ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ምሳ. 5:3– 14፣ ማቴ. 19:5፣ 1ቆሮ. 7:3-4፣ ምሳ. 13:22፣ 14:26፣ 17:22፣ 23:13፣ 31:10–31።
መታሰቢያ ጥቅስ:- “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፣ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል።” (ምሳ. 3፡5-6)።
ከ
ውልደታችን በኋላ ከወላጆቻችን ጋር የቱንም ዓይነት ግንኙነት ቢኖረንና
ዛሬ በየትኛውም የህይወት ምዕራፍ ልንገኝ ብንችል ጅማሮአችን ያው አባትና
እናታችን ናቸው። በሌላ በኩል አንዳንዶች ካደጉበት ከአንድ አባትና እናት
የሚወለዷቸው ወንድም እህቶች ወይም ዘመዶች ውጪ የራሳቸው ቤተሰብ
ኖሮአቸው ላያውቅ ይችላል።
በየትኛውም ዓይነት ሁናቴ ወይም የዕድሜ ክልል ልንገኝ ብንችል መጽሐፈ ምሳሌ
ለሁሉም ወገን የሚበጁ የህይወት መመሪያዎችን፣ ሥነ ግጥሞችን፣ መጠይቆችንና
የተዋጣላቸውን ጠቢባዊ አባባሎች ይዞአል። በመልእክቱ ቤተሰባዊ ግንኙነቶች
ቀጥተኛ ተደራሽነት ከማግኘታቸው በተጨማሪ ሌሎች ለቤትና ቤተሰብ መተግበር
የሚችሉ የጥበብ ቃላትም ቀርበዋል። መጽ
ሐፈ ምሳሌ ሲወርድ ሲዋረድ ከወላጅ
ወደ ልጅ የሚተላለፈውን እንደ አምላካዊው ፈቃድ የምንመላለስበትን ህይወት
ቁልፍ የያዘ ቤተሰባዊ ሰነድ ነው። መጽሐፈ ምሳሌ ወላጆች እነርሱን ተለይቶ ወደ
ኮሌጅ ለገባ ወይም በሥራ ርቆ ለሄደ ወንድ ወይም ሴት ልጃቸው ሊጽፉ የሚችሉት
ዓይነት ምክረ ሃሳብ ነው። “ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም
ምክር አትተው” (ምሳ. 1፡8)።
እንዲሁም ወላጆች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን
እምነት ለልጆቻቸው እንዲያስተላልፉ የዘዳግም መጽሐፍ ያዛል። መጽሐፈ ምሳሌ
የሚያደርገውም ይህንኑ ነው። ወላጅ አባታችን በሚያደርግልን ጥሪ ውስጥ
እንድንማርና እንድናውቅ የሚሻውን የሰማያዊውን አባታችንን ድምፅ እንሰማለን።
በምሳ. 5፡3-14 የቀረቡትን ከጋብቻ አስቀድሞ የሚስተዋሉ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነቶች ወይም በጋብቻ ላይ የሚደረጉ የምንዝር ግንኙነቶች የሚያስከትሉትን ጦስ ይዘርዝሩ።
በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው በትዳር ውስጥ ቢሆን ወይም ባይሆን ከግልብ
ስሜት የተጠበቀና ራሱን በጋብቻ ለተሳሰረው ጾታዊ ግንኙነት ብቻ ያስገዛ ነው።
ምንም እንኳ በመጽሐፈ ምሳሌ ወንዶች በተለይ ቢጠቀሱም በተመሳሳይ ጽንሰ
ሃሳብ ሴቶች በመኃልየ መሓልይ ተጠቅሰው እናገኛለን፡ (መኃል. 4፡12፣12-15)።
ለተከለከለው ፍቅር የመንበርከክ ችግር ኃጢአት ሊያስከትል ከሚችለው ጦስ አኳያ
ሊመዘን ይገባል።
በግዴለሽነትና በግብታዊነት የሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት ቁርጠኝነት
ስለሚጎድለው እውነተኛው ትስስር ላይ ለመድረስ ፍጹም የተሳነው ነው። ቁሳዊ፣
አካላዊና ስሜታዊ ሐብቶች በከንቱ ይባክናሉ። ከሁሉ በላቀ--አንድ ሰው በህይወቱ
ለሚያደርጋቸው ምርጫዎች ለእግዚአብሔር ምላሽ መስጠቱ የግድ ይሆናል።
እግዚአብሔር ለሰዎች ከሰጠው ስጦታ አንዱ የሆነው የጾታዊ ግንኙነት ዕውቀት
ልዩ መብትና ጥቅም የተሰጠው በጋብቻ ለተሳሰሩ ጥንዶች ብቻ ነው፡ (ማቴ. 19:5፣
1ቆሮ. 7:3-4፣ ዕብ. 13:4)። ተምሳሌታዊ አቀራረብን በተከተለው ጥቅስ እንደ እርካታ
ስሜት መጨመር ሆኖ በተትረፈረፈ ውሃ የተጠቀሰው ሃሳብ በጋብቻ የተሳሰሩ ጥንዶች
የሚያገኙትን ደስታና በጋራ የሚቋደሱትን ፍቅር ያሳያል።
መልእክቱ ታማኝነት
ሲጓደል የሚከሰተውን ብክነት በማነጻጸር ያቀርብልናል። “የልጅነት ሚስትህ” (ምሳ.
5፡18) በሚል የቀረበው አገላለጽ የሁለቱም ዕድሜ እየጎለበተ በሄደ መጠን እርስ
በርስ የተገባቡት ቃል እንደተጠበቀ እንደሚዘልቅ ያሳያል። በዚህ የህይወት ምዕራፍ
ቢደርሱም ባል አሁንም በሚስቱ ፍቅር እንደ ነሆለለ ነው (ምሳ. 5፡19)።
በኃጢአት የወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር በሚኝበት ሁኔታ፤ ጾታዊ ግንኙነት
ሰዎችን በደመነፍስ አባብሎ የማጥመድ ኃይል አለው። ይህም ቢሆን ሰዎች
የሚያመዛዝኑበትና የሚመርጡበት ኃይል በእግዚአብሔር ተችሮአቸዋል። እነዚህን
ፈተናዎች ያለማቋረጥ እንደጨቆንን የማናስቀርና ጸጥ የማናሰኝ ከሆነ ሰብረው
ገብተው ጉድ ያደርጉናል። በመለኮት ለተነደፈው ጋብቻ የሚኖር ጥብቅ ቁርጠኝነት፤
የተከለከለውን ጾታዊ ግንኙነት እድገት የመግታት ኃይል አለው። እግዚአብሔር
ላበጀው በጋብቻ የተሳሰረ ጾታዊ ግንኙነት የሚኖር የዕድሜ ልክ ታማኝነት አርቆ
ማሰብ ብቻ ሳይሆን የራሱን የተትረፈረፈ ወሮታ ጭምር ይዞ የሚመጣ ነው።
በጋብቻ ህይወት ውስጥ እያለ ትዳሩን ሊያፈርስ በሚችል ጾታዊ
ግንኙነት ውስጥ እየዋተተ ያለን ሰው ቢያውቁ ምን ዓይነት ምክረ
ሀሳብ ሊሰጡት ይችላሉ?
በልጆች ላይ ረጅም ውጤት የሚያስከትሉትንና አባቶችን ብቁ ሊያሰኙ የሚችሉትን በመጽሐፈ ምሳሌ የቀረቡትን የሚከተሉትን ባህሪያት ልብ ይሏል፡ ምሳ. 13:22፣ 27:23-24፡
ምሳ. 14:26፡
ምሳ. 15:1-18፣ 16:32፡
ምሳ. 15:27፡
ምሳ. 29:17፡
የአባቶች ባህሪ እንዲሁም የሚተውት ቅርስ በልጆቻቸው ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ
አለው። ልጆች ያላሰለሰ ድጋፍ፣ ታማኝ ፍቅር፣ ምሪትና ምሳሌነትን ፍለጋ ወደ
አባቶቻቸው ይመለከታሉ። መጽሐፈ ምሳሌ የቤተሰባቸውን ፍላጎት ለማሟላት
የሚተጉትን ብልህ መመኪያዎችና የቤተሰብ አስተዳዳሪ አባቶች ያሞግሳል። ሆኖም
ብዙ አባቶች የሚከተሉት መንገድ “ስስታም በቤተሰቡ ላይ ችግር ያመጣል” (ምሳ. 15፡
27) ተብሎ የቀረበውን መልእክት የሚደግፍ መሆኑ ያሳዝናል። አባቶች ከሥራቸው
ይልቅ ለቤተሰቦቻቸው ቅድሚያ ሊሰጡ እንደሚገባ መዘንጋት የለባቸውም።
ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው አባቶች ትዕግሥተኛና ስሜታቸውን
የሚቆጣጠሩ ሆነው ለመገኘት የተቻላቸውን ጥረት ያደርጋሉ። ልጆቻቸው በእነርሱ
ላይ ለሚኖራቸው መተማመን አክብሮት ይሰጣሉ።
ልጆቻቸውን ቀጥተው ከማሳደግ
ውጪ አጉል አዛዥ ናዛዥ ሆነው በልጆቻቸው ላይ ጉዳት ከማድረስ የተቆጠቡ
ጥንቁቆች ናቸው። ከሁሉ በላይ--ራሳቸውን ለመልካም አባትነት ያዋሉ አባቶች
የልጆቻቸው እግሮች በቀናው ጎዳና ይራመዱ ዘንድ እግዚአብሔርን መከተል፣
ብሎም በአምላካዊው ፍቅርና በቃሉ ስር መመላለስ ዓይነተኛ ፍላጎታቸው ነው።
በመጨረሻ--አባት ለልጆቹ ሊያደርግ የሚችለው እጅግ አስፈላጊው ነገር እናታቸውን
እንዲወዱ ማድረግ ነው። የእርሱ ታማኝነትና ለእርሷ ያለው የማያባራ ፍቅር ወይም
ከዚህ በተቃራኒ ሊስተዋል የሚችል ችግር ልጆች አድገው ራሳቸውን እስኪችሉ
በአእምሮአቸው ላይ ተቀርጾ የሚቀር ውጤት አለው።
ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን፣ ለትዳርና ቤተሰባዊ ህይወት ሊኖር የሚገባ ቁርጠኝነት
እንዲሁም አንድ ሰው ለራሱም ሆነ ለማኅበረሰቡ የሚኖረው እውነተኝነት በመጽሐፈ
ምሳሌ ቁልፍ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቀርቦአል። ጉብዝና በማንኛውም መልኩ መተማመን
የሚያደርገው በግለሰቡ የልብ ሁናቴ ላይ ነው። ዝሙት፣ ስንፍና እና ክፉ ምኞት
በተንሰራፋበት ሁናቴ--ጥበበኛ አባትና ባል ትክክለኛውን ምርጫ መምረጥ ይችል
ዘንድ ዘወትር የእግዚአብሔርን እርዳታ ይማጸናል።
እዚህ ላይ የቀረቡት የግብረገብ መርኅዎች አባት ለሆነ ወይም ላልሆነ-ለእያንዳንዱ ሰው አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? እርስዎ መልካም
ሆኑ ወይም መጥፎ ድርጊቶችዎ በልጆች ላይ ያላቸው ተጽእኖ
ምን ይመስላል? በየትኞቹ አቅጣጫዎች ይበልጥ ጥንቁቅ መሆን
ይጠበቅቦታል?
ልጅን ስለ መቅጣትና ማረም አስፈላጊነት መጽሐፈ ምሳሌ ምን ያስተምረናል? ምሳ. 10:17፣ 23:13-14፣ 29:1፣ 29:15።
ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲቀጡ ምክንያት ሊሆኗቸው ከሚችሉ ነገሮች መሃል
በማሕበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸውን ባህሪያት ሲያሳዩ፣ ባለመታዘዛቸው
ወይም በፈጸሙት የሚያሳፍር ድርጊት ደስ አለመሰኘታቸውን ለመግለጽ ሊሆን
ይችላል። ሆኖም እነዚህን ለጋ የቤተሰብ አባላት ከመቅጣት ጋር በተያያዘ አምላካዊው
እቅድ ምን ይመስላል? ሕፃናት ለነገው ማንነታቸው መልካም ተስፋ ይኖራቸው ዘንድ
ከወዲሁ ሥርዓት እንዲይዙ ሊደረጉ እንደሚገባ መጽሐፈ ምሳሌ ይነግረናል (ምሳ.
19፡18)። ሕፃናት ኃጢአተኛ ተፈጥሮ እንዳላቸው ፈሪሐ እግዚአብሔር ያላቸው
ወላጆች ያውቃሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊረዳቸው የሚችል አንድ ብቻ ኃይል
ያለ ሲሆን እርሱም ክርስቶስ ነው፡ (Ellen G. White, Education, p. 29)። ልጅ
መቅጣትን ያካተተው የክርስቲያን ወላጅነት፤ ተልእኮው ልጆችን ወደ እግዚአብሔር
መምራት ነው።
ለጋ ለሆነው ተክል ድጋፍ ማድረግ፡-- በክርስቶስ ሥርዓት ማስያዝ እንደ ቅጣት
ወይም የበላይነትን ማሳያ ሳይሆን ከስህተት እንደ መመለስና ማረም ይታያል።
አፍቃሪ ወላጆች የኃጢአትን ጥንካሬ ተገንዝበው ልጆቻቸውን በክርስቶስ ዱካ
ይመሩ ዘንድ አምላካዊው እቅድ ነው።
አትክልተኛው አዲስ ለተከላቸው ችግኞቹ
የተለየ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያደርግ ሁሉ፤ ልጆች በራስ መተማናቸው
ጎልብቶ በእግዚአብሔር የሚታመኑና የመለኮታዊው የደኅንነት ዕቅድ ተባባሪዎች
የሚያደርጋቸው ብስለት ላይ እስኪደርሱ ወላጆች ለእንቡጥ ልጆቻቸው ጥንቃቄ
የሚያደርጉ፣ በደግነትና በጽኑ እያረሙ ከስህተት የሚመልሱና የሚመሩ ሊሆኑ
ይገባል።
በሚከተሉት ጥቅሶች ለወላጆች የቀረበው መልእክት ምን ይመስላል--ምሳ. 13፡24፣
23፡13-14?
ልጆችን ሥርዓት ከማስያዝ ጋር በተያያዘ “አርጩሜ” የተሰኘው ቃል በጥቂት
ስፍራዎች ተጠቅሶ እንመለከታለን። ወላጆች ልጆቻቸውን ሥርዓት ለማስያዝ
የሚቆርጡት አርጩሜ ዓላማው ምን መምሰል ይኖርበታል በሚል ለሚንሸራሸረው
ሀሳብ ሰማያዊው እረኛ እንዴት መንጋውን እንደሚመራ የተገለጸበት ሥነ ጽሑፋዊ
አቀራረብ በክርስትናው ዓለም እጅግ ዝነኛ ነው (መዝ. 23፡4)።
ልጆችን በትዕግሥት
በማስተማር፣ መልካም ምሳሌ በመሆን፣ መልካም ግንኙነት በመፍጠርና የቀረበ
ጓደኝነትን በመመስረት በልጆች ላይ አዎንታዊ ለውጥ መምጣት እንደሚቻል
መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል (ዘዳ. 11፡18-19)። ልጅን በመቅጣት የታለመውን የማረምና
የማነጽ ውጤት ለማምጣት--ልጆች በወላጆቻቸው እንደሚወደዱ የሚሰማቸው
መሆኑ እጅግ ወሳኝ ነው (ምሳ. 13፡24)።
ቅጣት ጭካኔ በተሞላበት ወይም በተሳሳተ መንገድ የታለመለትን ግብ
ሲስት ወላጆች ይህን ችግር ከራሳቸው ከልጆቻቸው ጋር እንዴት ሊፈቱ
ይገባል?
በዕለት ከዕለት ኑሮ ሊያበሳጩ የሚችሉ ጉዳዮችን መጽሐፈ ምሳሌ ፈገግ እያደረገ የሚያስነብበው ለዛ ያለው አቀራረብ ምን ይመስላል? ምሳ. 21:9፣ 19፣ 27:15-16።
ብዛት ያላቸው የዚህ መጽሐፍ ምሳሌያዊ አነጋገሮች የተቀራረበውን ግንኙነታችንን
ተከትሎ አንዳችን ለሌላው ልናንጸባርቅ በምንችላቸው ስሜቶች ዙሪያ አጽንኦት
ይሰጣሉ። ላዘነ ልብ “እንደሚዘምረው” (ምሳ. 25፡20) እና ቤተሰቡ እንደተኛ ወፍ
ሳይንጫጫ ማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ “እንደሚመርቀው” (ምሳ. 27፡14) ዓይነቶቹን
በመጥቀስ ቀለል ባለና ለዛ ባለው አቀራረብ የተፈለገውን መልእክት ያስተላልፋሉ።
ስለ ጨቅጫቃዎቹ ሴቶች የተጻፉትን ጥቅሶች የሚያነቡ ሚስቶች በወንዶች ዙሪያ
አንዳንድ “ምሳሌያዊ አነጋገሮች” ማከል ይፈልጉ ይሆናል። ባሎች ቤት ውስጥ ላለው
ድባብ ኃላፊነቱን በእኩል እስከተጋሩ ድረስ ይህ ምሳሌያዊ ባህሪ በሚስቶች ላይ ብቻ
አነጣጥሮ የሚቀር ሳይሆን--ጨቅጫቃነት ባሎችንም መጨመሩ አይቀሬ ይሆናል።
(በቀያፋ ወይም ሐና ቤት መኖር ምን ሊመስል እንደሚችል በዐይነ ሕሊናዎ ይሳሉ)።
ፍልቅልቅ ልብ ጠቀሜታው ብዙ ነው። ለዛ ያላቸው አስቂኝ ቀልዶች ለቤተሰባዊው
ሕይወት ወሳኝ ናቸው። ሳቅና ጨዋታ ጭንቀትና ጥበት እንዲቀንስ የሚያደርግ
አካል አፍታች ዘይት ነው። “ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤ የተሰበረ ልብ ግን
መንፈስን ያደርቃል” (ምሳ. 17፡22)።
የመጽሐፈ ምሳሌ ተምሳሌታዊ አቀራረቦች
አንዳንድ የሚያስቸግሩንና የሚረብሹንን የገዛ ባህሪያችን ወስደው ሳንወድ በራሳችን
እንድንስቅ ያደርጉናል። ምናልባት ፈገግ ማለታችን ራሳችንን ስለሚረብሹን ወይም
ስለሚያስቸግሩን ባህሪያት ወይም ልምዶች ለመነጋገር የተሻለ ሁኔታ ላይ እንድንሆን
ያስችለናል። በሌላ በኩል ሳቅ ጽኑ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አሳንሰን
ወይም አድበስብሰን ለማለፍ የምንጠቀምበት መሣሪያ መሆን የለበትም።
መጠነኛ ትኩሳት የአንድ ብርቱ ህመም ምልክት ሊሆን እንደሚችል ሁሉ
በአንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብ አባል የሚታይ ጠብ፣ ንዝንዝና አቤቱታ በልብ
ውስጥ የታመቀ ቁጣ መኖሩን ያመላክታል። የችግሩ መንስኤ ምናልባት ከእርስ በርስ
ተግባቦት እጦት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ዋናው ህመም ፈውስ ማግኘት ከቻለ
የበሽታ ምልክት የማይጠፋበት ምክንያት አይኖርም። ቤተሰብ የተፈጠረውን ችግር
ዞር ለማድረግ በመሞከር ፋንታ አባላት በጌታ ላይ የተመሰረተ ፍቅር እንዲኖራቸውና
በሚያስፈልጋቸው ነገርም ሆነ ስሜታቸውን በመለዋወጡ ረገድ አንዱ ለሌላው
ቁርጠኛ የሚሆንበት መንፈሳዊ መላ ሲፈለግ በውስጣቸው የታመቀው ንዴት ከሥሩ
ተመንግሎ መወገድ ይችላል።
ሳቅ ለቤት ወሳኝ ቅመም የሆነው ለምንድን ነው? ሳቅ ለበጎ ወይም
ለክፉ ተጠምዝዞ መዋል የሚችለው እንዴት ነው? መልስዎን ይዘው
ይቅረቡ።
የመጽሐፈ ምሳሌ መልእክት ጠባየ መልካም የሆነችውን ሚስት በማወደስ ወደ ፍጻሜ ይመጣል። የተሞገሱትን ጸባዮችና ልዩ ችሎታዎች ለይተው ለማስቀመጥ ይሞክሩ፡ (ምሳ. 31፡10-31)።
በጥቅሱ የቀረበችው እንስት እንደ ሥነ ግጥሙ ለየት ብላ ባልተለመደ መንገድ
ተገልጻለች። ከምዕ. 13፡10 ጀምሮ የቀረበው እያንዳንዱ ጥቅስ ከ22ቱ የዕብራውያን
ፊደላት አደራደር ቅደም ተከተል ማለትም ከ “ሀ” እስከ “ፐ” ይዘልቃል። አንዱም
የዕብራውያን ፊደል ሳይጎድል ይህችን እንስት ለማሞገስ ያለውን አሟጦ በእንዲህ
ዓይነት የተሟላ አወቃቀር ለዚህች ሚስት አግባብ ያለው ክብር መስጠቱን አንባቢው
ሊያስተውል ይችላል።
መልካም አጋር የምትሆንን ሚስት ስለ ማግባት በመጽሐፈ ምሳሌ የተሰጠው አጽንኦት
በአይሁድ ረቢ አባባል “የባል ቤቱ ሚስቱ ናት” በሚል ተንጸባርቆአል። “መልካም
ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት” (ምሳ.
12፡4)።
እዚህ ላይ ማለትም በመጽሐፈ ምሳሌ መጨረሻ ላይ ይህች እንስት ብዛት
ያላቸው ልዩ ልዩ ችሎታዎች እንዳሏት ሆና ተስላለች፡ ፈትልና ልብስ ስፌት፣ መሬት
መግዛትና የዕርሻ ሥራ መሥራት፣ የቤትና የንግድ ሥራ አስተዳደር ከብዙ በጥቂቱ
ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለቤተሰቧ ተገቢውን ጥንቃቄ ታደርጋለች። የቤተሰቧ
አባላት ይወዷታል ያደንቋታልም።
እነዚህ መጠነ ሰፊ ክህሎቶች ከሁሉም ሴቶች መጠበቅ እንደሌለባቸው ሁሉ ባሎች
ለሚስቶቻቸው እንደ መለኪያ የሚወስዷቸው መስፈርት መሆንም አይችሉም።
ይልቁንም መጽሐፉ ለሴቶች በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑትንና (ወንዶችም ሳይዘነጉ)
ገጣሚነት ያሏቸውን እነዚህ ክህሎቶችና ልዩ ብቃቶች እየገለጸ ለአጠቃላዩ ግንኙነት
ገጣሚነት ያላቸውን መልእክቶች ያስተላልፋል፡ ታማኝ ባህሪ፣ ርኅራኄ፣ ጽኑ እና
የሚመኩበት፣ ደግነት እና ብርቱ ሠራተኛነት። ምሳ. 31፡30 እንደሚነግረን የእንዲህ
ዓይነቱ ህይወት ምስጢር “እግዚአብሔርን መፍራት” ነው።
“ጠባየ መልካም” ወይም “ልባም ሴት” (/1962 ትርጉም/ ምሳ. 31፡10) በሚል
የተጠቀሱት ቃላት “ብርቱ”፣ “ኃያል” ወይም “ሐብታም” የሚል ፍቺ አላቸው።
እንዲሁም በመዝ. 62፡10 “ባለጠግነት” (1962 ትርጉም) በሚል የተተረጎመው
ቃል በመጽሐፈ ኢያሱ “ጽኑአን ኃያላን” (ኢያ. 1፡14 /1962 ትርጉም/) የሚል
ፍቺ ተሰጥቶታል። ቦዔዝ ሩትን “ምግባረ መልካም” በሚሉ ቃላት ስታመሰግን
ይታያል። በምሳ. 31፡10 ግን ቃላቶቹ ከሐብት ወይም ብልጽግና ጋር ተያያዥ ጽንሰ
ሃሳብ እንዳላቸው እንመለከታለን። የእውነተኛ ባለጠግነት መሰረት ሐቀኝነትና
እግዚአብሔርን መፍራት ነው። ይህ በከበሩ ድንጋዮች ላይ ከተመሰረተው ሐብት
ይልቅ እጅግ የከበረና ዋጋ ያለው ነው።
በእርስዎ ህይወት ላይ ተጽእኖ ያሳደሩ ጀግኖችና ጠባየ መልካም ሴቶች እነማን
ናቸው? እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ልዩ መገለጫ መልካም ምግባሮች እንዴት
ይዘረዘራሉ?
: “ክርስቲያኖች ልቦቻቸውን በትጋት በመጠበቁ ረገድ ጥንቁቅ
ሊሆኑ ይገባል። ለአምልኮ ያላቸውን ፍቅር ሊያዳብሩና ለአገልግሎት ያላቸውንም
መንፈስ አጽንተው ሊይዙ የግድ ነው። ብዙዎች ለአምልኮ፣ አምላካዊውን ቃል
ለመመርመርና ለጸሎት የሚያውሉት ጊዜ እንደ ባከነ ሲቆጥሩና ሲቆጩ ይስተዋላሉ።
ሰዎች እነዚህን ነገሮች ከአምላካዊው ብርሃን አኳያ መመልከት ቢችሉ ከማንኛውም
ነገር በፊት ሰማያዊውን መንግሥት ማስቀደም በቻሉ ነበር።
አንድ ሰው ልቡ ከሰማይ
ጋር ትስስር እንዲፈጥር ሲፈቅድ ተግባሩ ሁሉ በብርታትና በወኔ የሚከወንና ህይወት
ያለው ይሆናል። አእምሮ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ሆኖ ሲገራ ጥረቶቻችን
ህይወትና ቅንነት ያገኛሉ” (ኤፌ. 4፡13) —Ellen G. White Comments, The
SDA Bible Commentary, vol. 3, p. 1157.
1.አያሌ ክርስቲያኖች ልቦቻቸውን ከፈተና ለመጠበቅ ባላቸው ያላሰለሰ
ምኞት በዚህ ዙሪያ ከተዋቀሩ ቡድኖች ልዩ እገዛና ድጋፍ ያገኛሉ።
ለመሆኑ ይህ ቡድን በጸሎት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በመንፈስ
ቅዱስ ላይ የመተማመን ድጋፍ የሚሰጠው እንዴት ነው? አንድ
ሰው የሚያባሩ በማይመስሉ ወደ ኃጢአት ከሚወስዱ ፈተናዎች ጋር
በሚያደርገው ግብ ግብ የባለሙያ እርዳታ ሊያስፈልገው የማይችልበት
ሁኔታ ይኖር ይሆን?
2.ለረቡዕ ትምህርት የመጨረሻ ጥያቄ መልስዎን ያቅርቡ። በቀረቡት
የተለያዩ መልሶች አንደምታ ዙሪያ ተወያዩ። እግዚአብሔር የሰጠን አያሌ
ድንቅ ነገሮች እንደመኖራቸው ሳቅና የጨዋታ ለዛ ጉዳት ሊያደርስ
ወደሚችል ሁኔታ መጠምዘዝ የሚችሉት እንዴት ነው?
3.በምሳ. 31 ከቀረበው በተቃራኒ ዘመን አመጣሹ ባህል በሴቶች ላይ
ገዝፈው እንዲታዩ እያደረገ ያለው የቱን ዓይነት ስብዕና ነው?
4.በአጠቃላይ ሲታይ በእርስዎ ማኅበረሰብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው
የቤተሰብ መርኅዎች ጋር በቀጥታ የሚጣረሱ አንዳንድ ባህላዊ
አመለካከቶች የትኞቹ ናቸው? በተቃራኒው ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው
መርኅዎች ጋር አግባብ ያላቸው ባህላዊ አመለካከቶች ይኖሩ ይሆን?
ካሉ የትኞቹ ናቸው? ቤተሰባዊውን እሴት በማጠንከር ረገድ ጥቅም ላይ
መዋል የሚችሉት እንዴት ነው?