
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዕብ. 5፡1-10፣ ዘፍ. 14፡ 18-20፣ 1 ጴጥ. 2፡9፣ ዕብ. 7፡1-3፣ ዕብ. 7፡11-16፣22፣26።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና” (ዕብራውያን 7፡26)
በ
እኛና በእግዚአብሔር መካከል የተፈጠረው ጉድጓድ በኃጢአት
ምክንያት የመጣ ነው። ችግሩ እንዲከፋ ያደረገው ደግሞ ኃጢአት
ተፈጥሯችንን ስለሚያበላሸው ነው። እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፤
በርሱ መገኘት ውስጥ ኃጢአት አብሮ ሊሆን አይችልም። ልክ ሁለት
ማግኔቶች በተቃራኒ በኩል ሲገናኙ እንደሚገፋፉት የተበላሸው ተፈጥሯችን
ከእግዚአብሔር ለይቶናል። በተጨማሪም የተበላሸው ማንነታችን
ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ እንዳንችል አድርጎናል። ኃጢአት ማስተዋል
ማጣትንም አምጥቷል። የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት ምስልን
አጥተውና ብዙ ከኛ የሚጠብቅ አድርገው ማየት ጀመሩ።
በዚህ ሳምንት ድልድይን ለመስራት አብና ወልድ ያደረጉትን አስደናቂ ነገር
እንመለከታለን። ዕብራውያን 5-7 የኢየሱስን ክህነት በጥንቃቄ ይተነትናል።
ፀሐፊው መነሻውንና አላማውን (ዕብ. 5፡1-10) በመግለፅ አንባቢዎች ችላ
እንዳይሉት (ዕብ. 5፡11-6፡8) በተቃራኒው የሚሰጠውን ተስፋ አጥብቀው
እንዲይዙት (ዕብ. 6፡9-20) ይመክራል። በተጨማሪም የርሱን ክህነት ይዘትና
(ዕብ. 7፡1-10) እግዚአብሔር ከአማኞቹ ጋር ባለው ግንኙነት ውስጥ ክህነቱ
ያለውን አንድምታ (ዕብ. 7፡11-28) ያብራራል። በዚህ ሳምንት በዕብራውያን
5፡1-10ና ዕብራውያን 7፡1-28 ላይ ያተኩራል።
ለጥር 28 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ዕብራውያን 5፡1-10ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ መሠረት የካህን ሚና ምንድነው? ኢየሱስስ ያንን የፈፀመው እንዴት ነው?
የካህን ዋና አላማ በኃጢአተኛው ሕዝብና በእግዚአብሔር መካከል ማማለድ
ነው። ካህናት ሰዎችን ወክለው እንዲያገለግሉ በእግዚአብሔር የሚሾሙ
ናቸው፤ ስለዚህ የሰዎችን ድክመት የሚረዱና የሚራሩ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
በዕብራውያን 5፡5-10፣ ጳውሎስ ኢየሱስ ያንን እንደሚያሟላ ያሳያል።
እግዚአብሔር ሾሞታል (ዕብ. 5፡5-6) እንዲሁም ኢየሱስ እርሱ ራሱ መከራን
ስለተቀበለ እኛን ያስተውለናል(ዕብ. 5፡7-8)።
ሆኖም አንዳንድ ዋና ዋና ልዩነቶችም አሉ። ኢየሱስ ከሰዎች መካከል
አልተመረጠም (ዕብ. 5፡1)። በተቃራኒው በኛ ምትክ ካህን ሆኖ ያገለግል
ዘንድ ኢየሱስ የሰውን ተፈጥሮ ለበሰ። ኢየሱስ ኃጢአት አልባ ስለነበረ ለራሱ
ኃጢአት መስዋዕት አላቀረበም(ዕብ. 4፡15፣ ዕብ. 7፡26-28)፤ ነገር ግን ስለኛ
ኃጢአት ብቻ አቀረበ።
የዕብራውያን መልዕክት እንደሚነግረን ኢየሱስ “ከሞት ሊያድነው ወደሚችል
ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም
ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” (ዕብ. 5፡7)። የዕብራውያን መልዕክት እግዚአብሔር
ኢየሱስን የታደገው ከሞት ሲነሳ ከሁለተኛው ሞት እንደነበር ይጠቅሳል(ዕብ.
13፡20)። በተጨማሪም መልዕክቱ ኢየሱስ “ከተቀበለው መከራ መታዘዝን
እንደተማረ” (ዕብ. 5፡8) ይናገራል። መታዘዝ ለኢየሱስ አዲስ ነገር ነበረ፤
ምክንያቱም ታዛዥ ስላልነበረ ሳይሆን አምላክ ስለነበረ ነው። በዓለማት
ላይ ሉዓላዊ እንደመሆኑ ኢየሱስ ማንንም አልታዘዘም፤ በተቃራኒው ሁሉም
ይታዘዙት ነበር።
የኢየሱስ መሰቃየትና በመስቀል ላይ መሞት የክህነት አገልግሎቱ አስፈላጊ
ክፍሎች ናቸው። መከራዎች ክርስቶስን ያስተማሩት ከግብረገብ አንፃር
አልነበረም። ስቃዮች እርሱን ሩህሩህ እንዲሆን አላደረጉትም። ሁሌም ሩህሩህ
ነበር፤ ለዚያ ነው ለእኛ የራራልን (ዕብ. 2፡17)። የእብራውያን መልዕክት እያለ
ያለው የኢየሱስ ወንድማዊ ፍቅር፣ የሰብዓዊነት ጥልቀቱና እንደ ሰው ልጅ
ወኪል ለአባቱ ፈቃድ የመገዛቱ ጥልቀት የታየውና የተገለፀው በመከራዎች
ውስጥ ነው ማለቱ ነው። ፍፁም ሆነ ሲባል መከራዎቹ ሊቀካህናችን እንዲሆን
ብቁ አደረጉት ማለቱ ነው። ሙሉ በሙሉ የመታዘዝ ህይወቱና በመስቀል ላይ
መሞቱ እንደ ካህን ኢየሱስ በአባቱ ፊት ያቀረበው መስዋዕት ይዘት ናቸው።
1ጴጥ. 2፡9 እንደሚናገረው እኛ የንጉስ ካህናት ነን። በዚህ
የተቀደሰ ኃላፊነት ውስጥ ስላለን የኢየሱስ ህይወት ከሌሎች ሰዎች
ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት ምን ይነግረናል?
ዘፍጥረት 14፡18-20ንና ዕብራውያን 7፡1-3ን ያንብቡ መልከ ጼዴቅ ማን ነበር? ኢየሱስንስ ያመላከተው እንዴት ነው?
መልከ ጼዴቅ ንጉስም ካህንም ነበር። አብርሃም ለርሱ አስራትን ስለሰጠው
ከአብርሃም በኋላ ነበረ።ልክ እንደዚያው ኢየሱስ ንጉስና ካህን ነው(ዕብ.1፡
3)፤ከመልከ ጼዴቅ በተቃራኒ ግን ኢየሱስ ኃጢአትን አላደረገም(ዕብ.7፡2628)።
ዕብራውያን 7፡15 እንደሚገልጸው ኢየሱስ “እንደ መልከ ጼዴቅ” ካህን እንደሆነ
ይገልጻል። ቀደም ብሎ “እንደመልከ ጼዴቅ ስርዓት(ዕብ 5፡6) የሚለው
አገላለጽ ይህንኑ ለማለት ነው። ኢየሱስ የመልከ ጼዴቅ አልጋ ወራሽ ሳይሆን
ክህነቱ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ነበር።
ለምሳሌ ጳውሎስ እንደሚናገረው መልከ ጼዴቅ አባት፣እናት፣የዘር
ሀረግ፣ለዘመኑ ጥን ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም። አንዳንዶች መልከ ጼዴቅ
በአብርሃም ዘመን ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ነው ብለው ይሞግታሉ። ነገር ግን ይህ
ኃሳብ ከዕብራውያን መልዕክት ሙግት ጋር አብሮ አይሄድም። መልከ ጼዴቅ
ኢየሱስን “ይመስላል” ማለት ከኢየሱስ የተለየ ነበረ ማለት ነው(ዕብ.7፡3)።
በሌላ በኩል ደግሞ መልከ ጼዴቅ ከሰማይ የመጣ ፍጡር ነው ተብሎ
ይታመናል፤ይህም የዕብራውያን መልዕክትን ያፈርሳል። መልከ ጼዴቅ ያለ
አባት፣ያለ እናት፣ያለ መጀመሪያና መጨረሻ ከነበረ ራሱ እግዚአብሔር ሆነ
ማለት ነው። ይህ ችግርን ያመጣል። የመልከ ጼዴቅ ሰማያዊና ሙሉ በሙሉ
መለኮታዊ የሆነ ክህነት ከኢየሱስ አገልግሎት በፊት ይሆን ነበር። ይህ ቢሆን
ኖሮ የዕብራውያን መልዕክት እንደሚለው “ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለምን
ያስፈልጋል?”(ዕብ.7፡11)።
በተቃራኒው የዕብራውያን መልዕክት የመልከ ጼዴቅን አባት፣እናት፣ሞትና
የዘር ሀረግ በተመለከተ የመጽሐፍ ቅዱስን ዝምታ በመጠቀም ለኢየሱስ
የክህነት አገልግሎት እና ኢየሱስ ዘላማዊ ለመሆኑ ምሳሌ ያደርገዋል(ዘፍ.14፡
18-20)። በአጭሩ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነ ከነዓናዊ ንጉስ-ካህን
ነበር።
ከፍ ያለው አምላክ ካህን በሆነው በመልከ ጼዴቅ በኩል ሲናገር የነበረው
ክርስቶስ ነበር። መልከ ጼዴቅ ክርስቶስ አልነበረም፤የአብ ወኪል ሆኖ በዚህ
ዓለም የእግዚአብሔር ድምጽ ነበረ።በቀደሙት ትውልዶች ሁሉ ክርስቶስ
ሲናገር ነበረ፤እርሱ ህዝቡን መርቷል እንዲሁም የዓለም ብርሃን ነበር።Ellen.G.White,selected Messages,book1,p.409
ስለ መልከ ጼዴቅ የተነገረው መገለጥ ሰው ሊመሰክርላቸው ባልቻለ
ሰዎች እንዴት እግዚአብሔር እንደሚሠራ ምን ያስተምረናል?
“ፍፁምነት የተገኘውና ሕጉ ለሕዝቡ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ቢሆን
ኖሮ፣ እንደ አሮን ሳይሆን እንደ መልከ ፄዴቅ ሹመት ለምን አስፈለገ?” (ዕብ.
7፡11)
ካህናት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል አማላጆች ናቸው። ሆኖም
የዕብራውያን መልዕክት እንደሚነግረን ሌዋውያኑ ካህናት ፍፅምናን መስጠት
ስላልቻሉ ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት አልቻሉም(ዕብ. 7፡11፣18፣19)።
ደግሞስ ራሳቸውም ፍፁማን አልነበሩም እንዴት ለሌሎች ፍፅምናን መስጠት
ይችላሉ?
የእንስሳት መስዋዕቱም የኃጢአተኛውን ህሊና ሊያነፁ አልቻሉም። አላማቸው
ብቻውን እውነተኛ ከኃጢአት መንፃትን ሊሰጥ ወደሚችለው ወደ ኢየሱስና
መስዋዕቱ ማመላከት ነበር(ዕብ. 9፡14፣ ዕብ. 10፡1-3፣ 10-14)። የሌዋውያኑ
ካህናት አገልግሎትና የሚያቀርቧቸው መስዋዕቶች ጊዜያዊና ተምሳሌታዊ
ነበሩ። በእነርሱ አገልግሎት እግዚአብሔር “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
የእግዚአብሔር በግ” በሆነው በኢየሱስ የወደፊት አገልግሎት ላይ እምነታቸውን
እንዲያደርጉ ሊመራቸው ፈለገ።
ዕብራውያን 7፡11-16ን ያንብቡ። ህጉን መቀየር ያስፈለገው
ለምን ነበር?
ዕብራውን 7፡12 የክህነት ለውጡ የህግ ለውጥ እንዲመጣ እንዳደረገ ይገልፃል።
ለምን? ምክንያቱም ህጉ በአሮን በኩል የሌዊ ዘር ያልሆነ ሰው እንደ ካህን
እንዲያገለግል ስለማይፈቅድ ነበር(ዘሁ. 3፡10፣ዘሁ. 16፡39-40)። ዕብራውያን
7፡13-14 እንደሚገልፀው ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ ስለሆነ ይህ ህግ ካህን ከመሆን
ከልክሎት ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደካህን ሲቀባው
ሕጉን ቀይሮታል ማለት ነው ብሎ ጳውሎስ ይከራከራል።
የኢየሱስ መምጣት የመስዋዕት ህጎቹ መቀየራቸውንም ያመላክታል።
ኃጢአተኞች ስርየትን ለማግኘት የተለያዩ አይነት መስዋዕቶችን ማቅረብ
ይጠበቅባቸው ነበር(ዘሌዋውያን 1-7)፤ አሁን ግን ኢየሱስ መጥቶ ፍፁም የሆነ
መስዋዕትን አቅርቧል። በዚህ እንዲሁም በአዲሱ ኪዳንና በድነት ዕቅድ ሙሉ
መገለጥ ምክንያት የእንስሳት መስዋዕቶቹ ቀርተዋል(ዕብ. 10፡17-18)።
በመተላለፍ ምክንያት ኢየሱስን ወደፊት እያመላከቱ መስዋዕት
ስለሆኑት እንስሳትና አንዳቸውም ለኃጢአት እውነተኛ ክፍያ
መክፈል አለመቻላቸውን ያስቡ። ይህንን የክርስቶስ ሞት ብቻ
ሊያደርግ የቻለው በምን ምክንያት ነው?
ዕብራውያን 7፡16ን ያንብቡ። ኢየሱስ ካህን የሆነው በምን አይነት መልክ ነው?
ኢየሱስ ክህነትን የተቀበለው ዘላለማዊ አግልግሎትን ስለያዘና የማይጠፋ
ህይወት ስላለው ነው። የነዚህ እውነቶች ፋይዳ አስደናቂ ነው። ይህ ማለት
የኢየሱስ አገልግሎት የማይናቅ ወይም ጊዜ የማያልፍበት ነው ማለት
ነው። ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ፣ለዘላለም እንዲሁም ፈጽሞ ያድናል (ዕብ.7፡
25)። ኢየሱስ የሚሰጠው ማዳን ሙሉ የሆነና የማያዳግም ነው። የሰውን
ልጅ ውስጣዊ ጥልቀት ይደርሳል(ዕብ.4፡12፣ዕብ.9፡14፣ዕብ.10፡1-4)።
በእግዚአብሔር ፊት የሚሆነው የኢየሱስ ምልጃ በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ያሉትን
በረከቶች ሁሉ ያጠቃልላል።
ከኃጢአት ይቅርታም ያለፈ ነው። ህጉን በልቦናችን ማረግን፣በርሱ ውስጥ
እኛን አዲስ ሰው ማድረግንና ለዓለም ወንጌል ማዳረስን ያካትታል(ዕብ.8፡1012)። ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንደመሆኑ በአብ ፊት ይወክለናል።
ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ እንደመስጠቱ ኢየሱስ በአብ ፊት ሞገስን
አግኝቷል።
ዕብ.7፡22ን ያንብቡ። ከአዲሱ ኪዳን ጋር በተያያዘ ኢየሱስ
ምንድነው?
ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ማረጋገጫ(ዋስትና) ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር
እርሱ ለዘላለም ካህን እንደሚሆን ምሏል(ዕብ.7፡21)። የዚህን መሃላ ፋይዳ
አለመረዳት እጅግ ቀላል ነው።ጳውሎስ እግዚአብሔር ለበረሃው ትውልድና
ለአብርሃም የገባቸውን መሃላዎች እየጠቀሰ ተናግሯል(ዕብ. 3፡7-11፣ዕብ. 6፡1315)። በነዚህ መሃላዎችና ለወልድ እግዚአብሔር በገባው መሃላ መካከል ያለው
ልዩነት እነዚያ መሃላዎች ለሟች ሰዎች የተነገሩ መሆናቸው ነው። መሃላዎች
የሚጸኑት የተማማሉት በህይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው። እግዚአብሔር
ለበረሃው ትውልድና ለአብርሃም የገባቸው መሃላዎች የሚጸኑት የበረሃው
ትውልድና የአብርሃም ዘሮች(ገላ. 3፡29) በህይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው።
ሆኖም የማያልፍ ህይወት ላለው ለወልድ የተገባው መሃላ ግን ለዘላለም የጸና
ነው። ለሌላ ሰው ዋስ የሆነ ሰው ያ ሰው የሚከፍለውን ቅጣት ሞትም ቢሆን
ሊከፍል ይገባዋል። እንዲህም ሆኖ አብ ከተስፋ ቃሎቹ እንዳያጎድል ኢየሱስን
የኛ ዋስ አደረገው። በኢየሱስ ስለተሰጠን መዳን እርጠኛ መሆን የምችለው ያን
ያክል ነው።
ዕብራውያን 7፡26ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ የኢየሱስ አምስት ባህሪያት ምንድናቸው?
ኢየሱስ ቅዱስ ነበር። ማለትም ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር በነበረው ግንኙነት
ያለ ነቀፋ(ያለ እንከን) ነበር(ዕብ.2፡18፣ዕብ.4፡15፣ዕብ.5፡7-8)። የብሉይ ኪዳን
የጥንት የግሪክ ትርጉም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ያላቸውን ቃልኪዳናዊ
ግንኙነት ጠብቀው የሚኖሩትን ለመግለጽ ተመሳሳዩን የግሪክ ቃል ተጠቅሟል።
ኢየሱስ ያልረከሰ ነበር። በሁሉም ነገር ቢፈተንም ንጹህና ክፋት ያልነካው
ሆኖ ጸና(ዕብ.4፡15)፣ዕብ.2፡18)። የኢየሱስ ፍጹም የሆነ ኃጢአት አልባነት
ለክህነቱ አስፈላጊ ነው። ብሉይ ኪዳን መስዋዕት የሚሆኑት በእግዚአብሔር
ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያለ እንከን መሆን እንዳለባቸው ይገልጻል(ዘሌ.1፡
3፣10)። በዚህ ምድር በነበረው አገልግሎት የኢየሱስ ፍጹም ታዛዥ መሆን
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መስዋዕት አድርጎ ራሱን እንዲያቀርብ
አስችሎታል(ዕብ.9፡14)።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ ከኃጢአተኞች ተለይቶ ነበር። የግሪኩ ቃል
የሚነግረን ይህ አንድ የሆነ ጊዜ ላይ የጀመረና እስካሁንም ኢየሱስ ያለበትን
እንደሚገልጽ ነው። ኢየሱስ በምድራዊ ህይወቱ ከኃጢአተኞች ግፍ
ቢደርስበትም አሸናፊ ሆኖ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል(ዕብ.12፡2-3)።
በተጨማሪም አየሱስ ፍጹም ከኃጢአት የነጻ ስለነበረ ከኃጢአተኞች ተለይቷል
ልንል እንችላለን(ዕብ.4፡15)።
ኢየሱስ ከሰማያት በላይ… ከፍ ብሏል። ማለትም ኢየሱስ ካለው ነገር ሁሉ ከፍ
ያለ ስለሆነ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ነው። በመዝሙረ ዳዊት በሰማያት ላይ
ከፍ ከፍ ያለው እግዚአብሔር ነው ይላል (መዝ. 57፡5፣መዝ. 108፡5)።
ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው የነበረ ቢሆንም እንደ እኛ ኃጢአተኛ
አልነበረም(ዕብ.2፡14-16፣ዕብ.4፡15)።ኢየሱስ ኃጢአት ስላላደረገ ብቻ ሳይሆን
እንደኛ በኃጢአት ስላልተበላሸ ፍጹም ነው።
ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ ሰው የነበረ ቢሆንም ምሳሌያችንም ነበረ።የህይወትን
ሩጫ
እንዴት
መሮጥ
እንዳለብን
አሳይቶናል(ዕብ.12፡1-4)።
ልንከተለው የሚገባን ምሳሌያችን እርሱ ነው(1ጴጥ. 2፡21-23)። እርሱ
“ቅዱስ፣ንጹህ፣ያልረከሰ፣ከኃጢአተኞች የተለየ”(ዕብ.7፡26) ስለሆነ አዳኛችን
ነው፤እኛም የርሱን ባህሪ መከተል እንችላለን።
ኢየሱስ እንደ እኛ ሰው የነበረ ቢሆን ኃጢአትን አላደረገም።
በዚህ ድንቅ ኃሳብ ላይ አእምሯችንን ማሳረፍ የምንችለው እንዴት
ነው? ምን ያክል ቅዱስ እንደነበረ ያስቡ። የርሱ ቅድስና በእምነት
የኛ መሆኑ ለመዳናችን ማረጋገጫ የሚሆነው እንዴት ነው?
“ክርስቶስ እያየ ነው። ስለ ሸክማችን፣ ስለ አስጊ
ሁኔታዎቻችን፣ ስለ ከበዱን ነገሮች ስለሚያውቅ አፉን ሞልቶ ስለ እኛ ሊከራከር
ይችላል። ልክ ለጴጥሮስ እንዳደረገው ለእያንዳንዱ ነፍስ ይማልዳል። . . .
አማላጃችን የተፈተኑትን፣በችግር ያሉትን ከሰይጣን ፈተናዎች ለመታደግ
የርሱ የሆነውን ለማስተማር ለኛ ይቆማል። የጠላትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ
ይተረጉምልናል። ትዕዛዝንም ያስተላልፋል።” Ellen G. White, SDA Bible
Commentary, vol. 7, p. 931 (Letter 90, 1906)
“በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ዘላለማዊ ልዩነትን ማምጣት የሰይጣን
አላማ ነበር፤ ነገር ግን በክርስቶስ አማካኝነት ከውድቀታችን በፊት ከነበርነው
በላይ የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ቀረብን።
የኛን ተፈጥሮ በመውሰድ
አዳኛችን ከሰብዓዊ ዘር ጋር ራሱን በማይበጠስ መልኩ አስተሳስሮናል።…ይህ
እግዚአብሔር ቃሉን እንደሚጠብቅ ማስተማመኛ ነው። ሕጻን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። እግዚአብሔር
በወልድ አካል ውስጥ የሰውን ተፈጥሮ ወስዷል፤ያንን ከፍ እስካለው ሰማይ
ድረስ ይዞ አውጥቶታል። የዓለማትን ገዢነት የተካፈለው “የሰው ልጅ” ነው።
ስሙ “ድንቅ፣መካር፣ኃያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሠላም አለቃ” የሚባለው
“የሰው ልጅ” ነው(ኢሳ.9፡6)።
በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከለኛ ሆኖ
በሁለቱም ላይ እጁን የጫነው እኔ ነኝ ያለው ያሕዌ ነው። “ቅዱስ፣ማንንም
የማይጎዳ፣ ያልረከሰ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ” የሆነው እርሱ ወንድሞቼ ብሎ
ሊጠራን አላፈረብንም (ዕብ. 7፡26፣2፡11)። በክርስቶስ የምድር ቤተሰብና
የሰማይ ቤተሰብ ተጣምረዋል። የከበረው ክርስቶስ ወንድማችን ነው። ሰማይ
በሰብአዊነት ውስጥ ተቀርጿል፤ ሰብአዊነትም በማያልቀው ፍቅር ክንድ
ታቅፏል።” ኤለን. ጂ. ኃይት፣የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 25፣26
1. ከላይ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ኃሳብ “ኢየሱስ አፉን ሞልቶ
ስለ እኛ ይከራከራል።” ይላል። ያ የተስፋ ቃል ለርስዎ ምን ትርጉም
አለው? ይህ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ምን እንደሚያስተምረን
ያስቡ። ይህ ኃሳብ የሚያበረታ የሆነው ለምንድነው? በኛ ፈንታ
የሚከራከርልን የፈለግነው ለምንድነው?
2. ከላይ የተጠቀሰው ሁለተኛው ጥቅስ “በክርስቶስ አማካኝነት
ከመውደቃችን በፊት ከነበርነው በላይ ወደ እግዚአብሔር
ቀረብን” ይላል። ያ ምን ማለት ነው? ያንን ቅርርብ መለማመድ
የምንችለው እንዴት ነው? ከዚያ ልምምድ ምን ማጽናኛን
እናገኛለን? በሰንበት ትምህርት ክፍልዎ ይህ መቀራረብ ምን
ማለት እንደሆነና ያንን መለማመድ እንዴት እንደሆነ ይግለጹ።
“በኛ ፈንታ መከራከሩ(መቆሙ)” ይህ ልምምድ እንዲኖረን
የሚያደርገው እንዴት ነው?