የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘኁ. 11:1–33፣ ዘኁ. 12:1–13፣ ዘኁ. 13:27–33፣ ዘኁ. 14:1–23፣ 1ቆሮ. 10:1–11፣ ዘኁ. 14:39–45።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ” (1ቆሮ. 10፡11)።
ባ
ለፉት መቶ ዓመታት በአንድ አካባቢ ርዕደ መሬት ከመድረሱ አስቀድሞ
ውሾች እና ሌሎች የቤት እንስሳት እንግዳ የሆነ የመቅበዝበዝ ባህሪ ስለ
ማሳየታቸው ብዙ ሰዎች ከሰጡት ምስክርነት ለመረዳት ተችሏል።
ከሁለተኛው የርዕደ መሬት ሞገድ አስቀድሞ የሚመጣውን የእንቅጥቅጥ
ሞገድ ግፊት እንስሳት ማወቅ መቻላቸውን የሳይንስ ሊቃውንት ደርሰውበታል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ከመጀመሩ በፊት የእንስሳት ግራ መጋባት ወይም
መቅበዝበዝ የተዘገበበትን ምክንያት ምናልባት ይህ ሊገልጽ ይችላል።
እንደ ዝሆኖች ያሉ አንዳንድ እንስሳት የሰው ልጆች በጭራሽ ሊገነዘቧቸው
የማይችሏቸውን የቅድመ ርዕደ መሬት ክፍል የሆኑ ዝቅተኛ፣ ድግግሞሽ
የድምፅ ሞገዶች እና ንዝረቶች ለይተው መገንዘብ ይችላሉ።
በጎርጎሮሳውያኑ ወርሃ ነሐሴ 23/2011 ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢን ከመታው
የ5.8 መጠን ርዕደ መሬት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ የስሚዝሶኒያን ተቋም
በሆነው ብሔራዊ መካነ እንስሳት ውስጥ አንዳንድ እንስሳት እንግዳ ባህሪ
ማሳየት ጀምረው ነበር። ከነዚህም መካከል ርዕደ መሬቱ ከመጀመሩ ጥቂት
ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ጦጣ መሰሎቹ ሊሙሮች/እንስሳት/ ድምጻቸውን ከፍ
አድርገው መጣራት ጀምረው እንደ ነበር ተዘግቧል።
በዚህ ሳምንት ጥናታችን እንደ ርዕደ መሬት በመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች
ሳይሆን መሠረታዊ ለሆነው የሰዎች በኃጢአት መውደቅ--ክርስቶስ በእምነትና
በመታዘዝ ወደ እርሱ ለሚመጡ በሰጠው ዕረፍት ያላረፉ፣ እንግዳ ሰብዓዊ
የመቅበዝበዝ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።
እስራኤላውያን ሲናን ለቀው ወደ ከነዓን ሲጓዙ የመቁነጥነጥ፣ የመቅበዝበዝና የሐዘን ስሜት ሳያሳዩ እንዳልቀሩ ይታመናል። ከግብፅ ከወጡ ከአንድ ዓመት በላይ አልፏቸዋል (ዘኁ. 1፡1)። ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ተዘጋጅተው ነበር። ተቆጥረዋል፣ ደግሞም ተደራጅተዋል። አስደናቂ የሆኑ የመለኮታዊ ሞገስ ማሳያዎችንና የአምላካዊውን ሕልዎት ግልጽ ምልክቶች ተመልክተዋል። ሆኖም ከሲና መነሳታቸውን ተከትሎ ብዙም ሳይቆዩ ገና በመጀመሪያው ስፍራ ሲያማርሩ ተገኙ ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘኁ. 11፡1-15። እስራኤላውያን ለምን አማረሩ?
እስራኤላውያን የግብፅን ሥጋ፣ ዱባ፣ ሀብሃብ፣ ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት
ተመኙ። “ ‘ምነው የምንበላው ሥጋ ባገኘን ኖሮ! በግብፅ ያለምንም ዋጋ የበላነው
ዓሣ እንዲሁም ዱባው፣ በጢኹ፣ ኩራቱ፣ ነጭ ሽንኩርቱ ትዝ ይለናል። አሁን ግን
የምግብ ፍላጎታችን ጠፍቷል፤ ከዚህ መና በስተቀር የምናየው የለም” (ዘኁ. 11፡
4-6)። እነዚህ ሕዝቦች ምግቡን አስታውሰው ሊታመን የማይችለውን አስከፊ
የባርነት ቀንበር መርሳታቸው--በለየለት የተሳሳተ የመምረጥ ትውስታ ሳይሰቃዩ
እንዳልቀሩ ያሳያል (ከዘፀ. ምዕ. 1 ጋር ያስተያዩ)።
የእግዚአብሔርን መና ከአንድ ዓመት በላይ እየተመገቡ ቢዘልቁም ዕረፍት
የማጣትና የመቅበዝበዝ ስሜት ስለነበራቸው ሌላ ነገር ፈለጉ። የሚቅበዘበዝን
ሕዝብ ለመምራት መሞከር ቀላል አይደለም። ሆኖም ሙሴ ፊቱን ወደ ማን ማዞር
እንዳለበት ያውቅ ነበር። “ ‘እንዲህ ያለውን መከራ በባሪያህ ላይ ለምን አመጣህ?
የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም የጫንክብኝስ ምን አስቀይሜህ ነው?’ ” (ዘኁ. 11፡11)
እግዚአብሔር ለቅሬታዎቹ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር? ዘኁ.
11፡16-33
ዕረፍት የለሽ ስሜት ሲሰማን እግዚአብሔር ፍላጎታችንን እንዳልሰማ
አይሆንም። የእስራኤላውያንን የሥጋ አምሮት ለማርካት ድርጭት ሰጣቸው።
ሆኖም እስራኤላውያን በእርግጥ የፈለጉት ሥጋ አልነበረም። ደስተኛ ሳንሆን፣
ስንቁነጠነጥና ስንበሳጭ--ያ የሚያበሳጨን ነገር የጉዳዩ አቀጣጣይ እንጂ
የግጭቱ መንስኤ አይደለም። የምንታገለው የግንኙነቶቻችንን መሰረት
የሚያቃውስ ጥልቅ ጉድለት በመኖሩ ነው። በየትኛውም ሁኔታ ላይ ልንገኝ
ብንችል እንኳ፣ እኛ ሁላችን ልንጠነቀቅበት በሚገባው፣ በአምላካዊው ምሪት
ላይ እስራኤል አመጸ።
ያሳለፍነው ዘመን በተጨባጭ ከነበረው ገጽታ ይልቅ የተሻለ
አድርገን ማስታወስ የሚቀለን ለምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘኁ. 12፡1-3። የማሪያም እና አሮን ቅሬታ መንስኤ ምን ነበር?
ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት በማግባቱ ማሪያም እና አሮን ደስተኞች አልነበሩም።
ኢትዮጵያዊቷ ሲፓራ ምድያማዊት ነበረች (ዘፀ. 3፡1)። በእስራኤል “ልሂቃን”
መሀል እንኳ የባህሪያችን ውድቀት ደስ በማይል መልኩ ተገልጦ እንደ ነበር
እናያለን።
ነገር ግን ይህ ሰበብ መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች በግልጽ ያሳያሉ።
የቅሬታቸው ዋንኛ ትኩረት የትንቢት ስጦታ ነበር። እግዚአብሔር የሙሴን
አስተዳደራዊ ሸክም ለማገዝ የሚረዱ ሰባ የእስራኤል ሽማግሌዎችን እንዲሾም
እንደነገረው በቀደመው ምዕራፍ ተመልክቷል (ዘኁ. 11፡16-17፣ 24-25)። አሮን
እና ማርያምም እንዲሁ ቁልፍ የአመራር ሚናዎችን ይጫወቱ ነበር (ዘፀ. 4፡1315፣ ሚክ. 6:4)። አሁን ግን በአዲሱ አመራር እንቅስቃሴ ስጋት ስለገባቸው፡
“ ‘ለመሆኑ እግዚአብሔር የተናገረው በሙሴ አማካይነት ብቻ ነውን? በእኛስ
አልተናገረም?’ ተበባሉ” (ዘኁ. 12፡2)።
እግዚአብሔር ለዚህ ቅሬታ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር? ዘኁ.
12፡4-13። እርሱ እንዲህ ያለውን ቆራጥ ውሳኔ ያሳልፋል ብለው
እንዲያስቡ የሚያደርጎት ምንድን ነው?
የእግዚአብሔር ምላሽ ፈጣን በመሆኑ ለትርጉም ክፍተት አልተወም።
ትንቢታዊ ስጦታ የበለጠ ሥልጣን ላይ የሚያወጣ መሣሪያ አይደለም። ሙሴ
በእግዚአብሔር ላይ ምን ያህል መመካት እንዳለበት በመማሩ የአመራርን
ጥበብ ጥሩ አድርጎ መላበስ ቻለ።
ማርያም ከአሮን በፊት በቁ. 1 መጠቀሷ በሙሴ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት
አነሳሽ ሳትሆን እንዳልቀረች ያሳያል። በዚህ ወቅት አሮን የእስራኤል ሊቀ
ካህን ሆኖ ያገለግል ነበር። እርሱ በለምጽ ቢመታ ኖሮ ወደ መገናኛው ድንኳን
መግባትም ሆነ ስለ ሕዝቡ ማገልገል ባልቻለ ነበረ። እግዚአብሔር ማርያምን
ጊዜያዊ በሆነ ለምጽ በመምታት መቅጣቱ፤ በሁለቱም ያለመደሰቱን በግልጽ
የሚያሳውቅ እና ይህ ቤተሰብ የሚያስፈልገውን የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ
የሚረዳ ነበር።
አሮን ስለ እርሷ ያቀረበው ተማጽኖ እርሱም የዚያ አካል
እንደነበር ያሳያል (ዘኁ. 12፡11)። እናም አሁን በትችት እና በመቅበዝበዝ ፋንታ
አሮን ስለ ማርያም ሲለምን--ሙሴም ስለ እርሷ ሲማልድ እናያለን (ዘኁ. 12፡
11-13)። ይህ እንግዲህ እግዚአብሔር በሕዝቡ መሃል ማየት የሚሻው ጠባይ
ነው። ጸሎትና ልመና የሚሰማው አምላክ እነሆ ማርያምን ፈወሳት።
ምንም እንኳ በቤተክርስቲያን አመራር ላይ ትችት መሰንዘር
ሁሌም ቀላል ቢሆንም፣ በየትኛውም ደረጃ ቢሆን ከማማረር
ይልቅ--ከእነሱ ጋር ባንስማማም እንኳ ብንማልድላቸው ቤተ
ክርስቲያናችንም ሆነች የራሳችን መንፈሳዊ ሕይወት ምን ያህል
የተሻለ ይሆን ነበር?
ታሪኩ በአዎንታዊ ማስታወሻ ይጀምራል። እስራኤላውያን በመጨረሻ ከነዓን ድንበር ደርሰው ምድሪቱን የሚሰልሉ 12 ሰዎች ላኩ። ሰላዮቹ ያቀረቡት የአሰሳ ውጤት ፍጹም ያልተለመደ ሆነ። የሰላዮቹን ዘገባ ያንብቡ፡ ዘኁ. 13፡27-33። የእስራኤላውያን ግምት ያረፈው በየትኛው ነጥብ ላይ ነበር?
የካሌብ ጣልቃ ገብነት ቢኖርም የጥርጣሬና አለማመን ድምፆች ግን አሸነፉ።
እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቃል የገባላቸውን ድል ለመንሳት ቁርጠኝነት
ጎደላቸው። በድል አድራጊነት ጉሮ ወሸባዬ ከማለት ይልቅ ቅብዝብዙ ልባቸው
ማንባትና ማጉረምረም መረጠ።
ልባችን ውስጥ ዕረፍት ከሌለ በእምነት ለመራመድ የምንታገል እንሆናለን።
ለነገሩ መቅበዝበዝ ስሜታችንን ብቻ አይጎዳም። እጅግ አነስተኛ በሆነ ዕረፍት
(ዕንቅልፍ ማጣትን ጨምሮ) እና ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ሱስ መቅበጥበጥ፣
ደስተኛ አለመሆን በሚያስከትሉ መጥፎ ምርጫዎች መካከል የመንስኤ እና
ውጤት ቀጥተኛ ተዛምዶ አለ ሲሉ የመስኩ ጠበብት ይናገራሉ።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘኁ. 14፡1-10። በቀጣይ ምን ተከሰተ?
ነገሮች ከቀድሞ ይልቅ የከፋ ገጽታ ተላበሱ። “ ‘ብቻ በእግዚአብሔር ላይ
አታምጹ’ ” (ዘኁ. 14፡9) ሲል የተደመጠው አሳዛኙ የካሌብ ጥሪ፤ የሚታዘዘው
ሳያገኝ መቅረቱ ሳያንስ መላው ማኅበር አመራሩን በድንጋይ ለመወግር ተዘጋጀ።
መቅበዝበዝ ወደ አመጽ፤ አመጽ ደግሞ ውሎ አድሮ ወደ ሞት ይመራል።
“እምነት የለሾቹ ሰላዮች ድምፆቻቸውን ከፍ አድርገው ካሌብንና ኢያሱን
ማውገዝ ጀመሩ። ጩኸታቸውና ልፍለፋቸው እየጨመረ በመሄድ እነርሱን
በድንጋይ ወደ መውገር ተለወጠ።
በደመነፍስ የሚንቀሳቀሰው ሕዝብ
የሚወግሩበትን ድንጋይ ይዘው እንደ እብድ እየለፈለፉ ወደ ፊት አመሩ። ነገር
ግን የጨበጧቸው ድንጋዮች በድንገት ከእጆቻቸው ሾልከው ሲወድቁ ጸጥታ
በላያቸው ሰፈነ። እግዚአብሔር የግድያ እቅዳቸውን ለማክሸፍ ጣልቃ ገብቶ
ነበር። እንደሚንበለበል እሳት የነበረው
የእግዚአብሔር ህልዎት ክብር መገናኛ ድንኳኑን አበራው። መላው ሕዝብ የጌታን
ምልክት ተመለከተ። ከዚህ በኋላ ማንም በተቃውሞ ለመግፋት አልደፈረም።
ይህን እርኩስ ዘገባ ያቀረቡ ሰላዮች በፍርሃት ተሞልተው ጉልበታቸው ይብረከረክ
ጀመር። ከዚያም በተቆራረጠ ትንፋሽ ወደየ ድንኳኖቻቸው ተፈተለኩ።”
የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት፡ ገጽ 444
በዚህን ጊዜ ጌታ ክብሩን በይፋ ገለጠ። በዘኁ. ምዕ. 14 የቀረበውን ታሪክ
ስናነብ የተጋጋለው ትዕይንት ቆፈን ከያዘው(ከቀዘቀዘ) በኋላ እግዚአብሔር
ከሙሴ ጋር ያደረገውን ምስጢራዊ ውይይት ለመስማት እንሞክራለን። ምንም
እንኳ ድንጋዮቹ ለሙሴ፣ ለካሌብ እና ለኢያሱ ቢታሰቡም፤ የአመጻው መጨረሻ
የሚያነጣጥረው በራሱ በእግዚአብሔር ላይ እንደሆነ ጌታ ያውቅ ነበር።
በዚህ የአመጽ ድርጊት መሀል እግዚአብሔር ለሙሴ ምን ዓይነት ዕድል እየሰጠው ነው? ዘኁ. 14፡11-12።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አጥፍቶ ሙሴን ሙሉ ለሙሉ አዲስ ለሆነ ሕዝብ አባት አድርጎ ሊያስነሣው ዕድል እየሰጠው ነበር። ሙሴ በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔርም ላይ ለተፈጸመው ለዚህ ግልጽ የአመጻ ተግባር የሰጠው ምላሽ ምን ነበር--ዘኁ. 14፡ 13-19?
ይህ እውነተኛውን የእግዚአብሔር ሰው ማየት የምንችልበት ወቅት ነው።
የሙሴ መልስ ከ1,400 ዓመታት በኋላ በደቀ መዛሙርቱ መከራና ሥቃይ
ወቅት አማላጁ ስለ እነርሱ የሚጸልየውን ጸሎት አስቀድሞ ያመላከተ ነበር
(ዮሐ. 17)። እርግጥ ነው፤ አያሌ የሥነ መለኮት ምሑራንና የመጽሐፍ ቅዱስ
ተማሪዎች ሙሴ በዚህ ስፍራ ያደረገውን ነገር ክርስቶስ ለእኛ ካደረገልን ምሳሌ
አኳያ ይመለከቱታል። የእነርሱም ሆነ የእኛ የጥፋተኝነት ስሜት ጥያቄ ውስጥ
የሚገባ አይደለም። “ ‘እንደ ፍቅርህ ታላቅነት መጠን’ ” (ዘኁ. 14፡19) እባክህ
የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል ሲል ሙሴ ስለ ሕዝቡ ይማልዳል። ጌታ
በሙሴ ምልጃ የተነሣ ይቅር እንዳለ ሁሉ፤ እኛንም በየሱስ ሞት፣ ትንሣኤና
ምልጃ ምክንያት ይቅር ይለናል።
“‘ከግብፅ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው ሁሉ
እንደ ፍቅርህ ታላቅነት መጠን እባክህ አሁንም የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር
በል።’ ” (ዘኁ. 14፡19)። ጸጋ በዋናነት አመጻንና መቅበዝበዝን ይዋጋል።
ይቅርታ ደግሞ አዲስ ጅማሬ ይሰጣል።
ሆኖም የሚያስከፍሉት ዋጋዎች ይኖራሉ። ጸጋ ፈጽሞ ርካሽ ሊሆን አይችልም።
ምንም እንኳ ይቅር ቢባሉም፤ አመጻቸው ባስከተለው መዘዝ ያ ትውልድ ወደ
ተስፋይቱ ምድር አልገባም (ዘኁ. 14፡20-23)።
አዎ፤ እግዚአብሔር ለተጨማሪ 38 ዓመታት በምድረ በዳ ደግፎ ያቆያቸዋል።
ይመግባቸዋል። በመገናኛ ድንኳኑ ሆኖ ያናግራቸዋል። በምድረ በዳ ከጎናቸው
ይሆናል። ነገር ግን እነርሱ ይሞቱና ተተኪው አዲስ ትውልድ በተስፋይቱ
ምድር ዕረፍት ያገኛል።
ላይ ላዩን ሲያዩት ፍርድ ቢመስልም፤ ነገር ግን እውነተኛ ጸጋ ነው። ይህ
ትውልድ በእግዚአብሔር ላይ መታመንን ሳይማር ኃያል የሆነውን የከነዓንን
ከተማ ግዛቶች ድል ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? እነርሱ ራሳቸው
በጨለማ ውስጥ እየተደናበሩ በየትኛው ስሌት ለአሕዛብ ብርሃን መሆን
ይችላሉ?
ይቅር የተባለ ኃጢአት ሊያስከትል ስለሚችለው መዘዝ ያገኙት
ብርቱ ትምህርት ምን ይመስላል?
በምድረ በዳ በተንከራተቱ እስራኤላውያን እና ከየሱስ ዳግም ምጽአት በፊት በሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ምን ዓይነት መመሳሰል ያያሉ? (1ቆሮ. 10፡1-11)
የእግዚአብሔር ሕዝቦች የተስፋይቱን ምድር ፍለጋ ለዘመናት በምድረ በዳ
ሲንከራተቱ ኖረዋል። ይህ ምድረ በዳ ብዙ ገጾች አሉት። በአሁኑ ሰዓት-የሚደመጠው የመገናኛ ብዙሃን የወሬ ጋጋታ፣ የማያቋርጥ የበይነ መረብ (ስልክ)
የገቢ መልእክት ጲጵ ድምፆች እንዲሁም የሚያደነቁር የመዝናኛ ኢንዱስትሪ
ጩኸት--ፈጽሞ ማለቂያ የሌለው ይመስላል። የብልግና ፊልሞችንና ምስሎችን
እንደ ችግራችን መልስ፣ እንደ ፍቅር የማስታወቂያ ቁሳቁስ ለመሸጥ ይሞክራል።
በመጠኑም ቢሆን ብቁ፣ ወጣት፣ ሀብታም እና መልካም ቁመና ያለን ከሆን-እነዚህ ነገሮች ለችግሮቻችን መፍትሔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተደርጎ ይታሰባል።
እንደ እስራኤላውያን ሁሉ እኛም ሰላም ለማግኘት በምናደርገው አሰሳ
ዕረፍት አልባዎች ነን። የሚገርመው ብዙውን ጊዜ ፍለጋውን የምናደርገው
በተሳሳተ ስፍራ ነው።
እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ፍርድ ምላሽ የሰጡበት እንዴት
ነበር--ዘኁ. 14፡39-1-45?
እስራኤላውያን ለመለኮታዊው ፍርድ የሰጡት ምላሽ ያው የተለመደው ዓይነት
ነው። “ኃጢአት ሠርተናል” አሉ “ ‘እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጠን ስፍራ
እንወጣለን’ ” (ዘኁ. 14፡40)።
የግማሽ ልብ ቁርጠኝነት ደካማ ሆኖ እንደ ተዘጋጀ ክትባት--አይሠራም።
አንድ ህጻን በተወለደ በ24 ሰዓታት ውስጥ የሄፕታይተስ ቢ ክትባት መውሰድ
አለበት ሲሉ ሐኪሞች ይመክራሉ። ይህ መልካም ጅማሮ ነው። ሆኖም ያንን
የመጀመሪያ ክትባት ተከትሎ በትክክለኛው ጊዜ እና በትክክለኛው መጠን
የሚወሰዱ ሁለት ወይም ሦስት ክትባቶች ካልተሰጡት ህጻኑ የሄፕታይተስ ቢ
መከላከያ በሰውነቱ ውስጥ ሊያበጅ አይችልም።
በዘኁ. 14 የመጨረሻ ቁጥሮች እንደ ተዘገበው እስራኤላውያን በስሜት
ተገፋፍተው ብቻ ለውጊያ ወጡ። እግዚአብሔር በአዲስ መልክ የሰጣቸውን
መመሪያዎች ለመቀበል ፈቃኛ ባለመሆናቸው የቃል ኪዳኑን ታቦት ሳይዙ ወይም
የሙሴ አመራር ሳይኖራቸው በግትርነት ጥቃት ለመሰንዘር በመውጣታቸው
ሞት እና ተስፋ መቁረጥ ደረሰባቸው።
አጉል ድፍረት ዋጋ ያስከፍላል። አጉል ድፍረት ወደ ሞት ይመራል። ብዙውን
ጊዜ የአጉል ድፍረት ጉልበት ፍርሃት ነው። አንድ የሚያስፈራን ነገር መኖሩን
ተከትሎ ኋላ ላይ የምንቆጭበትን ውሳኔ እንወስናለን።
በእምነት እንዲሁም በአጉል ድፍረት ርምጃ የወሰዱባቸውን
ጊዜያቶች ያስቡ። በሁለቱ መካከል ምን ዓይነት ወሳኝ ልዩነቶች
ነበሩ?
“ምንም እንኳ ለኃጢአተኛው ባህሪያቸው ከልብ የመነጨ
ንስሐ የገቡ ቢመስሉም፤ ነገር ግን ሐዘን የተሰማቸው የተከተሉት ክፉ አካሄድ
ባስከተለው መራራ ውጤት እንጂ ላሳዩት ምስጋና ቢስነትና የአመጸኝነት ስሜት
አልነበረም። ጌታ በትዕዛዙ እንደ ጸና ሲመለከቱ ያ የእኔነት ስሜት ዳግመኛ
አቆጠቆጠና ወደ ምድረ በዳው አንመለስም አሉ። ሕዝቡ ከልቡ ስለመመለሱ
ከጠላቶቻቸው ምድር እንዲወጡ በሰጣቸው ትእዛዝ እግዚአብሔር ፈተናቸው
--እውነተኛ አለመሆኑንም አረጋገጠ። ግልብ ስሜታቸው እንዲቆጣጠራቸው
መፍቀዳቸውና እግዚአብሔርን እንዲታዘዙ የተማጸኗቸውን ሰላዮች
ለመግደል ማሰባቸው ታላቅ ኃጢአት መሆኑን ተገንዝበዋል። የፈጸሙት
ስህተት ሊያስከትል የሚችለው ውጤት አደገኛ እንደሚሆን ከተገነዘቡ በኋላ
ግን ፍርሐት አደረባቸው። ልባቸው ባለመለወጡ ተመሳሳይ አመጻ ለማድረግ
አጋጣሚና ምክንያት ብቻ ይፈልጉ ነበር።
ሙሴ ከእግዚአብሔር በተሰጠው
ሥልጣን ወደ ምድረ በዳው ተመልሰው እንዲሄዱ ባዘዛቸው ወቅት ይህ ሁኔታ
ገሃድ ወጣ።” የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት፡ ገጽ446
“እምነት በራስ ከመተማመን ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በራስ
ከመተማመን ነጸ መሆን የሚችል እውነተኛ እምነት ያለው ሰው ብቻ ነው። በራስ
መተማመንን ሰይጣን የእውነተኛ እምነት ማሳሳቻ አድርጎ ይጠቀምበታል።
እምነት ያለው ሰው በእግዚአብሔር ተስፋ በመተማመን በታዛዥነት ፍሬ
ያፈራል። በራሱ የሚተማመንም እንደዚሁ በተስፋ ይተማመናል። ነገር
ግን ሰይጣን እንዳደረገው ሁሉ ተስፋን ለሚሠራው ኃጢአት ምክንያት
መፈለጊያ ያደርገዋል። እምነት የመጀመሪያ ወላጆቻችንን በእግዚአብሔር
ፍቅር እንዲተማመኑና ትእዛዙን እንዲያከብሩ ሊያደርጋቸው በተገባ ነበር።
የእግዚአብሔር ፍቅር ከኃጢአት ያድነናል ብለው በራሳቸው በመተማመን
ሕጉን ተላለፉ። እምነት ያለው ሰው ምሕረት ለማግኘት የሚያስፈልጉት
ሁኔታዎች ሳይመቻቹ ከእግዚአብሔር ልዩ አስተያየት አይጠብቅም። እውነተኛ
እምነት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሚገኙ ተስፋዎችና ችሮታዎች ላይ
የተመሠረተ ነው።” የዘመናት ምኞት ገጽ 112።
፡
1.በእምነት እና በአጉል ድፍረት መካከል ባሉ ልዩነቶች ዙሪያ
ተወያዩ። የከነዓንን ምድር ድል አድርጎ መያዝ መጀመሪያ በእምነት
እንደሚተገበር ድርጊት፤ ኋላ ላይ፣ እስራኤላውያን ጥቃት ሲሰነዝሩ
ግን እንደ አጉል ድፍረት የታየው ለምንድን ነው? በእምነት እና
በአጉል ድፍረት መካከል ባለው ልዩነት፤ አነሳሽ ምክንያቶች እና
ሁኔታዎች ትልቅ ሚና የሚጫወቱት እንዴት ነው?
2.ኃጢአት ይቅር ሊባል ቢችልም፤ ብዙውን ጊዜ ይኸው ኃጢአት
ካስከተለው መዘዝ ጋር መኖር የግድ ሊሆን ይችላል በሚለው
ተጨባጭ እውነታ ዙሪያ ምልከታ ያድርጉ። መተላፋቸው ይቀር
መባሉን ቢያውቁም ነገር ግን አሁንም ከአሉታዊ ተጽእኖ ያልወጡ
ወገኖችን እንዴት መርዳት ይችላሉ?