የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ሉቃስ 4:16–19፤ ኢሳ. 62:1፣ 2፤ ዘዳ. 15:11፤ ማቴ. 19:16–22፤ ሉቃስ 19:1–10፤ ኢዮብ 29:12–16።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” (ማቴዎስ 25:34)።
መ
ጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ስለ መጻተኞች (አንዳንድ ጊዜ ወገን የሌላቸው
ስለሚባሉት)፣ ስለ ወላጅ አልባ ልጆችና ባልቴቶች ይናገራል።
ኢየሱስ ‹‹ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ›› ብሎ
የሚጠቅሰው ይህን ቡድን ሰዎች ሊሆን ይችላል (ማቴ. 25፡40)።
ዛሬ ይህን ሕዝብ እንዴት ለይተን ማወቅ እንችላለን? የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን
መጻተኞች ምናልባት በጦርነት ወይም በረሃብ ምክንያት አገራቸውን ለመልቀቅ
የሚገደዱ ነበሩ። በእኛ ዘመን ከእነዚህ ጋር የሚመሳሰሉት ያለ ምርጫቸው
በሁኔታዎች ምክንያት እጦት የገጠማቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች
ሊሆኑ ይችላሉ።
ወላጅ አልባ የሚባሉት ወላጆቻቸውን በጦርነት፣ በአደጋ ወይም በሕመም
ምክንያት የተነጠቁ ናቸው። ይህ ቡድን ወላጆቻቸው በማረሚያ ቤት ያሉትን
ወይም የት እንዳሉ የማይታወቁትን ያካትታል። በዚህ ቦታ እንዴት ያለ ሰፊ
የአገልግሎት መስክ ነው የተገለጠው!
ባልቴቶች የተባሉት ከላይ ወላጅ አልባ ልጆች ያልናቸው ወላጆቻቸውን
ባጡባቸው ምክንያቶች የትዳር አጋራቸውን ያጡ ሴቶች ናቸው። ብዙዎች
ለብቻቸው የቤታቸው ራስ ሆነው እየመሩ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጣቸው
እርዳታ ሊጠቅማቸው ይችላል።
በዚህ ሳምንት እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ንብረት አስተዳዳሪዎች
ስለሆንን ድሆችን መርዳት ለእኛ አማራጭ ተግባር አይደለም። የኢየሱስን ምሳሌ
መከተልና ትዕዛዛቱን መታዘዝ ነው።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለየካቲት 11 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
ኢየሱስ በቀደምት የሕዝብ አገልግሎቱ በገሊላ ግዛት ወዳለው ወደ ገሊላ ከተማ ተጓዘ። ይህ የመኖሪያ ከተማው ስለነበር ሰዎች ስለ ሥራውና ተዓምራቶቹ ሰምተው ነበር። ኢየሱስ እንደ ልማዱ ወደ ምኩራብ በመሄድ የሰንበት አገልግሎትን ይከታተል ነበር። ኢየሱስ ሥርዓቱን የሚያከናውን መምህር ባይሆንም የፕሮግራሙ አስተባባሪ የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጥቶት ጥቅስ እንዲያነብ ጠየቀው። ኢየሱስ ኢሳይያስ ምዕራፍ 61፡1፣ 2ን አነበበ። ሉቃስ 4፡16-19ን ያንብቡና ከኢሳይያስ 61፡ 1፣ 2 ጋር ያነጻጽሩ (ሉቃስ 7፡19-23ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ ይህን የተለየ ጥቅስ ለምን የመረጠ ይመስሎታል? በኢሳይያስ ውስጥ ያሉ እነዚህ ቁጥሮች ስለ መሲሁ የሚናገሩ ጥቅሶች ተብለው የሚወሰዱት ለምንድር ነው? ስለ መሲሁ ሥራ ምን ገለጡ?
የኃይማኖት መሪዎች ስለ መሲሁ ስቃይ የሚናገሩ ትንቢቶችን ችላ ስላሉና ስለ
ዳግም ምጻቱ ግርማ የሚጠቁሙትን ትንቢቶች በተሳሳተ መልኩ ስለተገበሩት
(ትንቢትን ማስተዋል ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንድናስታውስ
የሚረዳን) አብዛኛው ሕዝብ የመሲሁ ተልዕኮ እሥራኤልን ከወረሩአቸውና
ከሚጨቁኑአቸው ከሮማውያን ነጻ ማውጣት እንደሆነ የሚገልጸውን የሀሰት
ሀሳብ አምነው ተቀብለው ነበር። የኢየሱስ የተልዕኮ ሀሳብ የመጣው ከኢሳይያስ
61፡1ና 2 ላይ መሆኑን ማሰብ እርግጠኛ ድንጋጤ የሚያስከትል መሆን ነበረበት።
ድሆች እንደ ቀራጮችና ነጋዴዎች ባሉ ግድ የለሽ ባለሥልጣናት እና
በጎሮቤቶቻቸው ጭምር ተንቀው ነበር።
በተለምዶ ድህነት የእግዚአብሔር
እርግማን ነው ተብሎ ይታሰብ ስለነበር ያሉበት አሳዛኝ ሁኔታ ከራሳቸው ጥፋት
የተነሣ የመጣ ነው ተብሎ ይታመን ነበር። ከዚህ ዓይነት የአእምሮ ውቅር የተነሳ
ለድሆችና ስለ እነርሱ አሳዛኝ መከራ ግድ የሚላቸው ሰዎች ጥቂት ነበሩ።
ነገር ግን ኢየሱስ ስለ እርሱ መሲህነት ለመጥምቁ ዮሐንስ ጥያቄ መልስ በመለሰ
ጊዜ እንደታየው ሁሉ እርሱ ለድሆች የነበረው ፍቅር ከእርሱ የመሲህነት ታላላቅ
ማስረጃዎች መካከል አንዱ ነበር (ማቴ. 11፡1-6ን ይመልከቱ)። “እንደ ኢየሱስ ደቀ
መዛሙርት ሁሉ መጥምቁ ዮሐንስም የክርስቶስን መንግስት ባህርይ አላስተዋለም
ነበር። ኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን ይቀበላል ብሎ ጠብቆ ነበር፤ ጊዜው እየገፋ
ሲሄድና መሲሁም የንጉሥነት ሥልጣን ይገባኛል ባለማለቱ ዮሐንስ ግራ ተጋባ
ተረበሸም”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 215.
“ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ
ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥
በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው” (ያዕቆብ 1:27)። ይህ
ጥቅስ በኃይማኖታችን ቅድሚያ መስጠት ለሚገቡን ነገሮች ቅድሚያ
እንድንሰጥ እንዴት ይረዳናል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲዎች በጽሁፎቻቸው ውስጥ ለድሆች፣ ለመጻተኞች፣ ለባልቴቶችና ወላጅ ለሌላቸው እግዚአብሔር ስላዘጋጃቸው ብዙ መሰናዶዎች አካትተዋል። ይህ የተመዘገበበት መረጃ ወደ ኋላ እስከ ሲና ተራራ ይደርሳል። “ስድስት ዓመት ምድርህን ዝራ፥ ፍሬዋንም አግባ፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ” (ዘጸ. 23:10, 11)። ዘሌዋውያን 23፡22ን እና ዘዳግም 15፡11ን ያንብቡ። አውዱ እኛ አሁን ከምንኖርበት ሕይወት የተለየ ቢሆንም ከእነዚህ ጥቅሶች ምን መርሆዎችን ለራሳችን መውሰድ እንችላለን?
በዚህ ቦታ ‹‹ወንድም›› የተባለው ቃል በአጠቃላይ የተስተዋለው እንደ እነርሱ ያሉ
እሥራኤላውያንን ወይም አማኞችን እንደሚያመለክት ነበር። እኛም ስለ እነርሱ
የምናስበው የተገቡ ድሆች ወይም ከእነዚህ ከሁሉ ከሚያንሱት አንዱ›› እንደሆኑ
ነው። ችግረኞችን እንዴት መርዳት እንዳለብን መዝሙረ ዳዊት አቅጣጫ
ይሰጣል። “ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ
አድርጉ፤ ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው”
(መዝ. 82:3፣4)። ይህ ንባብ የእኛ ተሳትፎ ምግብን ከመስጠት ያለፈ መሆኑን
ያመለክታል።
ችግረኞችን ለሚረዱ የተገቡ የተስፋ ቃሎች አሉ። “ለድሀ የሚሰጥ አያጣም”
(ምሳሌ 28:27)። “ለድሀ በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥ ዙፋኑ ለዘላለም ይጸናል።”
(ምሳሌ 29:14)። ንጉሱ ዳዊት እንዲህ ብሏል፡- “ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ
ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል” (መዝ. 41:1)። ይህ ጉዳይ
አንዳንድ ጊዜ ትኩረት ቢያጣም በጥንቷ እሥራኤል ሁልጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው
ነገር ነበር።
ከዚህ በተቃራኒ፣ በአሁኑ ዘመን እንኳን፣ በተለይ በእንግሊዝ አገር ‹‹ማህበራዊ
ዳርዊናዊነት›› ተብሎ በሚታወቅ ተጽእኖ ሥር ብዙዎች ድሆችን የመርዳት
የሞራል ግዴታ የለም ብለው የሚያስቡ ብቻ ሳይሆን እነርሱን መርዳት ስህተት
ነው እስከማለት ደርሰዋል። በዚህ ፋንታ፣ በደካማው ጉዳት ብርቱው ይኖራል
የሚለውን የተፈጥሮ ኃይላትን በመከተል፣ ‹‹ማህበራዊ ዳርዊናውያን›› ድሆችን፣
ህመምተኞችንና ምስኪኖችን መርዳት ለማህበረሰቡ ጎጂ ነው ብለው ያምናሉ።
ለዚህ ምክንያቱ እነዚህ ከተባዙ የመላውን አገር ማህበራዊ አቋም ስለሚያዳክሙ
ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው። ይህ አስተሳሰብ ጭካኔ የተሞላበት ቢሆንም
ከዝግመተ ለውጥ እምነትና ይህ ከሚያስተዋውቀው የውሸት ታሪክ የበቀለ ነው።
ወንጌል፣ ክርስቶስ ለሁሉም ሰው ሞተ የሚለው ሀሳብ፣ እኛ
በማንነታቸው ልዩነት ሳናደርግባቸው ሰዎችን በሙሉ እንዴት መያዝ
እንዳለብን ተጽእኖ ማሳደር ያለበት እንዴት ነው?
ስለ ሀብታሙ ወጣት ገዥ ወጣት፣ ገዥና ሀብታም ከመሆኑ በቀር ብዙ የምናውቀው ነገር የለም። ለመንፈሳዊ ነገሮችም ፍላጎት ነበረው። ጉልበታም ስለነበር ወደ ኢየሱስ እየሮጣ መጣ (ማር. 10፡17)። ስለ ዘላለማዊ ሕይወት ለመማር ፍላጎት ነበረው። ይህ ታሪክ እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሣ በሶስቱ ዋና ወንጌላት ውስጥ ተመዝግቦአል፡-ማቴዎስ 19፡16-22፤ ፣ ማርቆስ 10፡ 17-22፤ ሉቃስ 18፡18-23። ማቴ. 19:16–22ን ያንብቡ። ኢየሱስ “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ” ሲል ምን ማለቱ ነበር (ማቴ. 19:21)?
አብዛኞቻችን ያለንን ሁሉ ሽጠን ለድሆች እንድንሰጥ ኢየሱስ አይጠይቀንም። ነገር
ግን ለዚህ ወጣት ሰው ገንዘብ አምላኩ ስለነበር፣ ምንም እንኳን ኢየሱስ የጠየቀው
ነገር እጅግ ጨከን ያለ ነገር ቢመስልም፣ ለዚህ ሰው የነበረው ብቸኛው የድነት
ተስፋ ይህ እንደሆነ ኢየሱስ ስላወቀ ነበር።
ሀብታም ስለነበር እያዘነ እንደሄደ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ይህ ድርጊቱ ገንዘብን
ምን ያህል ያመልክ እንደነበረ ማስረጃ ነው። የዘላለም ሕይወትና የኢየሱስ የቅርብ
ወዳጅ የመሆን ዕድል ተሰጥቶት ነበር (ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት
ሲጠራ የተጠቀመው ‹‹ና ተከተለኝ›› የሚሉ ተመሳሳይ ቃላት ጥቅም ላይ
ውለዋል)። ሆኖም ስለዚህ ወጣት ከዚህ ጊዜ በኋላ በፍጹም አንሰማም። ዘላለምን
በምድራዊ ሀብቱ ቀየረው።
እንዴት ያለ አሳዛኝ ንግድ ነው--አሳዛኝ አልነበረም? እንዴት ያለ ‹‹የዘገየ ፍላጎትን
ማሟላት›› ያለመከተል ምሳሌ ነው! (ያለፈውን ሳምንት ትምህርት ይመልከቱ)።
ቁሳዊ ሀብት ለአሁኑ ምንም ነገር ቢሰጠንም ይፍጠንም ይዘግይም ሁላችንም
ስለምንሞትና ወደፊት ዘላለምን መጋፈጣችን ስለማይቀር ይህ ሰው የመረጠውን
ዓይነት ምርጫ መምረጥ መታለል ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ሀብታቸው ተስፋ
ያደረጉትን ሰላምና ደስታ እንደማይሰጥ ብዙ ሀብታሞች ተገንዝበዋል። በብዙ
አጋጣሚዎች የዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር የሚከሰት ነው የሚመስለው።
ብዙ
ሀብታም ሰዎች ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆኑ የሚገልጹ በርካታ የሕይወት ታሪኮች
ተጽፈዋል። ተጽፎ ባለው ታሪክ በሙሉ ሀብት እርካታ ሊሰጥ እንደማይችል
ከሚገልጹ መግለጫዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የሚገኘው በመክብብ መጽሐፍ
ውስጥ ነው። ከዚህ ላይ ሰው ምንም ዓይነት ሌሎች ትምህርቶች ቢያገኝም አንድ
ነጥብ ጥርት ብሎ ይወጣል፡- ያውም ገንዘብ ሰላምና ደስታ መግዛት አይችልም
የሚለው ነው።
“ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል
ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ
ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን
ይሰጣል?” (ማር. 8:35–37)። ስለ ወንጌል ነፍስን ማጥፋት ማለት ምን
ማለት ነው?
ዘኬዎች ለተጠሉ ሮማውያን ቀረጥ ሰብሳቢ በመሆን ገንዘብ ያፈራ ሀብታም አይሁዳዊ ነበር። ከዚህ የተነሣ እና እርሱና ሌሎች ቀረጥ ሰብሳቢዎች ከሚጠበቀው በላይ ቀረጥ በመጠየቃቸው ዘኬዎስ ይጠላና ‹‹ኃጢአተኛ›› ተብሎ ይጠራ ነበር። ዘኬዎስ ይኖር የነበረው ብዙ የንግድ እንቅስቃሴ በሚደረግበትና የንግድ መስመር በነበረችው በኢያርኮ ነበር። የዘኬዎስና የኢየሱስ መገናኘት የአጋጣሚ ጉዳይ አልነበረም። ዘኬዎስ መንፈሳዊ አመለካከትን ስለተቀበለ በሕይወቱ ለውጥ ለማድረግ ፈልጎ ነበር። ስለ ኢየሱስ ሰምቶ ስለነበር ሊያየው ፈለገ። ኢየሱስ አብሮአቸው የሚጓዘው ቡድን በዚያ ቀን ወደ ኢያርኮ እንደሚደርስ ወሬ ደርሶት ነበር። ኢየሱስ ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም በሚያደርገው ጉዞ በኢያርኮ በኩል ማለፍ ፈለገ። ክርስቶስ ለዘኬዎስ የተናገራቸው የመጀመሪያዎቹ ቃላት ወደ ከተማው ከመግባቱ በፊት እንኳን ስለ እርሱ ያውቅ እንደነበር ገለጡ። ሉቃስ 19:1–10ን ያንብቡ። በዚህ ሀብታም ሰው ልምምድና በሀብታሙ ወጣት ገዥ ልምምድ መካከል ያሉ ልዩነቶች ምንድር ናቸው?
ዘኬዎስና ሀብታሙ ወጣት ገዥ የጋራ የሆነ ነገር አላቸው። ሁለቱም ሀብታም
ነበሩ፤ ሁለቱም ኢየሱስን ማየት ፈልገው ነበር፣ ሁለቱም ዘላለማዊ ሕይወትን
ፈልገው ነበር። ነገር ግን መመሳሰላቸው በዚህ ቦታ ያቆማል።
ዘኬዎስ ‹‹ከንብረቴ ግማሹን›› (ሉቃስ 19፡8) ለድሆች እሰጣለሁ ሲል ኢየሱስ
ይህን አቋሙን የእውነተኛ መለወጥ መግለጫ አድርጎ እንደወሰደው ልብ በሉ።
ኢየሱስ ‹‹ዘኬዎስ ሆይ፣ አዝናለሁ፣ እንደ ሀብታሙ ወጣት ገዥ ሁሉንም መስጠት
ወይም ሁሉንም መከልከል ነው ያለብህ። ግማሽ በቂ አይደለም›› አላለውም።
ለምን? ለዚህ ምክንያቱ ዘኬዎስ በእርግጠኝነት ሀብቱን ቢወድም ለሀብታሙ
ወጣት ገዥ እንደነበረው ሀብቱ አምላኩ አልነበረም። ኢየሱስ በተለየ ሁኔታ ምን
እንዳለው ባናውቅም ገንዘብን ለድሆች ስለመስጠት አስቀድሞ የተናገረው ዘኬዎስ
ነበር። ከዚህ በተቃራኒ ለወጣቱ ሀብታም ገዥ ገንዘቡን ሁሉ እንዲሰጥ የነገረው
ኢየሱስ ነበር፤ ይህ ካልሆነ ግን ገንዘቡ ያጠፋው ነበር። ዘኬዎስ እንደ ማንኛውም
ሀብታም ሰው ስለ ሀብት አደጋዎች መጠንቀቅ ቢያስፈልገውም ከሀብታሙ ወጣት
ገዥ በተሻለ ሁኔታ ገንዘቡን ተቆጣጥሮት ነበር።
“ሀብታሙ ወጣት ገዥ ከኢየሱስ ተለይቶ ሲሄድ ‘ለሀብታሞች ወደ መንግስተ
ሰማያት መግባት ምንኛ ከባድ ነው’ በሚለው በጌታቸው ንግግር ደቀ መዛሙርት
ተደንቀው ነበር። ከዚያ በኋላ ‘እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል?’ በማለት እርስ
በርሳቸው ተነጋገሩ። ከዚያ በኋላ ‘ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል’
የሚለውን የእውነት መግለጫ ከክርስቶስ ቃላት አገኙ። ማርቆስ 10፡24፣ 26፤
ሉቃስ 18፡27። ሀብታም ሰው እንዴት በእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እርሱ መንግስት
መግባት እንደሚችል አሁን ተመለከቱ። ”—Ellen G. White, The Desire of
Ages, p. 555.
ኢዮብ 1:8ን ያንብቡ። ኢዮብ በእግዚአብሔር የተገለጸው እንዴት ነው?
ኢዮብ በእርሱ ዘመን ካሉ ሰዎች ማንም ሊስተካከለው እስከማይችል
ድረስ ፍጹምና ቅን ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር እንኳን “ፍጹም” እና “ቅን”
(ኢዮብ 1፡8)ብሎ መጥራቱ እጅግ መልካም ነው። በድጋሚ እግዚአብሔር ስለ
ኢዮብ የተናገራቸው ቀጥተኛ ቃላት አሉ።
መቅሰፍቶች አንዱ ሌላውን እየተከተሉ በኢዮብ ላይ ከደረሱ በኋላም ቢሆን፣
ከተጨመረው ሌላ ሀሳብ በስተቀር፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ እርሱ
የተናገራቸውን እነዚያኑ ቃላት፣ በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ፍጹምና ቅን ሰው
የለም በማለት ደገመለት። እግዚአብሔር ስለ ኢዮብ ለሰይጣን እንዲህ አለው፡“በከንቱም አጠፋው ዘንድ አንተ በእርሱ ላይ ብታንቀሳቅሰኝም እንኳን” (ኢዮብ
2:3) እርሱ አሁንም ያው ነው።
የተለያዩ ችግርሮች ቢደርሱበትም፣ ከሚስቱም “እስከ አሁን ፍጹምነትህን
ይዘሃልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት” (ኢዮብ 2:9) የሚል ማንጓጠጥ
ቢደርስበትም እግዚአብሔርን ባለመተው ስላሳየው የኢዮብ ፍጽምና እና ቅንነት
ኃይለኛ ጭላንጭል ብናገኝም መጽሐፉ እዚህ ከተገለጠው ድራማ በፊት የኢዮብን
ሌላኛውን ገጽታ ገልጧል።
ኢዮብ 29:12–16ን ያንብቡ። በኢዮብ ባህርይ ምስጢር ላይ የበለጠ
ግንዛቤ የሚሰጥ ምን ነገር እዚህ ተገልጦአል?
ምናልባትም እጅግ አስተዋይነቱን ያሳዩት የኢዮብ ቃላት የሚከተሉት ናቸው፡“የማላውቀውንም ሰው ሙግት መረመርሁ” (ኢዮብ 29:16)። በሌላ አገላለጽ የሆነ
ለማኝ ቡቱቶ ጨርቅ ለብሶ እንዲለምነኝ አልጠበቅሁም ማለቱ ነው። ይልቁንም
ችግረኞችን ፈልጎ በመርዳት ኢዮብ ተነሳሽነትን አሳይቶ ነበር።
ኤለን ጂ ኋይት እንዲህ ብላለች፡- “[ድሆች] ለችግሮቻቸው መፍትሄ
እንዲገኝ ትኩረትህን እስኪያገኙ ድረስ አትጠብቅ። ኢዮብ እንዳደረገ አድርግ።
እርሱ ያላወቀውን ነገር ለማወቅ ፈለገ። ምርመራ የማድረግ ጉዞ አድርግና
የሚፈለገው ነገር ምን እንደሆነ እና ያንን ነገር እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል
ተማር።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 151. ይህ ድርጊት ዛሬ
ያሉ አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ልጆች ከሚተገብሩት ያለፈ ገንዘብን የማስተዳደርና
የእግዚአብሔር ሀብቶች መጋቢ የመሆን ደረጃ ነው።
ኢሳይያስ 58:6–8ን ያንብቡ። እነዚህን የጥንት ቃላት ወስደን ዛሬ
ለራሳችን መተግበር የምንችለው እንዴት ነው?
:- “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን
መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ
ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል።’’
ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ የታላቁ ፍርድ ቀን ዕይታን ለደቀ መዛሙርቱ
አሳያቸው። ውሳኔው በአንድ ነጥብ ላይ እንደሚሽከረከር አድርጎ አቀረበ። ሕዝቦች
በፊቱ ሲሰበሰቡ ሁለት ክፍል ሰዎች ብቻ የሚኖሩ ሲሆን የዘላለም መዳረሻቸው
የሚወሰነው ለድሆችና በስቃይ ውስጥ ላሉት በአካል ተገኝተው ባደረጉት ወይም
ለማድረግ እምቢ ባሉት ልክ ነው።”—Ellen G. White, The Desire of Ages,
p. 637.
“የክርስቶስ ለሆኑት ድሆችና ሥቃይ ውስጥ ላሉት በራችሁን ስትከፍቱ
የማይታዩ መላእክትን በቤታችሁ እየተቀበላችሁ ነው። የሰማያዊ ፍጡራንን
ወዳጅነት እየጋበዛችሁ ነው። የተቀደሰ የሰላምና ደስታ ከባቢ አየርን ያመጣሉ።
በከናፍራቸው ውዳሴን ይዘው የሚመጡ ሲሆን ለዚያ ምላሽ የሚሰጥ ምት
ከሰማይ ይሰማል። እያንዳንዱ የምህረት ተግባር እዚያ ሙዚቃ ይፈጥራል። አብ
በዙፋኑ ላይ ሆኖ ራስ ወዳድ ያልሆኑ ሰራተኞችን እጅግ ክቡር ከሆኑ ንብረቶቹ
ጋር ይቆጥራቸዋል።”—The Desire of Ages, p. 639.
1ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና” (ዘዳ. 15:11)። ይህ
ትንቢት ምንም እንኳን በሺሆች የሚቆጠሩ አመታት ዕድሜ
ቢኖረውም ተፈጻሚ ከመሆኑ እውነታ ባሻገር ዛሬ እንዴት ነው
የምናስተውለው? ‹‹እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉ
ብሏል፤ ስለዚህ አሁንም ያለው ይህ ነው›› የሚል ምክንያት
በመስጠት አንዳንድ ሰዎች ድሆችን መርዳት እንደማያስፈልግ
ለማረጋገጥ እነዚህን ቃላት ተጠቅመዋል። የዚህ አስተሳሰብ
ስህተት ምንድር ነው?
2. 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:17–19ን ያንብቡ:- “በአሁኑ ዘመን ባለ
ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን
አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ
ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። እውነተኛውን ሕይወት
ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት
የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ
በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ
እንዲሆኑ ምከራቸው።” አደጋው ምን እንደሆነ ልብ ይበሉ፡ሕያው እግዚአብሔርን በሚቃወም መልኩ በራስ ሀብት መታመን።
ገንዘብ ያላቸው ሰዎች በመጨረሻ ገንዘባቸው በሙሉ በሕይወት
እንደማያኖራቸው ቢያውቁም በሀብታቸው መታመን የሚቀላቸው
ለምንድር ነው? ሁላችንም ከሕያው እግዚአብሔር ሌላ በምንም
ነገር እንዳንታመን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድር ነው?