡን ከብቦት የነበረውን የብልሹ አሠራር ተጽእኖ ተቋቁመው
በችግር ውስጥና በጭቆና ለነበሩት ጥንቃቄ ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር ያዕ.
1፡27)፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ያዕ. 2፡1-9፣ 5፡1-5፡፡ ያዕቆብ ለሀብታሞች የነበረው አስተሳሰብ
ከዘመኑ ማኅበረሰብ እሳቤ የተለየ የሆነው እንዴት ነበር? ሀብታሞች እና ድኾች
በቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ እንዴት መታየት እንዳለባቸው አጽንኦት የሚሰጡት
የእርሱ የተለዩ መመሪያዎች ምን ነበሩ?
ምስኪኖች በብርድና በረሃብ እየተሰቃዩ “በሰላም ሂዱ፣ አይብረዳችሁ፣ ጥገቡ”
የተሰኘው መልካም ምኞት ሊያመጣ የሚችለው መጽናናት እጅግ አነስተኛ ነው-ሲል ያዕቆብ ይሞግታል፡፡ ለችግረኛው የሚበላ ወይም የሚለበስ መጽዋት መስጠት
ከማንኛውም መልካም ምኞት በላቀ ለምስኪኑ ደኻ ያለንን ጭንቀት በተጨባጭ
ገልጦ ያሳያል (ያዕ. 2፡14-16)፡፡ ያዕቆብ ይህን የእምነትና የሥራ መስተጋብር
ምሳሌ ከእግዚአብሔር ጋር ካለን የግንኙነት ዐውድ ያቀርባል፡፡ እንዲሁም የሱስ
ባልንጀራን እንደ ራስ ስለ መውደድ ያስተማረውን (ያዕ. 2፡8) ትምህርት እንዴት
በየዕለቱ ህይወታችን መታዘዝ እንዳለብን በማሳየት ደግሞ አቅርቦታል፡፡ ይህ
ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሌሎች በምንሰጠው አገልግሎት በህይወታችን ገልጠን
የምናሳየው ነገር፤ የእውነተኛ እምነት መገለጫ እንጂ ደኅንነት እናገኝበታለን ብለን
የምናደርገው ነገር አይደለም፡፡
ከድኽነት ይልቅ ሀብትን በደመነፍስ እንኳ ለመምረጥ የሚቀለን
ለምንድን ነው?
Read Ellen G. White, “Dorcas—Her Ministry and
Its Influence,” pp. 66, 67, in Welfare Ministry; “A Liberal Church,”
pp. 335–345, in The Acts of the Apostles; “This Is Pure Religion,”
pp. 35–41, in Welfare Ministry.
“በሐዘን ውስጥ ላሉና ፈተና ለተጋረጠባቸው ነፍሳት ብቁ አገልግሎት የምትሰጥ
ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ሲል አዳኙ የከበረ ህይወቱን ሰጠ፡፡ አማኞች-ድኾች፣ በመደበኛው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያላለፉና የማይታወቁ
ቢሆኑ እንኳ፤ ነገር ግን በክርስቶስ አማካይነት--በቤታቸው፣ በጎረቤታቸው፣
በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በተለያዩ ርቀት ባላቸው ስፍራዎች የሚሰጧቸው
አገልግሎቶች ዘላለማዊ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላል፡፡”—Ellen G. White,
The Desire of Ages, p. 640.
“አማኞች የወንጌልን መልእክት በጨለማ ወዳሉት ለማድረስ ባደረጉት
ያላሰለሰ በጎነት ለራሱ ቅድሚያ ያልሰጠው ለጋስነት የቀደመችውን ቤተ
ክርስቲያን ወደ ሐሴት ጎዳና መራት፡፡ ደግነትና ርኅራኄአቸው የእግዚብሔርን
ጸጋ በከንቱ አለመቀበላቸውን መመስከር ቻለ፡፡ እንዲህ ያለው ለጋስነት
በመንፈስ ቅዱስ መቀደስ እንጂ ምን ሊያስገኝ ይችል ነበር? የአምላካዊው
ታምራት ጸጋ አማኝ በሆኑም ሆነ ባልሆኑ ዐይኖች በጉልህ ይታይ ነበር፡፡”—
Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p. 344.
1.የቤተ ክርስቲያንዎ ማኅበረሰብ በአመዛኙ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ
የመጀመሪያ ምዕራፎች እንደተገለጸው ዓይነት መሆን የሚችለው እንዴት
ነው? ቤተ ክርስቲያንን በዚህ አቅጣጫ ለማበረታታት የሚችለው አመራር
በሥራ ላይ ሊያውላቸው የሚችሉ ቅደም ተከተሎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
2.ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዐሥራትና ስጦታ በተለያዩ የዓለም
ክፍል እንዲከፋፈል በማድረግ አንዳንዶቹን በዚህ ሣምንት የተነጋገርንባቸውን
መርኅዎች ጥቅም ላይ በማዋል በዓለማቀፍ ደረጃ እየሠራችበት ትገኛለች።
ሀብትን በዚህ መልኩ በዓለማቀፍ ደረጃ የማከፋፈል ዘዴ መከተል ምን
ዓይነት ጥቅሞች ያስገኛል?
3.ለምሳሌ በሮሜ 12 የቀረቡት ዓይነት የህይወት መመሪያዎች በህይወታችን
በተግባር መገለጽ የሚችሉ ናቸው? በገሀዱ ዓለም ሥራ ላይ መዋል ይችሉ
ይሆን? ወይስ ቆየት ባሉ አብያተ ክርስቲያናት የመስታወት መስኮቶች ላይ
የተሳሉ ፍጹም የሆኑ “ቅዱሳን” ምስል ዓይነት ስሜት ይሰጣሉ?
4.ከብሉይ ኪዳን ነቢያት የሚያስተጋቡ ዓይነት ጠንከር ያሉ ቃላትና
ማስጠንቀቂያዎች በያዕ. 5፡1-5 ቀርቦአል፡፡ እንዲህ ያለው ጠንካራ አገላለጽ
ተገቢና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ማጠቃለያ፡ በየሱስ ተልዕኮና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተበረታቱት
ደቀ መዛሙርት እና የቀደሙት አማኞች የየሱስን መልእክትና
ተልዕኮ በተቻላቸው መጠን በስፋት ማስተጋባት ጀመሩ፡፡ የየሱስን
አስተምህሮና የብሉይ ኪዳንን መልእክቶች አጣምራ የያዘችው
የቀደመችው ቤተ ክርስቲያን አባላት ያላቸው ለሌላቸው የሚያካፍሉበት
አዲስ ዓይነት ማኅበረሰብ አቅፋ ይዛ ነበር፡፡ የቀደሙት የክርስትና
እምነት መሪዎች በምሳሌነታቸውና በትምህርታቸው ለእነዚህ ቤተ
ክርስቲያኖች በጻፏቸው ደብዳቤዎች አማኞች በታማኝነት እንዲኖሩና
እንዲያገለግሉ--በተለይም ችግርተኞችን! አጥብቀው አስገንዝበዋል፡፡