የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ማሳደግ



2ኛ ሩብ ዓመት 2026


ሚያዝያ 24 - 30

6ኛ ትምህርት

May 2 - 8




የጸሎት ተዋጊዎች



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዳን. 2:20-23፤ ዳን. 6:10-11፤ የሐዋርያት ሥራ 20:36፤ ዘፍ. 5:22-24፤ ዘጸ. 33:15-23፤ ዘጸ. 32:31-32።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።” (መዝሙር 116:1-2)።

ከቅርብ ጓደኛዎ ወይም ከትዳር አጋርዎ ጋር እምብዛም ባይነጋገሩ ብለው ያስቡ። ብዙም ሳይቆይ ግንኙነቱ ይፈርሳል፣ ችግርም ይሆናል። በተመሳሳይ መንገድ፣ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር አስፈላጊ ነው። ይህ እያንዳንዳችን የሚያስፈልገን እና ልናጠናክረው የምንችለው ወሳኝ የአምልኮ ልማድ ነው።

በቀጣይነት የማንፀልይ ከሆነ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ከጌታ መለየታችን አይቀርም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ በተለያዩ መንገዶች ስለጸለዩ የተለያዩ ግለሰቦች ሕይወት እንማራለን። ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ኅብረት ከእርሱ ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደረ፣ እንዴት እና ምን መጸለይ እንደምንችል እና ጸሎታቸው የሌሎችን ሕይወት እንዴት እንደ ለወጠው ለማየት ወደ ኋላ መለስ ብለን ማየት እንችላለን።

በእርግጥም የጸሎት ሕይወታችን እኛን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይነካል። ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ይህ የጸሎት ርዕስ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊሸፈን ከሚችለው በላይ ትልቅ፣ አስፈላጊ እና በጣም ሰፊ ነው። በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመመሥረት ጸሎት ምን ያህል ማዕከላዊ እንደሆነ ካሳዩን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ሰዎች አንዳንድ ትምህርቶችን እንማራለን። ከምሳሌዎቻቸው እንማር። *ለግንቦት 1 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ።

ሚያዝያ 25
May 3

ታማኙ ዳንኤል


ዳንኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ታላላቅ ጀግኖች አንዱ ነው። የመጀመሪያውን ታሪክም እናውቃለን (ዳንኤል 1ን ይመልከቱ)፡- “ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እንዳይረክስ በልቡ አሰበ” (ዳን. 1፡8)። እንዲሁም ለዳንኤልና ለሦስቱ ጓደኞቹ፣ “እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ” (ዳን. 1:17)። መጽሐፍ ቅዱስ ዳንኤልን የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ውስጥ ስለነበረ (ዳን. 4:9፣18፤ ዳን. 5:14፤ ዳን. 6:3)፣ እና በሰማይ እጅግ የተወደደ ስለነበረ (ዳን. 9:23፣ ዳን. 10:11) ጥበበኛ ይለዋል (ዳን. 1:20፤ ዳን. 2:14፣ 21፣ 23፣ 48)። እነዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ጠንካራና ዘላቂ ግንኙነት የነበረው ሰው አንዳንድ መገለጫዎች ናቸው።

በዳንኤል 2፣ ንጉሥ ናቡከደነፆር በባቢሎን ውስጥ ላሉ ጠቢባን ሁሉ የሞት አዋጅ ባወጣ ጊዜ፣ ዳንኤል የሕልሙን ምስጢር በተመለከተ የእግዚአብሔርን ምሕረት ፈለገ (ዳን. 2:18)። እግዚአብሔር የንጉሡን ሕልም ለዳንኤል ሲገልጥለት ወዲያውኑ ጸለየ። ዳንኤል 2:20-23ን ያንብቡ። ዳንኤል የጸለየው ለምን ነበር? እና ከዚህ ጸሎት ምን እንማራለን?



ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ነገሥታትም ተነሥተው ሲወድቁ፣ ዳንኤል የነገሥታቱ አማካሪ ሆኖ ቀጠለ እና “መልካም መንፈስ ስላለው ከአለቆችና ከመሳፍንት በለጠ፤ ንጉሡም በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ይሾመው ዘንድ አሰበ።” (ዳን. 6:3) ተብሎ ተገልጾ ነበር። “የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም።” (ዳን. 6:4)። በሥራ ባልደረቦቹ በኩል ከባድ ቅናት እና የክፋት ሴራ (ዳን. 6:5-9) ቢኖርም፣ ዳንኤል በጸሎት ሕይወቱ ውስጥ ሁልጊዜም የማይናወጥ እና ፍርሃት አልባ ሆኖ ቆመ። ዳን. 6:10-11ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ዳንኤል ምን ይነግሩናል?



ዳንኤል አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው ጸለየ። ምንም እንኳን ዛቻው በሕይወቱ ላይ ቢሆንም፣ በጸሎት (እንደ ልማዱ በቀን ሦስት ጊዜ) እና ሊገመት በሚችል (በቀን ሦስት ጊዜ ክፍት በሆነው መስኮቱ ወደ ኢየሩሳሌም ፊቱን አዙሮ) ሁኔታ ፀለየ። ጸሎቱ አካላዊ ተግባር ነበር (ተንበርክኳል) እና በምስጋና እና በልመና ላይ ያተኮረ ነበር። በዚህ ታሪክ መሠረት፣ እኛ ላለመጸለይ ያቀረብናቸው ሰበቦች ምን ያህል ደካማ ናቸው?

ሚያዝያ 26
May 4

የፀሎት አካላዊ አቋም


በሕይወታችን ውስጥ አንድ ነገር ሲበላሽ፣ አብዛኞቻችን ስለ ጉዳዩ ለማውራት የቅርብ ጓደኞቻችን ጋ እንደውላለን። መልካም ዜና ሲኖረን፣ የምናካፍለው ሰው እንፈልጋለን።

ከእግዚአብሔርም ጋር እንዲሁ ማድረግ እንችላለን። “ጸሎት ለጓደኛ እንደምናደርገው ልባችንን ለእግዚአብሔር መክፈት ነው።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ፣ ገጽ 93። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ይዘን እንድንቆይ የሚረዳን ብቻ ሳይሆን የማን እንደሆንን ለዲያብሎስ የሚናገር ነው። ጠዋት ለመጸለይ ስንንበረከክ፣ ዛሬ እግዚአብሔርን እንደመረጥን ለጨለማ ኃይሎች አካላዊ መግለጫ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ስንጸልይ እግዚአብሔር መላእክቱን ወደ እኛ ይልካል፤ እናም ከጨለማ ኃይላት እንጠበቃለን፤ እንከለላለን (መዝሙር 91)። ራስን በማስገዛት ስሜት መንበርከክ አካላዊ የትህትና አቋምን ያሳያል። ተንበርክከን ስንጸልይ ወንበር ላይ ከመቀመጥ ወይም በአልጋ ላይ ከመተኛት የተለየ ነው፣ (ምንም እንኳን በእነዚህ ሁኔታዎች መጸለይ ብንችልም)። ሆኖም በእግዚአብሔር ፊት ስንንበረከክ፣ ሰውነታችንና ቃላችን እርሱ ሉዓላዊ እንደሆነና እኛ ፍጡራን ልጆቹ ብቻ እንደሆንን ስለሚናገሩ፣ ልባችን በቀላሉ እጅ ይሰጣል። የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያንብቡና ተንበርክከው የሚፀልዩትን የእነዚህን ግለሰቦች ሕይወት ያሰላስሉ፡ ዳን. 6:10፣ ሉቃስ 22:41፣ የሐዋርያት ሥራ 7:60፣ የሐዋርያት ሥራ 9:40፣ የሐዋርያት ሥራ 20:36።



በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሲፀልዩ መቆም የተለመደ ተግባር ነበር (2 ዜና መዋዕል 20:5፣ 6፣ 13፤ 1 ሳሙኤል 1:26፤ ኢዮብ 30:20፤ ሉቃስ 18:11)። መጽሐፍ ቅዱስ ቁጭ ብለው የፀለዩ ሰዎችንም ምሳሌዎችን ይጠቅሳል (2 ሳሙኤል 7:18፣ 2 ነገሥት 4:38)። ሌሎች ደግሞ ፊታቸውን በምድር ላይ አድርገው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ - ምንም እንኳን ይህ ከጸሎት ይልቅ ራስን ለበላይ ከማስገዛት ጋር ቢያያዝም (1 ነገሥት 1:47፣ ማርቆስ 14:35)። በጸሎት ጊዜ እርስዎ የለመዱት የፀሎት አካላዊ አቋም የትኛው ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም የተለየ አቋም እንድንጸልይ አይጠብቅብንም፣ ነገር ግን አክብሮታችንን፣ ውስጣዊ ስሜታችንን እና ለእግዚአብሔር ለመገዛት ያለንን ፍላጎት ስለሚያንጸባርቁ አካላዊ አቋሞች አስፈላጊ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች መንበርከክ አይችሉም፣ ስለዚህ በዋናነት በጣም አስፈላጊው የልብ ሁኔታ ነው። መንበርከክ እየቻሉ ብዙውን ጊዜ ተንበርክከው የማይፀልዩ ከሆነ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ሲፀልዩ ለምን ተንበርክከው ከእግዚአብሔር ጋር ባለዎ ግንኙነት ላይ ይህ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አያዩም? መጽሐፍ ቅዱስ “ያለማቋረጥ እንድንጸልይ” (1 ተሰ. 5:17) ይጋብዘናል፣ ይህም ጽናት (ቆላ. 4:2) እና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን (ሮሜ. 12:12) የሚመክር ነው። ዛሬ ስትቆሙ፣ ስትቀመጡ፣ ስትተኙ ወይም ስትራመዱ፣ ሀሳብዎን ወደ እግዚአብሔር ይመልሱና እንደ ጓደኛ ያነጋግሩት። አሁኑኑ ይጀምሩ።

ሚያዝያ 27
May 5

ሄኖክ ተናገረም ኖረም


ዘፍጥረት 5:22-24ን ያንብቡ። ስለ ሄኖክ በትክክል ምን እናውቃለን?



መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሄኖክ ሕይወት ብዙ አያወራም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ሰማይ እስኪወስደው ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር ለ300 ዓመታት እንደተጓዘ ይነግረናል።

ለእግዚአብሔር በቀጣይነት ራስን መስጠት የዚያን ሰው ሕይወት የሚገልጽበት ሁኔታ እንዴት ውብ ነው! ሄኖክ “በጸሎቱ የፀና” (ሮሜ 12:12) ሊሆን እንደሚችል እንዲሁም በዕለት ተዕለት ልምዶቹ በእምነት ወደ እግዚአብሔር እየቀረበና እየተጋ እንደነበረ ማወቅ እንችላለን። እርሱ በኖረበት ዘመን ምድር እየከፋች ብትሄድም ሄኖክ እግዚአብሔርን በማገልገል ተጠመደ።

ይህም በጌታ ሳይኖር ያከናወነው ነገር አልነበረም። “በንቃት በሚሠራበት ሕይወት ውስጥ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት በጽናት ጠበቀ። ድካሙ በጨመረ ቁጥር ጸሎቱ የበለጠ ቀጣይነት ያለውና የፀና ሆነ። . . . ለተወሰነ ጊዜ በሕዝቡ መካከል በመሆን በትምህርቱና በምሳሌው እነሱን ለመጥቀም ቢጥርም፣ ከእግዚአብሔር ብቻ ሊያገኝ የሚችለውን መለኮታዊ እውቀት ስለተራበና ስለተጠማ ለተወሰነ ጊዜ ብቻውን ለማሳለፍ ይወጣ ነበር። በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ሄኖክ መለኮታዊውን ምስል ማንጸባረቁ እየጨመረ መጣ። . . . ክፉዎች እንኳን በፊቱ ላይ የሰማይን ገጽታ በአድናቆት ተመለከቱ።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ የሐይማኖት አባቶችና ነቢያት፣ ገጽ 86-87።

እግዚአብሔር እንደ ባህታዊ ወይም መነኩሴ ከዓለም ተለይተን እንድንኖር አልጠየቀንም።

እንደ ሄኖክ፣ በዙሪያችን ስላሉት ጥያቄዎች ማወቅ እና ውጤታማ መሆን እንችላለን፣ ነገር ግን በእኛ በኩል አስደናቂ ባህሪው የሚንፀባረቀው በቋሚና ዘላቂ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር በመራመድና በመነጋገር ብቻ ነው። በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ መጸለይ እንችላለን።

እግዚአብሔር ሊያየን ወይም ሊሰማን የማይችልበት በምድር ላይ ያለ ቦታ የለም (መዝ. 139:7-12)፤ የትም ብንሆን የልባችንን ጩኸት ሁልጊዜ ይሰማል (ሰቆ. 3:55-57ን ያንብቡ)።

ሆኖም በአእምሮአችን ውስጥ ብቻ ሳይሆን ጮክ ብለን በመጸለይ መናገርም አለብን። በጸጥታ ስንጸልይ፣ ትኩረታችን ሊከፋፈል ወይም አስተሳሰባችንን ወይም ዓረፍተ ነገሩን እንኳን ላናጠናቅቅ እንችላለን፣ እና ሀሳባችን ትኩረት ላያደርግ ይችላል። ነገር ግን በሹክሹክታ ወይም በተለመደው ቃና ጮክ ብለን ስንጸልይ፣ እግዚአብሔር እውን እንደሆነ፣ እንደሚያዳምጠን እና ከእርሱ ጋር የምንነጋገርበት የተለየ ነገር እንዳለን ለራሳችን እያስታወስን ነው። ዛሬ በውሏችሁ፣ ከኢየሱስ ጋር በፀሎት የምትገናኙት የት እና እንዴት ነው?

ሚያዝያ 28
May 6

ሙሴ፣ መንፈሳዊ የሆነ መሪ


ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት እንደነበረው ግልጽ ቢሆንም፣ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው ግንኙነት የበለጠ ግንዛቤ አለን፤ በተጨማሪም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረው ውይይት በርካታ ዘገባዎችን ማንበብ እንችላለን። በዚህ ትሑት መሪ ሕይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ ከሙሴ ጋር አብረን ስንጓዝ፣ በሕይወቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ክፍል እና እንደ መንፈሳዊ መሪ የስኬቱ ምስጢር ከእግዚአብሔር ጋር የማያቋርጥ እና ዘላቂ ግንኙነት መሆኑን ደጋግመን እናያለን። ዘጸአት 33:15-23ን ያንብቡ። በሙሴ እና በጌታ መካከል የነበረው ውይይት ይዘት እና የንግግር ሁኔታ ምን ይመስላል?



ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እና ድምፁን በግልጽ መስማት ምን እንደሚመስል አስቡት። እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲህ ዓይነቱን ኅብረት አለመፈለጋቸውና ከዚያ ይልቅ ሙሴ በእግዚአብሔር ስም እንዲነግራቸው መለመናቸው የሚያስገርም ነው (ዘጸአት 20:18-21)። ሆኖም፣ በተመሳሳይ ተራራ ላይ በሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ ከነበራቸው ግንኙነት ጀምሮ እግዚአብሔር ሙሴን ለዚህ አዘጋጅቶት ነበር። ሙሴ ስለፀለያቸው ሌሎች የግል ጸሎቶች ብናነብም፣ ለሚመራው ሕዝብ ምሪትን በመጠየቅና በመማለድ ዘወትር በእግዚአብሔር መገኘት ፊት እንደሆነ እናያለን። ሙሴ በሁለት አጋጣሚዎች ለቤተሰቡ አባላት በፀሎት ማልዷል። ምልጃውን የከበቡት ምን ሁኔታዎች ነበሩ፣ እና ክፍተቱን ለማስተካከል ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር?

ከሚሪያም ጋር ስላለው ግንኙነት በተለይ የሚያስደንቀው ነገር ሙሴ የእሷን መልካም ያልሆነ ባህሪና ቅናት ተቀባይ መሆኑ ነው። በቀላሉ ወደ ኋላ ቆሞ እግዚአብሔር በማርያምና አሮን ላይ የሚገባቸውን ቅጣት እንዲያደርስባቸው ሊፈቅድለት ይችል ነበር። በምትኩ፣ እህቱን ይቅር ለማለትና እንድትፈወስ ለመፀለይ ፈጣን ነበር። በሙሴ ድርጊት ውስጥ ለኃጢአተኞች የእግዚአብሔር ይቅር ባይ ጸጋ ኃይለኛ ነጸብራቅ ይታያል። ማቴዎስ 5፡44 እና ቆላስይስ 3፡13ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተነገረንን ማድረግን እንዴት መማር እንችላለን? ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድነው?

ሚያዝያ 29
May 7

ሙሴ ለሕዝቡ ማለደ


ዘጸአት 32:31-32ን ያንብቡ። ይህ ስለ ሙሴና ስለ ጸሎት ምን ያስተምረናል?



ሙሴ በግልፅነት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ደጋግሞ ማለደ። ሙሴ ሕዝቡ በተጠማ ጊዜ (ዘጸአት 15:25፤ ዘጸአት 17:2-6)፣ ሕዝቡ በተራበ ጊዜ (ዘኍልቍ 11:21, 22)፣ እና በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ(ዘኍልቍ 11:11-15) ወደ እግዚአብሔር ፀለየ። እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወዲያውኑ የወርቅ ጥጃውን ሲሠሩ፣ ሙሴ “እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ፥ እንደ ፊተኛው በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም። እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።”(ዘዳግም 9:19) ሲል አስታወሰ ። ሰላዮቹ ከተስፋዪቱ ምድር ሲመለሱ ሙሴ “እግዚአብሔርም፦ አጠፋችኋለሁ ብሎ ስለ ተናገረ በወደቅሁበት ዘመን አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ።”(ዘዳግም 9:25) ሲል አስታወሰ። ሌዊ በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ከሌሎች ነገዶች ሲለይ፣ ሙሴ “እኔም እንደ ፊተኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተራራው ላይ ተቀመጥሁ፤ እግዚአብሔርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ አልወደደም።”(ዘዳግም 10:10) ሲል አስታወሰ።

እግዚአብሔር የሙሴን ልመና ሰማ። ከሙሴ ሕይወት ስለ ጸሎትና እግዚአብሔርን ስለ መጣበቅ ብዙ መማር እንችላለን፡ ሙሴ ለእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ነበረው፣

ሙሴ ለእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ነበረው፣ እና ስለ ባህሪው ግልጽ ምስል ነበረው። እግዚአብሔር በዘጸአት 34:6 ላይ ራሱን ለሙሴ ገልጾለታል፡ “እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፦ እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት…” ሲል አወጀ። ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር በተጓዘበት ወቅት በውጣ ውረዱ ጉዞ እግዚአብሔርን በመያዝ ግልፅና ታማኝ ነበር። በመያዝ ግልፅና ታማኝ ነበር። እኛ ሁላችንም እንደምንታገለው ትግል ቢኖርበትም ሙሴ በራሱ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ኃይል፣ መገኘትና ምሪቱን ይተማመን ነበር (ዘጸ. 33:13)። ሙሴ እግዚአብሔርን ስለ ቃል ኪዳኑ አስታወሰው (ዘጸ. 32:13)፣ ለሕዝቡ ሲል የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃላት የራሱ አድርጎ አውጇል (ዘዳ. 7:8)፣ እና ቀደም ብሎ የሆነውን የእግዚአብሔርን መሪነት አስታወሰ (ዘዳ. 8:2)። ሙሴ ለጸሎቶቹ ይሆናልም አይሆንምም ቢሆኑ እግዚአብሔር የሰጠውን መልሶች ተቀብሏል። ተቀብሏል። ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት መኖሩ ሁልጊዜ የምንፈልገውን እናገኛለን ማለት አይደለም (ዘዳ. 3:23-29)፣ ነገር ግን በጽናት መጸለይ አለብን (ሉቃስ 18:1-8)። አሁን የምልጃ ጸሎቶችዎ የሚያስፈልገው ማነው? አሁን ከመጸለይ የሚያግድዎትስ ምንድን ነው?

ሚያዝያ 30
May 8


ተጨማሪ ሀሳብ


እግዚአብሔርን በጣም ስለምንወደው መጸለይ አለብን፣ እና በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ሁሉ ደስታችንን እና የሕይወታችንን “ድል”፣ ሸክማችንን፣ ጭንቀታችንን፣ ጥያቄዎቻችንን እና የዕለት ተዕለት ፍላጎቶቻችንን ለእርሱ አለመንገር አንችልም:: “ወደ እግዚአብሔር በጣም ከመቅረባችን የተነሳ፣ አበባው ወደ ፀሐይ እንደሚዞር ባልተጠበቀ ፈተና ሁሉ ሀሳባችን ወደ እርሱ ይመለሳል። ፍላጎቶቻችሁን፣ ደስታዎቻችሁን፣ ሀዘናችሁን፣ ጭንቀታችሁንና ፍርሃታችሁን በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጡ። ሸክም ልታበዙበት ወይም ልታደክሙት አትችሉም። የጭንቅላታችንን ፀጉር የሚቆጥረው እርሱ ለልጆቹ ፍላጎት ግድየለሽ አይደለም። . . . የፍቅር ልቡ በሰቆቃችንና ስለሀዘናችን በምንናገረው ነገር ይነካል። አእምሯችሁን የሚያደናግረውን ነገር ሁሉ ወደ እርሱ ውሰዱት። ሊሸከመው የማይችለው ምንም ነገር የለም፣ ምክንያቱም ዓለማትን ያፀናው እርሱ ነው፡ እርሱ የአጽናፈ ዓለሙን ጉዳዮች ሁሉ ይገዛል። በምንም መልኩ ሰላማችንን ሊያውክ የሚችል ምንም ነገር በእርሱ ዘንድ አይናቅም። ለእርሱ ለማንበብ የሚያስቸግረው የጨለመ የህይወት ምዕራፍ የለንም፡ እርሱ ሊያስወግደው የሚከብደው ጭንቀት የለንም። የሰማይ አባታችን የማያየው ወይም የእርሱን ትኩረት የማይስብ ምንም አይነት መከራ ከልጆቹ መካከል ታናሽ በሆነ ላይ እንኳን አይመጣም፣ ምንም አይነት ጭንቀት ነፍስን አያሰቃይም፡ እንዲሁም እርሱ የማያዳምጠውና ትኩረት የማይሰጠው አንድም እውነተኛ ፀሎት ከከንፈር አይወጣም። . . . በእግዚአብሔርና በእያንዳንዷ ነፍስ መካከል ያለው ግንኙነት በጣም የግል እና የጠበቀ ከመሆኑም ባሻገር ይህ ግንኙነት በምድር ላይ የእርሱ ጥበቃ የሚያስፈልጋት ነፍስ አንድ ብቻ እንኳን ብትሆን ጥበቃውን ለመለገስና፣ ለእርሷ ደህንነት ሲል የሚወደውን አንድያ ልጁን ለመስጠት የሚያስችል አይነት ግንኙነት ነው።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ፣ ገጽ 95-96።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. እርስዎ ጸሎትን የሚገልጹት ውብ ወይስ ከባድ አድርገው ይሆን? ለዚህ አመለካከትዎ አስተዋጽኦ ያደረገው ምንድን ነው?

2. ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ በጣም ብዙ ትምህርት የሚሰጡ መልእክቶች አሉ። ከእርስዎ አስተሳሰብ ጋር የሚስማማው ወይም ልብዎን የነካው የትኛው ነው?

3. በዚህ ሳምንት ከተጠኑት ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ገፀ-ባህሪያት (ዳንኤል፣ ሄኖክ እና ሙሴ)፣ እርስዎ ከማን የጸሎት ሕይወት ጋር በጣም የተቆራኙ ነዎት? ለምን? ማጠቃለያ፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉት የፀሎት አርበኞች ስናነብ እኛ በዚያ ደረጃ ወደ እግዚአብሔር የቀረበ እና የተሰጠ ልምምድ ሊኖረን አይችልም ብሎ ማሰብ ሊቀለን ይችላል።

ነገር ግን እንችላለን። ልክ እንደ ዳንኤል ተቃውሞ ቢኖርብንም በየቀኑ በመንበርከክ ታማኝና ፅኑ መሆን እንችላለን። እንደ ሔኖክ ፣ እርሱ እንድንሰራ የጠራንንም ሥራ ከመሥራታችን በፊት እርሱን በማማከር ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርን ከርሱ ጋር መራመድ እንችላለን።

እንደ ሙሴ ከሁሉን ቻዩ ጥላ በታች ለመጠለል ስንመርጥ ለቤተሰባችንና በዙሪያችን ላሉት በመፀለይ(በመማለድ) በተፅዕኖ ክበባችን ውስጥ ያሉትን መምራት እንችላለን።




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL