የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ማርቆስ 8:11-12፤ ማቴ. 15:21-28፤ ሉቃስ 7:1-10፤ ኤፌ. 2:8፤ ዕብራውያን 11፤ ራዕይ 14:12።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር
የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” (ዕብራውያን 11:1)።
አንድ ሰው በአንድ ወቅት “እምነት እንደ ዋይፋይ(ገመድ አልባ ኔትወርክ) ነው።
አይታይም፣ ነገር ግን ከሚያስፈልገን ነገር ጋር ሊያገናኘን ኃይል አለው።” ያለ እምነት
ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት እንደማይኖር ምንም ጥርጥር የለውም፡።
ዛሬ እምነትዎ ምን ደረጃ ላይ ነው? በእግዚአብሔር ላይ ያለዎት እምነት ተናግቶ ይሆን?
ምናልባት ከእግዚአብሔር ጋር ባለዎት ግንኙነት እንዴት ወደፊት መሄድ እንዳለብዎት
የማያውቁበት ደረጃ ላይ የደረሱበት ሁኔታ ይኖር ይሆናል። ወይስ እምነትዎ ከአረንጓዴ
ግንድ ወደ ትንሽ ቡቃያ እያደገች፣ በመጨረሻም ወደ ደማቅ፣ በቀለማት ያሸበረቀች አበባ ሆና
ክፍሉን በማይረሳ መዓዛ የምትሞላ ጽጌረዳ ናት? በእውነት፣ “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው
ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” (ዕብ. 11:1)።
“እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን ስላካፈለ” (ሮሜ. 12:3) እምነት ከራሳችን
የምናመነጨው ነገር አይደለም። እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው (ኤፌ. 2:8-9)፣
በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እውን የሚሆነው እግዚአብሔር አስቀድሞ በእኛ ውስጥ
እና ለእኛ እያደረገ ባለው ነገር ምክንያት ብቻ ነው።
በዚህ ሳምንት ስለ እምነት እንመርምር፡- ጥርጥር እና አለማመንን ምን ማድረግ
እንዳለብን፤ እንደ ኢየሱስ ገለጻ ጠንካራ እምነት ምን እንደሚመስል፤ እና “የኢየሱስ እምነት
ያለው” ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ እንመለከታለን።
*ለግንቦት 15 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ምናልባት “ቀይ ባሕር ሲከፈል ወይም መና መሬት ላይ ወርዶ ወይም ኢየሱስ ዕውሩን ሲያበራ ማየት ብችል ኖሮ፣ አምን ነበር” ብለው ሰዎች ሲናገሩ ሰምታችሁ ይሆናል። ወይም ምናልባት እርስዎ ራስዎ እንደዚህ አይነት ሀሳቦች አስበው ይሆናል። በሌላ በኩል፣ ከጥንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ይልቅ አሁን ማመን ቀላል የሚሆንልን ለምንድነው? እስራኤላውያን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ አልነበራቸውም፤ በተጨማሪም እንደኛ ወደ ኋላ መለስ ብለው ለማየት ረጅም ታሪክ አልነበራቸውም። ሙሴ የእግዚአብሔርን አመራርና ቸርነት ለማስታወስ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመልከት አስፈላጊ መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ ተናግሯል (ዘዳግም 4:7-10፣ ዘዳግም 8:2-3ን ይመልከቱ)። ከእስራኤላውያን በተለየ መልኩ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የምንጠቅስበት የ6,000 ዓመታት ታሪክ አለን (ዮሐንስ 20:30-31)። እያንዳንዱ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፣ የእኛም የተለየ አይደለም። ነገር ግን ምልክቶች በዙሪያችን አሉ። ማቴዎስ 24ን ካነበብን፣ አሁን እንኳን ስንት ነገሮች እንደተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ እንደሆነ እናያለን። በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች እንኳን ብዙ ምልክቶች ቢሰጣቸውም ኢየሱስ በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ምላሽ የሰጣቸው እንዴት ነበር? (ማርቆስ 8:11-12ን)
እንደ ፈሪሳውያን ከኢየሱስ ጋር እንከራከር እና እንፈትነው ይሆን? ለማመን
የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶን እያለ፣ በእምነታችን ማነስ ምክንያት “መንፈሱ አጥብቆ
እንዲያዝን” (ማርቆስ 8:12) እናደርገው ይሆን?
“አይሁዳውያን የፈለጉት እነዚያን ምልክቶች አልነበረም። ምንም ውጫዊ ማስረጃ
ሊጠቅማቸው አልቻለም። የሚያስፈልጋቸው የአዕምሮ እውቀት ሳይሆን መንፈሳዊ እድሳት
ነበር።” - ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 406። እኛስ እውነተኛ መንፈሳዊ እድሳትና
ከአምላክ ጋር ዕለት ተዕለት የሚደረግ ጉዞ ያስፈልገን ይሆን? ምናልባት ምልክት አያስፈልገን
ይሆናል፣ ምክንያቱም በጣቶቻችን ጫፍ ላይ ብዙ እውቀት ስላለን፣ በተለይም ከራሳችን
መጽሐፍ ቅዱስ።
ስለዚህ፣ ኢየሱስን በእምነት እጦታችን ምክንያት “በጥልቅ እንዲያዝን” ከማድረግ ይልቅ፣
ኢየሱስ ለቶማስ የተናገራቸውን ቃላት እናስታውስ፡- “‘ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው!’”
(ዮሐንስ 20፡29፤ ዕብ. 11፡1ን)። እግዚአብሔር እውር እምነት እንዲኖረን አይጠይቀንም፤
አስቀድሞ ለማመን ብዙ ምክንያቶችን ሰጥቶናል። ሆኖም፣ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች፣
ሁልጊዜም ለጥርጣሬ ቦታ አለ። ቁልፉ ጥርጣሬን በሚያመጣው ነገር ላይ ሳይሆን እምነትን
በሚያረጋግጠው ነገር ላይ ማተኮር ነው።
በ60 ሰከንዶች ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለዎትን እምነት እንዴት ይገልፁታል?
መልስዎ ከእግዚአብሔር ጋር እያደረጉ ስላሉት ጉዞ ምን ይነግርዎታል?
ኢየሱስ በማርቆስ 4፡40 ላይ የደቀ መዛሙርቱን እምነት በማቴዎስ 15፡21-28 ላይ
ካለችው ሴት እምነት ጋር እንዴት እንደገለጸ ይመልከቱና ያነፃፅሩ።
ኢየሱስን እየተከተልን ስለሆነ ብቻ እምነታችን ጠንካራ ነው ማለት አይደለም።
እንደውም አንዳንድ ሰዎች እንደሚያምኑ ቢናገሩም፣ ኢየሱስ በልባቸው ውስጥ ያለውን
በትክክል ተረድቷል (ዮሐንስ 2:23-25)።
ሉቃስ 7:1-10ን ያንብቡ። ከዚህ ታሪክ ስለ እምነት ምን እንማራለን?
በማርቆስ 9 ላይ፣ ኢየሱስ ከልጁ ጋኔኑን እንዲያወጣለት ወደ ኢየሱስ ስለመጣው ሰው
እናነባለን፣ ነገር ግን “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው!” (ማርቆስ 9:24) ለማለት
የሚያስችል እምነት ብቻ ነው የነበረው።
ከላይ በተጠቀሱት በእያንዳንዱ ግንኙነቶች፣ ኢየሱስ የሰዎችን እምነት መኖር ወይም
ጉድለት አስተውሎ በእምነታቸው ምክንያት ወይም እምነታቸውን ለማጠናከር ሲል
ተአምራትን አድርጓል።
መንፈስ ቅዱስ እንድናምን በሚያነሳሳን መጠን፣ የነፍሳት ጠላት በሕይወታችን ውስጥ
የእግዚአብሔርን መገኘት እንድንጠራጠር ይሠራል። “በነፍስ ውስጥ አለማመን ቦታ
ከተሰጠው አስማታዊ ኃይል አለው። የተዘሩት የጥርጣሬ ዘሮች ፍሬያቸውን ያፈራሉ ነገር
ግን የአለማመንን ሥር ሁሉ ቆፍሮ ከሥሩ መንቀል ያስፈልጋል። እነዚህ መርዛማ ተክሎች
ሲነቀሉ፣ ከጥርጥር ቃላትም ሆነ ከተግባር የሚያገኙትን ምግብ ስለሚያጡ ማደግ ያቆማሉ።
ነፍስ የእምነትና የፍቅር ውድ ተክሎችን በልብ አፈር ውስጥ መትከልና ማሳደግ አለባት።” -
ኤለን ጂ. ኋይት፣ እምነት እና ስራ፣ ገጽ 17።
ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ባህሪው ወይም ስለ ቃሉ ጥርጣሬ ሲኖረን፣ ምን እናደርጋለን?
እርሱ በአምሳሉ ስለፈጠረን እግዚአብሔር የሰውን አስተሳሰብ ችላ አይልም ወይም ሳያይ
አያልፈውም፣ ከአብርሃም፣ ከሙሴ እና ከኢዮብ ጋር እንዳደረገው ሁሉ እኛም ከእርሱ
ጋር እንድንነጋገር ይጋብዘናል። አንዳንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ላልገባን ነገር እጅ መስጠት
ቢኖርብንም እንኳ ታላቅ በሆነውና ማለቂያ በሌለው የእግዚአብሔር አሠራር ውስጥ
መሥራትን እንድንማር ይጋብዘናል።
ለእምነት ያለዎትን ምክንያታዊ መከራከሪዎችን(አመክንዮዎችን) ያስቡ። በተመሳሳዩ
ደግሞ፣ አመክንዮ ቆሞ ጠንካራ እምነት መተግበር የሚኖርብን መቼ ነው?
ኢየሱስ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ትንሽ እምነት ካላችሁ፣ ተራሮችን ታንቀሳቅሳላችሁ ብሏል (ማቴ. 17:20)። የሰናፍጭ ዘር አይታችሁ የምታውቁ ከሆነ፣ ምን ያህል ትንሽ እንደሆነች ታስተውላላችሁ። ሆኖም ግን፣ ይህች ትንሽ እምነት እንዲህ አይነት ትልቅ ለውጥ ልታመጣ ትችላለች። ስለዚህ፣ እምነት በጣም አስፈላጊ ነው እና ከሰው አቅም በላይ የሆነን ነገር ለማድረግም ኃይለኛ እና ጠንካራ መሆን አለበት። ከሰው በላይ የሆነ ነገር። ሆኖም፣ ልክ የሰናፍጭ ዘር ወደ ትልቅ ዛፍ ሊያድግ እንደሚችል (ማቴ. 13:31, 32)፣ እምነታችን የሚያድግ እንጂ የማያድግ ሆኖ መቆየት የለበትም። በእርግጥም፣ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የተወሰነ እምነት ያስፈልገናል (ሮሜ. 12:3ን ይመልከቱ)። ኤፌሶን 2:8 በመዳን ውስጥ እምነት ስላለው ሚና ምን ይነግረናል? አንድ ሰው “እግዚአብሔር ምንም ስላልሰጠኝ እምነት የለኝም” ብሎ ቢናገር ትክክል የማይሆነው ለምንድን ነው?
መጀመሪያ እምነት ቁሳዊ ነገር እንዳልሆነ መረዳት አለብን፤ በመንፈስ ቅዱስ የሚነሳሳ
የሰው ምላሽ ነው። እግዚአብሔር ቸር አስጀማሪ ነው፣ እሱም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት
እንዲሰራ ስንፈቅድለት ወደ ራሱ ይስበናል (ኤር. 31:3)። በኢየሱስ ሞት በኩል ለተሰጠን
የእግዚአብሔር ጸጋ ምላሽ በሆነው እምነት ምክንያት ድነናል። የዳንነው በእግዚአብሔር
ጸጋ ምክንያት ስላመንን ነው። ይህ ከእርሱ ጋር ግንኙነት የመፍጠራችን ዋና ማዕከል ነው።
በመቀጠል፣ እምነት ስሜት እንዳልሆነ ማስታወስ አለብን። “ብዙዎች እምነትን በተግባር
ላይ ማዋል መብታቸውና ግዴታቸው ሆኖ ሳለ ብዙውን ጊዜ እምነት ብቻ ሊያመጣ
የሚችለውን ስሜት እየጠበቁ አይለማመዱትም። ስሜት እምነት አይደለም… እምነት እኛ
እንድንለማመደው የተሰጠን ነው፣ ነገር ግን አስደሳች ስሜት እና በረከት ከእግዚአብሔር
የሚሰጥ ነው።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ 72
አንዳንድ ሰዎች ለእግዚአብሔር ቅርብ ስላልሆኑ ወይም እንደ ክርስቲያን መሆን
ሲገባቸው ስላልሆኑ እምነት እንደሌላቸው ሊሰማቸው ይችላል። ነገር ግን እምነት ማለት
በጥሩ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በህይወትዎ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ ሙሉ በሙሉ
መረዳት በማይችሉበት በጨለማ ወይም በማዕበል ጊዜም እንኳ እግዚአብሔርን ማመን
እና መተማመን ነው። ስሜቶች የሃይማኖት ልምምዳችንን ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት መቆጣጠር የለባቸውም። እምነታችንን በተግባር ማሳየት እና መጥራት
የሚያስፈልገን ከእግዚአብሔር የራቅን እንደሆንን ስናስብ ነው (በማርቆስ 9:24 ላይ ያለው
አባት እንዳደረገው)።
የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይመልከቱ እና ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር
ያለዎትን ግንኙነት ለማጠናከር በእምነት የራስዎ አድርገው ይቁጠሯቸው፦ ዕብ. 12:1-2፤ 2
ዜና 15:7፤ ሮሜ. 3:23-26፤ ሉቃስ 7:50። ወደ እግዚአብሔር በሚጸልዩበት ጊዜ ጥቅሶቹን
ጮክ ብለው ይናገሯቸው።
ዛሬ ታላቁን የእምነት ምዕራፍ ዕብራውያን 11ን በማጥናት የተወሰነ ጊዜ ያሳልፉ።
መጀመሪያ ሳያቋርጡ ጮክ ብለው ያንብቡት ። ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ያንብቡት፣ እና
ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልሶችዎን ይፃፉ፡
y
ቁጥር 1ን እንደገና ያንብቡ። ዛሬ እስካሁን ያላዩትን ምን ተስፋ እያደረጉ
ነው? (ስለ አስቸኳይ ፍላጎቶች እና ዘላለማዊ ሕልሞች ያስቡ።)
y
በግል ምስክርነትዎ እና በመለወጥዎ ውስጥ እምነት ምን ሚና ይጫወታል?
y
ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ፍጥረታቱ የሚናገረውን ቁጥር 3ን እንደገና
ያንብቡ። በብዙ መንገዶች የፈጣሪ አምላክን መኖር በእምነት መቀበል ቀላሉ
ነገር የሆነው ለምንድን ነው?
y
ቁጥር 6ን ያንብቡ እና የዚህን ጥቅስ መልእክት በራስዎ ቃላት ይፃፉ።
ከቁጥር 7-40 የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችን ሕይወት ይገልፃሉ። እነዚህ ሰዎች
ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጥንካሬ ለመግለጽ እምነት ማዕከላዊ ነገር የሆነው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔርን ማወቅ እና ከእርሱ ጋር ሕያው እና ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖረን
እምነትን ይጠይቃል። እርስዎ እምነትዎን እንዴት ማጠናከር ይችላሉ? እምነቱ እየተወዛወዘ
ያለን ሰው እንዴት ማበረታታት ይችላሉ? ጥቂት ሀሳቦች እነሆ፡-
ትንሽ እምነት (እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት) ኃይለኛ ነው እና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
ለማሳደግ የሚያስፈልገውም እሱ ብቻ ነው (ማቴ. 17:20)። እርስዎ ከእርሱ ጋር ለመሥራት
ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ፣ እግዚአብሔር እምነትዎ እንዲያድግ ይረዳዎታል።
እምነት የሚመጣው እግዚአብሔር በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲናገረን ከመስማት ነው
(ሮሜ. 10:17)። በየዕለቱ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ጸሎት ቁርጠኛ ይሁኑ።
እግዚአብሔር እምነትዎን እንዲጨምርልዎ ይጠይቁት (ሉቃስ 17:5)። ልክ ወደ ኢየሱስ፣
እየጮኸ “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው!’” (ማርቆስ 9:24) እንዳለው አባት
አለማመናችንን ለይተን ማወቅ እንችላለን እና እምነታችንን እንዲጨምር እግዚአብሔርን
መጠየቅ እንችላለን። እምነት እና ጥርጣሬ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ (ማርቆስ 9:24)።
ጥያቄዎች ስላሉዎት ብቻ ከእግዚአብሔር አይራቁ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ መዳንዎን በፍርሃትና
በመንቀጥቀጥ (ፊልጵ. 2:12–16) መፈፀም እና እምነትዎን ልክ አምስቱ ሰነፍ ደናግልት ለማድረግ
እንደሞከሩት (ማቴ. 25:8) ከሌላ ሰው ከመበደር ይልቅ “የራስ ማድረግ” አስፈላጊ ነው።
ለመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ምላሽ ይስጡ እና በሕይወትዎ ውስጥ ከእርሱ የበለጠ እንዲሰጥዎት
ይጠይቁ። እምነትዎን ይለማመዱ። እምነት ስሜት ሳይሆን የማመን ውሳኔ መሆኑን
ያስታውሱ። በጨለማ ውስጥ ሊያዩት በማይችሉበት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር እዚያ
እንዳለ ያስታውሱ (2 ቆሮ. 5:7)።
እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ የምስጋና ጸሎታችሁ ክፍል እንዲሆን፣ “ታላቅ ታማኝነት”
የሚለውን የመዝሙር ቃላት ያሰላስሉ።
ይህ ዓለም ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ፣ የሦስቱ መላእክት መልእክት አንድ ክፍል የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስለሚጠብቁ እና የኢየሱስ እምነት ስለሚኖራቸው ሰዎች ይናገራል። ራዕይ 14:12ን ያንብቡ። “የኢየሱስ እምነት” ምን ማለት ነው?
የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች በእምነት መጽደቅን እንዴት እንደተረዱ ስታጠኑ፣ በ1890ዎቹ ውስጥ የኢየሱስን እምነት እና የሦስቱን መላእክት መልእክቶች መረዳት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠናክሮ እንደነበር ታያላችሁ። እስከዚያ ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗ በሕጉ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ ነበር፣ እና የበለጠ የወንጌል አጽንዖት ያስፈልጋት ነበር። ኤለን ጂ. ኋይት በሚገባ ጠቅለል ስታደርገው እንዲህ ብላለች፡- “የእግዚአብሔር ትእዛዛት ታውጀዋል፣ ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስ እምነት በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እኩል ዋጋ እንዳለው፣ ሕግና ወንጌል አብረው እንደሚሄዱ አልታወጀም።”—የተመረጡ መልእክቶች፣ መጽሐፍ 3፣ ገጽ 172። ዕብራውያን 11 ጠንካራ እምነት የነበራቸውን ጻድቅ ሰዎችን ቢዘረዝርም፣ ማንም ሰው ከኢየሱስ እምነት ጋር የሚመሳሰል እምነት አልነበረውም። ማቴዎስ 26፡36-42ን ያንብቡ። ይህ በዚህ ወሳኝ ወቅት ስለ ኢየሱስ እምነት ምን ይነግረናል?
የኢየሱስን እምነት ስንይዝ፣ ለእርሱና ለቃሉ በመታዘዝ በእግዚአብሔር የነበረውን
እምነት የራሳችን እናደርጋለን ማለት ብቻ ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ንቁ እና ሕያው የዕለት
ተዕለት ተሞክሮ ይኖረናል ማለት ነው። ኢየሱስን የዕለት ተዕለት ሕይወታችን ማዕከል
ሳናደርግ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያድን ግንኙነት ሊኖረን እንደማይችል ማወቅ እና በተግባር
ማሳየት ነው።
የኢየሱስን እምነት መያዝ ማለት ኢየሱስ በእኛ ውስጥ እንዲኖር ማድረግ ማለት ነው፣
እናም ኢየሱስ የእምነታችን እውነተኛ መሠረት ስለሆነ በልባችን የእርሱን እምነት መያዝ
ነው። አንዳንድ ጊዜ እምነታችን ደካማ እና ልፍስፍስ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ግን ክብር
የሚገባው ነው (ራዕ. 5:9)፣ እናም እምነቱ ለሚያምኑ ሁሉ በራሳችን ተሞክሮ ውስጥ
የሚንጸባረቅ፣ እና በጸጋው ስጦታ ለእኛ ሊቆጠርልን የሚችል ነው።
የኢየሱስን እምነት ምን ያህል እንፈልገዋለን? በትህትና እግዚአብሔርን ይህንን
እንዲሰጠን እንጠይቀው እና ዕብራውያን 11:6ን እንደ ግል ጸሎት አድርገን እንጠይቅ፣ “ጌታ
ሆይ፣ ያለ እምነት አንተን ማስደሰት አይቻልም። ወደ አንተ እመጣለሁ፣ አንተ እንዳለህ እና
ተግተው ለሚፈልጉህ ዋጋ እንደምትሰጥ አምናለሁ። ያንንም አሁን አደርገዋለሁ።” እንበል።
የፀደቅነው (ምህረት ያገኘነውና ከእግዚአብሔር ጋር
ስምምነትን ያገኘነው) በእምነት ነው(ሮሜ 5:1)። ከዚያም በእምነት(ሐዋ. ሥራ 26:18)
እንቀደሳለን(እንደ ኢየሱስ ለመሆን ኃይል መቀበል)። ኢየሱስን ወደ ህይወታችን ስንጋብዘው
በእምነት የእግዚአብሔር ልጆች(ዮሐ. 1:12) እንሆናለን። የምንኖረውም በእግዚአብሔር ልጅ
ላይ ባለን እምነት ነው(ገላ. 2፡20)።
“ባዶነቷን እንደ ተረዳች እና በአዳኟ ሥራ ላይ ሙሉ በሙሉ እንደ ተደገፈች ነፍስ ረዳተ ቢስ
የምትመስል ነገር ግን በእርግጥም አይበገሬ የሆነች ነፍስ የለችም። በፀሎት፣ ቃሉን በማጥናት፣
ከእርሱ ጋር በእምነት ተጣብቆ በመኖር የሰብዓዊ ዘር ድካም ህያው ከሆነው ክርስቶስ ጋር
ሲገናኝ እርሱ በማይለቀው እጁ ይያዛል። Ellen G. White, The Ministry of Healing, p. 182
“በብርቱ ፀሎት፣ ጾምና ልባዊ ትህትና እምነታቸውን ማጠንከር ነበረባቸው። እራሳቸውን
ባዶ አድርገው በመንፈስና በእግዚአብሔር ኃይል መሞላት ነበረባቸው። ሰዎች በዚህ ጨለማ
ዘመን ከሚገዙት ገዥዎች፣ ከባለስልጣናትና በከፍታ ሥፍራ ካሉት የርኩሳን መናፍስት ሠራዊት
ጋር በሚያደርጉት ተጋድሎ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለማግኘት የሚችሉት በእግዚአብሔር
ላይ ሙሉ በሙሉ በመተማመንና ለእርሱ ሥራ ያለ አንዳች ማወላወል ራስን ቀድሶ ሰጥቶ
በቅንነትና ያለመታከት በመፀለይ ብቻ ነው።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 443
1.
ጠላትን ለመቃወም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስለ መትባበር ስናስብ ከላይ የተጠቀሰው ጥቅስ
የሚዘረዝራቸው አምስት ዋና ነጥቦች ምንድናቸው?
2. በዚህ ጦርነት ውስጥ የእምነት ሚና ምንድነው?
3. ይህንን በህይወትዎ ውስጥ እያዩት ያሉት እንዴት ነው?
4. ዕብ. 10:23ን ያንብቡ። ያመንነውን አፅንተን መያዝ ያለብን ለምንድነው?
5. ከባባድ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ ላይ እንድንደገፍ የሚረዳ ዕድል እንደሆነ
የሚናገረው እውነት ረዳተቢስነት ሲሰማን ምን ያክል እናስበዋለን?
ማጠቃለያ፦ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የእምነቱን መጠን የሚያካፍለው ከእርሱ
ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መሠረት እንዲሆን ነው። እንደ እምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ ኢየሱስ
የእምነት ኃይል ምሳሌያችን ነው። እምነታችን ትንሽ ሆኖ በዕንባ እና ራስን በማስረከብ
መንፈስ ወደ እርሱ ስንመጣ እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ ተዓምራትን ያደርጋል(ኤር.
31:2-4 ፣ 9፣11፣12)። ዳግም እንዳንደናቀፍ በእርሱ ቀጥተኛ መንገድ ይመራናል፡ ያኔ ሰላም
ይኖረናል። ኢየሱስ በሁሉም ነገር ፍፁም የሆነ ምሳሌያችን ስለሆነ የእርሱን እምነት መያዝ
የእርሱን ሕዝብ ከሌላው ይለየዋል።