
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዕብ. 9፡15፣ ዘፍ. 15፡ 6-21፣ ኤር. 34፡8-22፣ ኤፌ. 3፡14-19፣ ዕብ. 7፡27፣ ዕብ. 10፡10፣ ዕብ. 9፡ 22-28
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም አድርጎአቸዋልና።” (ዕብ. 10፡14) ፍጹማን
አ
ንድ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለና የተሰቀለ ሰው እንደ አምላክ ይመለክ
የሚለው ኃሳብ ለጥንታዊው አእምሮ የስድብ ያክል ነበር። በሮም
ስነፅሁፍ ውስጥ ይህንን ኃሳብ የሚቃወሙ ጥቂት ማጣቀሻዎች
ይገኛሉ። ለአይሁዳውያኑ በእንጨት ላይ የሚሰቀል በእግዚአብሔር የተረገመ
እንደሆነ ህጉ ይናገራል(ዘዳ. 21፡23)።
ስለዚህ በካታኮምቦ የምናገኛቸው የክርስትያን ስዕሎች የበቀቀን(ዘላለማዊነትን
ያመለክታል ተብሎ ስለሚታሰብ)፣ የርግብ፣ የአሸናፊ ሯጭ እጆች እና የአሳ
ነበሩ። ቆየት ብሎ ደግሞ የኖህ መርከብ፣ አብርሃም በይስሃቅ ፈንታ በጉን
ሲሰዋ፣ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ፣ ዮናስ ከአሳው ሆድ ሲተፋ፣
ጠቦት የያዘ እረኛ፣ ወይም ሽባው ሲፈወስና አልአዛር ከሞት ሲነሳ የሚያሳዩ
የተዓምራት ስዕሎችን መጠቀም ጀመሩ።
እነዚህ የመዳን፣ የድልና የእንክብካቤ
ምልክቶች ነበሩ። በሌላ መልኩ መስቀሉ የመሸነፍንና የማፈርን መልዕክት
ያስተላልፋል። ሆኖም የክርስትና አርማ የሆነው መስቀሉ ነበር። እንደውም
ጳውሎስ ወንጌሉን “የመስቀሉ ቃል”(1 ቆሮ. 1፡18) ብሎ ጠርቶታል።
በዚህ ሳምንት መስቀሉን ከዕብራውያን መልዕክት አንፃር እንመለከተዋለን።
ለየካቲት 19 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ዕብራውያን.9፡15 እንደሚገልጽልን ኢየሱስ እንደ መስዋዕት መሞቱ
በመጀመሪያው ኪዳን ሕግን የተላለፉትን የመቤዠት አላማ የነበረው ሲሆን
ይህ ደግ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የዘላለም ርስትን መቀበል እንዲችሉ
የሚያስችል ነው።
በጥንታዊው የቅርብ ምስራቅ በሁለት ሰዎች ወይም ሕዝቦች መካከል የሚካሄድ
ኪዳን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነበር። በመሃል ቃል መገባባትን የያዘ ስነስርዓት
ነው። አምላኮቻቸው መሃላውን የሻረውን(ያላከበረውን) ሰው ይቀጡታል
ብለው ያምኑ ነበር። ብዙ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ቃልኪዳኖች በእንስሳ መስዋዕት
የሚጸኑ ነበሩ።
ለምሳሌ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃል ሲገባ ያ ስነስርዓት እንስሶች
ለሁለት መክፈልን የያዘ ነበረ(ዘፍ.15፡6-21)። ሁለቱ ተዋዋዮች በእንስሳቱ
አካል መካከል በማለፍ ኪዳን ካፈረስኩ እንደዚህ እንስሳ ልከፈል ይላሉ። ልዩ
በሆነ ሁኔታ ኪዳኑን እንደማያፈርስ ለአብርሃም በመግለጽ በእንስሳቱ መካከል
ያለፈው እግዚአብሔር ብቻ ነበር።
ዘፍጥረት 15፡6-21ንና ኤርሚያስ 34፡8-22ን ያነጻጽሩ። እነዚህ
ጥቅሶች ስለ ኪዳኑ ምን ያስተምሩናል?
እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባቱ የተስፋይቱን ምድር እንደ
ርስት እንዲወስዱ አስቻላቸው። ሆኖም ብዙ ትዕዛዛትንና በመሰዊያው ላይ
የደም መረጨትን ያካተተ ነበር። ይህ ደም መርጨት ኪዳኑን ያፈረሰው ሰውን
ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ ነው። የዕብራውያን መልዕክት ደም ሳይፈስ የሐጢያት
ስርየት የለም የሚለው ለዚህ ነው(ዕብ.9፡22)።
እስራኤል ኪዳኑን ሲያፈርስ እግዚአብሔር ህመም በሞላበት አጣብቂኝ ውስጥ
ገባ።ኪዳኑ የተላለፈውን ሞት የሚጠይቅ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ሕዝቡን
ይወድ ነበር። እግዚአብሔር እንዳላየ ቢሆንና ተላላፊዎችን አልቀጣም ቢል
ትዕዛዛቱ የሚያስገድዱ ሆነው ይህች ዓለም ወደ ቀውስ ባመራች ነበር።
የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱን በተለዋጭነት አቀረበ። እኛ ዘላለማዊውን ርስት
መቀበል እንድንችል በኛ ቦታ ሞተ(ዕብ.9፡15፣26፣ሮሜ 3፡21-26)። ማለትም
የህጉን ቅድስና ከፍ አድርጎ እንደያዘ ህጉን ያልታዘዙትን ደግሞ አድኗቸዋል።
ይህንን ሊያደርግ የሚችለው በመስቀሉ ብቻ ነበር።
ህጉ ለወንጌሉ መልዕክት ማዕከል የሆነበትን ምክንያት በዚህ ቦታ
ማየት የምንችለው እንዴት ነው?
የኢየሱስ ሞት ለኃጢአታችን ይቅርታን ወይም ስርየትን አስገኝቶልናል። የኃጢአት ስርየቱ ኪዳኑን ለመተላለፋችን የሚገባንን ቅጣት ከመሰረዝ በላይ ነው። ሌሎች አስፈላጊ ይዘቶችም ነበሩት። የእስራኤላውያኑ የመስዋዕት ስርዓት አምስት አይነት መስዋዕቶች የነበሩት ለዚያ ነው። እያንዳንዱ መስዋዕት የክርስቶስን መስቀል የበለፀገ ትርጉም ለመግለፅ ያገለግል ነበረ። ኤፌሶን 3፡14-19ን ያንብቡ። ጳውሎስ እንዲፀለይ የጠየቀው ስለምን ነበር? አማኞቹን ወክሎ
የሚቃጠል መስዋዕት እንስሳው ሙሉ በሙሉ በመስዋዕቱ ላይ ተቃጥሎ
የሚያልቅበት ነው(ዘሌዋውያን 1)። ይህም ለኛ ሲል ሙሉ በሙሉ ህይወቱን
ያጣውን ኢየሱስን ይወክል ነበር። ስርየት የኢየሱስን ሙሉ መሰጠት የሚጠይቅ
ነው። ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የነበረ ቢሆንም “የባርያን መልክ በመያዝ
ራሱን ባዶ አደረገ” (ፊል. 2፡5-8)።
የእህል ቁርባን (መስዋዕት) እግዚአብሔር ለህዝቡ ምግብን ስለሰጠ የምስጋና
ስጦታ ነበር (ዘሌዋውያን 2)። የዘላለም ህይወት ያገኘንበትንና “የህይወት
እንጀራ” የሆነውን ኢየሱስንም ይወክል ነበር (ዮሐ. 6፡35፣ 48)።
የደህንነት ወይም የህብረት መስዋዕት እግዚአብሔር ስለሰጠው ደህንነት
ከወዳጆችና ከቤተሰቦች ጋር አብሮ መመገብን የሚያሳይ ነው። በመስዋዕቱ
ሰላምን ለኛ የሰጠውን ክርስቶስን ይወክላል (ኢሳ. 53፡5፣ ሮሜ 5፡1፣ ኤፌ.
2፡14)። ደግሞም ስጋውንና ደሙን በመጠጣት በኢየሱስ መስዋዕት አብረን
መካፈል እንዳለብን ያስተምረናል (ዮሐ. 6፡51-56)።
የኃጢአት መስዋዕት ለኃጢአት ስርየት የሚገኝበት ነበር (ዘሌ. 4፡1-5፡13)።
ይህ መስዋዕት መቤዥትን ለማምጣት(ዘሌ. 17፡11) የሚሞተውን የእንስሳውን
ህይወት የሚወክለውን ደም ሚና ያሳያል። ይህም ከኃጢአታችን የዋጀንን
የኢየሱስን ደም ያመላክት ነበር (ማቴ. 26፡28፣ ሮሜ 3፡25፣ ዕብ. 9፡14)።
ለበደል መስዋዕት (ዘሌ. 5፡14 - 6፡7) የካሳ ክፍያ መክፈል በሚቻልባቸው
ጉዳዮች ይቅርታን ያሰጡ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ምህረት ለበደልናቸው
ሰዎች ካሳን ከመክፈል ነፃ እንደማያደርገን ያስተምረናል።
የቤተመቅደስ መስዋዕቶቹ የመዳን ልምምድ ኢየሱስን እንደ ምትክ ከመቀበል
በላይ እንደሆነ ያስተምሩናል። ከርሱ ልንመገብ፣ እርሱ ያካፈለንን ለሌሎች
ልናካፍልና ለበደልናቸው ሰዎች ካሳን ልንከፍል እንደሚገባን ያስተምሩናል።
ዕብራውያን 7፡27ንና ዕብራውያን 10፡10ን ያንብቡ። በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የኢየሱስ መስዋዕት የተገለፀው እንዴት ነው?
“በአገልግሎት እንዳይቀጥሉ ሞት ስለከለከላቸው ዘሌዋውያን ካህናቱ
ቁጥራቸው ብዙ” ሲሆን(ዕብ. 7፡23) ዘላለም ከሚኖረውና ዘላለማዊ ክህነት
ካለው ከኢየሱስ ጋር በንፅፅር ተቀምጧል(ዕብ. 7፡24-25)። ዘሌዋውያን
ካህናቱ በየዕለቱ በየዓመቱ “የአምላኪውን ህሊና የማያነፁ”(ዕብ. 9፡9፣ ዕብ.
10፡1-4) መስዋዕቶችንና ስጦታዎችን ያቀርቡ ነበር።
ኢየሱስ ግን አንድ ጊዜ ራሱን የማያዳግም መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ (ዕብ.
10፡10-14) ህሊናችንን በማንፃት(ዕብ. 9፡14፣ ዕብ. 10፡1-10) ኃጢአታችንን
አስወግዶልናል(ዕብ. 9፡26)። የኢየሱስ መስዋዕት ከእንስሳቱ መስዋዕት
የሚበልጠው እርሱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ የፈፀመ
የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ ነው(ዕብ. 7፡26-28፣ ዕብ. 10፡5-10)።
የኢየሱስ መስዋዕት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሆኑ የተለያዩ ትርጓሜዎች
ይኖሩታል።
በመጀመሪያ የኢየሱስ መስዋዕት ሙሉ በሙሉ ውጤታማና በሌሎች ሊበለጥ
የማይችል መስዋዕት ነበር። የሌዋውያኑ መስዋእቶች ውጤታማ ስላልነበሩ
መደጋገም ነበረባቸው፤ “ፍፁም ሊያደርጋቸው ቢችል ኖሮ መስዋዕት ማቅረቡን
ይተዉት አልነበረምን? (ዕብ. 10፡2)።
በሁለተኛ ደረጃ በብሉይኪዳን የነበሩት የተለያዩ አይነት መስዋዕቶች በሙሉ
ፍፃሜያቸውን ያገኙት በመስቀሉ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እኛን ከኃጢአት
ማንፃት(ዕብ. 9፡14) ብቻ ሳይሆን ኃጢአትን ከህይወታችን አውጥቶ በመጣል
ቅድስናንም ይሰጠናል(ዕብ. 10፡10-14፣ ዕብ. 9፡26)። ካህናቱ ህዝቡን ወክለው
በቤተመቅደሱ ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ከመቆማቸው በፊት መንፃትና
ራሳቸውን ቀድሰው መስጠት ነበረባቸው(ዘሌዋውያን 8፣9)።
የኢየሱስ
መስዋዕት በድፍረት በእግዚአብሔር ፊት እንድንቀርብና(ዕብ. 10፡10-14) እንደ
“ንጉስ ካህናት” እንድናገለግለው(ዕብ. 9፡14፣ 1ጴጥ. 2፡9) ያነፃናል እንዲሁም
ይቀድሰናል(ዕብ. 10፡10-14)።
በመጨረሻም የኢየሱስ መስዋዕት ለመንፈሳዊ ህይወታችን ምግብን ይሰጠናል።
ተመልክተን ልንከተል የሚገባንን ምሳሌ ይሰጠናል። ስለዚህ የእብራውያን
መልዕክት አይናችንን በኢየሱስ ላይ በተለይም በመስቀሉ ላይ ወደተካሄዱት
ክስተቶች ተመልክተን ምሳሌውን እንድንከተል ይጋብዘናል (ዕብ. 12፡1-4፣
ዕብ. 13፡12-13)።
መስቀሉ እግዚአብሔር በኛ ላይ የሚያፈሳቸው በረከቶች ሁሉ
መሠረት ነው። ከኃጢአት መንፃትን፣ ለማገልገል መቀደስንና
ለዕድገት ምግብን ይሰጠናል። በኢየሱስ የተሰጠንን ልምምድ
በተሻለ መልኩ መለማመድ የምንችለው እንዴት ነው?
ዕብራውያን 9፡22-28ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ክርስቶስ በሰማያዊው ቤተመቅደስ ስለሚሰራው ሥራ ምን ይነግረናል?
ሰማያዊ ቤተመቅደስ መንጻት ያስፈልገዋል የሚለው ኃሳብ ትርጉም የሚሰጠው
በብሉይ ኪዳን ቤተመቅደስ አውድ ነው። ቤተመቅደሱ የእግዚአብሔር
ምልክት ሲሆን ( 1 ሳሙ.4፡4፣2ሳሙ.6፡2) እግዚአብሔር የህዝቡን ኃጢያት
የሚያስተናግድበት ሁኔታ የርሱ መንግስት ፍትሃዊነት እይታ ላይ ተጸዕኖ
ያሳድራል(መዝ.97፡2)። እንደ ገዢ እግዚአብሔር የሕዝቡ ፈራጅ ሲሆን
ያላጠፋውን እንዲያነጻና ጥፋተኛውን እንዲኮንን ይጠበቅበታል። ስለዚህ
እግዚአብሔር ኃጢአተኛውን ይቅር ሲል ፍትሃዊ የመሆን ኃላፊነት አለበት።
የእግዚአብሔርን ባህሪና አስተዳደር የሚወክለው ቤተመቅደስ ቆሽሿል።
እግዚአብሔር ይቅር ሲል ለምን እንደሚሸከም ይህ ይገልጻል(ዘፀ. 34፡7፣
ዘሁ.14፡17-19 በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ይቅር ማለት” የሚለው የመጀመሪያው
የግሪኩ ቃል “መሸከም” የሚል ትርጉም አለው)።
በእስራኤላውያን ቤተመቅደስ የመስዋዕቶች ስርዓት ይህንን ነጥብ በምሳሌ
ይገልጻል። አንድ ሰው ምህረትን ሲፈልግ በሱ ፋንታ የእንስሳ መስዋዕት
አቅርቦ፣ኃጢአቱን በርሱ ላይ ተናዞ ያርደዋል። የእንስሳው ደም በመሰዊያው
ዙሪያ ባሉት ቀንዶች ይቀባል ወይም በቅዱሱ ክፍል ባለው መጋረጃ ላይ
ይረጫል። ስለዚህ በምሳሌነት ኃጢአቱ ወደ ቤተመቅደሱ ተላልፏል።
እግዚአብሔር የህዝቡን ኃጢአት ወስዶ ራሱ ተሸከመው።
በእስራኤላውያኑ ስርዓት የኃጢአት ስርየት ወይም ከኃጢአት መንጻት በሁለት
ሂደቶች ይከናወን ነበር። በዓመቱ ቀናት ውስጥ ንስሐ የሚገባው ኃጢአተኛ
ወደ ቤተመቅደሱ መስዋዕትን አምጥቶ ከኃጢአቱ ይነጻል፤ካህኑ ግን ወደ
ቤተመቅደሱ ሰይጣንን ወደሚወክለው ወደ አዛዜል በማስተላለፍ ፍትሃዊ
የመሆን ኃላፊነቱን ይወጣል፤ቤተመቅደሱን ያነጻል(ዘሌ.16፡15-22)።
ባለ ሁለት ክፍል የሆነው ስርዓት፤የሰማያዊው ቤተመቅደስ ምሳሌ የሆነውና
በምድራዊው ቤተመቅደስ ውስጥ ባሉ ሁለት ክፍሎች የተወከለው ስርዓት
(ዘጸ.25፡9፣ዕብ.8፡5) እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ምህረትንና ፍትህን
እንዲያደርግ አስችሎታል። በዓመቱ ቀናት ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙት ሰዎች
ተረጋግተው በማረፍና ራቸውን በማጎሳቆል ለእግዚአብሔር ታማኝነታቸውን
ያሳዩ ነበር(ዘሌ.16፡29-30)። ታማኝ ያልሆኑት ግን ይገለሉ ነበር(ዘሌ.23፡2732)።
ለኃጢአትዎ ፍትሃዊ ቅጣትን ማግኘት ግድ ቢሆንብዎት ምን
እንደሚገጥምዎት ያስቡ። ያ እውነት ክርስቶስ ያደረገልዎትን ነገር
እስዲያስተውሉ የሚረዳዎት እንዴት ነው?
ሮሜ 3፡21-26ን፣ ሮሜ 1፡16-17ንና ሮሜ 5፡8ን ያንብቡ። ለኃጢአታችን ይቅርታ በመስቀሉ መቤዠት ማግኘታችን ስለ እግዚአብሔር ምን ይነግረናል?
ለኃጢአቶቻችን ይቅርታ ማግኘታችን ሁለት ሂደቶች ያሉት ሲሆን ቤተመቅደስ
በሚገኙት ሁለት ክፍሎች በሚሆነው የክርስቶስ ምልጃ የሚከናወን ነው።
በመጀመሪያ ኢየሱስ ኃጢአታችንን አስወግዶ በርሱ ለሚያምን ሁሉ ምህረትን
ለማስገኘት በመስቀል ላይ ራሱ ተሸከማቸው(የሐዋ.2፡38፣ የሐዋ. ሥራ 5፡31)።
በመስቀል ላይ ኢየሱስ ኃጢአታቸውን ስለተሸከመ በርሱ የሚያምኑትን ሁሉ
ይቅር የማለት መብትን ወሰደ። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የእግዚአብሔርን
ሕግ በልባቸው መጻፍ የሚያስችለውን አዲስ ኪዳንንም አስጀምሯል(ዕብ.8፡
10-12፣ሕዝ.36፡25-27)።
በኢየሱስ አገልግሎት ያለው ሁለተኛው ክፍል(ሂደት) የቅድመ ዳግም ምጻት
ፍርድን የያዘ ነበር፤ከዕብራውያን አንጻር ያኔም ወደፊት የሚሆን ነበር(ዕብ.2፡
1-4፣ዕብ.6፡2፣ ዕብ.9፡27-28፣ ዕብ.10፡25)። ይህ ፍድ በእግዚአብሔር
ሰዎች የሚጀምር ሲሆን በዳንኤል 7፡9-27፣ ማቴ.22፡1-4ን ራዕይ 14፡7 ላይ
የተገለጸው ነው። አላማው እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር በማለቱ ውስጥ ጻድቅ
መሆኑን ማሳየት ነው። በዚህ ፍርድ የህይወታቸው ዝርዝር ታሪክ በዓለማት
ላሉ ሁሉ ክፍት ሆኖ ይታያል። እግዚአብሔር በአማኞቹ ልብ ውስጥ ምን
እንዳካሄደ ኢየሱስን እንደ አዳኛቸው እንዴት እንደተቀበሉትና መንፈሱን
በህይወታቸው እንዴት እንደተቀበሉት ያሳያል።
ስለዚህ ፍርድ ኤለን ጂ ኋይት ስትናር ሰው በራሱ እነዚህን ክሶች ሊመልስ
አይችልም። በኃጢአት በቆሸሸው ልብሱ ኃጢአቱን ሲናዘዝ በእግዚአብሔር
ፊት ይቆማል። የነፍሳችንን አደራ በንስሃና በእምነት ለርሱ ለምንሰጥ ሁሉ
ጠበቃችን ኢየሱስ በኛ ፋንታ ውጤታማ የሆነ ምልጃን ያደርግልናል። ስለ
ጥፋታችን ተሟግቶ ከሳሻችንን በቀራንዮ ብርቱ ሙግት ያሸንፈዋል።እስከ
መስቀል ሞት ድረስም ቢሆን በመሄድ ለአባቱ ህግ ፍጹም ታዛዥ መሆኑ
በሰማይና በምድር ያለውን ስልጣን ሁሉ ሰጥቶታል፤ለኃጢአተኛው ሰው
ምህረትና እርቅን ይለምናል።…..ያለንበትን ኃጢአተኛ ሁኔታ ስንረዳ እንደ
ጽድቃችን፣እንደ ቅድስናችንና እንደ ቤዛችን በርሱ ላይ ልንደገፍ ያስፈልጋል።
ሰይጣን በኛ ላይ ያለውን ክስ መመለስ አንችልም። በኛ ፋንታ ውጤታማ
ምልጃን ማካሄድ የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው። ከሳሻችን በኛ ሥራ ላይ
ሳይሆን በራሱ ላይ በተመሰረተ መከራከሪያ ዝም ሊያሰኘው ይችላል። Testimonies for the church,vol.5,pp.471-472.
መስቀሉና ክርስቶስ እኛን ወክሎ የሚያርገው አገልግሎት ስለ
ፍርዱ በድፍረት እንዲሁም በትህትናና በንስሃ እንድንመለከት
የሚያደርገን ለምድነው?
ከዘመናት ምኞት ላይ ቀራንዮ የሚለውንና ተፈጸመ የሚል
ርዕስ ያላቸውን ምዕራፎች ያንብቡ።
ፕሮፌሰር ጄሪ ሞስካላ ስለ ቅድመ ዳግም ምጻት ፍርድ ተናግረዋል።
“እግዚአብሔር እዚያ ጋ ያለው የኔን ኃጢአቶች ልክ እንደ ሱቅ መስታወት
ሊያሳይ አይደለም። በተቃራኒው በቅድሚያ ወደ አስደናቂው የሚለውጥ
ጸጋው ለመላው ዩኒቨርስ እያሳየ ስለ እኔ ህይወት እውነተኛ ምስክር ሆኖ
ለእግዚአብሔር ስላለኝ አመለካከት፣ ስለ መነሳሻ ኃሳቦቼ፣ ስለ አስተሳሰቤና
ስለ ህይወቴ አቅጣጫ ማብራሪያን ይሰጣል። ሁሉን ነገር ያሳያል። ኢየሱስ ብዙ
ስህተቶችን እንደሰራሁ ቅዱስ ህጉን እንደተላለፍኩ ነገር ግን ምህረትን ፈልጌ
ንስሀ እንደገባሁና በጸጋው እንደተለወጥኩ ይመሰክራል። ለኃጢአተኛው ደሜ
በቂ ነው፤የህይወት አቅጣጫው በኔ ይሁን፤ ስለኔና ስለሌሎች ሰዎች ያለው
አመለካከት ትኩስና ራስ ወዳድ ያልሆነ ነው፤እርሱ የሚታመን ነው፤ እርሱ የኔ
መልካምና ታማኝ አገልጋይ ነው።” ይላል። Theology of God’s Judgment:
A Celebration of the Cross in Seven Phases of Divine Universal
Judgment,” Journal of the Adventist Theological Society 15 (Spring
2004): p. 155.
“የተዋጁትና ያልወደቁት ሁለቱም አይነት ሰዎች በክርስቶስ መስቀል ውስጥ
ሳይንሳቸውንና መዝሙራቸውን ያገኛሉ። በኢየሱስ ላይ የሚያበራው ክብር
መስዋዕት ያደረገ ፍቅር ክብር እንደሆነ ይታያል።ከቀራንዮ በወጣው ብርሃን
ራስን የመካድ ፍቅር ለምድርና ለሰማይ የህይወት ህግ መሆኑ እንዲሁም
የራሱን የማይፈልገው ፍቅር ከእግዚአብሔር ልብ እንደፈለቀና በትሁቱ
ሰው ህይወት ውስጥ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የሚኖረው እርሱ
ባህሪውን እንደሚገልጽ ይታያል።”የዘመናት ምኞት ገጽ.19-20
1. የሰው ልጆች ለመዳን የተለያዩ አይነት መስዋዕቶችን የማቅረብ
ዝንባሌ ሁልጊዜም አላቸው።አንዳንዶች ጀግንነት የተሞሉ ተግባራትን
(ረዥም ጉዞዎች ወ.ዘ.ተ)፣ሌሎች የህይወት ሙሉ አገልግሎት
ወይም ራስን ማጎሳቆል ወ.ዘ.ተ ይፈጽማሉ። በኢየሱስ መስዋዕትና
መስቀሉ ሁሉንም መስዋዕቶች ወደ ፍጻሜ በማምጣቱ ብርሃን
እነዚህ ተግባራት እንዴት ይታያሉ (ዳን.9፡27፤ ዕብ.10፡18)?
2. በተመሳሳይ በአማኙ ህይወት ውስጥ የመስዋዕት ሚና
ምንድነው? ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ(ማቴ.16፡24)
ሲልና ጳውሎስ ሰውነታችንን ህያው ቅዱስ መስዋዕት አድርገን
መስጠት አለብን(ሮሜ 12፡1)ሲል ምን ማቱ ነው? በክርስቶስና
በጳውሎስ ትዕዛዛት እንዲሁም በዕብራውያን 13፡15-16 መካከል
ያለው ግንኑነት ምንድነው?