
የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብባችሁ ለሰንበት ተዘጋጁ። ዕብ. 12፡18-29፤ ዘጸ. 32፡32፣ ዳን. 7፡9-10፤ 13-22፤ ሐጌ 2፡6-9፤ 20-22፤ መዝ. 15፡5፤ መዝ. 16፡ 8፤ ዕብ. 13፡15-16።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ” (ዕብ. 12፡28)
የ
ዚህ ሳምንት ጥቅሳችን የሆነው ዕብራውያን 12፡18-29 መልዕክቱ ጡዘት
ላይ የሚደርስበት ሲሆን የመጀመሪያውን ሀሳብ ማለትም እግዚአብሔር
በልጁ በኩል ለኛ ስለመናገሩ በመግለፅ ለእርሱ ተገቢውን ትኩረት
ልንቸር እንደሚገባን ይነግረናል (ዕብ. 1፡1-2፤ ዕብ. 12፡ 25)። በዕብራውያን 12፡
22-24 ላይ ስለ ኢየሱስ የተገለጸው ልዩ ልዩ ሀሳቦችን አጠቃሎ ያስቀመጠበት
ሲሆን ኢየሱስ የአዲሱ ኪዳን መካከለኛና ደሙም ለአማኞች ድነትን የሚያመጣ
ነው። ለኛ የቆመው የእርሱ ንጉሳዊና ካህናዊ አገልግሎት ላልወደቁት ሰማያዊ
ፍጥረታት ደስታ ምክንያት ነው። በስተመጨረሻም ዕብራውያን 12፡25-29
የመጨረሻውና ጡዘት ላይ የደረሰውን ሃሳብ ያነሳል፡- የእግዚአብሔር ፍርድ
እየመጣች ነው። ፍርዱም በጠላቶቹ ላይ ጥፋትን ለህዝቡ ግን ፅድቅንና
መንግስትን ያመጣል (ዕብ. 12፡28-29)።
የመጨረሻው ሀሳብ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተቀዳጀው ድል ፋይዳ
እንደገና በማረጋገጥ አማኞች በኢየሱስ ድል ውስጥ እንዲገቡ ይመራቸዋል።
ጳውሎስ ከዳንኤል 7 ላይ ያለውን ምስል ለአንባቢያን በማስታወስ ኢየሱስ
ከእግዚአብሔርን መንግስትና ፍርድን እንደተቀበለ ይነግረናል (ዳን. 7፡9-14)፤
ይህንን መንግስትም ከአማኞቹ “ከልዑሉ ቅዱሳን” ጋር ይጋራል (ዳን. 7፡18)
ለዘላለምም ይኖሩበታል።
የዚህ ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለመጋቢት 10 ሰንበት ይዘጋጁ፤
ዕብ. 12፡22-24 ያንብቡ፤ ጳውሎስ ስለምን እያብራራ ነው ያለው?
የዕብራውያን መልዕክት ወደ ፅዮን ተራራ እንደደረስንና በታላቁ ድግስ
እንደምንሳተፍ ያረጋግጥልናል። “ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው
እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም
ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት” (ዕብ. 12፡22)። እኛን ወክሎ
በቀረበው ኢየሱስ በኩል በእምነት ደርሰናል። በዚህ ደስታ ውስጥ ሊቆጠሩ
የማይችሉ መላዕክታት እግዚአብሔር አብ ራሱ እና የክብረበዓሉ ማዕከል
የሆነው ኢየሱስም ይገኛሉ። “በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር”
አባል ሆነን መጥተናል (ዕብ. 12፡23)። ስማችን የእግዚአብሔር ምርጦች
በተዘረዘሩበት በሰማይ መዝገብ ተመዝግቧል (ዘፀ. 32፡32፤ መዝ. 56፡8፤ ዳን.
12፡1፤ ሚል. 3፡16፤ ሉቃስ 10፡20፤ ራዕ. 13፡8፤ ራዕ. 17፡8)
እኛ “በኩሮች” የሆንነው በኩር የሆነው ኢየሱስ የወረሰውን ውርስ ስለተካፈልን
ነው (ዕብ. 1፡6)። ስለዚህ እንደ እንግዶች ሳይሆን እንደ ዜጋ ተቆጠርን (ፊሊ.
3፡20 ጋር ያነፃሩ)። “ፍፁማንም ወደ ሆኑት ወደ ፃድቃን መንፈሶች” ተብለን
ተገልጸናል (ዕብ. 12፡23)። ይህ አገላለጽ የሰብአዊ ተፈጥሮአችን አንዱ ገፅታ
ሁሉንም ወክሎ መቅረቡን የሚያሳይ ነው። “ለመናፍስት አባት” ከሚለው
አገላለፅ ጋር አብሮ ይሄዳል (ዕብ. 12፡9)። ይህም እግዚአብሔር መንፈሳዊ
ለሆኑ ሰብአዊ ዘሮች በሙሉ አባት መሆኑን የሚገልፅ ነው።
ይህ የደስታ ስብስብ እያከበረ ያለው የክርስቶስን ንጉሳዊ አገዛዝ፣ የክህነት
አገልግሎትና የአዲስ ኪዳን መጀመርን ነው። በዕብራውያን መጽሐፍ እነዚህ
ሁሉ ክስተቶች እየተከናወኑ ያሉት በጽዮን ተራራ ላይ ነው። በዕብ. 1፡5-14
ላይ የምናገኛቸው ሶስቱ መዝሙሮች የሚያብራሩት ስለ ልጁ በዙፋን ላይ
መቀመጥ እና ነገሩም የተከናወነው በጽዮን ተራራ ላይ እንደሆነ ነው (መዝ. 2፡
6-7፤ መዝ. 110፡1-2፤ መዝ. 102፡21-27)።
የጽዮን ተራራ ልጁ “የዘላለም ካህን” እንዲሆን የተሾመበት ስፍራም ነው (ዕብ.
5፡6) ጥቅሱ የተወሰደውም ከመዝ. 110፡4 ላይ ነው። በመዝ. 110 መሰረት
የልጁ ሊቀ ካህን ሆኖ መሾም የተከናወነው በጽዮን ተራራ ላይ ነው (መዝ.
110፡2)።
በስተመጨረሻም የዕብራውያን መጽሐፍ የሚነግረን የኢየሱስ ሊቀ
ካህን መሆን አዲሱ ኪዳን በይፋ መጀመሩን አመላካች ነው (ዕብ. 7፡11-22)።
ስለዚህ የጽዮን ተራራ አዲሱ ኪዳን የጸደቀበት ስፍራ ነው። ዕብ. 12፡22-24
የሚገልጽልን ኢየሱስ ባረገበት ሰአት ስለተከናወነው የደስታ ስነ ስርዓት ነው።
በህይወታችንና አምልኮአችን ውስጥ የየሱስን የክህነት አገልግሎት
እንዲሁም አዲሱን ኪዳን ልናከብረው የምንችለው በምን አይነት
ተግባራዊ መንገድ ነው? በዚህ ታላቅ እውነት ሀሴት ማድረግ
እምነታችንን የሚያረጋግጠው ለምንድነው?
ዕብ. 12፡23ን ያንብቡ። ይህ የደስታ በአል ከሆነ ለምንድው ታዲያ እግዚአብሔር እንደ ዳኛ የተገለፀው? ዳኛ እንዴት ሆኖ ነው የደስታ በአል አከባበሩ ክፍል ወይንም ምክንያት የሚሆነው? ዳን. 7፡9-10፤ 13-22ን ያንብቡ።
የደስታው አከባበር በዕብ. 12፡22-24 ሲገለፅ የወደፊቱን ፍርድ እያመለከተን
ነው። ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር አለ፤ መጽሐፍትም ጥቅም ላይ ውለዋል፤
በመጽሐፍቱ በኩል የሚመጣው ይህ የወደፊት ፍርድ ውጤት የእግዚአብሔር
ህዝቦች መንግስቱን መውረሳቸው ነው (ዕብ. 12፡28)።
ይህ ትእይንት በዳን. 7 ላይ ስለተጠቀሰው ከምጻቱ በፊት ስላለው ፍርድ
የሚያብራራ ሲሆን ስለ ፍርዱ ትዕይንት ሲገልጽም “በዘመናት” የሸመገለው
እግዚአብሔር (ዳን. 7፡9) በእሳት ዙፋን ተቀምጦና “ሺህ ጊዜ ሺህ እና እልፍ
ጊዜ እልፍ” መላዕክት እንደሚያገለግሉት ይናገራል (ዳን. 7፡10)። መጽሐፎችም
ተከፈቱ(ዳን. 7፡10)፤ ለልዑሉ ቅዱሳንም ተፈረደላቸው፤ ከዚያም “መንግስትን
ወረሱ” (ዳን. 7፡22)።
በተመሳሳይ ሁኔታ ዕብ. 12፡22-29 በጽዮን ተራራ ላይ የነበረውን ፍርድ
ሲገልጸው “በሁሉ ላይ ዳኛ የሆነው” እግዚአብሔር በሰማዊቱ ኢየሩሳሌም
“ሺህ ጊዜ ሺኅ እና እልፍ ጊዜ እልፍ” መላዕክት ተከቦአል። ትዕይንቱ በእሳት
የተሞላ ነበር (ዕብ. 12፡29)። መፅሐፍትንም አካትቷል ምክንያቱም ቅዱሳን
በመጽሐፉ ላይ “ተፅፈዋል” (ዕብ. 12፡23)። ይህም ፍርድ ለቅዱሳን በጎ ነገርን
እንዳመጣላቸው አመላካች ነው።
የሱስ የትዕይንቱ ሁሉ ማዕከል ነው (ዕብ. 12፡24)። ዕብ. 2 ላይ በኛ ምትክ
“ሞትን” ከቀመሰ በኋላ “የክብርና የምስጋና ዘውድ” የጫነውንና የሰው ልጅ
የተባለውን ኢየሱስ ያሳየናል (ዕብ. 2፡9)። በዕብራውያን 2፡10 መሠረት
“የሰው ልጅ” (ዕብ. 2፡6ን ይመልከቱ) “ብዙ ልጆችን ወደ ክብሩ ለማምጣት”
አማኞችም እንደ እርሱ “በክብርና በምስጋና ዘውድ” ይሸለሙ ዘንድ ተሰቃየ
ነው። ልጁ አሁን አማኞችን በአዲስ ኪዳን በረከት በኩል ቃል ወደተገባላቸው
መንግስት(ዕብ. 12፡28)፣ ወደ ጽዮን፣ ወደ ሰማይቱ ኢየሩሳሌም አምጥቷቸዋል
(ዕብ. 12፡22-24)።
ይህ ፍርድ በእርግጥም ለአማኞች የምስራች ነው፤ ምክንያቱም ፍርዱ
ለእነርሱ የሚፈርድ ስለሆነ ነው። ነፃም ያወጣቸዋል። ፍርዱ አስፈሪ ከሆኑት
ለዘመናትም አማኞችን ካሳደዱትና (ዳን. 7) ወደፊትም ከሚያሳድዱት(ራዕይ
13) አውሬዎች ጀርባ ያለው ባለጋራ የሆነው ዘንዶ የሚረታበት ነው።
ዛሬ ያጠናነው ትምህርት በሶስቱ መላዕክት መልዕክት ውስጥ ያለው
የእግዚአብሔር ፍርድ “መልካም ዜና” እንደሆነ የሚያስረዳን
እንዴት ነው? (ራዕይ 14፡6-7ን ከዘዳ. 32፡36 እና 1 ዜና 16፡
33-35 ጋር ያነፃፅሩ)
በሰማይ ስለነበረው ደስታ ጳውሎስ ከገለፀ በኋላ አንባቢያን ለእግዚአብሔር ድምፅ ትኩረት እንዲሰጡ ያስጠነቅቃል። ምክንያቱም እግዚአብሔር “አንድ ጊዜ ደግሞ… ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማይን ሊያናውጥ” (ዕብ. 12፡26) ስለሆነ ነው። ጳውሎስ እንደሚነግረን ኢየሱስ በሰማይ ዙፋን ላይ ቢነግስም ድነታችን አልተፈፀመም። አስፈላጊ የሆነ ክስተት ሊከናወን ስለሆነ ትኩረታችንን ልናደርግ ይገባል። ሐጌ 2፡6-9፣ 20-22ን፣ ከመዝ. 96፡9-10፣ መዝ. 99፡1 እና ዕብ. 12፡26-27 ጋር ያነፃፅሩ። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን የማናወጡ አላማ ምንድን ነው? ምንስ ትርጓሜ አለው?
በብሉይ ኪዳን የመሬት መንቀጥቀጥ ህዝቡን ነፃ ሊያወጣ የሚመጣው
የእግዚአብሔር መገኘት አመላካች ነው። ዲቦራና ባራክ ከሲሳራ ጋር ሲዋጉ
እግዚአብሔር በነርሱ ፈንታ ከሰማይ ተዋጋ(መሳ. 5፡20)። ከእግዚአብሔር
መገኘት የተነሳም ታላቅ የምድር መናወጥ፣ የምድር እና የተራሮችም
መንቀጥቀጥ ተብሎ ተገልጧል(መሳ. 5፡4-5)። ይኸው ተመሳሳይ ምስል
በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የተጨቆኑትን ነፃ ለማውጣት ሲገለጥ
ተነግሯል (መዝ. 68፡7-8፤ መዝ. 60፤2፤ መዝ. 77፡17-18)። ስለዚህ ይህ
መናወጥ የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክት ሲሆን በምድር ላይ ባሉ ህዝቦች
ሁሉ ላይ ያለውን ስልጣን የሚያረጋግጥበት ነው። ነብያት በጌታ ቀን ይህ
እንደሚሆን ተንብየዋል (ኢሳ. 13፡13፤ ኢሳ. 24፡18-23)
በዕብራውያን መጽሐፍ አገላለፅ የምድርና የሰማይ “መናወጥ” የሚያመለክተው
የእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ነው። ኢየሱስ በሚነግስበት
ጊዜም እግዚአብሔር ቃል የገባው ይህንኑ ነው። እግዚአብሔር “ጠላቶችህን
የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” (ዕብ. 1፡13) ብሎታል።
ስለዚህም ኢየሱስ ጠላቶቹን አሸነፈ (ዕብ. 2፡14-16) እናም ነገሰ (ዕብ. 1፡
5-14)፤ ነገር ግን ጠላቶቹ እስካሁን አልተደመሰሱም (ዕብ. 10፡11-14፤ 1 ቆሮ.
15፡23-25)።
ነገር ግን እግዚአብሔር እነዚህን ጠላቶች ሰማይና ምድርን ሲያናውጥ
ያጠፋቸዋል። የሰማይና የምድር መናወጥ ማለት የእግዚአብሔርን ህዝቦች
ያሳደደው ምድራዊ ሀይሎች ከምንም በላይ ደግሞ ከምድራዊ ሀይሎቹ ጀርባ
ቆመው የሚቆጣጠሯቸው ሰማያዊ ሀይሎች (ሰይጣንና መላዕክቱ) መጥፋትን
ነው።
አንድ ቀን ፍትህ እንደሚመጣ፣ በአለም ላይ ተንሰራፍቶ ያለው
ክፉ አንድ ቀን እንደሚጠፋ ተስፋ ማግኘታችን ለሁላችን በተለይም
በቀጥታ በክፉ እጅ ለተሰቃዩ ያለው ትርጉም ምን ያህል ነው?
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን “እንደሚያናውጥ” ሲናገር ጠላቶችን ሁሉ እንደሚያጠፋቸው መናገሩ ነው። ሊናወጡና ሊጠፉ የማይችሉ አንዳንድ ነገሮች አሉ። መዝ. 15፡5ን፣ መዝ. 16፡8፣ መዝ. 21፡7 መዝ .62፡2፤ መዝ. 112፡6ን ከዕብ 12፡27 ጋር ያነፃፅሩ። ሊናወጡ የማይችሉ ምን ነገሮች አሉ?
አያሌ የዕብራውያን 12፡27 ዘመናዊ ተርጓሚዎች እንደሚናገሩት ሰማይና
ምድር ሲናወጡ ለዘላለም መወገዳቸውን ለመግለፅ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ግልፅ ነው፤ እግዚአብሔር አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን
ይፈጥራል (ኢሳ. 65፡17፤ ራዕ. 21፡1-4) እኛም ከሞት ተነስተን በዚችው ምድር
አዲስን አካል እንለብሳለን (1 ተሰ. 4፡13-17፤ ፊሊ. 3፡20)። ስለዚህ “መናወጥ”
የሚያመለክተን ነገር ቢኖር መፅዳትንና እንደ አዲስ መፈጠርን እንጂ ሙሉ
በሙሉ መወገድን አይደለም። ይህ የነበረ ነገር እንደገና ይፈጠራል፤ የዳኑ
የሚኖሩበት ቦታ ይሆናል።
ሊናወጥ የማይችል ነገር ግን አለ። ይህም ፃድቃንን ያካትታል። የማይናወጡት
በእግዚአብሔር ስለታመኑ ነው። ፈጣሪ ይጠብቃቸዋል፤ ለመኖራቸውም
ዋስትና ይሰጣቸዋል።
በዕብራውያን መጽሐፍ ዘላለማዊነት እና ጸንቶ መቆየት ከየሱስ ጋር የተያያዘ
እንደሆነ ይነግረናል። ዕብ. 1፡10-12 ላይ ስለ የሱስ ሲናገር “ደግሞ ጌታ ሆይ አንተ
ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማዮችንም እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ
ይለወጡማል አንተ ግን አንተ ነህ ዓመታቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል”።
የዕብራውያን መጽሐፍ የክርስቶስ ክህነት ለዘላለም እንደሚቆይም ይነግረናል
(ዕብ 7፡3፤ 24) የዳኑ ሰዎች ወራሽነትም ልክ እንደዚሁ (ዕብ. 10፡34)።
በመጨረሻው ፍርድ “በኢየሱስ” የሆኑ ሁሉ አይናወጡም (መዝ. 46፡5)።
ዕብ. 12፡28ም “የማይናወጥ መንግስት” እንደምንቀበል ይነግረናል። ዳን. 7፡18
ላይም ቅዱሳ “ለዘላለም መንግስትን እንደሚወርሱ” ተፅፏል። ይህ መንግስትም
“ለዘላለም የማይፈርስ መንግስት ነው (ዳን. 2፡44)። የዚህ መንግስት ባለቤት
ልጁ ቢሆንም ለእኛ ያካፍለናል። ራዕ. 20፡4 እንደሚነግረን ባሳደደን የክፉ
ሀይል ላይ ከኢየሱስ ጋር አብረን እንፈርዳለን (1ቆሮ. 6፡3)።
ከመናወጥ ጋር በተያያዘ አሁን ላይ ምን ይሰማዎታል? መልካም
ስሜት ካልተሰማዎ በዚህ ጉዳይ ላይ እገዛ የሚያደርግሎትን ምን
አይነት ምርጫ ማድረግ ይችላሉ? (ኤፌ. 4፡14ን ይመልከቱ)
የዕብራውያን መጽሐፍ ይህንን ክፍል የሚያጠቃልለው እግዚአብሔር ለእኛ ስላደረገው አስደናቂ ነገር የምንመልሰው ተገቢው ምላሽ ትክክለኛውን አምልኮ በመስጠት ምስጋናችንን መስጠት እንደሆነ በማስታወስ ነው። ዕብ. 12፡28ን ከዕብ. 13፡15-16 ጋር ያነፃፅሩ። ለእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው አምልኮ የምንሰጠው እንዴት ነው?
በብሉይ ኪዳን ስርአት ሰዎች ንስሃ እና ምስጋናቸውን የሚያሳዩበት መንገድ
የእንስሳት መስዋዕት ነበር። ነገር ግን እነዚህ መስዋዕቶች በአምላኪው ልብ
ውስጥ ያለውን ምስጋናና ንስሃ ማሳያ ነበሩ። ስለዚህ እግዚአብሔር በመዝሙረ
ዳዊትና በነብያት በኩል ግልጽ አድርጎ እንዳስቀመጠልን እርሱን ልናስደስት
የምንችለው በእንስሶች ደም ሳይሆን ምስጋናን በመስጠት፣ በመልካም
ተግባራትና በቅድስና ነው (መዝ. 50፡7-23፤ ኢሳ. 1፡11-17)።
ስለዚህም ጳውሎስ በሰማያዊ ቤተ መቅደስ የምስጋና፣ የንስሃና የመልካም
ተግባራት መስዋዕትን በመሰዋት እንድናመልከው ይጋብዘናል። ይህንን
መስዋዕት በምድር እናመጣለን፤ ነገር ግን በሰማይ እግዚአብሔርን እንዳስደሰቱ
ተደርገው ተቀባይነት ያገኛሉ።
ይህ ምክር ፀሐፊው በጽሁፉ ሁሉ ውስጥ
የመከረንን ማለትም ስለኢየሱስ ስም እንድንመሰክርና (ዕብ. 3፤1፤ ዕብ. 4፡14፤
ዕብ. 10፡23) መልካም ስራን እየሰራን እንድንቀጥል (ዕብ. 6፡10-12፤ ዕብ. 13፡
1-2፤ 16) የነገረንን ይጠቀልላል።
ጳውሎስ አንባቢያኑ “ለእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው አምልኮ” እንዲሰጡ
(ዕብ. 12፡28) ያቀረበው ጥሪ የሚያመለክተው አማኞች አሁን ላይ በትክክልም
የካህናት ህዝብ እና በኢየሱስ መስዋዕትነት ፍጹምና ጻድቅ መሆናቸውን
ነው (ዕብ. 10፡10-14፤ 19-23)። ይህም እግዚአብሔር ለእስራኤል አስቀድሞ
የነበረው አላማን ያም የካህናት ህዝብ ሆነው ለአለም መልካሙን ዜና
እንዲያውጁ (ዘፀ. 19፡4-6፤ 1ጴጥ. 2፡9-10፤ ራዕ. 1፡6፤ ራዕ. 5፡10) ያቀደውን
ተፈፃሚ የሚያደርግ ነው።
ዕብ. 13፡1-6ን ተግባራዊ በሆነ አለገላለፅ መልካም ማድረግ እና ያለንን ማካፈል
ምን ማለት እንደሆነ ይነግረናል። ይህም ኢየሱስ ወንድማዊ ፍቅርን እንዳሳየን
እኛም ወንድማዊ ፍቅርን እንድናሳይ ነው (ዕብ. 2፡11-12)። የተጨነቁትንና
በእስር ቤት ያሉትን መጠየቅና መርዳት (ዕብ. 13፡3) እንዲሁም አመንዝራነትንና
ክፉ ምኞትን እምቢ ማለት ነው።
መልካም ሥራን እና ያለንን ማካፈል እግዚአብሔርን የማምለካችን
ክፍል ማድረግ ያስፈለገው ለምንድን ነው? መንፈሳዊ መስዋዕታችን
ሊበላሽ የሚችልባቸው ተግባራዊ መንገዶችስ የትኞቹ ናቸው
(ኢሳ. 1፡11-17)?
“በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ትንሳኤ መካከል ባለው
የሺው ዓመት ጊዜ የሀጢያት ፍርድ ይከናወናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን
ፍርድ ሲገልፀው ከሁለተኛው ምጽአት በኋላ ተከትሎ የሚመጣ እንደሆነ
ነው። “ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ
የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች
አትፍረዱ” 1 ቆሮ. 4፡5። ዳንኤል እንደሚነግረን በዘመናት የሸመገለው
እስኪመጣ ድረስ “ፍርድ ለልዑል ቅዱሳን ተሰጥቷል” ዳን. 7፡22። በዚህ ጊዜ
ጻድቃን እንደ ንጉስ እና ካህናት ሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ይነግሳሉ።
ዮሐንስ
በራእዩ “ዙፋኖችንም አየሁ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው
“ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን
ሺህ አመት ይነግሳሉ” ራዕይ 20፤4፤ 6 በዚህ ጊዜ ነው ጳውሎስ እንደሚነግረን
“ቅደሳን በምድር ላይ ይፈርዳሉ” 1 ቆሮ. 6፡2 ከክርስቶስ ጋር ባላቸው ህብረት
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማመሳከር በሀጢአን ላይ ይፈርዳሉ።
የተደረገው
ነገር እንደየ ጉዳዩ ትክክል መሆኑን ያረጋግጣሉ ሀጢያተኞች እንደ ስራቸው
መጠን ስቃያቸውን እንደሚቀበሉ በስማቸው ፊት ለፊት በሞት መጽሐፍ ላይ
ተጽፎአል”
“ሰይጣን እንዲሁም እርኩሳን መላዕክት በክርስቶስ እና ህዝቦቹ አማካኝነት
ይፈረድባቸዋል። ጳውሎስ ሲናገር “መላዕክታት ላይ እንደምንፈርድ
አታውቁምን ይለናል 1 ቆሮ. 6፡3። ይሁዳ ሲያብራራ ደግሞ “መኖሪያቸውንም
የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላዕክት በዘላለም እስራት
ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ድረስ ጠብቆአቸዋል” (ይሁዳ 6) Ellen G.
White, The Great Controversy, pp. 660, 661
1.በሀጢአን ፍርድ ላይ የቅዱሳን ተሳትፎ (1 ቆሮ. 6፡3፤ ይሁዳ.
6) ስለ እግዚአብሔር እና ሁሉን ግልጽ ስለ ማድረጉ፣ ሀጢአት እና
ክፋትን በምን መልክ እንደሚመለከት እና የርሱን መልካምነትና
ፍትሃዊነት እንዴት ያሳያል?
2.ዘፀ. 32፡32፤ መዝ. 56፡8፤ መዝ. 69፡28፤ መዝ. 139፡
16፤ ኢሳ. 43፤ ዳን. 12፡1፤ ሚልኪያስ 3፡16፤ ሉቃ. 10፡
20፤ ራዕ. 13፡8 እና ራዕይ 17፡8ን ያንብቡ። እነዚህ በሰማይ
ለእግዚአብሔር መጽሐፍ ማጣቀሻ ናቸው። በነዚህ መጽሐፎች
ውስጥ ተመዝግበው ያሉ ምን ምን ነገሮች አሉ? ለምሳሌ
እግዚአብሔር እንባችንን እንኳን የመመዝገቡ አስፈላጊነት ምን
ያክል ነው (መዝ. 56፡8)? እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የሚያውቅ
ከሆነ የነዚህ መፅሐፎች ወይንም መዝገቦች አላማ ምንድነው?
3.የዕብራውያን መጽሐፍ ሙግቱን ከዳ 7 ቃል ኪዳን ጋር አያይዞ
የማጠናቀቁ አስፈላጊነት ምን ይመስሎታል? እነዚህ ከየሱስ ሰማያዊ
አገልግሎት ጋር ያላቸው ግንኙነትና አስፈላጊነት ምንድን ነው?
ዳን. 7 ስለ ምድር ፍፃሜ እና ስለወደቁት ነገሮች የሚያስተምረን
ምን ነገር አለው?