
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዕብ. 6፡4-6፣ ማቴ. 16፡ 24 ፣ ሮሜ 6፡6፣ ዕብ. 10፡26-29፣ ዕብ. 6፡9-13፣ ዕብ. 6፡17-20።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤ በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ።” ዕብ. 6፡19-20
ዕ
ብራውያን 5፡11 – 6፡20 ኢየሱስ በኛ ፋንታ ስለሚያደርገው ክህነት
የሚገልፀውን ስነመለኮታዊ ማብራሪያ ያቋርጣል። እዚህ ጋ ጳውሎስ
ከክርስቶስ ስለ መውደቅ አደጋ ማስጠንቀቂያ ያዘለውን መልዕክት
ያስገባል።
በግልፅ በሚታይ ሁኔታ ህዝቡ ራስን በመውደድና እምነት አልባ በመሆን ወደ
ኋላ የመንሸራተት አደጋ አጋጥሟቸው ነበር። ጳውሎስ አንባቢዎቹና ሰሚዎቹ
በገጠሟቸው ከባድ ሁኔታዎች መንፈሳዊ ስሜታቸው ዶልዱሞ ለወንጌሉ
ያላቸው መረዳትና ልምምድ ማደጉን አቁሞ እንዳይሆን ፈርቶ ነበር።
ይህ በእኛም ላይ አደጋ የጋረጠ ነገር አይደለምን? - በመከራዎች ተስፋ ቆርጦ
ወደ ኋላ ማፈግፈግ።
ሆኖም ከበድ ያለው ማስጠንቀቂያ ልባዊ የሆነ ማበረታቻንም ይዟል። ጳውሎስ
በአንባቢዎቹ ላይ ያለውን እምነት እየገለፀ ኢየሱስን ደግሞ የማይለወጠው
የእግዚአብሔር የማዳን ተስፋ በአካል መገለፅ እንደመሆኑ ከፍ ያደርገዋል
(ዕብ. 6፡9-20)። ይህ አይነቱ የማስጠንቀቅያና የማበረታቻ አብሮ መገለፅ
(ኡደት) በዕብራውያን 10፡26-39 ላይም ተደግሟል።
ይህንን ዑደት የምናጠና ሲሆን ኢየሱስ በሚሰጠን ጠንካራ ማበረታቻዎች ላይ
እናተኩራለን።
የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለየካቲት 5 ሰንበት ይዘጋጁ።
ዕብራውያን 6፡4-5ን ያንብቡ። አማኞች ለክርስቶስ ታማኝ በመሆናቸው ምን ተሰጥቷቸዋል?
ብርሃን የበራለት መሆን ማለት ለውጥን መለማመድ ማለት ነው (ዕብ. 10፡32)። ከሰይጣን ኃይል “ጨለማ” ወደ እግዚአብሔር “ብርሃን” የተመለሱትን
የሚወክል ቃል ነው( የሐዋ. ሥራ 26፡17-18)። ከ“ኃጢአትና” “ከአለማወቅ”
ነፃ መውጣትን ያመለክታል (ኤፌ. 5፡11፣ 1 ተሰ. 5፡4-5)። ቃሉ ይህ የብርሃን
መብራት “የክብሩ መንፀባረቅ” በሆነው ኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር
የሚያደርገው እንደሆነ ይናገራል(ዕብ. 1፡3)።
“ሰማያዊውን ስጦታ ማጣጣምና” “ከመንፈሱ ተካፋይ መሆን” ተመሳሳይ
አገላለፆች ናቸው። የእግዚአብሔር ስጦታ ፀጋውን (ሮሜ 5፡15) ወይም
እግዚአብሔር ፀጋውን የሚያፈስበትን መንፈስ ቅዱስን ሊያመላክት
ይችላል(ሐዋ. ሥራ 2፡38)። መንፈስ ቅዱስን የቀመሱት (ዮሐ. 7፡37-39፣
1 ቆሮ. 12፡13) የእግዚአብሔርን ፀጋም ተለማምደውታል፤ ይህም ፈቃዱን
የመፈፀም ኃይልንም ይመለከታል(ገላ. 5፡22-23)
የቃሉን መልካምነት ማጣጣም (ዕብ. 6፡5) በግለሰብ ደረጃ የወንጌሉን እውነት
መለማመድ ማለት ነው(1 ጴጥ. 2፡2-3)። “የሚመጡት ዘመናት ኃይላት”
የሚለው ወደፊት እግዚአብሔር ለአማኞቹ የሚፈፅማቸውን ተዓምራት፡
ማለትም ትንሳኤ(ዮሐንስ 5፡28-29)፣ የአካላችንን መለወጥና ዘላለማዊ
ህይወታችን ነው። ሆኖም አማኞች አሁን ያንኑ ማጣጣም ጀምረዋል።
መንፈሳዊ ትንሳኤን (ቆላ. 2፡12-13)፣ የታደሰ አእምሮን(ሮሜ 12፡2) እና
በክርስቶስ ዘላለማዊ ህይወትን (ዮሐ. 5፡24) ተለማምደዋል።
ምናልባትም ጳውሎስ በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን ፀጋና ማዳን
የተለማመመዱትን ትውልድ በአእምሮው እያሰበ ይሆናል። በምድረ በዳ
የነበረው ትውልድ በእሳት አምድ ብርሃን በርቶለታል(ነህ. 9፡12፣ መዝ. 105፡
39)፣ የሰማይ ስጦታ የሆነውን መና በልቷል(ዘፀ. 16፡15) መንፈስ ቅዱስን
ተለማምዷል (ነህ. 9፡20) የእግዚአብሔርን መልካም ቃልና(ኢያሱ 21፡
45) ከግብፅ ሲወጡ ባዩአቸው ተዓምራት ውስጥ “የሚመጡትን ዘመናት
ኃይል” (የሐዋ. ሥራ 7፡36) አጣጥመዋል።
ሆኖም ጳውሎስ እንደሚናገረው
የምድረበዳው ትውልድ እነዚያን ሁሉ ማስረጃዎች እያዩ እግዚአብሔርን
እንደካዱ የዕብራውያን መልዕክት አንባቢያንም ምንም እንኳን ብዙ
የእግዚአብሔርን ፀጋዎች ማሳያ የሆኑ ማስረጃዎች ቢኖሩም የእስራኤልን
ስህተት የመድገም አደጋ ውስጥ ነበሩ።
በዕብራውያን ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ጥቅሶች የሚናገሩት አይነት
የራሰዎ ልምምድ ካለዎት ቢያካፍሉት? ለምሳሌ ይህ ጥቅስ
የሚናገርለትን ብርሃን እርስዎ የተለማመዱት እንዴት ነበር?
ዕብ.6፡4-6ን፣ማቴዎስ 16፡24ን፣ሮሜ 6፡6ን፣ገላ.2፡20፣ገላ 5፡24ንና ገላ.6፡14ን ያነጻጽሩ። ይህ ንጽጽር ክርስቶስን መስቀል ላይ ምን ማለት እንደሆነ ምን ይነግረናል?
በግሪኩ የመጀመሪያው(ኦርጅናሉ) ቃል የማይቻል የሚለው ላይ ያጠነክራል።
ለእግዚአብሔር የወደቁትን ለመመለስ የማይቻል ነው ምክንያቱም
የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና እየሰቀሉት ስለሆነ ነው(ዕብ.6፡6)። ጳውሎስ
በክርስቶስ በኩል ካልሆነ ሌላ መጽደቂያ መንገድ የለም የሚባለውን ማጠንከር
ፈልጓል(የሐ.ሥራ 4፡12)። በሌላ መንገድ መዳን ልክ እግዚአብሔር መዋሸት
እንደማይችለው ወይም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የመሞከርን
ያህል የማይቻል ነው(ዕብ.11፡6)።
የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና መስቀል የሚለው በክርስቶስና በአማኙ
መካከል ባለ የግል ግንኙነት ውስጥ የሚፈጠረውን ለመግለጽ የሚጠቅም
ዘይቤያዊ(ምሳሌያዊ) አገላለጽ ነው።
የሃይማኖት መሪዎቹ ኢየሱስን ሲሰቅሉት ለስልጣናቸውና ለታላቅነታቸው
አስጊ ነው ብለው ስላሰቡ ነበር። ስለዚህ እንደ አንድ ግለሰብ ኢየሱስን
አስወግደው ኃይለኛና አደገኛ ጠላትን ለማጥፋት ተስፋን ሰነቁ። በተመሳሳይ
ወንጌሉ እጅግ ማዕከላዊ በሆነ ደረጃ የአንድን ሰው ልዕልናና ውሳኔ
ይገዳደራል። የክርስትና ህይወት ትርጉም መስቀሉን መሸከምና ራስን መካድ
ነው(ማቴ 16፡24)። ይህም ማለት አለምን (ገላ.6፡14)፣ የድሮው ሰው(ሮሜ.6፡
6) እና ስጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር(ገላ.5፡24) መስቀል ማለት ነው።
የክርስትና ህይወት አላማ ሞት የሚመስል ነገርን መለማመድ ነው። ይህንን
ለራስ መሞትን ካልተለማመድን እግዚአብሔር ሊሰጠን የሚፈልገውን አዲሱን
ህይወት መቀበል አንችልም(ሮሜ.6፡1-11)።
በኢየሱስና በራስ መካከል ያለው ትግል እስከሞት ድረስ(ሮሜ.8፡7-8፣ገላ.5፡
17)። በአንድ ጊዜ የማናሸንፈው ከባድ ጦርነት ነው። ይህ ጥቅስ ከአሮጌው
ሰው እና ከስጋ ጋር ባለ ጦርነት አንዳንድ ጊዜ የሚወድቀውን ሰው ሁኔታ
እየገለጸ አይደለም።
ይህ ኃጢአት የተገለጠውን መዳንና የያዛቸውን በረከቶች
ከተለማመደ በኋላ እርሱ ለሚመኘው ህይወት ኢየሱስን እንደ እንቅፋት ቆጥሮ
ከርሱ ጋ የነበረውን ግንኙነት ለመግደል የሚንቀሳቀሰውን ሰው የሚመለከት
ነው። ይህ ማለት አንድ ሰው ለክርስቶስ ሙሉ ለሙሉ ጀርባውን ለመስጠት
እስካልመረጠ ድረስ የመዳን ተስፋ አለ ማለት ነው።
ለራስ መሞት፣መስቀሉን መሸከም ማለት ምን ማለት ነው ለኢየሱስ
ለመገዛት እጅግ ከባድ የሚሆንበት ነገር ምንድነው?
በዕብራውያን 6፡4-6 ላይ ያለው ማስጠንቀቂያ በዕብራውያን 10፡26-29 ካለው ጋር እጅግ ይመሳሰላል። ጳውሎስ እንደሚናገረው የኢየሱስን መስዋዕት መግፋት ከእርሱ ሌላ ምህረት የማግኛ መንገድ ስለሌለ አንባቢዎችን ያለ ምህረት ማግኛ መንገድ ይተዋቸዋል (ዕብ. 10፡1-14)። ዕብ. 10፡26-29ን ያንብቡ። ፀሐፊው ይቅርታ የሌለውን ኃጢአት የገለፀባቸው ሶስት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
ፀሐፊው አንድ ሰው የእውነትን እውቀት ከተቀበለ በኋላ ኃጢአት ቢሰራ
ስርየት አያገኝም እያለ አይደለም። እግዚአብሔር ኢየሱስን ጠበቃችን አድርጎ
ሾሞታል (1 ዮሐ. 2፡1)። በርሱ በኩል የኃጢአት ይቅርታ አግኝተናል (1 ዮሐ. 1፡
9)። ስርየት የሌለው ኃጢአት የእግዚአብሔርን ልጅ መርገጥ፣ የኪዳኑን ደም
እንደ እርኩስ ነገር መቁጠርና መንፈስ ቅዱስን ማክፋፋት(ዕብ. 10፡29) ተብሎ
ተጠርቷል። የእነዚህን አገላለፆች ትርጉም እስኪ እንመልከት።
የእግዚአብሔርን ልጅ መርገጥ(ዕብ. 10፡29) የሚለው አገላለፅ የኢየሱስን
ገዢነት አለመቀበልን የሚገልፅ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው መጠሪያ
አንባቢዎቹን እግዚአብሔር ኢየሱስን በቀኙ ማስቀመጡንና ጠላቶቹን
ከእግሮቹ በታች እንደሚያደርግለት የገባለትን ቃል ያስታውሳል (ዕብ. 1፡3፣ 1፡
5፣ 1፡12፣ 1፡14)። ኢየሱስ ከእግር በታች መርገጥ የሚያሳየው ያ የሳተው ሰው
ኢየሱስን እንደጠላት እንደሚመለከተው ነው።
በሙግቱ ዓውድ ላይ ተመስርተን(ዕብ. 1፡13) በሳተው ሰው ህይወት ኢየሱስ
ከዙፋኑ ተወግዶ(በምትኩ ራሱ ተቀምጦበት) በተቃራኒው ከእግሩ በታች
ሆኗል። ሉሲፈር በሰማይ ሊያደርግ የፈለገውና(ኢሳ. 14፡12-14) ወደፊት ደግሞ
“የአመፅ ሰው” ለማድረግ የሚሞክረው ይህንኑ ነው(2 ተሰ. 2፡3-4)።
“የኪዳኑን ደም እንደ እርኩስ ነገር መቁጠር” የሚለው አገላለፅ የኢየሱስን
መስዋዕት አለመቀበልን የሚያሳይ ነው(ዕብ. 9፡15-22)። የኢየሱስ ደም
የማንፃት ኃይሉን መከልከሉን ይገልፃል።
የፀጋውን መንፈስ ማክፋፋት(ዕብ. 10፡29) የሚለው አገላለፅ እጅግ ኃይለኛ
ነው። “ኢኒብሪሳስ” የሚለው የግሪኩ ቃል ባዶ የሆነ ጉራን ማለትም ስድና
ትዕቢተኛ መሆንን የሚገልፅ ነው። ይህ አገላለፅ መንፈስ ቅዱስን “የፀጋ መንፈስ”
ብሎ ከመጥራቱ ጋር እጅግ የተቃረነ ነው። የካደው ሰው ለእግዚአብሔር የፀጋ
ስጦታ በስድብ ምላሽ መስጠቱን ያመላክታል።
የካደው ሰው መመለስ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ኢየሱስን፣
መስዋዕቱንና መንፈስ ቅዱስን አልተቀበለም።
በዕብራውያን 6፡4-8 ከሚገኘው ጠንካራና ልባዊ ማስጠንቀቂያ በኋላ የመልዕክቱ አንባቢዎች ከክርስቶስ ተለይተው እንዳልወደቁ ወደፊትም እንደማይወድቁ ጳውሎስ እምነቱን ይገልጻል። እንባቢዎቹ ማስጠንቀቂያውን ሰምተው ተገቢውን ፍሬ እንደሚያፈሩ ያምናል። ልክ በእግዚአብሔር እንደታረሱ መሬት እና እርሱ የሚጠብቅባትን ፍሬ እንዳፈራች “መሬት” ናቸው። እነዚህ ሕዝቦች ከእግዚአብሔር በረከትን ይቀበላሉ(ዕብ.6፡7) እርሱም “መዳን” ነው(ዕብ.6፡9)። ዕብራውያን 6.9-12ን ያንብቡ። አንባቢዎቹ ያደረጓቸውንና እያደረጓቸው ያሉትን ነገሮች ዘርዝረዘችሁ ምን ማለት እንደሆኑ ግለጿቸው።
አማኞች ለእግዚአብሔር ስም ማለትም ለራሱ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር
የሚያሳዩት ለቅዱሳን በሚያደርጉት አገልግሎት ነው። እነዚህ በቀደመው ጊዜ
ብቻ የተፈጸሙ ተግባራት ብቻ ሳይሆኑ እስካሁን የቀጠሉ ተግባራት ናቸው።
እጅግ የተለዩ መልካም ተግባራት የአንድን ሰው እውነተኛ ባህሪ አያሳዩም።
እግዚአብሔርን ለመውደዳችን እጅግ ከባዱ ማስረጃ “ሃይማኖታዊ”
ተግባራት ብቻ ሳይሆኑ ለሌሎች ሰዎች በተለይም ለተጎዱት የምናሳየው ፍቅር
ነው(ማቴ.10፡42፣ማቴ.25፡31-46)።ስለዚህ ጳውሎስ መልካም ማድረግን
እንዳይረሱ ይመክራቸዋል(ዕብ.13፡2፣16)።
ዕብራውያን 6፡12ን ይመልቱ። ዳተኛ እንዳይሆኑ ማለትም መብሰል ያልቻና
የመውደቅ አደጋ ውስጥ ያሉ እንዳይሆኑ ያስጠነቅቃቸዋል(ዕብ.5፡11፣ዕብ.6፡
12)። ተስፋ ህያው ሆኖ የሚቆየው በአዕምሮ በማወቅና በሃሳብ በመለማድ
ብቻ ሳይሆን በፍቅር ተግባራት በሚገለጽ እምነት ነው(ሮሜ 13፡8-10)።
ጳውሎስ በእምነትና በትዕግስት ተስፋውን ያገኙትን እንድንመስል ይፈልጋል።
በአሉታዊ መልኩ እምነትና ጽናትን አጥተው የተገባላቸውን ተስፋ መጨበጥ
ያልቻሉትን የምድረ በዳውን ትውልድ ለትምህርት አቅርቧቸዋል።
ከዚያም
በእምነትና በትዕግስት የተገባለትን ተስፋ ያየውን አብርሃምን እንደ ምሳሌ
ያቀርባል(ዕብ.6፡13-15)። የመልካም ምሳሌዎቹ ዝርዝር ከእምነት ሰዎቹ ጋር
በዕብራውያን 11 የተቀመጠ ሲሆን ዕብራውያን 12 ላይ የዕምነትና የትዕግስት
ታላቁ ምሳሌያችን በሆነው በኢየሱስ ከፍ ብሎ ይደመደማል(ዕብ.12፡1-4)።
በራዕይ 14፡12 ላይ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚገኙት ቅዱሳን ባህሪያት ተብለው
የተጠቀሱት እምነት፣ትዕግስትና መታዘዝ ናቸው።
አንዳንድ ጊዜ የምንወዳቸውን ሰዎች ማስጠንቀቅ ይኖርብናል።
ማስጠንቀቅንና ማበረታታትን በተመለከተ ከሐዋርያው ምን
እንማራለን?
ጳውሎስ በክህደት ላይ ማስጠንቀቁን እንዲሁም ፍቅርና እምነትን ማበረታታቱን የሚደመድመው እጅግ ባማረ ሁኔታ በክርስቶስ ላይ እርግጠኝነትን በመስጠት ነው። ዕብራውያን 6፡17-20ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለኛ የገባውን ተስፋ ያረጋገጠልን እንዴት ነው?
እግዚአብሔር የገባልንን የተስፋ ቃላት በተለያዩ መንገዶች አረጋግጦልናል።
በመጀመሪያ የተስፋ ቃሎቹን ያረጋገጠው በመሃላ ነው(ዕብ. 6፡17)። እንደ
መጽሐፍ ቅዱስ ገለፃ እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የገባላቸው የተስፋ
ቃላት እርሱ ለእስራኤል ስላለው የፀና የፀጋ አቋም ጠንካራ ማረጋገጫ ሆኗል።
ሙሴ እግዚአብሔር እስራኤልን የወርቅ ጥጃ ከሰሩ በኋላ ይቅርታን እንዲያገኙ
ሲጠይቅ ለአብርሃም የገባውን መሃላ አስታውሶታል(ዘፀ. 32፡11-14፣ ዘፍ. 22፡
16-18)። የምልጃው ጥንካሬ የሚያሳየው የእግዚአብሔር መሃላ የማይሻር
መሆኑን ነው(ሮሜ 9፡4፣ ሮሜ 11፡28-29)።
በተመሳሳዩ መዝሙረኛው በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሲማልድ
እግዚአብሔር ለዳዊት የገባውን መሃላ መያዣ አድርጎ ነበር። እግዚአብሔር
“ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም። ዳዊትን
እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ። ዘሩ ለዘላለም፥ ዙፋኑም በፊቴ
እንደ ፀሐይ ይኖራል። ለዘላለም እንደ ጨረቃ ይጸናል ምስክርነቱ በሰማይ
የታመነ ነው።”(መዝ. 89፡34-37) ብሎ ተናግሯል። በአዲስ ኪዳን መሠረት
ሁለቱም መሃላዎች የአብርሃም ዘር በሆነውና በዳዊት ዙፋን ላይ በተቀመጠው
በክርስቶስ ተፈፃሚነትን አግኝተዋል(ገላ. 3፡13-16፣ ሉቃስ 1፡31-33፣ 54፣
55)።
በሁለተኛ ደረጃ እግዚአብሔር ለኛ የገባቸውን የተስፋ ቃላት ኢየሱስን በቀኙ
በማስቀመጥ አረጋግጦልናል። የኢየሱስ ማረግ ለአማኞች የተገባው ተስፋ
ማረጋገጫ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ያረገው “በኛ ፋንታ ከፊታችን ቀድሞ”
ስለሆነ ነው(ዕብ. 6፡20)። ስለዚህ እርገቱ የእግዚአብሔርን ማዳን እርግጠኛ
መሆኑን ይገልፅልናል። እግዚአብሔር ኢየሱስን ወደ ክብር የመራው ብዙ
ልጆችን ወደ ክብር ያመጣ ዘንድ(ዕብ. 2፡9-10) ለሁሉም ሰው እንዲሞት
በማድረግ ነው። የኢየሱስ በአብ ፊት መሆን ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር
የተያያዘ የነፍስ መልህቅ ነው(ዕብ. 6፡19)። በኢየሱስ በኩል ለኛ የገባው የተስፋ
ቃል ፍፃሜ በማግኘቱ ለእግዚአብሔር ገዢነት ክብር እንሰጣለን።
እግዚአብሔር ከአንተ/ቺ ጋር መሃላ መግባቱን ሲያስቡ ምን
ይሰማዎታል? ያለመገባት ሲሰማንም ቢሆን እንኳን ያ ኃሳብ
ብቻውን ስለመዳናችን እርግጠኛ የሚያደርገን እንዴት ነው?
Acts of the Apostles በሚለው መጽሐፍ ውስጥ “John
the Beloved” የሚለውን ርዕስ ከገጽ 539-545 ድረስ ያለውን እንዲሁም
የዘመናት ምኞት በተባለው መጽሐፍ ውስጥ “ይሁዳ” የሚል ርዕስ ያለውን
ምዕራፍ ያንብቡ።
“ከራስ ጋር የሚደረገው ጦርነት ከተደረጉት ጦርነቶች ሁሉ እጅግ ታላቁ ነው።
ራስን ማስገዛት፣ ሙሉ ፈቃድን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስረከብ ትግልን
ይጠይቃል፤ ነገር ግን ነፍስ በቅድስና ከመታደሷ በፊት ለእግዚአብሔር ልትገዛ
ያስፈልጋታል።” ኤለን ጂ ኋይት ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንድ ገጽ 44።
ዮሐንስ እንደ ኢየሱስ መሆንን ተመኘ በሚለውጠው በክርስቶስ ፍቅር ኃይል
ትሁት መሆን ቻለ። ራስ በኢየሱስ ውስጥ ተደብቆ ነበር። ከጓደኞቹ ሁሉ በላይ
ዮሐንስ ለዚያ አስደናቂ ህይወት ኃይል ራሱን አስገዛ።
ዮሃንስ ሁልጊዜ ከኢየሱስ ጎን ወደመሆን የመራው ለእርሱ ያለው ጥልቅ ፍቅር
ነበር። አዳኛችን ሁሉንም አስራ ሁለቱን ይወድ ነበር። ነገር ግን ዮሐንስ የበዛ
የመቀበል መንፈስ ነበረው ከሌሎቹ ይልቅ በዕድሜው ትንሽ የነበረ ሲሆን
እንደ ልጅ በመተማመን ልቡን ለኢየሱስ ከፈተ ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር እጅግ
ተቀራረበ፤በርሱ በኩል የአዳኙ ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቶች ለህዝቡ ተላለፉ።
“እርሱን የቀየረው የቅድስና ውበት ክርስቶስን በመሰለ ነጸብራቅ ከፊቱ
ተንጸባረቀ። አዳኙን በፍቅር ትኩር ብሎ በመመልከት እርሱን መምሰል
ቻለ፤ከርሱ ጋር ህብረት ማድረግ የእርሱ ብቸኛ ፍላጎቱ ሆነ፤በባህሪው
ውስጥም የጌታው ባህሪ ተንጸባረቀ።”ኤለን ጂ ኃይት፣The Actes of the
Apostles,pp.544-545
1.የተወደደው ደቀመዝሙር የዩሐንስና የአስቆሮቱ ይሁዳ
ሕይወቶች አስገራሚ ንጽጽር አላቸው። ኢየሱስ ዩሐንስንና
ወንድሙን ሲመለከታቸው የነጎድጓድ ልጆች ብሎ ጠርቷቸው
ነበር። ዩሐንስ ከባድ እንከኖች ነበሩት። ይሁዳም እንከኖች ነበሩት
ነገር ግን የርሱ ከዩሐንስ ይልቀ ከበድ ያሉ ነበሩ። ዩሐንስ ኢየሱስን
ወደመምሰል የተለወጠውና በተቃራኒው ይሁዳ በመንፈስ ቅዱስ
ላይ ያመጸው ለምንድነው? ልዩነቱ ምን ነበር?
2.ኢየሱስ አማኞች መስቀሎቻውን ተሸክመው እንዲከተሉት
ይጋብዛል። መስቀሉን መሸከምና ሌሎች እንዲጎዱን ራስን
መስጠት የሚለያዩት ለምንድነው?
3. እግዚአብሔር ህይወታችንን ሙሉ በሙሉ እንድናስረክበው
የሚጠይቀን ለምንድነው? በነጻ ፈቃድና በመዳን መካከል ያለው
ግንኙነት ምንድነው?