
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዕብ. 10፡35-39፣ ሮሜ 1፡17፣ ዕብ. 11፣ ኢያሱ 2፡9-11፣ ዕብ. 12፡1-3።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብ. 12፡2)
ዕ
ብራውያን 11 እና 12 ከዕብራውያን መልዕክት ምዕራፎች ሁሉ እጅግ
የሚወደዱ ናቸው። የክርስትና ህይወትን ሁሉም የሚሳተፉበትና
ታማኝ ሆነው የሚጸኑት ሽልማቱን የሚቀበሉበት ውድድር
አድርገው ያስቀምጡታል። ምዕራፎቹ የድነትን ታሪክ በቀደመው
ዘመን የነበሩ የእምነት ሰዎች በመከራዎች ውስጥ የጸኑበትና እስካሁን
ሽልማታቸውን ያልተቀበሉበት ውድድር አድርገው ይገልጹታል።
ያ የሆነበት ምክንያት በነርሱ ብቻ ሳይሆን ታሪኩ በኛ ስለሚጠናቀቅ ነው።
በኛ ነው የሚደመደመው ድራማው የሚያበቃው የመጨረሻውን የውድድር
ክፍል እኛ ገብተንበት ስንሮጥና ከኢየሱስ ጋር በአብ ቀኝ ስንቀመጥ ነው።
ኢየሱስ ብርታት ሆኖን ሩጫውን እንዴት መሮጥ እንዳለብንም ምሳሌ ሆኖ
ይመራናል።ሽልማቱ የእውነት መሆኑን የሚመሰክርልን ትክክለኛው ምስክር
እርሱ ሲሆን መንገዱን የሚከፍትልን ቀዳሚያችም እርሱ ነው(ዕብ.6፡1920፣ዕብ.10፡19-23)።
ዕብራውያን 11 እምነት እስካሁን ተፈጽመው ባናያቸውም በእግዚአብሔር
የተስፋ ቃላት ላይ መታመን እንደሆነ ይናገራል። ይህ ትምህርት እምነት ምን
እንደሆነና ካለፉት ምሳሌዎች በተለይም የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነውን
ኢየሱስን በመመልከት እንዴት እንደሚገኝ ያስገነዝበናል።
ለመጋቢት 3 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ፡-
ዕብ.10፡35-39ን ያንብቡ። በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ እግዚአብሔር እየተናገረን ያለው ምንድነው?
ጽናት የእግዚአብሔር የመጨረሻ ዘመን ሕዝቦች አንዱ ባህሪ ነው፤የተስፋ
ቃላቱን ያለጽናት ሊቀበሉ አይችሉም(ራዕ.13፡10፣ራዕ.14፡12)።ለመጽናት
ደግሞ አማኞች እምነታቸውን አጥብቀው ሊይዙ ይገባል(ዕብ.10፡23፣ዕብ.4፡
14)።ጳውሎስ እንደነገረን የምድረ በዳው ትውልድ የተስፋይቱን ምድር
ሊወርሱ ያልቻሉት እምነት ስለጎደላቸው ነበር(ዕብ. 3፡19)። የዕብራውያን
መልዕክት አማኞች በተስፋው ፍጻሜ ጫፍ ላይ እንደደረሱና (ዕብ. 9፡28፣
ዕብ. 10፡25፣ 36-38) ተስፋውን መውረስ ከፈለጉ እምነትን መለማመድ
እንዳለባቸው ይገልጻል(ዕብ.10፡39)።
ጳውሎስ ስለ እምነት ማብራራቱን ከዕንባቆም 2፡2-4 በመጥቀስ ይጀምራል።
ዕንባቆም ክፉ ሰዎች ጻድቁን ሲያስጨንቁት እግዚአብሔር አይቶ ለምን
ዝም እንዳለ ጠይቋል (ዕን. 1፡12-17) ነብዩና ህዝቡ እንደተሰቃዩ ስለነበር
እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ ፈለጉ። እግዚአብሔር ደግሞ የርሱ የተስፋ
ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ስለተቀጠረ እንዲጠብቁ ነገራቸው(ዕንባ. 2፡2-4)።
ዕንባቆምና ህዝቡ ልክ እንደ እኛ በተስፋ ቃሉና በፍጻሜው ጊዜዎች መካከል
ይኖሩ ነበር። የእግዚአብሔር መልዕክት በዕብራውያን ውስጥም ቀጥሎ ሊመጣ
ያለው ይመጣል፤አይዘገይምም (ዕብ.10፡37) ይላል።
መልዕክቱ የሚናገረው ስለ ኢየሱስ ነው።ጻድቅ የሆነው፤እምነትን በአካል
የገለጠው፣አብን ደስ የሚያሰኘውና ለሰው ህይወትን የሚሰጠው እርሱ
ነው(ዕብ.10፡5-10)።
ታዲያ ለምን ይዘገያል? አይዘገይም።አንዴ ሊሞትልን መጥቷል (ዕብ.9፡1526)፤ደግሞም በተቀጠረው ጊዜ በርግጥም እንደገና ይመጣል(ዕብ.9፡2728፣ዕብ.10፡ 25)።
የእግዚአብሔር መልዕክት ቀጥሎም ጻድቁ በእምነት ይኖራል(ዕብ.10፡
38) ይላል።ጳውሎስ ተመሳሳዩን መልዕክት በሮሜ 1፡17ና ገላትያ 3፡11 ላይ
አስቀምጧል። በተለይ ሮሜ 1፡16-17 የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ
እምነት ይገለጣል ብሎ ስለሚናገር ብርሃንን ይፈነጥቃል።ጳውሎስ ሊል
የፈለገው የእግዚአብሔር ለተስፋ ቃሎቹ ታማኝ መሆን ይቀድማል ከዚያም
የርሱ ታማኝነት የኛን እምነት/ታማኝነት ያመጣል።
እግዚአብሔር ለሰጠን የተስፋ ቃላት ታማኝ ሆኖ ስለሚኖር(2ጢሞ.2፡13)
በምላሹ ጻድቁ በታማኝነት ይጸናል።
የኛ እምነትና ቀጣይነቱም ከእግዚአብሔር ታማኝነት የመነጨ
መሆኑን መረዳት የሚጠቅመን ለምንድነው? እርሱ ለኛና ለገባቸው
የተስፋ ቃላት ታማኝ በመሆኑ ላይ የበለጠ መተማመን የምንችለው
እንዴት ነው?
የዕብራውያን መልዕክት እምነትን ሲተረጉም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ (ዕብ.11፡1) ነው ይላል። ከዚያ ከእስራኤል ታሪክ እምነትን በምሳሌ ያሳዩ ታማኝ ሰዎችን ዝርዝር በመግለጽ እምታቸውን በተግባሮቻቸው እንዴት እንደገለጹ ያሳያል። ዕብ.11፡1-19ን ያንብቡ። የዕምነት ጀግኖቹ በተግባር ያሳዩትና ምሳሌ የሆኑት እንዴት ነበር? እምነታቸውን _
ምናልባትም አብርሃም በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እጅግ ወሳኙ ባለ ታሪክ ነው።
በተለይ የአብርሃም የመጨረሻው የእምነት ተግባር ስለ እውነተኛ እምነት
ትልቅ ትምህርትን የሚሰጥ ነው።
የዕብራውያን መልዕክት እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጁን ይስሃቅን መስዋዕት
አድርጎ እንዲያቀርብ መጠየቁ በእግዚአብሔር በኩል ልክ ያልሆነ ነገርን
እንደሚያሳይ አመላክቷል(ዕብ.11፡17-18)። ይስሐቅ የአብርሃም ብቸኛ ልጅ
አልነበረም። የአብርሃም የበኩር ልጅ እስማኤል ቢሆንም አብርሃም የሳራን ምክር
ሰምቶ እስማኤልንና እናቱን እንዲያስወጣቸው እግዚአብሔር ሲፈቅድለት
እንመለከታለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለሚጠነቀቅላቸውና የአብርሃም
ዘር በይስሃቅ ስለሚጠራ ነው(ዘፍ.21፡12-13)።
ሆኖም በቀጣዩ ምዕራፍ
አብርሃም ልጁን ይስሃቅን መስዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብለት እግዚአብሔር
ይጠይቀዋል። በዘፍጥረት 22 እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር በዘፍጥረት 12-21
ላይ እግዚአብሔር የገባቸውን ቃላት በግልጽ የሚቃረን ይመስላል።
የዕብራውን መልዕክት ሲደመደም አብርሃም ይስሃቅን ከሰዋው በኋላ
እግዚአብሔር እንደሚያስነሳው በማመን እንቆቅልሹን እንደፈታው በመናገር
ይደመድማል። ይህ አስደናቂ ነው ምክንያቱም ማንም ገና ከሞት አልተነሳም
ነበር። ሆኖም አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው የቀደመ ልምምድ
ወደዚያ ድምዳሜ የመራው ይመስላል።ዕብራውያን 11፡12 እንደሚገልጸው
ይስሃቅ የተጸነሰው የሞተን ሰው ከመሰለው ከአንዱ በእግዚአብሔር ኃይል
ነበር።
አብርሃም የሞተን ሰው ቢመስልም ሳራም መካን ብትሆንም በተስፋ
የብዙ ህዝብ አባት እንደሚሆን እግዚአብሔር ለሞተው ነገር ህይወትን
እንደሚሰጥና የሌለውን እንዳለ አድርጎ እንደሚጠራ (ሮሜ 4፡17-20) እንዳመነ
ጳውሎስ ይናገራል።ስለዚህ አብርሃም ለይስሃቅ ከሞተው ውስጥ ህይወትን
ከሰጠው አሁንም ያን ሊያደርግ እንደሚችል አምኗል ማለት ነው።ቀደም ብሎ
በነበረው በእግዚአብሔር አመራር ውስጥ ወደፊት ምን ሊያደርግ እንደሚችል
አብርሃም ተመለከተ።
ትላንት እግዚአብሔር እንዴት እንደመራን ማሰላሰል አሁን በርሱ
ላይ የሚኖረንን እምነት ሁኔታ የሚወስነው እንዴት ነው?
ዕብራውያን 11፡20-28ን ያንብቡ። እነዚህ የእምነት ሰዎች ምን አደረጉ? ተግባሮቻቸው ከተስፋና ካልታዩ ነገሮች ጋር የሚገናኙት እንዴት ነው?
በዚህ የእምነት ምዕራፍ ሙሴ ሁለተኛው ዋና ምሳሌ ነው።የሙሴ ህይወት
የተጀመረውና የተጠናቀቀው ለንጉሱ ባሳያቸው ሁለት እምቢተኝነቶች
ነው።ወላጆቹ የንጉሱን አዋጅ ስላልፈሩ ሙሴ ህጻን እያለ ደበቁት(ዕብ.11፡
23)፤እናም ሙሴ የንጉሱን ቁጣ ሳይፈራ ከግብጽ ወጣ(ዕብ.11፡27)። የሙሴ
እጅግ ልዩ የሆነው ተግባር የልጅ ልጅ እንዳይባል እምቢ ማለቱ ነበር (ዕብ.11፡
24)። የሙሴ አሳዳጊ እናትን የፈርኦን ሴት ልጅ ብሎ መጥራቱ ቀጣዩ
ፈርኦን እንዲሆን እንደታጨ የሚገልጽ ነው። ሆኖም ሙሴ ነጻ የወጡት
ባሮች(እንደውም ስደተኞች)መሪ ለመሆን ሲል በጊዜው ታላቅ የነበረችው
ሀገር መሪ መሆንን ለመተው ፈቅዶ ነበር።
ዕብራውያን 11፡24-27ና ዕብራውያን 10፡32-35ን ያነጻጽሩ።
የዕብራውያን መልዕክት የተጻፈላቸው ሰዎችና የሙሴ ልምምድ
ምን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ?
የሙሴ ታላቅነት ከግብጽ ንጉስ አሻግሮ ማየት መቻሉና የማይታየውን ማለትም
የእግዚአብሔርን ተስፋ ማየት መቻሉ ነው።ዕብራውያን እንደሚለው የሙሴ
አይኖች ከግብጽ ሀብቶች ይልቅ በሽልማቱ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። ይህ ሽልማት
በዕብራውያን 10፡35 ላይ የተጠቀሰውና እግዚአብሔር በርሱ ለሚያምት ሁሉ
ተስፋ የሰጠው(ቃል የገባው)ነው።
ስለ ሙሴ ውሳኔ የተናራቸው የጳውሎስ ቃላት በመጀመሪያዎቹ አንባዎች
ልብ በኋይል ያስተጋቡ ነበር።
በክርስቶስ በማመናቸው ምክንያት
መገፋቶችንና ስድቦችን ሲቋቋሙ ቆይተዋል። ተገፍተውም ንብረቶቻቸውን
አጥተዋል(ዕብ.10፡32-34)።አንዳንዶች በእስር ቤት ውስጥ ነበሩ(ዕብ.13፡
3)። በተመሳሳይ ሙሴ ግብጽ ልትሰጥ የምችለው የትኛውም ነገር ክርስቶስ
ከሚሰጠው ሽልማት እንደማይበልጥ ስላመነ የግብጽን ሀብት ከክርስቶስ ጋር
በመሆን በመሰደብ ለውጦ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መቀበልን
መረጠ።
እርስዎ በእምነትዎ ምክንያት ምን አይነት ችግሮችን ተጋፍጠዋል?
ምን መተው ነበረብዎት አሁን ላይ ማየት ባይችሉም ሽልማቱ ሌላ
ነገር ሊተዉለት የሚገባ የሆነው ለምንድነው?
ዕብ.11፡31ንና ኢያሱ 2፡9-11ን ያንብቡ።አረማዊ የሆነችው ረዓብ ከቅዱሳን ተርታ የተሰለፈችው ለምን ነበር?
ረዓብ በዕብራውያን 11 ከምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ እጅግ ያልተጠበቀችው
ነች።ረዓብ በስም ከተጠቀሱቱ ሁለት ሴቶች አንዷ ነች። በመጀመሪያ ቀደምት
አባቶች ከዚያም የእስራኤል ጻድቅ የእምነት አባቶች በተጠቀሱበት ዝርዝር እሷ
በአስረኛ ደረጃ ስሟ ተጠቅሷል።ወደርሷ ስንመጣ ሴት መሆኗ ብቻ ሳይሆን
ከአሕዛብ ዘር የሆነች ጋለሞታ ነበረች።
እጅግ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ በምዕራፉ የመልዕክት ማዕከልና ጡዘት ላይ
መሆኗ ነው።ዝርዝሩ ለየት ባመልኩ የተዋቀረ ነው። ሁሉም ሲጀምር በእምነት
የሚልን ሀረግ ይጠቀማል። ዋና አካሄዱ በእምነት አክሎ ይህንንና ያንን አደረገ
ወይም በእምነት ያና ይሄ ለእከሌ ሆኑለት የሚል ነው።እንዲህ እያለ እየደጋገመ
ሲሄድ ኢያሱ በእምነት ህዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር መራ የሚል መልዕክት
አንባቢዎች እንዲጠብቁ ያስገድዳል።
ጥቅሱ የሚለው ግን ያንን አይደለም። በተቃራኒው ኢያሱ ይታለፍና ጋለሞታይቱ
የርሱን ቦታ ትይዛለች። ረዓብ ከተጠቀሰች በኋላ እየደጋገመ የሚሄድበትን
አካሄድ አቁሞ “እንግዲህ ምን እላለሁ?(ዕብ.11፡32) ይላል። ከዚያ ጳውሎስ
በፍጥነት ስሞችንና በዝርዝር የማይገልጻቸውን ክስተቶች ይዘረዝራል።
የረዓብ የእምነት ተግባር መስማቷ፣ማመኗ ባይታይም መታዘዟ ነበር። የግብጽን
መቅሰፍቶች፣ወይም በቀይ ባህር መሻገራቸውን፣ ውሃ ከዓለት ሲፈልቅ፣
ወይም መና ከሰማይ ሲወርድ አላየችም፤ ነገር ግን አመነች። ኢየሱስ ሲሰብክ
ወይም ተዓምራትን ሲያደርግ ላላዩት የዕብራውያን አንባቢዎች ለኛም ላላየነው
መልካም ምሳሌ ሆነች።
ረዓብ በኢያሪኮ ውስጥ የምትኖር ሴተኛ አዳሪ ነበረች። ከተማይቱን ለመሰለል
የተላኩትን ሁለት የእስራኤል ሰላዮች ደበቀች። ለነርሱ ስላሳየችው ደግነትና
ስለ እግዚአብሔር ነገር ሰላዮቹ ኢያሪኮን ሲያጠቁ እርሷና ቤተሰቦቿን
እንደሚያተርፉላት ቃል ገቡላት።Daughters of God p.35.
ከዚያም ጳውሎስ ብዙዎች የተጋፈጡትን ትግል መዘርዘሩን ይቀጥላል(ዕብ.11፡
35-38)። መዳንን ሳይቀበሉ(ዕብ.11፡35) የሚለው ሀረግ ማምለጥ እየቻሉ
አይኖቻቸው በእግዚአብሔር ሽልማት ላይ ስላተኮረ ራሳቸውን ሳያድኑ
መቅረታቸውን የሚያሳይ ነው።
እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በአይኖቻችን ባናይም (የስድስት ቀን
ፍጥረት፣ከግብጽ መውጣት፣የክርስቶስ መስቀልን) ስለመፈጸማቸው
እንድናምን ብዙ ምክያቶች ያሉን ለምንድነው?
ዕብራውያን 12፡1-3ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ምን እንድናደርግ እየጠየቁን ነው?
ስለ እምነት የተገለጹት ነገሮች ከፍታ በዕብራውያን 12 ላይ ኢየሱስ ጋ ይደርሳል።
ጳውሎስ በሚመጣውና በማይዘገየው ኃሳቡን ይጀምርና የእምነታችን ፈጻሚ
በሆነው ኢየሰስ ይደመድማል (ዕብ.12፡2)። ኢየሱስ የእምታችን ጀማሪና
ፈጻሚ ነው። ይህ ማለት እምነት እንዲኖረን የሚያስችለንና እምነት ምን ማለት
እንደሆነ በአካል ምሳሌ የሆነን ኢየሱስ ነው ማለት ነው።ከኢየሱስ ጋር እምነት
ፍጹም መግለጫውን አግኝቷል።
ኢየሱስ የእምታችን ጀማሪ የሆነባቸውን ቢያንስ ሶስት ነገሮች እንጥቀስ።
በመጀመሪያ ሩጫውን ሙሉ በሙሉ ሮጦ የጨረሰው እሱ ብቻ ነው።
በቀደመው ምዕራፍ የተነገረላቸው ሰዎች ግባቸውን ገና አልደረሱም (ዕብ.11፡
39-40)። ኢየሱስ ግን በሰማይ ወደ እግዚአብሔር እረፍት ገብቶ በአባቱ ቀኝ
ተቀምጧል። እኛም ከነዚያ ጋር ወደፊት ከኢየሱስ ጋር እንነግሳለን(ራዕ.20፡
4)።
በሁለተኛ ደረጃ ሌሎች ሩጫቸውን እንዲሮጡ ያስቻለው የኢየሱስ ፍጹም
ህይወት መኖር ነበር(ዕብ.10፡5-14)። ኢየሱስ ባይመጣ ኖሮ የሁሉም ሰው
ሩጫ ከንቱ ይሆን ነበር።
በመጨረሻም እምነት ያለን በኢየሱስ ምክንያት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር
አንድ እንደመሆኑ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ታማኝነት ገለጸ። እግዚአብሔር
እኛን ለማዳን ያለውን ጥረት አላቋረጠም ስለዚህ እኛም ካላቋረጥን ወደ
ሽልማቱ እንደርሳለን። ኢየሱስ በትዕግስት ሲሮጥ እኛ ታማኝ ባልነበርንበት
ጊዜ እንኳን ታማኝ ሆነ(2 ጢሞ.2፡13)።የኛ እምነት ለርሱ ታማኝነት መልስ
ብቻ ነው።
በመጨረሻ ኢየሱስ የእምነት ሩጫ እንዴት እንደሚሮጥ ምሳሌ ሆኖ ስላሳየን
የእምነታችን ፈጻሚ ነው።እንዴት ነበር የሮጠው ለኛ ሲል ሁሉን በመተው
ሸክም የሚሆኑበትን ነገሮች ሁሉ ጣለ(ፊል.2፡5-8)። መቼም ኃጢአትን
አላረገም። ኢየሱስ አይኑን በሽልማቱ ማለትም በፊቱ ባለው ደስታ ማለትም
በርሱ ጸጋ የሰው ዘር መዳን ላይ አተኮረ። ስለዚህ አለመስተዋልን፣መገፋትን
ተቋቁሞ የመስቀሉን ሀፍረት ናቀ(ዕብ.12፡2-3)።
አሁን መሮጥ የኛ ተራ ነው። በኛ ብርታት ኢየሱስ የደረሰበትን መቼም መድረስ
ባንችልም ምሳሌው ከፊታችን አለልን። ስለዚህ በርሱ በማመንና አይናችንን
በርሱ ላይ በማድረግ (ከኛ በፊት የነበሩት እንዳደረጉት) ታላቅ ሽልማት
እንደሚሰጠን የገባልንን ቃል በማመን በእምነት ወደፊት እንቀጥላለን።
“በእምነት የክርስቶስ ትሆናላችሁ፤ በእምነትም በርሱ
ሆናችሁ ልታድጉ ይገባል- በመስጠትና በመውሰድ። ልባችሁን፣ ፈቃዳችሁን፣
አገልግሎቶቻችሁን ማለትም ሁለመናችሁን ለርሱ በማስረከብ የርሱን ትዕዛዝ
ልትታዘዙ ይገባችኋል። እናም ሁሉንም ማለትም የበረከት ሙላት የሆነውን
ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር፣ ብርታታችሁ፣ ፅድቃችሁ፣ ዘላለማዊ ረዳታችሁ
እንዲሆንና እንድትታዘዙ ኃይል እንዲሰጣችሁ የራሳችሁ ልታደርጉት
ይገባል።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ፣ ገፅ 70
“እግዚአብሔር እምነታችንን የምንመሰርትበት በቂ ማስረጃ ሳይሰጠን
እንድናምነው አይጠይቀንም።
መኖሩ፣ ባህሪውና፣ የቃሉ እውነትነት ሁሉም
ምክንያታዊ በሆኑ ምስክሮች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ እነዚህም ምስክሮች
የተትረፈረፉ ናቸው። ሆኖም እግዚአብሔር የጥርጥር በርን አልዘጋም።
በዓይን የሚታይ ማረጋገጫ ባናገኝም እምነታችን በማስረጃዎች ላይ መመስረት
አለበት። መጠራጠር ለሚፈልጉ መግቢያን ሊያገኙ ይችላሉ፤ እውነትን ማወቅ
ለሚፈልጉ እምነታቸውን የሚመሠርቱባቸው ብዙ ማስረጃዎችን ያገኛሉ።”
“ውስን የሆኑት አእምሮዎች ገደብ የሌለውን የርሱን ሥራዎችና ባህሪ ሙሉ
በሙሉ መረዳት አይችሉም።
እጅግ ብልህና እጅግ ተምሬያለሁ ብሎ
ለሚያምነው ሰው ቅዱስ ማንነቱ ሚስጥር ይሆንበታል። “የእግዚአብሔርን
ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ፈጽመህ
ልትመረምር ትችላለህን?” (ኢዮብ 11፡7-8)” ኤለን ጂ. ኋይት፣ ወደ ክርስቶስ
የሚመራ መንገድ፣ ገፅ 105
1.አንድ ቀደምት ተመራማሪ ክርስትያን በላቲን ቋንቋ ክሪዶ ኡት
ኢንተሊጋም ወይም በአማርኛ “ማስተዋል እንድችል አምናለሁ”
ብሎ ነበር። ዕብ. 11፡3 ላይ “. . . በእምነት እናስተውላለን”
ይላል። በማመንና በማስተዋል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድነው?
በአብዛኛው እምነት ከማስተዋል በፊት የሚመጣው ለምንድነው?
ማለትም አንዳንድ ጊዜ መጀመሪያ ላይ መረዳት ባልቻልናቸው
ጉዳዮች ላይ በእምነት መሄድና የበለጠው መረዳት ቆየት ብሎ
የሚመጣው ለምንድነው?
2.“ፒስቲስ” የሚለው የግሪኩ ቃል “እምነትም” “ታማኝነትም”
የሚል ትርጉም አለው። በእምነት መኖር የሚለውን ኃሳብ
ለመረዳት ሁለቱም ትርጉሞች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው?
በዕብራውያን 11 ያሉት ሰዎች እምነታቸው እውነት መሆኑን
ታማኝ በመሆን ያሳዩት እንዴት ነበር? እኛስ ተመሳሳዩን ነገር
ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
3.እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ብናስተውልም(ሮሜ
12፡3) ያንን ስጦታ በመቀበልና በማቆየት ረገድ ምን አይነት
ሚና ልንጫወት እንችላለን?