የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኤር. 31:31–34፣ ማቴ. 5:17–28፣ ሆሴ 2:18–20፣ ኢሳ. 56:6-7፣ ዕብ. 8:7-8፣ ዕብ. 10:4፣ ማቴ. 27:51።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ ‘ከእስራኤል ቤትና፣ ከይሁዳ ቤት ጋር ይላል እግዚአብሔር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል’ ” (ኤር. 31፡ 31)፡፡
ከ
ዓመታት በፊት በወጣ አንድ መጽሔት የካርቱን ሥዕል ላይ--በቢሮ ውስጥ፣
አንድ የንግድ ሥራ አስፈጻሚ ከሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ቡድኖች ፊት ቆሞ
ይታያል። የሥራ አስፈጻሚው በውስጡ የንጽህና መጠበቂያ የያዘ እሽግ
ካርቶን የያዘ ሲሆን፤ ይህንኑ ለሌሎቹ ወንዶችና ሴቶች ያሳያቸዋል። በካርቶኑ ላይ ጎላ
ብሎ የተጻፈውን አዲስ የሚል ፊደል በኩራት ይጠቁማቸዋል። ከሁኔታው መረዳት
እንደሚቻለው ምርቱ አዲስ እንደነበር ያሳያል። ሥራ አስፈጻሚው በመቀጠል “ይህ
አዲስ በሆነ ካርቶን ላይ የሰፈረ ‘አዲስ’ የሚል ቃል ነው” ይላቸዋል። በሌላ አነጋገር
ተለውጧል፣ አዲስ ነው፣ የተባለው--“አዲስ” የሚለው ቃል ብቻ ነበር። ከዚህ ውጪ
ማንኛውም ነገር ተመሳሳይ ነበር።
ምናልባት አንድ ሰው አዲሱ ኪዳን ይህን ይመስላል ሊል ይችላል። የቃል ኪዳኑ
መሠረት፣ ለእኛ ያለው መሠረታዊ ተስፋና የተቀመጡት ሁናቴዎች መሠረት በአሮጌው
ኪዳን ውስጥ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይ ነው። ሁሌም ቢሆን ሰብዓዊውን ድካም እና
ሽንፈት የሚያስንቅ በፍቅር ላይ የተመሰረተ አምላካዊው ጸጋና ምሕረት ኪዳን ነው።
ሣምንቱ በጨረፍታ፡ በአሮጌው እና በአዲሱ ቃል ኪዳን መካከል ምን ዓይነት
መመሳሰል ይስተዋላል? ሕጉ በኪዳኑ ላይ የሚጫወተው ሚና ምንድን ነው? ቃል
ኪዳኖቹ የተቋቋሙት ከነማን ጋር ነበር? የዕብራውያን መጽሐፍ ኪዳኑ “በሚሻል
ኪዳን” (ዕብ. 8፡6 /1962 ትርጉም/) ሲል ምን ማለቱ ነው? በቃል ኪዳኑ እና
በሰማያዊው መቅደስ መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ እና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ፡ ኤር.
31:31–34
1.የኪዳኑ አነሳሽ ማን ነው?
2.ስለ ማን ሕግ ነው እየተነገረ ያለው?
3.እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር እንዲኖረው ለሚፈልገው የግንኙነት ገጽታ
አጽንኦት የሚሰጡት የትኞቹ ቁጥሮች ናቸው?
4.እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ የሚሠራው ምን ዓይነት ሥራ ነው--የዚያን
ኪዳናዊ ግንኙነት መሠረት የሚፈጥረው?
አዲሱ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በሲና ተራራ ከገባው አሮጌው ጋር
በብዙ የሚለያይ አለመሆኑ ግልጽ ነው። በእርግጥ የሲና ቃል ኪዳን ችግር ማርጀቱ
ወይም ጊዜ ያለፈበት መሆኑ አልነበረም። ይልቁንም ችግሩ ቃል ኪዳኑ መጣሱ ነበር
(ኤር. 31፡32)።
ከላይ የቀረቡት ጥያቄዎች መልሶች በሙሉ በእነዚህ አራት ጥቅሶች ውስጥ
መገኘታቸው፤ አብዛኞቹ “አሮጌው ቃል ኪዳኖች” በአዲሱ ውስጥ ለመቅረታቸው
ማረጋገጫ ነው። “አዲስ ቃል ኪዳን” በተወሰነ መልኩ “የታደሰ ቃል ኪዳን” የሚል
ስሜት የያዘ ሲሆን፤ ይኸውም የመጀመሪያው ማጠናቀቂያ ወይም ፍጻሜ ነው።
ጌታ ዓመጻቸውንና የሕዝቡን ኃጢአት ይቅር እንደሚል በሚናገርበት በመጨረሻው
የኤር. 31፡34 ክፍል ላይ ትኩረት ያድርጉ። ምንም እንኳ ጌታ ሕጉን በልባችን
እንደሚያጽናና በውስጣችን እንደሚያኖር ቢናገርም፤ በልባችን ውስጥ
የተጻፈውን ሕግ የሚጻረረውን ኃጢአታችንን እና በደላችንን ይቅር
እንደሚል አሁንም በአጽንኦት ይናገራል። በእነዚህ ጽንሰ ሀሳቦች
መካከል ተቃርኖ ወይም ውዝግብ ይመለከታሉ? ካልተመለከቱ ለምን?
ሮሜ 2፡15 ስለ ሕጉ ትእዛዝ በልባችን መጻፍ ያመለክታል። ይህ ምን
ማለት ነው? (ማቴ. 5: 17–28)
ለዛሬ ጥናት የቀረበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይመልከቱ። በአዲስ ኪዳን ዐሥርቱ ትእዛዛት (ወይም በተለይ ሰንበት) ተሽሯል በሚል ለሚነሣው ሙግት እንዴት መልስ ለመስጠት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ? በጥቅሶቹ ውስጥ ይህን ሀሳብ ሊደግፉ የሚችሉ ነጥቦች ካሉ፤ ስለ ሕጉ ዘላለማዊነት አስመልክቶ እንዴት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ?
የደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ፍጻሜ በተቃረበበትና ሕዝቡ ወደ ባቢሎን ምርኮ
በተወሰደበት ወቅት እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካይነት “አዲሱን ቃል
ኪዳን” አሳወቀ። ይህ አሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲገለጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ሆኖም
ዐሥሩ የሰሜናዊ እስራኤል መንግሥት ጎሳዎች ሊጠፉ ባለበት ወቅት (ከኤርምያስ
ዘመን መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ገደማ) የሌላ ቃል ኪዳን አሳብ እንደተናገረ ተጠቅሶ
ነበር። ይህ የሆነው በሆሴዕ ነበር (ሆሴ 2፡18-20)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሆሴ 2፡18-20። ጌታ በዚህ ቦታ ለሕዝቡ የሚለው-በኤር. 31፡31-34 ከተናገረው ጋር ያለውን ተመሳሳይነት ልብ
ይበሉ። ምን የተለመደ መግለጫ ጥቅም ላይ ውሏል? ስለ ቃል ኪዳኑ
መሠረታዊ ፍቺ እና ተፈጥሮ ምን ይላል?
እግዚአብሔር ለቃል ኪዳን ሕዝቦቹ ያለው ዕቅድ በተለያዩ ዘመናት በአመጻቸው
እና አለማመናቸው ሲሰናከል፤ ከታማኞቹ ጋር ያለው የቃል ኪዳን ታሪክ ወደ ፍጻሜ
አለመምጣቱን ለማወጅ ነቢያትን ይልክ ነበር። ሕዝቡ የቱንም ያህል ታማኝነት
የጎደለው፣ ከሃዲ፣ አመጸኛና የማይታዘዝ ሊሆን ቢችልም እንኳ፤ ነገር ግን ንስሐ
ለመግባት፣ ለመታዘዝና ተስፋዎቹን የራሳቸው ለማድረግ ፈቃደኞች እስከሆኑ ድረስ፤
ጌታ ከሁሉም ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እሺታውን በይፋ ያሳውቅ
ነበር።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ይመልከቱ። ምንም እንኳ በተለይ ስለ አዲሱ ቃል
ኪዳን ባይጠቅሱም፤ ከአዲሱ ቃል ኪዳን በስተጀርባ ያሉ መርኅዎችን
የሚያንጸባርቁ ምን ዓይነት ባህሪያት በውስጣቸው አሉ?
ሕዝ. 11:19________________________________________________________
ሕዝ. 18:31________________________________________________________
ሕዝ. 36:26________________________________________________________
“ ‘እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ’ ” (ኤር. 24፡7)።
“ ‘ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ’ ” (ሕዝ. 11፡
19)። “ ‘አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስም በውስጣችሁ አሳድራለሁ’ ”
(ሕዝ. 36፡26)። ደግሞም እንዲህ ይላል፡ “ ‘መንፈሴን በውስጣችሁ አሳድራለሁ’ ”
(ሕዝ. 36፡27)። ይህ የእግዚአብሔር ሥራ የሆነው አዲስ ቃል ኪዳን መሠረት ነው።
አንድ ሰው ወደ እርስዎ መጥቶ “አዲስ ልብ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፣
ሕጉ በልቤ ውስጥ እንዲጻፍ እፈልጋለሁ፣ ጌታን የሚያውቅ ልብ
እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ--ነገር ግን እንዴት እንደማገኘው አላውቅም”
ቢልዎት ምን ይሉታል?
“ ‘እርሱን ለማገልገል፣ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያቆራኙ መጻተኞች፣
የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣ እርሱንም በማምለክ፣ ሰንበትን ሳያረክሱ
የሚያከብሩትን ሁሉ፣ ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ
አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ። የሚቃጠል
መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣ በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤
ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።’ ” (ኢሳ. 56:6-7)
አዲሱ ቃል ኪዳን “ከእስራኤል ቤት” ጋር እንደሚከወን ኤርምያስ ይናገራል
(ኤር. 31፡33)።
አባባሉ--የቃል ኪዳኑን ተስፋዎች የሚቀበሉት አብርሃምን በደም
የሚዛመዱት የእርሱ ትውልድ አይሁዳውያን ብቻ ናቸው--የሚል ፍቺ አለው?
የለውም! አባባሉ በብሉይ ኪዳን ዘመን እንኳ ተቀባይነት አልነበረውም። የቃል
ኪዳን ተስፋዎቹ በአጠቃላይ ለዕብራውያን ሕዝቦች መሰጠታቸው እርግጥ ነው።
ሆኖም ማንንም በማግለል የተሰጡ ግን አልነበሩም። በተቃራኒው፤ ሁሉም አይሁዳዊ
ወይም አሕዛብ የተስፋ ቃሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘው የነበረ ቢሆንም፤ ነገር ግን
ወደ ቃል ኪዳኑ ለመግባት መስማማት ነበረባቸው።
ከላይ ከኢሳያያስ መጽሐፍ የተጠቀሱትን ጥቅሶች ያንብቡ። ጌታን ለማገልገል
ለሚፈልጉ ምን ዓይነት ሁኔታዎችን ያስቀምጣሉ? እግዚአብሔር እነርሱን
በጠየቃቸው እና ዛሬ እኛን በሚጠይቀን መካከል ልዩነት አለ? መልስዎን ያብራሩ።
ምንም እንኳ አዲሱ ቃል ኪዳን “የበለጠ” (የረቡዕን ጥናት ይመልከቱ) ተብሎ
ቢጠራም፤ በአሮጌው እና አዲሱ ቃል ኪዳን መሠረታዊ ባህሪያት ላይ ምንም ልዩነት
የለም። ደኅንነትን በተመሳሳይ የጸጋ መንገድ የሚያቀርበው ያው ራሱ እግዚአብሔር
ነው (ዘፀ. 34፡6፣ ሮሜ 3፡24)። አምላካዊውን የይቅርታ የተስፋ ቃል በእምነት
የራሱ የሚያደርግና የሚታዘዝ ሕዝብ እንዲኖረው የሚጠይቀው ያው እግዚአብሔር
ነው (ኤር. 31፡34፣ ዕብ. 8፡12)። አይሁድ ሆነ አሕዛብ--በእምነት ግንኙነት እርሱን
በሚከተሉ ሰዎች ልብ ውስጥ ሕጉን ለመጻፍ የሚፈልገው ያው እግዚአብሔር ነው
(ኤር. 31፡33፣ ዕብ. 8፡10)።
በአዲስ ኪዳን አይሁዳውያን ለጸጋው መመረጥ ምላሽ በመስጠት የሱስ ክርስቶስን
እና የእርሱን ወንጌል ተቀበሉ። ለተወሰነ ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልብ የነበሩት
“ልባቸው ከደነደነው” (ሮሜ 11፡7) በተቃራኒ “በጸጋ የተመረጡ ትሩፋን” (ሮሜ
11፡5) ነበሩ። በተመሳሳይ ቀደም ሲል አማኝ ያልነበሩ አሕዛብ፣ ከየትኛውም ወገን
ወይም ዘር ቢመጡም፤ ወንጌልን ተቀብለው በእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝቦች
መሃል ተተከሉ (ሮሜ 11፡13-24)። ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡
“በዚያን ዘመን ከክርስቶስ ተለይታችሁ፣ ከእስራኤል ወገንነት ርቃችሁ፣ ለኪዳኑም
ተስፋ ባዕዳን ሆናችሁ… አሁን ግን በክርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል” (አፌ.
2፡12-13)። ብሔር ወይም ዘር ሳይባል ለሁሉም አማኞች “ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን
መካከለኛ ነው” (ዕብ. 9፡15)።
ስለዚህ ጉዳይ ያስቡ፡ አንድ ሰው ከምድራዊው ቤተ መቅደስ አገልግሎት
የእንስሳት መሥዋዕት ሥርዓት ብቻ ሊያገኝ ከሚችለው መረዳት ይልቅ
ስለ ክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት እና በሰማይ ስለ እኛ እያከናወነ ስለሚገኘው
የሊቀ ካህንነት አገልግሎቱ ማወቁ የተሻለ የሚሆነው ለምንድን ነው?
የዕብራውያን መጽሐፍ በሰማያዊው መቅደስ አገልግሎት እየሰጠ ስለሚገኘው ሊቀ
ካህናችን የሱስ ከፍ ያለ አጽንኦት ይሰጣል። ስለ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ትኩረት
በመስጠት ስለ አዲሱ ኪዳን ግልጽ መግለጫ የሚያቀርበው የዕብራውያን መጽሐፍ
መሆኑ እሙን ነው። ይህ አጋጣሚ አይደለም። የክርስቶስ ሰማያዊ አገልግሎት
ከአዲሱ ቃል ኪዳን ተስፋዎች ጋር ውስብስብ በሆነ ሁኔታ የተሳሰረ ነው።
የብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮጌዎቹ ኪዳናዊ እውነቶች መማሪያ
ነበር። መሥዋዕትን እና ማማለድን ማዕከላዊ ያደረገ ነበር። እንስሳት ታርደው
ደማቸው በካህናት ምልጃ ይቀርብ ነበር። በእርግጥ እነዚህ ሁሉ በየሱስ ብቻ
ለሚገኘው ደኅንነት ምሣሌ ነበሩ። ከዚህ ውጪ በራሳቸው የሚያስገኙት አንዳችም
ደኅንነት አልነበረም።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዕብ. 10፡4። በእነዚህ እንስሳት ሞት መዳን የሌለው
ለምንድን ነው? የእንስሳ ሞት ደኅንነት ለማምጣት በቂ ያልሆነው
ለምንድን ነው?
እነዚህ ሁሉ መሥዋዕቶች እና ያጀቧቸው ካህናዊ ምልጃዎች በክርስቶስ ፍጻሜ
አገኙ። የሱስ የአዲሱ ቃል ኪዳን ደም የጸናበት መሥዋዕት ሆነ። የክርስቶስ ደም
የሲናን ቃል ኪዳን እና የመሥዋዕት ሥርዓት “አሮጌ” ወይም የማይጸና በማድረግ
አዲሱን ቃል ኪዳን አጸደቀ። እውነተኛው መሥዋዕት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እውን
ሆነ (ዕብ. 9፡26)። ክርስቶስ አንዴ ከሞተ በኋላ ምንም ዓይነት የእንስሳ መሥዋዕት
ማቅረብ አላስፈለገም ነበር። ምድራዊው የመቅደሱ አገልግሎቶች አገልግሎታቸውን
አጠናቀው ነበር።
የሱስ በሞተ ጊዜ በምድራዊው መቅደስ ውስጥ የነበረው መጋረጃ
እንዴት እንደተቀደደ የሚናገረውን ይህን ጥቅስ ያንብቡ፡ ማቴ. 27፡
51። ክስተቱ ምድራዊው መቅደስ ለምን እንደተተወ እንድናስተውል
እንዴት ይረዳናል?
በምድራዊው መቅደስ ስለ ሕዝቡ ምልጃና መሥዋዕት የሚያቀርቡት ሌዋውያን
ካህናዊ አገልግሎት ከእንስሳ መሥዋዕት ሥርዓት ጋር የተሳሰረ መሆኑ እሙን ነው።
የመሥዋዕት ሥርዓቱ አንዴ ካበቃ፤ የእነርሱ አገልግሎት አስፈላጊነትም እንዲሁ
ያከትማል። ማንኛውም ነገር አሁን በሰማያዊው መቅደስ በገዛ ደሙ እያገለገለን ባለው
የሱስ ፍጻሜ አግኝቷል (ዕብ. 8፡1-5)። ዕብራውያን የራሱን ደም በማፍሰስ (ዕብ. 9፡
12) በሊቀ ካህንነት ስለ እኛ በሰማይ እየማለደ ላለው ክርስቶስ ከፍ ያለ አጽንኦት
ይሰጣሉ። ይህ ያለንበት--የአዲሱ ቃል ኪዳን ተስፋ እና የቃል ኪዳን መሠረት ነው።
የሱስ በአሁኑ ወቅት እንኳ ስለ እርስዎ በሰማያዊው ቤተ መቅደስ
በደሙ እያገለገለ መሆኑን መረዳትዎ ምን ዓይነት ስሜት ይፈጥርቦታል?
ደኅንነትን አስመልክቶ ምን ያህል በራስ መተማመን እና ማረጋገጫ
ይሰጦታል?
“ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ኅብስቱን በመብላትና
ጽዋውን በመጠጣት አዳኛቸው ለመሆኑ ቃል ገባላቸው። እርሱን የሚቀበሉ ሁሉ
የእግዚአብሔር ልጆችና ከእርሱ ጋር ወራሾች የሚሆበትን አዲስ ኪዳን ሰጣቸው።
በዚህ ቃል ኪዳን መሠረት ለዚህኛውም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ከሰማይ ሊወርድ
የሚችል በረከት ሁሉ ለእነርሱ ተሰጠ። ይህ ቃል ኪዳን የሚጸድቀው በክርስቶስ ደም
ነው። ደቀ መዛሙርቱ በኃጢአት የወደቀው ሰብአዊ ቤተሰብ አባል እንደመሆናቸው
ለእያንዳንዳቸው የተከፈለውን ከፍኛ መሥዋዕት በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ዘወትር
ማስታወስ ነበረባቸው።” የዘመናት ምኞት፡ ገጽ 693።
“ይህ የሰላም ቃል ኪዳን እጅግ አስደናቂ ባህሪ አለው፤ በደለኛው የሚጸጸትና
ከኃጢአት መንገዱ የሚመለስ ከሆነ፤ የተገለጸለት ይቅርታና ምህረት እጅግ
የተትረፈረፈ ነው። መንፈስ ቅዱስ--በአምላካዊው ርኅራኄ ይቅርታ እንደተገኘ መዳን
አድርጎ ወንጌልን ይገልጸዋል። ጌታ ንስሐ ለሚገቡት እንዲህ ይላል፡ ‘በደላቸውን
ይቅር እላለሁ፤ ኃጢአታቸውን ከእንግዲህ አላስብም’ (ዕብ. 8፡12)። እግዚአብሔር
ለኃጢአተኛው ምህረት ለማሳየት ፍትሐዊ አሠራሩን ይተዋል? አይተውም።
እግዚአብሔር በደለኛውን ሳይቀጣ በመተው ሕጉን አለማክበር አይችልም።
በአዲሱ ኪዳን መሠረት ሕይወት በፍጹም መታዘዝ ሁኔታ ውስጥ ልትገኝ ይገባል።
ኃጢአተኛው ንስሐ ገብቶ ኃጢአቱን የሚናዘዝ ከሆነ ይቅርታ ያገኛል። በበደለኛው
ምትክ በተከፈለው የክርስቶስ መሥዋዕትነት ይቅርታ አግኝቷል። በእያንዳንዱ ንስሐ
በሚገባ አማኝ ኃጢአተኛ ላይ ሕጉ የሚጠይቀውን በሙሉ ክርስቶስ ከፍሏል።”—
Ellen G. White, God’s Amazing Grace, p. 138.
1.በድንጋይ ጽላቶች ላይ የተቀረጸን ሕግ በተቃራኒው በልብ ላይ
የመፃፉ ጥቅም ምንድነው? የትኛውን መርሳት ይቀላል--በድንጋይ ላይ
የተጻፈውን ወይስ በልብ ውስጥ የተጻፈውን ሕግ?
2.ከሰው ልጅ ውድቀት አንስቶ ደኅንነት የሚገኘው በየሱስ ብቻ ነው-ምንም እንኳ ያ እውነት የተገለጠበት መንገድ ከዘመን ዘመን የተለያየ
ቢሆንም። ቃል ኪዳኖቹ በተመሳሳይ መንገድ አይሠሩም?
3.ከላይ በሁለተኛው አንቀጽ የቀረበውን የኤለን ኋይት ጽሑፍ
ይመልከቱ። ኪዳናዊ ግንኙነቱ የሚጠይቀውን አስመልክቶ “ፍጹም
መታዘዝ” ስትል ምን ማለቷ ነው? “ፍጹም መታዘዝ” ያስገኘልን
ብቸኛ የሆነው እርሱ ማን ነው? ያ መታዘዝ ሕጉ ከእኛ የሚጠይቀውን
እንዴት ይመልሳል?
ማጠቃለያ፡ የመቤዠት ዕቅድ ታላቅና ይበልጥ የተሟላ ሆኖ በተሻለ በአዲሱ
ቃል ኪዳን ተገልጧል። እነሆ እኛ በልባችን ውስጥ ለተጻፈው ሕግ በመታዘዝ
ራሱን የሚገልጥ እምነት ተካፋዮች ነን።